cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አቡ አዒሻ العلم نور

የዚህ ቻናል ዋና አላማ ሱናን ማንገስ ሽርክን ማርከስ ነው!! የሱና መሻይኮችና የሱና ዳዒዎች የሚላክበት የዳዕዋ የደርስ ሴንተር ቻናል ነው ሐሳብ አስተያትን ያለምንም ጥበት እንቀበላለን ቅድሚያ ለተውሂድ በተግባር

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 387
المشتركون
+124 ساعات
+747 أيام
+32730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🔉አዲስ ወሳኝ  ሙሀድራ⤵ እለተ እሁድ ሙሀረም 1 /1/ 1446 ሂ /አ በውላውላ ሰለፍዮች ግሩፕ  Online ቀጥታ ሥርጭት የተደረገ ሙሀድራ 🕌 🎙በሸይኽ ሙሀመድ ሀያት (ሀፊዘሁሏህ) 📌ርዕስ ሰለ ተውሂድ አገብጋቢነት 📆 ┈➤ የተጠቀሱ ፈዋኢዶች📌 ┈➤ ሺርክና የአምልኮ ቦታዎች የአካባቢው ቃልቻ ነን ተብዮች ሀድራ የሚሉት ተውሂድን የሚያፈርስ ተግባር ⤴️ ┈➤ ዶሪሆችን /መቃብርን ጧዋፍ ማድረግ ነዘር/ ስለት ከአሏህ ውጭ እደማይፈቀድ እርድ ለአሏህ ብቻ እደሚገባ📌 📢【ሼር ይደረግ➷➷➷ @YweIaweIa_Groups https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
إظهار الكل...
record.ogg9.37 MB
╔══════ ❁✿❁ ══════╗      ❗️❗ተውሒድ የሌለው ሰው ❗️❗️         በዱኒያም በዛኛውም አለም                 ምንም የለውም !! ☑️ ተውሒድ ማለት⏩ አሏህን በኢባዳ አንድ ማድረግ መነጠል ማለት ነው።  ይህ ጉዳይ ትልቅ የሆነ የዲናችን መሰረት ነው ። አላህ መልክተኞቸን ﷺ የላከበት መጽሐፎችን ያወረደበት  አጋንትንም ሆነ እኛን የሰው ልጆች ወደ እዝች ምድር ያመጣን ለተውሒድ እንደሆነ  ጠንቅቀን ልናቅ ይገባል። አሏህም እንዲህ ይለናል  :- قال الله: ـ ﴿وَما خَلَقتُ الجِنَّ وَالإِنسَ إِلّا لِيَعبُدونِ ۝ ما أُريدُ مِنهُم مِن رِزقٍ وَما أُريدُ أَن يُطعِمونِ﴾ [الذاريات: ٥٦-٥٧] አሏህ እንድህ አለ፦ ( የሰው ልጆችንም ሆነ አጋንቶችን አልፈጠርኮቸውም እኔን ሊገዙኝ ቢሆን እንጂ )  አሁንም አሏህ እንዲህ ይለናል:- قال الله تعالى: ـ ﴿وَقَضى رَبُّكَ أَلّا تَعبُدوا إِلّا إِيّاهُ﴾ [الإسراء: ٢٣] ( እሱን እንጂ ላታመልኩ  ጌታህ ወሰነ ፈረደ።) አል ኢስራእ : 23 قال الله تعلى :- ﴿وَلَقَد بَعَثنا في كُلِّ أُمَّةٍ رَسولًا أَنِ اعبُدُوا اللَّهَ وَاجتَنِبُوا الطّاغوتَ﴾ [النحل: ٣٦] "አሏህን ብቻ ተገዙ ጣዖታትንም ራቁ የሚል  መልዕክተኛን ለእያንዳንዱ ህዝብ በእርግጥም ልከናል።" አነህል: 36 📨 ሁሉም የሏህ መልዕክተኞች ወደ ተውሂድ በመጣራት ላይ መጥተዋል እንደዚሁም ሁሉም መጽሐፎች ተውሒድን በማብራራትና እሷን የሚቃረናትና የሚያጓሏትን በመግለፅና በማብራራት ላይ ወርደዋል ። ሁሉም የሰው ልጂ በዚሁም ታዞል ። ከማንኛውም ነገር በፊት ይህን አሳሳቢና አንገብጋቢ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ። በተለይ አቂዳ ነክ የሆነን !     ምክነያቱም ተውሒድ የሰው ልጆች ባጠቃላይ በዱኒያም ሆነ በዛኛው አለም  ትልቅ  ደስታን የሚጎናፀፉበት ዋነኛው ምክነያት ነው። قال الله تعالى :- ﴿فَمَن يَكفُر بِالطّاغوتِ وَيُؤمِن بِاللَّهِ فَقَدِ استَمسَكَ بِالعُروَةِ الوُثقى لَا انفِصامَ لَها﴾ [البقرة: ٢٥٦] " በጣዖታት  የካደ በአሏህ ያመነ በእርግጥም አስተማማኝ /መበጠሻ/ የለላትን ገመድ ይዟል" ይላል አሏህ። 👌 ይህችን አቂዳ ያባከነ እና ያመለጠችው ⚠️  ሰው ስሜቱንና ባጢል /ውሸትን ከንቱን/  የሚይዝ  መሆኑ አይቀርም። ለመሆኑ  " ከሀቅ ቡኃላ ጥመት እንጂ  አይኖርምና።" قال الله تعلى:- (﴿ذلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الحَقُّ وَأَنَّ ما يَدعونَ مِن دونِهِ هُوَ الباطِلُ﴾ [الحج: ٦٢] " እሱ  አላህ እውነተኛው አምላክ ነውና ነው  ከሱ ውጭ የሚጣሩት ሁሉ እሱ ከንቱ ነው። " 🚫 እውነተኛውን ጌታ اللهን ከማምለክ የተዘናገሰ ተውሂድን የለቀቀ ሰው ሰው ጉዞው - አሏህ ይጠብቀንና - መመለሻዋ የከፋ ወደሆነው እሳት ይሆናል ። ✅ ነገር ግን አቂዳው 📚 አሏህ መልክተኞችን በላከበትና መጽሐፎችን ባወረደበት  አስተምህሮ  የገጠመ ከሆነ ! ይህቺ ትክክለኛና ሰላም የሆነች  ከአሏህ ቅጣት ነጃ  የምታወጣና በዱኒያም በኣኼራም አለም ደሰታን የምታስገኝ የስኬት መንገድን ይዟል ። 👌 ትክክለኛ ሰላም የሆነች አቂዳ /ተውሒድ/ ገንዘብን ፣ ደምን ሀራም  ታደርጋለች በሀቅ ሲቀር ። كمــا قال النَّبيﷺ :-" أُمرت أن أقاتل الناس حتَّىٰ يقولوا  لا إله إلَّا الله فإذا قالوها ، عصموا منِّي دماءَهم وأموالهم  إلّّا بحقِّهـا" رواهُ مــســلــم. "ሰዎች لا إله إلَّا الله እስኪሉ ድረስ ልጋደላቸው ታዝዣለሁ ፣ ካሉ ግን ደማቸውንም ሆነ ገንዘባቸውን ከኔ ጠበቁ / ሀራም ሆነች / በሀቋ ሲቀር " . 👍 እንደዚሁም በመጪው አለም ከአላህ ቅጣት ነጃ ታወጣለች ። روىٰ مسلم . عن جابر .... أن رسول الله. قال " من لقي الله لا يشرك بَه شـيئًا ، دخل الجنه ،ومن لقيه يشرك بـه دخـل النار " وفي "الصحيحين" من حديث عتبان بن مالك   :- فإن الله قد حرم علىٰ النار من قال لا إله إلا الله ، يبتغي بذالك وجَه اللهِ" " የአሏህን ፊት ፈልጎ  لا إله إلا الله ያለን ሰው ስጋ አሏህ በእርግጥም በእሳት እርም አደርጓል" ✅✅ እንደዚሁም ትክክለኛና እውነተኛ  አቂዳ  ያለው  ትንንሽ ወንጀል  እንኳ በስህተት ቢሰራ  🚫 በዚህ ትክክለኛና ሰላም በሆነ  አቂዳ አሏህ እንዲምረው ትልቅ ምክነያት ነው ። فقد روىٰ الترمزي وحسنه عن أنس رضي الله عنه قال سمعت رسول الله يقول " قال الله تعالىٰ يا ابن آدم ! إنك لو أتيتني بقراب الأرض خطايا ، ثم لقيتني لاتشرك بي شيئًا ، لأتيتك بقرابها مغفرة." " አንተ ያአደም ልጅ ሆይ! መሬትን ሊሚሞላ የቀረበ ወንጀል ይዘህ ብትመጣኝ, ከዛም  በኔ ምንንም ሳታጋራ  ከተገናኘህኝ, እኔ መሬትን የሚሞላ ምህረት ይዤ  እመጣህ ነበር። " ☑️ ይህን የአሏህን ምህረት ልናገኘ መስፈርት ተደርጎ የቀረበው  አቂዳ  ነው። ✅እንደዚሁም ትክክለኛ የሆነ አቂዳ ያለው  ሰው ሌሎች መልካም  ስራዎች ተቀባይነተ እንዲኖረው ያደርጋል ። قال  الله تعالى:- ﴿مَن عَمِلَ صالِحًا مِن ذَكَرٍ أَو أُنثى وَهُوَ مُؤمِنٌ فَلَنُحيِيَنَّهُ حَياةً طَيِّبَةً وَلَنَجزِيَنَّهُم أَجرَهُم بِأَحسَنِ ما كانوا يَعمَلونَ﴾ [النحل: ٩٧] "በአሏህ ያመነ ሲሆን  ከወንድም ሆነ ከሴት መልካም  ስራን  የሰራ በእርግጥም ጥሩ ህይወትን እናኖረዋለን  እንደዚሁም ሲሰሩ በነበሩት በተሻለ መልኩ ደሞዛቸውን  እንመነዳቸዋለን /እንከፋላቸዋለን" ) ይላል። ☑️በዚህ ተቃራኒ ትክክለኛ ያልሆነ የተበላሸ  ዓቂዳ ባጠቃላይ መልካም ስራን ሁሉ ገደል ታስገባለች። قال الله :-﴿لَئِن أَشرَكتَ لَيَحبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكونَنَّ مِنَ الخاسِرينَ﴾ [الزمر: ٦٥] "ብታጋራ ስራህ ይታበሳል ከከሳሪዎችም ትሆናለህ። "ይላቸዋል መልዕክተኛውን ﷺ ✅  ዓቂዳው በሽርክ  የተበላሸ የሆነ አካል  ጀነት ከመግባትና ማህርታን ከማግኘት ትከለክለዋለች ። ቅጣትን ታስፈርድበታለች እሳትም ውስጥ ዘውታሪ ይሆናል!!  አሏህ ይጠብቀን ?? قال الله تعالى:- ( إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا ) النساء (48) https://t.me/hussenhas
إظهار الكل...
አቡ አዒሻ العلم نور

የዚህ ቻናል ዋና አላማ ሱናን ማንገስ ሽርክን ማርከስ ነው!! የሱና መሻይኮችና የሱና ዳዒዎች የሚላክበት የዳዕዋ የደርስ ሴንተር ቻናል ነው ሐሳብ አስተያትን ያለምንም ጥበት እንቀበላለን ቅድሚያ ለተውሂድ በተግባር

የጁሙዓ ኹጥባ (ምክር))).mp35.05 MB
ኡስታዝ ኑረድን ከሀራ ጎንፎ.mp310.60 MB
ሸይኽ_ሰኢድ_መሀመድ_ከረምበር_ጎንፎ.mp35.78 MB
ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት ጎንፎ.mp38.54 MB
ሸይኽ ሁሴን ከረም ሀራ ጎንፎ.mp34.36 MB
ሸይኽ ሁሴን አባስ ወርቄ ጎንፎ.mp312.85 MB
በሰላም ከዋልንበት የዳዕዋ ዝግጅት ወሊላሂል ሃምድ በሰላም ለመለስ ችለናል ባማረና በሰመረ ቆርኬ ወረጋራ ጎንፎ መስጅዴ ፉርቃን ባማረ ባሽበረቀ ተውሂድን በማንገስ ሽርክን በማርከስ ሱናን በማስታዎቅ ቢዳዓን በማንኮታኮት አስፈላጊ ወሳኝ ወቅታውይ እርዕሶችን በምንዎዳቸውና በምናከብራቸው ብርቅየ መሻይኾቻችን ሃቅን ሲያስፋፋ ባጢልን በቅንጭላቱ ሲደፍኑና ሲንኮታኩቱ ውለዋል የተሰጣቸውን ሰአት በሚገባ ባማረ ግብ በመምታት ሽርክን ላወቁ ይበልጥ እንድርቁ ጭራሹኑ ላላወቁና ላልተጠነቀቁ በተጨባጭ ሲያሳውቁ  ሁጃንንና በቦታው ላይ መረጃን ሲጠቅሱና ሲዳስሱ ውለዋል ባረከሏሁ ፊኩም ጀዛኩሙሏህ ኸይረን እድሜና ጤና ይስጣቸው ይጭምርላቸው ያካባቢውም ወጣት ደስ በሚል አቀባበልና መስተንግዶ ሲሯሯጡ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ኡማውን ሲካድሙ ሃቂቀተን በርካታ ሰዎችን በተውሂድ መማረካቸውን በርግጥም ለማየት ችለናል ለብዙ ወጣቶቸ ወደ ሃቅ ለመመለስ ስበብ ሁነው ተገኝተዋል ለመልካም አቀባበላችሁና ለመስተንግዷችሁ እጅግ በጣም እናመሰግናለን እንወዳችሁ አለን በድጋሜ አላህ በሰላም በተሳሳይ መድረክና ካብሳ የምነገናኝ ያድርገን ሃቅን በሃቅነቱ አላህ ያሳየን ወደን የምንቀበልም ያድርገን ባጢልን በባጢልነቱ ያሳየን ጠልተን የምንርቀውም ያድርገን ሙሉ የድምፅ ፋይሎችን በዚህ ቻናል የሚለቀቁ ስለሚሆን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ👌 https://t.me/hussenhas
إظهار الكل...
አቡ አዒሻ العلم نور

የዚህ ቻናል ዋና አላማ ሱናን ማንገስ ሽርክን ማርከስ ነው!! የሱና መሻይኮችና የሱና ዳዒዎች የሚላክበት የዳዕዋ የደርስ ሴንተር ቻናል ነው ሐሳብ አስተያትን ያለምንም ጥበት እንቀበላለን ቅድሚያ ለተውሂድ በተግባር

ስላዳመጣችሁን አናመስግናለን ለዛሬ በዚሁ እንሰናበታለን
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.