cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ሐኪም~ኢትዮ-ጤና

ስለጤናችን ግንዛቤ የምንጨብጥበት፤ ያለንን እውቀት የምናሰፋበት ፤የራሳችንን ጤና የምንጠብቅበት እና ያወቅነውንም የምናሳውቅበት ነው።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
199
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-1030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🌿ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ ምክሮች🌿፦ 🌸በሰውነታችን ላይ የስብ መከማቸት ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚዳርግ የሚታወቅ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ ✔️ ለልብ ሕመም ✔️ ለስኳር ሕመም ✔️ ለደም ግፊት መጨመር ✔️ ለከፍተኛ ኮሌስትሮል 🌸በአብዛኛው ስብ የሚከማችበት ቦታ ሆድ አካባቢ ሲሆን ይህም ቦርጭ ብለን የምንጠራው ነው፡፡ ቦርጭን ሊያመጡ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ✔️ ሊተኙ ሲሉ መመገብ ✔️ ሰዓትን ጠብቆ አለመመገብ ✔️ በሰውነታችን የሚገኙ ሆርሞኖች ለውጥ ✔️ ጭንቀት ✔️ ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ ✔️ በተፈጥሮ የሚመጣ 🌸 ቦርጭን ለማጥፋት ✔️ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ብርጭቆ ሎሚ ያለው ውኃን ጠዋት መጠጣት ✔️ ስብ የማቃጠል ችሎታ ያላቸው ምግቦችን መመገብ፡- እነዚህም እንደ ብሮክሊ፤ካሮት፤ጎመን ያሉ አትክልቶቸ፤ እንዲሁም እንደ ፖም፤ ሃብሃብ፤ ፓፓዬ ያሉ ፍራፍሬዎችን ማዘውተር ✔️ ጤናማ የሆነ አመጋገብ እንዲኖረን ማድረግ ፡- የተመጣጠነ እና አትክልት የበዛበት የምግብ ባሕልን ማዳበር ✔️ በቀን ውስጥ የምንጠጣውን የውኃ መጠን መጨመር ✔️ ቁርስን በሚገባ መመገብ፡- ይህን ማድረግ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማንና ማስታገሻ የሚሆኑ ተጨማሪ ስኳር እና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች እንዳንመገብ ያደርጋል፡፡ ✔️ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ዋና መዋኘትን ማዘውተር በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል የእግር መንገድ መሄድ ✔️ እንቅልፍ አለማብዛት ✔️ ጭንቀት ማስወገድ ✔️ ለስላሳ መጠጦችን መተው ናቸው፡፡ በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም) https://t.me/Health1science01
إظهار الكل...
ሐኪም~ኢትዮ-ጤና

ስለጤናችን ግንዛቤ የምንጨብጥበት፤ ያለንን እውቀት የምናሰፋበት ፤የራሳችንን ጤና የምንጠብቅበት እና ያወቅነውንም የምናሳውቅበት ነው።

👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የህፃናት ፎሮፎር 👉አንዳንድ ህፃናት ከእናታቸው በሚተላለፍላቸው ሆርሞን ምክንያት እንደፎሮፎር ጭንቅላታቸው ላይ ሊወጣባቸው ይችላል። 👉ስስ በሆኑ የህፃናት ብሩሽ ጭንቅላታቸው ላይ የተጋገረውን ነገር አርጥባችሁ ማንሳት ከዚያም ፓራፊን በመቀባት ማከም ትችላላችሁ። በዚህ ካልተሻለ በሀኪም ሚታዘዙ ክሬሞች አሉ። 👉ካልተንከባከባችሁት እስከ ዘጠኝ ወር እየተመላለሰ ሊቆይ ይችላል። ከዛ ግን በራሱ ይጠፋል።
إظهار الكل...
🌺የዓይን ግፊት ህመም ወይም ግላኮማ ምንድነው ?🌺፦ 🌿ግላኮማ ወይም በተለምዶ የዓይን ግፊት ህመም ተብሉ የሚጠራው የዓይን ህመም የዓይናችን ግፊት ከተለመደው በላይ በመጨመር መልዕክትን ከዓይናችን ወደ ኋለኛው የአንጓላችን ክፍል (Occipital lobe) የሚያስተላልፈውን የዓይን ነርብ (Optic nerve) በመጉዳት ሊመለስ ወደማይችል ዓይነስውርነት(irreversible blindness ) የሚዳርግ አደገኛ የዓይን ህመም ነው። 🌿ግላኮማ ዓይነ-ስውርነትን በማምጣት ከዓይን ሞራ ህመም ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ይጠቀሳል። ግላኮማ በማነኛውም እድሜ ክልል፣ በጨቅላ ህፃናት ፣ በታዳጊዎች ፣ በአዋቂዎች እንዲሁም እድሜያቸው በገፋ ሰዎች ላይ ሊከሰት ይችላል። 🌿በይበልጥ ለዚህ ህመም ተጋላጭ የሆኑት🌿፦ 🍀እድሜያቸው ከ40ዓመት በላይ የሆኑ 🍀 በቅርብ ዘመዶቻቸው (first degree relative) ማለትም በወላጅ አባት ወይም እናት:በደም ከሚተሳሰሩ እህት ወይም ወንድሞች መካከል የግላኮማ ህመም ወይም ምክነያቱ የልታወቀ ዓይነ ስዉርነት ካለ። 🍀የቆየ የዓይን ኳስ ምት ወይም አደጋ ከነበረ 🍀የተለያዩ የዓየይን ህመሞች ለምሳሌ የቆየና የልታከመ የዓይን ሞራ 🌿በተለያዩ ተጓዳኝ ህመሞች ተጠቂ ከሆኑ ፦ 🌴የስኳር ህመም 🌴 የደም ግፊት ህመም 🌴 የልብ ህመም 🌴ለረጅም ጊዜ steroid የተባለውን መድሐኒት የሚጠቀሙ ሰዎች። ለምሳሌ 🌸የአስም ህመምተኞች 🌸የመገጣጠሚያ ህመምተኞች 🌿 የግላኮማ ህመም ምልክቶች🌿፦ 🌸ባጠቃላይ ሁለት ዓይነት የግላኮማ ህመሞች አሉ። 🍀አጣዳፊ የዓይን ግፊት ህመም (Acute Glaucoma)፦ ይህ አይነቱ የዓይን ግፊት ህመም በወቅቱ እና በድንገተኛ ካልታከመ እይታችንን በሰዓታት እና በቀናት ውስጥ ሊነጥቀን ይችላል። አጣዳፊ የዓይን ግፊት በሚጨምርበት ወቅት የሚከተሉትን ምልክቶች ይከሰታሉ፦ 🌴ከፍተኛ የሆነ የራስና የዓይን ህመም 🌴የዓይን መቅላት 🌴ብርሃን መፍራት 🌴ማልቀስ፣መቆርቆር 🌴የእይታ መቀነስ 🌴ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ 🌴እይታችን ላይ ቀስተደመና (halo) መታየተት 🍀'ምልክት የለለው'(Chronic glaucoma)፦ ይህ አይነቱ የዓይን ግፊት ህመም ምንም አይነት ምልክት የለለው፣ የዕይታ አድማሳችንን ከውጭ ወደ ውስጥ ቀስ በቀስ እያጠበበ የሚመጣና በመጨረሻም ማዕከላዊ የእይታ አድማስ የሚነጥቅ እና ሊመለስ የማይችል ዓይነ-ስውርነትን ያመጣል። በዚህ ባህሪዉ ይህ የግላኮማ አይነት ''ምልክት አልባ የዓይን ብርሀን ሌባ (silent thief of sight)' በመባል ይታወቃል። 🌸የግላኮማ ህክምናው ምን ይመስላል?፦ 🌿የግላኮማ ህመም ህክምና መከላከልን መሰረት የደረገ ነው።ይህም ማለት በግላኮማ ህመም ምክንያት የተከሰተውን የእይታ ጉዳት መመለስ የማይቻል ሲሆን ነገር ግን የዓይናችንን ግፊት በተለያየ መንገዶች በመቀነስ ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን ተጨማሪ የዕይታ ጉዳት መከላከል /ማስቆም ነው። እድሚያቸው ከ40አመት በላይ የሆነ እንዲሁም በቤተሰብ የዓይን ግፊት ታሪክ ያለበት ሰው የዓይን ግፊት ልኬት እና የዓይን ነርብ ጤንነት ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ይመከራል። በዶ/ር ሰሎሞን ተከወ : በእንጅባራ ዩንቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር : በእንጅባራ ጠ/ሆስፒታል የዓይን ስፔሻሊስት ሀኪም https://t.me/Health1science01
إظهار الكل...
ሐኪም~ኢትዮ-ጤና

ስለጤናችን ግንዛቤ የምንጨብጥበት፤ ያለንን እውቀት የምናሰፋበት ፤የራሳችንን ጤና የምንጠብቅበት እና ያወቅነውንም የምናሳውቅበት ነው።

🌺ጥርስን ለማንጣት የሚጠቅም🌺፦ ------------------ በተፈጥሮአዊ መንገድ ህክምና ድረስ መሄድ ሳያስፈልገን ቤታችን ውስጥ ጥርሳችን እንዴት ማንጣት እንችላለን? በተፈጥሮአዊ መንገድ ዘወትር በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተአምር ትመለከታለህ...!!እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? መጠን...!! .. 1. 🌿ለብ ያለ ውሃ ሁለት ብርጭቆ!! 2. 🌿የተፈጨ ቀረፋ አንድ ማንኪያ!! 3. 🌿የንብ ማር አንድ ማንኪያ!! 4. 🌿የሎሚ ጠብታዎች!! .. አዘገጃጀት...!! ትንሽ ተለቅ ባለ ብርጭቆ ውሃውን እንጨምራለን...!!ከዚያም ቀረፋውን እና ማሩን እናስከትላለን!! በመጨረሻም ከአምስት የማይበልጡ የሎሚ ጠብታዎችን እንጨምርበትና በደንብ አዋህደን ስናበቃ ዘውትር ጠዋት አፋችንን እንጉመጠመጥበታለን...!! https://t.me/Health1science01
إظهار الكل...
ሐኪም~ኢትዮ-ጤና

ስለጤናችን ግንዛቤ የምንጨብጥበት፤ ያለንን እውቀት የምናሰፋበት ፤የራሳችንን ጤና የምንጠብቅበት እና ያወቅነውንም የምናሳውቅበት ነው።

🌿🌺የዝንጅብል ሻይ🌺 - 10 የጤና በረከቶች🌿፦ 1. 🌿በመኪና ሲጓዙ ለሚያስመልሳቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ 2. 🌿ከማይግሬን የራስ ህመም ይገላግልዎታል፡፡ 3.🌿በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ቁርጠትን ይቀንሳል፡፡ 4.🌿 የትልቅ አንጀት ካንሰርን ይከላከላል፡፡ 5.🍀 በስኳር በሽታ ምክንያት የሚመጣን የኩላሊት ህመም/ጉዳትን ይከላከላል፡፡ 6. 🌿በቃር ለሚሰቃዩ ፍቱን ነው፡፡ 7. 🌿ህመምና ኢንፍላሜሽን (የሰውነት መቆጣትን) እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ 8. 🌿ጠዋት ጠዋት ለሚከሰቱ ህመሞች ፍቱን ነው፡፡ 9.🌿 ለጉንፋን እና ፍሉ ህመሞች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ 10. 🌿የእንቁላል ከረጢት ካንሰርን ይከላከላል፡፡ https://t.me/Health1science01
إظهار الكل...
ሐኪም~ኢትዮ-ጤና

ስለጤናችን ግንዛቤ የምንጨብጥበት፤ ያለንን እውቀት የምናሰፋበት ፤የራሳችንን ጤና የምንጠብቅበት እና ያወቅነውንም የምናሳውቅበት ነው።

🌺«ጥርት ያለ የፊት ቆዳ ለማግኘት»🌺፦ 🌸የፊት ቆዳችንን በአግባቡ ካልተንከባከብነው በቀላሉ የሚጎዳ ሲሆን ቀጥሎ ያሉትን የፊት ቆዳን መንከባከቢያ መንገዶች ይመልከቱ። - 🌿ፊትን በቀን ሁለቴ መታጠብ - 🌿የፊት ሳሙና ወይም ሌላ ቅባት ሲቀቡ የፊትዎን ቆዳ ከመፈተግ ይቆጠቡ ይልቁንም በለስላሳና ክባዊ እንቅስቃሴ ቀስ ብለው ይቀቡት - 🌿ለፊት ቆዳዎት የሚስማማ ማርጠቢያ ክሬሞችን ይጠቀሙ ከመተኛትዎትም በፊት ሊጠቀሙት ይችላሉ - 🌿የፊት ቆዳ ቀዳዳን ከሚደፍኑ ዘይታማ ከሆኑ ሜክአፖችና የቆዳ ክሬሞች ይራቁ - 🌿የቆዳችን ንፅህና መጠበቅ በተለይ ብጉር የሚያስቸግረን ከሆነ ቤንዞይል ፐርኦክሳይድ፣ ፊዞርሲኖል፣ ሳሊክሊክ አሲድ ወይም ሰልፈር ያለው ለፊትዎ የሚስማማ ሳሙና መጠቀም ብጉሩ በዚህ ካልቀነሰ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል 🌸በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መድሃኒት፦ በተለያየ ምክንያት የፊትና ሌላ የቆዳ አካል ላይ የቀረን ምልክትን ለማጥፋት ከፈለጉ የሚከተለውን በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ህክምናን ሊጠቀሙ ይችላሉ። •🌴 አራት የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጁስ • 🌴አራት የሻይ ማንኪያ ማር •🌴 አንድ አስኳሉ የወጣለት እንቁላል አዘገጃጀት፦ • 🍀ፊትዎ/ቆዳዎ ንፁህና ደረቅ መሆን ስላለበት ይታጠቡት • 🍀በመቀጠልም ከላይ የተዘረዘሩትን በንፁህ እቃ ውስጥ በደንብ ያደባልቁ • 🍀ከዚያም ምልክት ባለበት የቆዳዎ ክፍል ላይ ይቀቡት • 🍀ከ15 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ይታጠቡት ጥሩ ውጤት ለማግኘት በሳምንት ሁለት ጊዜ እንዲጠቀሙት ይመከራል። https://t.me/Health1science01
إظهار الكل...
ሐኪም~ኢትዮ-ጤና

ስለጤናችን ግንዛቤ የምንጨብጥበት፤ ያለንን እውቀት የምናሰፋበት ፤የራሳችንን ጤና የምንጠብቅበት እና ያወቅነውንም የምናሳውቅበት ነው።

Photo unavailableShow in Telegram
👉ፎሮፎር ካለባችሁ ቅቤ አትቀቡ። 👉ለጊዜው ለውጥ ያገኘ ቢመስልም አገርሽቶና ተባብሶ መመለሱ አይቀርም ለማግኘት @urskincare
إظهار الكل...
🌸መጥፎ የአፍ ጠረን መንስኤዎች🌸፦ 1. 🌿የአፍ ንፅህና ጉድለት 2.🌿 በጥርስዎ፣በምላስዎ ወይም በድዲዎ ላይ ያሉ ተህዋሲያን 3.🌿 በጨጓራ ግድግዳ ላይ የሚገኝ የኤች ፖይሎሪ ባክቴሪያ 4.🌿 GERD የሚባል የጨጓራ በሽታ 5. 🌿የስኳር በሽታ 6. 🌿የሳንባ ኢንፌክሽን 7. 🌿የጉሮሮ በሽታ 8. 🌿የአፍንጫ ኢንፌክሽን 9.🌿 አንዳንድ ዓይነት መድሃኒቶች 10. 🌿እንደ ነጭ ሽንኩርት, ቀይ ሽንኩርት እና ቅመሞችን የመሳሰሉ የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ 11.🌿 እንደ ቡና እና አልኮል ያሉ መጠጥ መጠጣት 12. 🌿ማጨስ 13. 🌿ምግብ አለመመገብ እና ዝቅተኛ-ካርቦሃይድሬት ያላቸው ምግቦችን መመገብ ~~~የመጥፎ አፍ ጠረን መንስኤዎች ናቸው። ቀድመን በመታከም ራሳችንን እንጠብቅ። https://t.me/Health1science01
إظهار الكل...
ሐኪም~ኢትዮ-ጤና

ስለጤናችን ግንዛቤ የምንጨብጥበት፤ ያለንን እውቀት የምናሰፋበት ፤የራሳችንን ጤና የምንጠብቅበት እና ያወቅነውንም የምናሳውቅበት ነው።

🌸ፀሐይ ለሕፃናት 🌸፦ 🌿ፀሐይ ለልጆች ለአጥንታቸው ተጨማሪ ንጥረ ነገር መሆኑን ሳንዘነጋ እስከ 12 ወር ድረስ ማሞቅ ይኖርብናል ፡፡ 🌸ከ 10-20 ደቂቃ ማሞቅ !!! 🍀ዋናው ነገር ልጆቻችን የፀሐይ ብርሀን ማግኝት የግድ መሆኑን እንዳንዘነጋ ነው !!! 🍀በተለያዪ ምክንያቶች ልጆቻችንን በቂ የፀሀይ ብርሀን ሳያገኙ በመቅረታቸው መራመድ ሲጀምሩ የተቸገሩ ልጆች እያየን ስለሆነ ልጆቻችንን ፀሐይ ማሞቅ ግድ ይለናል!!!! https://t.me/Health1science01
إظهار الكل...
ሐኪም~ኢትዮ-ጤና

ስለጤናችን ግንዛቤ የምንጨብጥበት፤ ያለንን እውቀት የምናሰፋበት ፤የራሳችንን ጤና የምንጠብቅበት እና ያወቅነውንም የምናሳውቅበት ነው።

🌸ውሃ🌸 🌸ልጆች ውሃ መጠጣት የሚጀምሩት መቼ ነው?🌸፦ 🌿ለልጆች ከ6 ወር በፊት ውሃ መስጠት አያስፈልጋቸውም ምክንያቱም ከሚጠጡት የጡት ወተት/የድቄት ወተት በቂ ስለሚያገኙ ፡፡ በመሆኑም ልጆች ከ 6ወር በኃላ እስከ 1 ዓመታቸው በቀን ውስጥ የተወሰነ መስጠት ፡፡ በዚህ ወቅትም (ከ6ወር-1 ዓመት) አብዝቶ መስጠት በቀላሉ ሆዳቸው ስለሚሞላ በደንብ እንዳይበሉ ይከለክላቸዋል ፡፡ ውሀን በደንብ መጠጣት ያለባቸው እነሱ እንደጠማቸው ከ 1 አመታቸው በኃላ ነው ፡፡ https://t.me/Health1science01
إظهار الكل...
ሐኪም~ኢትዮ-ጤና

ስለጤናችን ግንዛቤ የምንጨብጥበት፤ ያለንን እውቀት የምናሰፋበት ፤የራሳችንን ጤና የምንጠብቅበት እና ያወቅነውንም የምናሳውቅበት ነው።

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.