Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union
الذهاب إلى القناة على Telegram
This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.
إظهار المزيد4 433
المشتركون
-124 ساعات
-147 أيام
-8530 أيام
أرشيف المشاركات
Haggantoonni majliisa fedeeraalaa, waa'ee barattoota musliima ilaalchisee ministeera barnoota akka ta'an dhageenyeerra.
Jumu'aa waan ta'ef du'aaii irratti haa jabaannu.
"እንዳንቺ አይነት መምህር ግቢያችን አያውቅም!" - የዲላ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ታምራት የተናገረው
በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምትገኝ ሌክቸር የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት "ወይ ከትምህርትሽ ወይ ከኒቃብሽ ምረጪ አለኝ:: ኒቃቤን ብዬ በቀጠልኩ ማግስት ደግሞ እንደ አንቺ አይነት መምህር በግቢያችን ውስጥ አናውቅም አለኝ::" እያለች ታለቅሳለች::
ይሄንን ንግግር የተናገረው በምስሉ ላይ የሚታየው ዶክተር ታምራት ነው:: ቢላሂል አዚም ጥላቻቸው ከኒቃቡ ሳይሆን ከእስልምናችን ነው::
በአላህ ፈቃድ መብታችንን እስከ ጥግ ታግለን እናስከብራለን::
መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝም!
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!
@MohammadamminKassaw
የፌደራል መጅሊስ አመራሮች ስለ ዲላዎች ለመወያየት ትምህርት ሚኒስቴር እንደሆኑ ሰምተናል::
ጁምዓ ነውና በዱዓ እንወጥር ••• መልካሙን ያሰማን!
ነፃነት በትግል እንጅ በነፃ አይገኝም!!
@MohammadamminKassaw
"Niqaaba Osoo hin baasin hin baatan!" Yunivarsiiti diillaa.
Barattoota Mutaniqqiba sababa godhachun jibbaa fi tuffi hawaasa musliima irratti kan banee yunivarsiitin diillaa, guyyaa guyyaatti cunqursaawwan kessuummaa ta'an raawwachaa jira. Mutaniqqiiboota mooraa irraa ari'un, baruumsa, nyaata fi siree irraa eerga isaan fageesse guyyaa jahaffaa isaa har'a guteera. Ministeera barnoota irraa kaase, dhaabbilee mindaan isaani gibiira hawaasa biyyattin kaffalamun of bulchaa jiranis callisani jiru. Kan nama ajaa'ibu, har'aa barattoni modeela qormaata bahumsa biyyoleessaa (Exit Exam) fudhachuf konkolaataadhan seenan eerga qormaaticha xumuran booda niqaaba uuffachu isaani qalbeessan eerga ilaalan booda "Niqaaba keessan Osoo hin baasin bahuu hin dandeessan" jeechun dhorkaa dabarsani Falmii baay'een booda bahan.
yeroo jibbi nama jaameessu akkana... Kan ala jiran yoo baastan malee hin seentan jeechun, nyaata, barnootaa fi sireen isaan sodaachiisaa. Kan keessa jiranis, yoo baastan malee hin baatan, jeechun hidhamaa dhaabbi goochun Sodaachiisu yaalaa.
Ta'ees hin milkaa'ani, Cunqursi ifaan mul'achaa dhufee, Dhaloota isaan caala baratee fi barsiisee karaa qaroomaatin qabsaa'uu dhufeera.
Haqa barattoota musliimaa yunivarsiiti dillaaf!
Haqa barattoota musliimaa yunivarsiiti Ityoophiyaaf!
https://t.me/EHEMSU
"ኒቃብ ሳታወልቁ አትወጡም!" - ዲላ ዩኒቨርሲቲ
ኒቃቢስት ተማሪዎችን አስታኮ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ጥግ የደረሰ የጥላቻ እና ንቀት ጦርነት የከፈተው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ቀን ተቀን እንግዳ የሆኑ ጭቆናዎችን እየፈፀመ ነው:: ኒቃቢስት ተማሪዎችን ከግቢ አባሮ ከትምህርት ከምግብ እና ከመኝታ ካራቀ 6 ቀናት ዛሬ ደፍኗል:: ከትምህርት ሚኒስቴር ጀምሮ ከሀገሪቱ ህዝብ ግብር ደመወዝ የሚተነፍሱ ተቋማትም ፀጥ ረጭ ብለዋል::
የሚገርመው ዛሬ ለራሱ ከሌላ ቦታ የEXIT EXAM ሞዴል ለመውሰድ በመኪና የገቡ ኒቃቢስቶችን ፈተና እንደጨረሱ ኒቃብ መልበሳቸውን አስተውሎ "ኒቃባችሁን ካላወለቃችሁ ከዩኒቨርሲቲው አትወጡም!" የሚልን ክልከላ አስተላልፎ በብዙ ጭቅጭቅ ነበር ተማሪዎች የወጡት::
ጥላቻ ሲያውር እንዲህ ነው ••• ከውጭ ያሉትን ካላወለቃችሁ አትገቡም በማለት በምግብ በትምሀርት እና በማደሪያ ያስፈራራል:: ከውስጥ ያሉትንም ካላወለቃችሁ አትወጡም ብሎ የቁም እስረኛ በማድረግ ለማስፈራራት ይሞክራል::
ሆኖም አይሳካላቸውም ••• አግጥጦ የመጣን ጭቆና ከእነርሱ በተሻለ ተምሮ አስተምሮ በሰለጠነ መንገድ የሚታገል ትውልድ መጥቷል::
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!
@MohammadamminKassaw
Kaawunsilin Dargaggoota musliima Ityoophiyaa, Dillaatti argamun barattoota musliimaa yunivarsiiti diillaa wajjin mari'ateera.
https://t.me/EHEMSU
Bilisummaan bilisaan hin argamu!
+1
የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በዲላ በመገኘት ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር ተወያይቷል::
WELL DONE😍
ነፃነት በትግል እንጅ በነፃ አይገኝም!
@MohammadamminKassaw
የፌደራል መጅሊስ ስለ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ለትምህርት ሚኒስቴር ደብዳቤ ፅፏል:: የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በአፋጣኝ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ብሎም ችግሩን በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘላቂነት እንዲፈታ ሲል አሳውቋል::
https://t.me/EHEMSU
ዲላ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው ኒቃቢስት መምህራንንም በኒቃብ መግባት እና ማስተማርን ከለከለ!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአመታት እስልምናዋ የሚያዛትን ኒቃብ ለብሳ ስታስተምር የነበረች ሌክቸር ከትላንት ጀምሮ "ወይ ስራሽን ወይ ኒቃብሽን ምረጪ?" የሚል ትዕዛዝ እንደተላለፈላት ተገልፇል:: "ስራዬንም እምነቴንም ይዤ እቀጥላለሁ!" የሚል መልስ ብትሰጥም ለመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እና ክልከላ በዛሬው እለት ጠርተዋታል::
በተማሪዎቹ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ አይበቃው ያለው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ወደ እስታፍ ሰራተኞችም ተሸጋገረ:: ይህ ግልፅ የሆነ ሙስሊም ጠልነት ነው:: አዳጊ ወጣቶችን ከግቢ ውጭ ያለምግብ ያለትምህርት ያለማደሪያ የሚያሳድረው ተቋም የሀገሪቱን እናቶችንም በእምነት እየለዬ ማስለቀሱን ጀመረ::
ይህ አውሬያዊ ጭካኔ የተሞላበት ግፍ ነው!
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም መምህራን!
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ማህበረሰብ!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች!
https://t.me/EHEMSU
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በዲላ ዩኒቨርሲቲ እየተፈፀመ ስላለው የመብት ጥሰት ለፌደራል መጅሊስ አቤት ብሏል!
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!
ኒቃብ በጉንችሬ ተከልክሏል
ኒቃብ በAAU ተከልክሏል
ኒቃብ በአክሱም ተከልክሏል
ኒቃብ በሰላሌ ተከልክሏል
ኒቃብ በጂማ ተከልክሏል
ኒቃብ በዲላ እየተከለከለ ነው
•
•
•
•
•
ዝምታችን በዚህ ከቀጠለም በሁሉም ቦታ ይከለከላል:: በዚሁ ከቀጠሉም ከትምህርት ቤት ባሻገር በመኖሪያ ቤትም መከልከላቸው አይቀርም::
ዝምታ ይብቃ !
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!
https://t.me/EHEMSU
Kun Ityophiyaatti magaala diilla keessatti... Hammana garaa waljabaanne jirraa?
Ilaalaa...Hunduu akka beekus Share goodhaa!
Mutaniqqibootaa dukkana keessaa yeroo isaan deebisan mul'ata. Galu hin dandeessani jeechun mooraa hanga har'aatti seenani itti barachaa turan irraa isaan deebisan. Eessatti haa buulan? Eessatti haa baratan? Kan illee hin yaadani? Namuummaan hin jiru? Hanga kana bineensa ta'aniru.
Yunivarsiiti diillaa keessatti Islaamaa fi muslimootaaf jibiinaa hangana gahuu tulamee jiraa!
Haqa barattoota yunivarsiiti dillaaf
Haqa barattoota musliimaa yunivarsiiti Ityoophiyaaf
Gamtaan barattoota musliima dhaabbilee Olaanoo Ityophiyaa Midiyaa Harun walin Marii taasiise!
Kaleessa Amajji 13/2017 A.L.I
Hogantoonni Gamtaa barattoota musliimaa dhaabbilee barnoota Olaanoo Ityophiyaa, muslimoota ilaalchisee Hojii gaggeessaa Midiyaa Harun jan ta'an Bahru Abbaas waliin marii bal'aa taasiisaniiru. Sarbiinsa miirga fi qabsoo barattoota musliima ilaalchiise marii kan goodhamee yoo ta'uu jijjirama fiduf shoorri midiyaachi qabus ka'ee jiira. Midiyaan Harun qabsoo barattoonni musliima cunqursaan isanirratti gahaa jiruu yeroo dhumaaf fala akka argatu taasiisaa jiran bukkee dhaabbachun itti gaafatamuummaa inni bahaacha jiruf kabaja guddaa qabnaa. Cunqursii barattoota musliima irratti gahaa jiru Mormu fi fala barbaadu irratti, Nammoonni bebbekamoo, dhabbattotaa fi hoggantoonni gahee isaani akka bahaatan waammicha keenyaa in dhiyeessiinaa.
Gamtaa barattoota Musliima dhaabbilee Ol'aanoo Ityophiyaa.
https://t.me/EHEMSU
+1
ሌላው ይቅር ••• ሴት ልጅ ፀንሳ አልወለደቻቸውም? ሴት ልጅስ የላቸውም? ነገ በእኔ ብለው አያስቡም? እንዴት ቢጨከን ነው ሴት ልጅ ክብሬን ልልበስ ገላዬ ይሸፈን ስላለች ብቻ ልትኖርበት ልትማርበት ከገባችበት ዩኒቨርሲቲ በምሽት 3:00 አትገቢም ተብላ የምትመለሰው?
ይህ ሁሉንም ይመለከታል ••• ዜጎቹን በፍትሕ ሊያስተዳድር ቃለ-መሐላ ገብቶ ከወንበር የተቀመጠውን መንግስት ይመለከታል:: የሙስሊሞችን መብት እና ጥቅም ሊያስከብር የተቋቋመውን መጅሊስ ይመለከታል:: ስለሙስሊሞች እንጨነቃለን ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ይመለከታል:: ሙስሊሙን ማህበረሰብ ሁሉ ይመለከታል:: ሰብዓዊ ፍጡርን ሁሉ ይመለከታል::
••• የኢትዮጵያ ልጆችን ሊያስምር በኢትዮጵያ ህዝብ የተገነባው ዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ልጆችን ሙስሊም ሆነው ሒጃብ ስለለበሱ ብቻ በምሽት ከበር እየመለሰ ነው:: ይህ ለመላው ኢትዮጵያ ውርደት ነው ••• በራስ እጅ መነከስ ያማል!
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!!
@MohammadamminKassaw
ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ በዲላ ከተማ ነው ••• የዚህን ያክል ተጨካክነናል?
ተመልከቱት ••• ሁሉም ያውቀው ዘንድም Share አድርጉት!
ኒቃቢስቶቹን በጨለማ ያለምንም ርህራሄ ሲመልሷቸው ይታያል:: አትገቡም ብለው ••• እስከዛሬ ገብተው ሲማሩበት ሲኖሩበት ከነበረው ግቢ መለሷቸው:: የት ይደሩ? የት ይማሩ? ይህንን እንኳን አያስቡም? ሰብዓዊነት የለም? የዚህን ያክል አውሬ ሆነዋል::
ለእስልምና እና ለሙስሊሞች በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከባድ የጥላቻ ክምር ተቆልሏል::
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!
@MohammadamminKassaw
ዲላ ዩንቨርስቲ "ኒቃብ" የደህንነት ስጋት ነው በሚል ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ካገደ አምስት ቀናት መቆጠሩ ተገለፀ!
- ከትምህርት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎችም የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ሀሩን ሚድያ፥ ጥር 14/2017፣ ደቡብ ስቱድዮ
በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ጌድኦ ዞን ውስጥ የሚገኘው ዲላ ዩንቨርስቲ ኒቃብ የደህንነት ስጋት ነው በሚል ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ውጪ ካደረገ አምስት ቀናት መቆጠሩን ተማሪዎቹ ለሀሩን ሚድያ ተናግረዋል።
በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች በተጣለው የኒቃብ ክልከላ የሚማሩበትን ግቢ ለቀው የወጡት ቅዳሜ ጥር 10/2017 መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ክልከላውን የጣሉት የዩኒቨርሲቲው ሁለት ካምፓሶች ናቸው፡፡ ካምፓሶቹም ነባሩ ግቢ እና ኦዳያ የተሰኙት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም ሰኞ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ል ከሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረገው የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር "ኒቃብ ለደህንነት ስጋት ስለሆነ በግቢ ውስጥ ለብሶ መግባትም ሆነ መንቀሳቀስ አይቻልም" የሚል መልስ እንደሰጣቸው ተማሪዎቹ አሳውቀዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌድኦ ዞን እስልምና ጉዳች ምክር ቤት ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ጥር 5/2017 በጻፈው ደብዳቤ፤ የተጣለው ክልከላ ተገቢ እንዳልሆነ በማሳወቅ ተቃውሞውን አቅርቧል፡፡
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ባለፈው ታኅሣሥ ወር በሰጠው ፈትዋ (ብይን) “ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ” የፈጣሪ ትዕዛዝ የሆነውን አለባበስ “መከልከልም ሆነ ማደናቀፍ” እንደሌለበት ማሳሰቢያ መስጠቱን በማስታወስ ተማሪዎች የተወጡት ኢስላማዊ ግዴታ መሆኑን ጠቁሟል።
በተጨማሪም የከፍተኛ ተማሪዎች የዲሲፕሊን መመሪያ፤ በዩኒቨርሲቲ ቅጽር ግቢ የተከለከሉ ተግባራትን በሚዘረዝርበት ጊዜ “ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ መልዕክት ያላቸውን አልባሳት፣ ቅርጻ ቅርጽ፣ ጌጣጌጥ፣ የተለያዩ ቦርሳዎችና መያዣዎችን መጠቀም” የሚለውን ከማንኛውም ሃይማኖታዊ አለባበስ ጋር ማያያዝ፤ “የብሔር ወይም የሃይማኖት ማንነትን ሳያወልቁ የትምህርት ቅጥር ግቢ ውስጥ መግባት አይቻልም እንደማለት” መሆኑንም አብራርቷል፡፡
አያይዞም የተከለከሉ አለባበሶች ዝርዝር ውስጥም ቢሆን የሙስሊም ሴቶች ኢስላማዊ አለባበስ እንደሌለ የመመሪያውን አንቀጽ 7 ቁጥር 17.2ን በመጥቀስ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቋል።
▣ ሀሩን ሚድያ በዲላ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደምናደርስ ለመግለፅ እንወዳለን።
© ሀሩን ሚድያ
https://t.me/EHEMSU
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ከከሀሩን ሚዲያ ጋር ተወያየ!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ትላንት ማለትም ጥር 13/2017 ዓ.ል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ከፍተኛ አመራሮች በሙስሊሙ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ከሚንቀሳቀሰው ሀሩን ሚዲያ ዋና ማናጀር አቶ ባህሩ አባስ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል:: በውይይቱም ስለ ሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጭቆና እና ትግል ዙሪያ ዳሰሳ የተደረገ ሲሆን አዎንታዊ ለውጥ በማምጣት ረገድ ሚዲያው ሊኖረው ስለሚችለው አስተዋፅዖም ተነስቷል::
ሀሩን ሚዲያ ሙስሊሙ ተማሪ እየደረሰበት ያለውን ግፍ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት እያደረገ ያለውን ትግል ከጎን ሆኖ በማገዝ እያደረገ ለሚገኘው ታረካዊ ሀላፊነት አክብሮታችንን እንገልፃለን:: በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በመቃወም እና መፍትሔ በመፈለግ ረገድ ታዋቂ ግለሰቦች: ተቋማት እና አመራሮችም የበኩላቸውን አስተዋፅዖ በማበርከት በሀላፊነታቸውን ይወጡ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን::
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!
https://t.me/EHEMSU
ድላ ዩኒቨርሲቲ ታስሮ የነበረው ወንድማችን ጧት ላይ ተፈትሏል:: አልሐምዱሊላህ ••• ትግል ይቀጥላል::
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!
https://t.me/EHEMSU
ይደንቃል ••• ቁራጭ ልብስ ጣል አድርጎ መንቀሳቀስ ከነፃነት ተቆጥሮ ሰውነቴን ልሸፍን በሚል ሰልፍ ይወጣል:: ጥያቄ ይጠየቃል:: ትግል ይደረጋል::
ግን ሀገራችንን የሚመሩ ሰዎች እሳቤ ምን ያክል ቢያጥር ነው የዚህን ያክል ከሕግ እና ከጤና ያፈነገጠ ጭቆና የነገሰው? ያም ሆነ ይህ ግን አጥፊዎች ሳይፈሩ ሳያፍሩ እያጠፋ እኛ ለሐቅ እና ለነፃነት ማፈር እና መፍራት አይጠበቅብንም:: ነፃነት በነፃ አይገኝምና!
https://t.me/EHEMSU
