ar
Feedback
ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት

ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። የቴሌግራም ቻናል:-  @Finote_Wongel የቴሌግራም ግሩፕ:- @FinoteWongel27 የቲክቶክ ገፅ:- https://www.tiktok.com/@finotewongel27 Youtube:- https://www.youtube.com/@Finote_Wongel ©ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት

إظهار المزيد
668
المشتركون
-124 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
🛑 ሞተሃልና ስለኔ - ድንቅ የስቅለት መዝሙር 🛑 👉 https://youtu.be/T0XLAUtMvK8 👈 👉 https://youtu.be/T0XLAUtMvK8 👈 👉 https://youtu.be/T0
🛑 ሞተሃልና ስለኔ - ድንቅ የስቅለት መዝሙር 🛑 👉  https://youtu.be/T0XLAUtMvK8  👈 👉  https://youtu.be/T0XLAUtMvK8  👈 👉  https://youtu.be/T0XLAUtMvK8  👈

🛑 ሞተሃልና ስለኔ - ድንቅ የስቅለት መዝሙር 🛑 👉  https://youtu.be/T0XLAUtMvK8  👈 👉  https://youtu.be/T0XLAUtMvK8  👈 👉  https://youtu.be/T0XLAUtMvK8  👈

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/T0XLAUtMvK8?si=9AGkKolTXv3BKasP https://youtu.be/T0XLAUtMvK8?si
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/T0XLAUtMvK8?si=9AGkKolTXv3BKasP https://youtu.be/T0XLAUtMvK8?si=9AGkKolTXv3BKasP

✞ ዐብይ ጾምን እንዴት እንጹም? ✞ አባ ሱርኤል የተባሉ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህን የጻፉት "A Practical Journey through Lent" የሚል መጽሐፍ አለ። መጽሐፉ እጅግ ትን
✞ ዐብይ ጾምን እንዴት እንጹም? ✞ አባ ሱርኤል የተባሉ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህን የጻፉት "A Practical Journey through Lent" የሚል መጽሐፍ አለ። መጽሐፉ እጅግ ትንሽ ሲሆን፥ የዐብይ ጾምን በምንጾምበት ወቅት ሊረዱን የሚችሉ ነጥቦችን ያስቀምጣል። እነዚህን ነጥቦች እንመልከት። ዐቢይ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ከፍተኛውን አጽንኦት የሚሰጠው ጾም ነው። አባ ሱርኤል ሲገልጹትም "ዓመቱን ሙሉ የሚዘልቅ መንፈሳዊነትን ስንቅ አድርገን የምንይዝበት ጾም ነው" በማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ "እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።" [ፊል 3:10] እንዳለው ሁሉ፥ እኛም በዚህ የጾም ወቅት ክርስቶስን በሚገባ የምናውቅበት እንዲሆንልን መጣር ይኖርብናል። - ጊዜያችሁን መንፈሳዊ መጽሐፍት ለማንበብ እና ለመጸለይ ተጠቀሙበት። መልካም ጾም ለሁላችን!  የአሰላ ደ/መ/መ/ዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት 👇👇👇  👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel የቴሌግራም ግሩፕ:- T.me/FinoteWongel27 የቲክቶክ ገጽ:- tiktok.com/@finotewongel27 Youtube:- youtube.com/@Finote_Wongel Instagram:- https://www.instagram.com/finote_wongel

የፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት Youtube ቻናል Subscribe አድርገዋል? 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 Youtube.com/@Finote_Wongel
የፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት Youtube ቻናል Subscribe አድርገዋል? 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 Youtube.com/@Finote_Wongel

ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን ሰቀሉህ ወይ የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ /2/ የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመስቀል የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት  /2/ ንጹሕ ክርስቶስ ሆንክ ወንጀለኛ ብለህ ስለኛ መስቀል አሸክመው አስረው ገረፉህ እያዳፉህ  /2/ ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ /2/ እጅና እግርህ በችንካር ተመታ የዓለም ጌታ የሾህ አክሊል ደፋህ ጎንህም ተወጋ አልፋ ኦሜጋ /2/ በመስቀል ላይ ተጠማው ስትል ታላቅ በደል ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው /2/ ይቅር ባይ ግልጽ በደላችን ሁሉን ሳታይ አንተ ይቅር በለን በኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ /2/ የአሰላ ደ/መ/መ/ዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት 👇👇👇  👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel የቴሌግራም ግሩፕ:- T.me/FinoteWongel27 የቲክቶክ ገጽ:- tiktok.com/@finotewongel27 Youtube:- youtube.com/@Finote_Wongel Instagram:- https://www.instagram.com/finote_wongel

#ምስባክ #ዘወረደ ዘመጋቢት ፭ ፣ ፮ ወ ፯ የአሰላ ደ/መ/መ/ዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት 👇👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናል:- T.me/Finote_Wo
#ምስባክ #ዘወረደ ዘመጋቢት ፭ ፣ ፮ ወ ፯ የአሰላ ደ/መ/መ/ዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት 👇👇👇  👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel የቴሌግራም ግሩፕ:- T.me/FinoteWongel27 የቲክቶክ ገጽ:- tiktok.com/@finotewongel27 Youtube:- youtube.com/@Finote_Wongel Instagram:- https://www.instagram.com/finote_wongel

“ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ ወታጸምም ኵሎ ፍትወታተ ዘሥጋ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና" ቅዱስ ያሬድ ጾምን ቀድሱ ጉባኤውንም ዐውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ኹሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር
“ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ ወታጸምም ኵሎ ፍትወታተ ዘሥጋ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና" ቅዱስ ያሬድ ጾምን ቀድሱ ጉባኤውንም ዐውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ኹሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ ወደእግዚአብሔርም ጩኹ። ት.ኢዩ ፩ ፥፲፬ የአሰላ ደ/መ/መ/ዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት 👇👇👇  👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel የቴሌግራም ግሩፕ:- T.me/FinoteWongel27 የቲክቶክ ገጽ:- tiktok.com/@finotewongel27 Youtube:- youtube.com/@Finote_Wongel Instagram:- https://www.instagram.com/finote_wongel

✨እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ✨ ዘወረደ የመጀመሪያ የዐቢይ ጾም መግቢያ እሑድ ዘወረደ /ጾመ ሕርቃል/ ይባላል፡፡ «ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ
✨እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ✨ ዘወረደ የመጀመሪያ የዐቢይ ጾም መግቢያ እሑድ ዘወረደ /ጾመ ሕርቃል/  ይባላል፡፡ «ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡  አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤  ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት  የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት   ነው፡፡     እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባው ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ”ገላ 4፥4 እንዳለ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የጠፋውን አዳም ፍለጋ ከአባቱ  ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መውረዱን የምናዘክርበት ነው።       ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ጾመ ሕርቃል ተብሎም ይጠራል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው ፡፡ ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም  ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፥ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው። የአሰላ ደ/መ/መ/ዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት

1. #ዘወረደ ይህ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ከጾመ ሕርቃል በተጨማሪ ዘወረደ ይባላል፡፡ ይኸውም በባሕርዩ ከላይ ያለውን ለማውረድ መንጠራራት ከታች ያለውንም ለማንሳት ማጎንበስ የሌለበት፣ ሥልጣን ሁሉ የባሕርይ ገንዘቡ የሆነለት፣ የሚታየውና የማይታየውም ሁሉ በእጁ መዳፍ የተያዘለት አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ሊያድን ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ፍጹም ሰው መሆኑ የሚዘከርበት ሳምንት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ተጠመቀ፣ በገዳመ ቆሮንጦስ ጾመ፣ በጌቴሴማኒ ጸለየ፣ በቀራንዮ ተሰቀለ፣ ሞተ፣ተቀበረ፣ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፣ ወደ ሰማይ ዐረገ ለሚለው ሁሉ ጥንቱ ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ተፀነሰ፣ ተወለደ የሚለው ነው፡፡ ለዚህም ቢሆን ጥንት አለው፤ ይኸውም ወንጌላዊው ዮሐንስ ‹‹በመጀመሪያ ቃል ነበር›› (ዮሐ 1፥1) የሚለው ነው፡፡ በዚህ ሳምንት የወልደ እግዚአብሔር ከሰማያት መውረዱና ሰው መሆኑ ይዘከራል። በዚህ ሳምንት ከዳዊት መዝሙር ‹‹ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፤ በረዓድም ደስ ይበላችሁ›› (መዝ 2፥11) የሚለው ሲሆን ከወንጌል ክፍል ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአይሁድን አለቃ ኒቆዲሞስን ባስተማረበት ትምህርቱ ‹‹ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው›› (ዮሐ 3፥10-29) ብሎ ያስተማረውን ሊቃውንት ያስተምሩታል ያብራሩታልም።           ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ወንጌል አንድምታ (ማቴ 4፥1-3) ፣ ሰባቱ አጽዋማት ━━━━━✦📖 ❖ 📖✦━━━━━                   ዐቢይ ጾም “በዓለም ሳለችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።” ዮሐ ፮ ፥ ፴፫ የአሰላ ደ/መ/መ/ዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት 👇👇👇  👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel የቴሌግራም ግሩፕ:- T.me/FinoteWongel27 የቲክቶክ ገጽ:- tiktok.com/@finotewongel27 Youtube:- youtube.com/@Finote_Wongel Instagram:- https://www.instagram.com/finote_wongel