cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

"ኑ:ወደ አላህ እንመለስ!!የሱኒዮች ጉሩፕ🇸🇦

"ኑ:ወደ አላህ እንመለስ!! አላህ ወደ ሀቅ መመለስን እና በሀቅ ላይ ፅናትን ይስጠን፡፡ ሰዎች ምንም ቢሉ አላህ የወሰነዉ አይቀርም !! ጉድ እኮነዉ አሉ ሸይኻችን!! ✍🏻የተለያዩ ኡስታዞችን ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ👇👇 https://t.me/nuwedaalahienemalas https://t.me/nuwedaalahienemalas

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
977
المشتركون
+724 ساعات
+107 أيام
+3130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Repost from N/a
00:13
Video unavailableShow in Telegram
ምንድነው አላማህ የምትለፋበት? መቀላቀል ሆነ የሌለው መሰረት እሳትን ከውሃ ካልቀላቀልኩ ማለት ምንድነው አላማህ የምትለፋበት ምንድነው መሮጡ ከርስህን ለሞምላት ንቃ እንጂ ወንድሜ ዱንያኮ ጠፊ ናት ተውሂድና ሱናን አትነግድበት ለሚጠፋ ነገር ለማትዘዎትርበት የሱና ወንድሜ ፅና ባለህበት አላህ ይጠብቀህ እስክንሰናበት ✏️አቡ ፊርደውስ https://t.me/abdu_somed https://t.me/abdu_somed
إظهار الكل...
2.27 MB
ጀመረ ጀመረ
⤵️⤵️⤵️⤵️ በጉግት ሲጠበቅ የነበረው የወንድማችን ሀመድና የእህታችን አይሻ የኒካ ፕሮግራም በማስመልካት  ልዩ ነሲሃ በኡስታዝ🎤አቡ ፊርዶስ ሀፊዘሁሏህ ኑኑኑ ኑ አያየፍቹ https://t.me/alfarukmedrasa
إظهار الكل...
📚📚የአል ፋሩቅ መድረሳ ኦድዮዎች የሚለቀቁበት ቻናል📚📚

‏قال العلامة الفوزان - حفظهُ الله-: "من انحرف عن طريقة الرسول ﷺ فإنه لا يُتَّبع ولا يُقْتَدى به ولو كان عالماً" 📚أهمية التوحيد - صف36

በሸይኽ ሁሴን አባስ ከጉራ ወርቄ ርዕስ"የላኢሀ ኢለሏህን ትርጉም ማብራራት በሚል ዙሪያ እንካችሁ ይሉናል ከልብ ሰምተን ወደተግባር እንቀይርረው https://t.me/hussenhas
إظهار الكل...
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ውድ የሸይኽ ሙሐመድ ሐያትን አዲስ pdf ያሰራጫችሁ ወንድሞች pdf በጣም ጠቃሚና ለሁሉም መድረስ ያለበት ነው ። ነገር ግን አንዳንድ የፊደል ግድፈቶች ስላለበት መስተካከሉ የግድ እንደሆነ ሸይኻችን ሸይኽ ሑሰይን ነግሮኛል ። በመሆኑም የተሰራጨው እንዲጠፋና አላህ ካለ ቶሎ ተስተካክሎ እንዲሰራጭ እንተባበር ። http://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:- 🔹“የዚል ሒጀህ ቀናቶች ልክ እንደ መብረቅ በፍጥነት አለፉ፣ አያሙ ተሽሪቅም ተከተለቻትና ልክ እንደ ዓይን እርግብግብታ የተቆጠሩ ደቂቃዎችን በሚመስሉ መልኩ ፈጥነው አለፉ። ልክ እንደዚሁ ነው እድሜያችን በፍጥነት የሚያበቃው፣ ሞት ድንገት ይመጣናል፣ ልክ ህይወትህ በፍጥነት ከማለፏ የተነሳ ጥፍጥናዋንና ፍጥነቷን ሁሉ እንደ ቅዠት እስክትመለከት ድረስ ይሁንብሃል፣ እንደ ዳመና በፍጥነት ታልፋለች። ብልህ የሆነ ሰው ጊዜውን አላህን በመታዘዝ፣ ወደ አላህ በሚያቃርቡ ነገሮች፣ የአላህን ፀጋ በማስታወስና እርሱንም በማመስገን የተጠቀመው ሰው ነው። አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏልና:- وَمَا بِكُم مِّن نِّعْمَةٍ فَمِنَ اللَّهِ «ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ፀጋ ከአላህ ነው፡፡» አን-ነህል 53 ከፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ የተውሒድና የሱንና ፀጋ ነው!! በዚህ ላይ እስከ እለተ ሞት ድረስ መፅናት ነው!! በእርግጥም በሶሂህ አል-ቡኻሪይ ከዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ - ረዲየላሁ ዐንሁ - መርፉዕ የሆነ እንዲህ የሚል ሀዲስ ተዘግቧል:- “በብዙ ሰዎች ላይ ስውር የሆኑባቸው አለያም ሰዎች የዘነጓቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: እነሱም ጤናማነትና ጊዜ ናቸው።” ኢማሙ አህመድ - ረሂመሁላህ - እንዲህ ብለዋል:- “በእስልምና እና በሱና ላይ የሞተ ሰው መልካም በተባለ ነገር ሁሉ ላይ ሆኖ ነው የሞተው።” [አስ-ሰይር] : የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
إظهار الكل...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

🌸أذكار المساء✅✅ اَمْسَيْنَا وَاَمْسَ الْمُلْكُ لِلَّهِ وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، لَا إِلَهَ إِلَّّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، رَبِّ أَسْأَلُكَ خَيْرَ مَا فِيْ هَذَا اللَّيْلَةِ وَخَيْرَ مَا بَعْـدَهـا، وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِي هَذَا اللَّيْلَةِ وَشَرِّ مَا بَعْـدَهـا، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنَ الْكَسَلِ، وَسُوءِ الْكِبَرِ، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ فِيْ النَّارِ وَعَذَابٍ فِيْ الْقَبْرِ. ✅اللَّهُمَّ بِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوتُ وَإِلَـيْكَ المَصِيْر ✅اللَّهُمَّ مَا أََمْسَ بِي مِنْ نِعْمَةٍ أَوْ بِأَحَدٍ مِنْ خَلْقِكَ فَمِنْكَ وَحْدَكَ لَا شَرِيكَ لَكَ، فَلَكَ الْحَمْدُ وَلَكَ الشُّكْرُ.
إظهار الكل...
👍 1
اَللَّهُمَّ بِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوْتُ وَإِلَيْكَ النُّشُوْرُ.
አልሀምዱሊሏህ ለንጋት በቅተናል በእዝነትህክ ውቧን ፀሀይ አይተናል አመስጋኝ  ሁነን  አንግተናል አስታዋሽ  አመስጋኞች ባንተ  ትእዛዝም ደስተኞች ባንተ  ተወካዬችም  ሁነናል ምስጋና ስግደት ላንተ ይገባሀል……!!
ጌታችን  ሆይ  ከፀጋዎችህ  በእኛ  ላይ አድርግ  በዱኒያም  በአኬራም  ምህረትህን  ለግሰን  يارب      🔊 መልካም ቀን⤵️ https://t.me/terbyataselef
إظهار الكل...
1.95 MB
Repost from lbnu keyradinn
🚫 እህቶችን መሰረት ያደረገ የሿሿ ጥቃት ሿሿ ማለት የሚታወቀው በአንድ ሚኒ ባስ ታክሲ ላይ ከስብእና የወጡ ሴቶች የሽማግሌ ቀላሎችና ወሮበላ ወጣቶች ተሰባስበው የሶስት ሰው ቦታ ከፊት ከመሀልና ኋላ ክፍት አድርገው ከተሳፋሪ ውስጥ የሚፈልጉትን ሲያገኙ አንድ ሰው ብቻ ብለው ያስገባሉ ። በክብር ቦታ የተለቀቀለት በማስመሰል የሚፈልጉት ቦታ እንዲቀመጥ ይደረጋል ። ያ ቦታ ማለት የተዋጣለት ፈታሽ የተዘጋጀበት ቦታ ነው ። ፈታሹ ስራውን ሲጀምር ውስጥ ያለው የውርጋጦች ስብስብ ረብሻ ይፈጥራል ። ሹፌሩ መኪናውን የሚገለብጠው ይመስላል ። በዚህ መሀል ግራ በመጋባት ምን እንደተፈጠረ ሳይገባው በፍተሻው የተራቆተው እንግዳ ተሳፋሪ እንዲወርድ ይደረጋል ። ወደራሱ ሳይመለስ ግራ እንደተጋባ ቆሞ ታክሲውን ያያል ። ታክሲው ትቶት ይፈተለካል ። ወደራሱ ሲመለስና ኪሱን ሲፈትሽ ተራቁቷል ። ለመደወል ስልክ የለም ለመሳፈር ሳንቲም የለም ። የዚህን ጊዜ ነው የድራማው ሚስጢር የሚገባው ። ይህ ነው ከዚህ በፊት በሿሿ የሚታወቀው ። የአሁኑ ሿሿ የረቀቀና ከውጭ የመጡ ወይም የውጭ ሀገር እድል ያገኙ እህቶችን መሰረት ያደረገ ነው ። በአብዛኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢና እንዲሁም ኤምባሲዎች አካባቢ ነው የወጥመዱ አካባቢዮች ። ይህን በድራማ መልኩ የሚሰራ ትእይንተ ዘረፋ የሚያካሄዱ ዋልጌዎች በተቀናጀ መልኩ ስፍራ ስፍራቸውን ይይዛሉ ። በቅርብ ርቀት ቦታና የስራ ድርሻ ይመዳደባሉ ። የተንጣለለ ጊቢ ተከራይተው ለእኩይ ተግባራቸው ያዘጋጃሉ ። በአብዛኛው ሒጃብ የለበሱ ሴቶችና ፂም ያስረዘሙ ሱሪ ያሳጠሩ ኮፍያ ያጠለቁ የሙስሊም ገፀባህሪ ተደርገው የተዘጋጁ የድራማው ተሳታፊ ይሆናሉ ። በዚህም በቀላሉ የሙስሊም እህቶችን ዐይን ይስባሉ ። ከቀረጥ ነፃ ወረቀት ውክልና ሰጥተው ለማረጋገጥ ወደ ውጪ ጉዳይ የሚሄዱ , የጋብቻ ወይም የልደት አሊያም የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥም ወደዚያ የሚያመሩ እህቶች በተለይ ከተማውን የማያውቁ ከሆኑ ቶሎ ይታወቃሉ ። ወዲያው በእነዚያ በተዘረጋ ሰንሰለት አቀባበል ይደረግላቸዋል ። ሙስሊሞች ከሆኑ በባለ ሒጃቧ ወዴት ነው ? ተብለው ይጠየቃሉ ያለ ምንም መጠራጠር ለምን ጉዳይ ወዴት መሄድ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ ። እኔም ወደዛው ነኝ አብረን እንሄዳለን ይባላሉ ። ጉዞ ይጀመራል ። ከደቂቃ በኋላ መኪና ይዞ የቆመ የሰንሰለቱ ተዋናይ ጋር ይደርሳሉ ። ባለ ሂጃቧ ውጪ ጉዳይ በየት በኩል ነበር የሚያስገባው ? ብላ ትጠይቃለች ። ተዋናዩም ግቡ ላድርሳችሁ ይላል ። ወደ ትወናው ቢሮ ጊቢ አድርሶ ያው ብሎ አውርዶ ይሄዳል ። በድራማው የተመለመሉ የወንድና ሴት ጥበቃዎች የት ነበር ብለው ይጠይቃሉ ይነገራቸዋል ። እዚህ ጋር የሚሰራውን ድራማ ለመረዳት ወደ ተለያዩ በጣም ጥብቅ የሆኑ የመንግስት ተቋማት ሲገባ ያለውን ሁኔታ ላስታውሳችሁ ። እንደ ሰላም ሚኒስቴር ፣ ደህንነትና መረጃ ፣ ኤር ፖርትና የመሳሰሉ ቦታዎች ሲገባ አንድ ሰው ወንድም ይሁን ሴት ወደ ውስጥ ለማለፍ ፍተሻ አልፎ ነው የሚገባው ። ፍተሻው ጋር ኤክስሬ ማሽን አለ ። ማንም ሰው በእጁም በኪሱም የያዘውን ማንኛውንም ብረት ነክ ነገር እንደ ሰአት ፣ ቁልፍ ጌጣጌጥ ፣ ቀበቶም ጭምር አውጥቶ በማሽኑ እንዲያልፍ አድርጎ ራሱም በሌላ ፈታሽ ማሽን አልፎ ይሄድና ያ በማሽን እንዲያልፍ ያደረገውን ንብረቱን ይወስዳል ። ከዚህ በኋላ ወደ መስሪያ ቤቱ ቢሮ ያመራል ። ይህ ታዲያ እነዚህ ድራማ ሰሪዮች እንዴት እንደሚጠቀሙበት እንይ : – ይህች ድራማ የሚሰራባት ምስኪን እህት በእነዚህ ተልእኮ በተሰጣቸው ሴት ፈታሾች ምንም ብረት ነክ ነገር ይዞ መግባት አይፈቀድም ስለዚህ ሰአት ፣ ሞባይል ፣ ጌጣ ጌጦችን በሙሉ አውጥተሽ በቦርሳሽ ውስጥ አድርጊ ትባላለች ። ምስኪኗ እህትም የተባሉትን በሙሉ በቦርሳው ውስጥ ያለውን ብርም ጭምር ታስረክባለች ። ምናልባት ፓስፖርትና የሚረጋገጠው ወረቀት ቦርሳው ውስጥ ካለ በፓስፖርቱ ውስጥ መቶ ብር ተደርጎ ይሰጣታል ። ወደ ተባለው ቢሮ ስትገባ ማንም የለም ትንሽ ቆዪ ይመጣሉ ትባላለች ። ይሁን እንጂ የሚመጣ የለም ለመጠየቅ ስትወጣ ዘበኛው ተቀይሮ ሌላ ነው ። ስትጠይቀው ቢሮ ገና ሰው ያልገባበት ባዶ ነው ። የምን የውጪ ጉዳይ ነው እንዲህ የሚብል ነገር አላቅም ይላል ። ‼ ኤምባሲ ከሆነ ድራማ ሰሪዮቹ በታክሲ ወደ ኤንባሲ የመጡ እህቶችን አዛኝ መስለው ኤምባሲው ከዚህ ለቋል ተብለን ነው ኑ ወደ አዲሱ ቢሮ አብረን እንሄዳለን በማለት የተለመደውን ድራማ ይሰራሉ ። ሴቶችን መሰረት ያደረገው ሿሿ ይህን ይመስላልና እህቶች ራሳችሁን ጠብቁ ። ወጪ ለመቀነስ ብላችሁ በታክሲ ከመሳፈር በሚታወቁ ታማኝ ራይዶች ሄዳችሁ ጉዳያችሁን ፈፅማችሁ በሰላም ተመልሳችሁ ተመጣጣኝ ዋጋ ብትከፍሉ ከአስደንጋጭ ዘረፋ ትድናላችሁና ለማንኛውም ተጠንቀቁ ። http://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.