የኔ ግጥም
الذهاب إلى القناة على Telegram
Welcome to our channel 🙏 Join my channel & enjoy poems. For any comment @Giyanna19 እንኳን ወደ ቻናሉ በደህና መጡ🙏 የተለያዩ :- ✍️ግጥሞችና ✍️ወጎች የሚለቀቁበት ቻናል ነው።
إظهار المزيد1 384
المشتركون
+124 ساعات
+37 أيام
+2830 أيام
أرشيف المشاركات
1 384
Repost from ፍሬያማ ሀሳቦች
(ከላይ የቀጠለ)
ልለው ነበር ግን አልቻልኩም።አንዴ አምኖኛላ እንዳላፈቀርኩ።
አልፈልግሞ አልኩት
ደነገጠ አይኑን እያስለመለመ በልመና አይነት እባክሽ እራሪልኝ በሚል አስተያየት እያየኝ ።ግን ለምን? አለኝ
ለምንም።ስለደከመኝ
ምኑ?
ሰዶ ማሳደዱ እውነቱን አፈረጥኩት።
መሳደዱን እሺ አሳደሽም ነበር?ቀጠለ
ነበር ድሮ ልጅ እያለሁ የእቃቃ ባሌን
ሳቀ
ደስ አለኝ አስቀየስኩ።
በመሀል እንኳን ደህና መጣሽ አለችኝ አንድ የውብ ፈገግታ ባለቤት ከጎኔ ቆማ።
ኦ ሳልነግርሽ በነገራችን ላይ ቤቱ የእሷ ነው
ባለቤቴ ነች ተዋወቁ ብሎኝ ደገፍ አለ።
ወቸው ጉድ ይህ ሁሉ ቃለ ምልልስ ታዲያ ለምን ተቀዳ 🙄😁
✍️ @Giyanna19
@FreamaHasaboch
@FreamaHasaboch
1 384
Repost from ፍሬያማ ሀሳቦች
አፍቅረሽ ታውቂያለሽ?
''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
ፀጥ ያለ ሬስቶራንት ወሰደኝ።የቤቱ ባለቤት ደን ልማት ሚኒስቴር ነበረች መሰለኝ።ዙሪያ ገባው በተክል ተንቆጥቁጣል።
እንደተለመደው አይነት ረብሻ የለበትም።ሁሉም በእራሱ አለም ነጉዷል።
ዝምታውን ለመስበር በሚመስል መልኩ ጋባዤ የቀረበለትን ማኪያቶ ፉት ብሎ እየተደገፈ አፍቅረሽ ታውቂያለሽ? ብሎ ጠየቀኝ።
ምነው ወንድም አለም ዝምታ እኮ አያስከፍልም ልለው ፈልጌ ነበር ግን ተወት አድርጌ ኧረ ምን በወጣኝ አልኩት
እስከ ዛሬ እዚህ እስክትደርሺ?አለኝ መልሶ በመገረም
የት ደረስኩ?መቼ ደረስኩ?ማን ጋር ደረስኩ?
ግራ ገባኝ።እስከ እዚህ የሚባልበት ደረጃ ላይ ነው እንዴ እድሜዬ ያለው ብዬ አሰብኩ።
እንግዲህ የአንደኛ አመት ልደቴ ሲከበር ከኋላዬ የተሰቀለው ወረቀት ላይ ዓመተ-ምህረት ነበረው እድሜዬን ልሳሳት አልችልም።ሌላ ነገር ማለት ፈልጎ ይሆናል ብዬ ከእድሜ ሀሳብ ወጣሁ ተውኩት ።
አዎ እዚህ እስክደርስ በመንገዴ ፍቅር አላየሁም።በተቃራኒው ጥላቻና መገፋት እንዲሁም መተፋትን አይቻለሁ። ምናልባት ፍቅር በሌላ መንገድ ሄዶ ይሆናል አልኩት።
ሳቅ አለ።ደስ ያለው ይመስላል።የብቻዬ አደረኩሽ አይነት የወኔ ሳቅ ነው።
ቲሽ! አመነኝ።ተናደድኩ እንዴት በቀላሉ ያምናል!ምን ጉድ ነው?😊 ቲንሽ ገፍቶበት ቢጠይቀኝ እኮ ለአምስት አመታት ያለማቋረጥ የኔ እንደማይሆን እያወኩ ስላፈቀርኩት ሰው የፍቅር ጀብዴን እነግረው ነበር።
እና አሁን ፍቅር በመንገድሽ ከመጣስ?አስከትሎ ጠየቀኝ
አንድ አይኑን አጥፍቼ፣አንድ እግሩንና አንድ ደሞ እጁን እሰብረዋለሁ።
ለምን?አለ
እኔም በአንድ አይኔ ጨፍኜ በአንዱ እንዳይ፣እንዳልደርስበት አንድ እግሬን ሰብሮ አንካሳ ስላረገኝ፣እንዳላቅፈው አንድ እጄን ስለሰበረኝ ።
✍️Giya
1 384
Repost from ፍሬያማ ሀሳቦች
ምን ብለሽ ፀልየሽ ነው?
''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
የምትገርም ሙሽራ አለች ከጎኔ የተቀመጠችው ቀጨጭ ጠቆር ያለች ልጅ።ጓደኛዬ አይደለችም።እንዲሁ ግን እንቀራረባለን።ለጓደኝነት ሩብ ጉዳይ አይነት ነገር።
ሁለታችንም የምንዋዳት ጓደኛችን ማግባቷን እና አዲስ ቤት ገዝታ መግባቷን አስመልክቶ ቤት ለእንቦሳ ለማለት ነበር አካሄዳችን።
ከጎኔ የነበረችው ቀጫጫ ልጅ ሴና አፏም፣እጇም አያርፍም።የሰራ አካላቷ ይቁነጠነጣል እረፍት የላትም።
በመጨረሻ ሙሺሪት ጉድጉድ ብላ ያቀረበችውን ምግብ ተመግበን እንዳበቃን ቡና ማፍላት ጀመረች።
ሴና አጋጣሚዎች አምልጠዋት ሌላ ወሬ ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብላ ሳባ ግን ምን ብለሽ ፀልየሽ ነው እንዲህ አይነት ትዳር የሰጠሽ?አለቻት
ሳባ ያገባችው በተክሊል ነው።የቤታቸው ሳሎን ውስጥ በተክሊል የተጋቡበት ፎቶ በትልቅ ፍሬም ተሰቅሏል።
ብዙ ነገር ነው የፀለይኩት አለች ሳባ ቀበል አርጋ።
(ለምሳሌ?)
በየመንገዱ ድንጋይ እያሞቀ ከሚላከፍ ወንድ ፍቅር እንዳይዘኝ ፀልያለሁ፣ድንገት የወንድ ጓደኛዬ ለፍቅር ተመኝቶኝ ነገሮችን አፈጣጥኖ ከንፈሬን ሊስመኝ ሲንደረደር አምላኬ ሆይ ከዚህ ሰው የመኪና ጎማ በሚያህል ከንፈሩ 😁 ከመሳም የማመልጥበትን ጥበብ ስጠኝ ብዬ ፀልዬ አምልጫለሁ ፣
አንዳንድ መንገድ አመጣሽ ፍቅር ላይ ጥሎኝም ያውቃል።የማንም መንገደኛ ስሜት ማብረጃ ከመሆን እንዲታደገኝ ፀልያለሁ፣
በዚያው ልክ ፈጣሪ ሆይ ለእኔም ለአንተም የሚታዘዘን ትሁት ሰው ስጠኝ ብያለሁ።
በቤትክ እከብር ዘንድ ከርካሽ ቦታ እንዳልገኝ ፣የወደቀም እንዳያነሳኝ ለምኛለሁ።ምን አለፋሽ ብቻ
ብዙ ነው ልመናው ብላ ደመደመደች።
ለሴና ይሄን መስማት የሞት ያህል ነበር።አፈቀርኩሽ ያለ ሁሉ ደረት ኪሱ ከቷት የምትዞር አለሌ ናት።
ምን ስትል ጠየቀች አልኩ በልቤ።ዘንዶ ጎሮጓሪ የእናቱን ሞት ይረዳል ነው የሚሉት አይደል!።
ቁስሏ የተነካ ይመስል ፊቷ ፍም መሰለ።
እንደዛ እንዳልሆነች ታውቀዋለቻ።ይህ ፀሎት ለእሷ አይሰራም።ለእሷ የሚሰራው ፀሎት ወደ ቀልቤ መልሰኝ የሚለው ነው።
የሰው ልጅ ግን መልሱ የሚያስደነግጠውን ጥያቄ ለምን ይጠይቃል?!!! አይዞሽ ሴና!
✍️Giyanna
Join & Share 🙏
@FreamaHasaboch
@FreamaHasaboch
@FreamaHasaboch
1 384
አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?
አሁንም ግፍ አይበቃሽም
ዘንድሮም ለምለም ትያለሽ
ካቀፍሽው ቅጠል ባለፈ
የለመለመ ምን አለሽ?
ካቻምናም አምናም መተሻል
አቅፈንሽ አጥነን ደግሰን
አመትሽ ውበቱ ላይቆይ
እያደር ሊያተራምሰን
አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?
አምና ተስፋ አስደረግሺኝ
ደክሜ ቤቴን ሰራሁኝ
አልቅሼ ልገባበት ስል
ይፈርሳል ሁሉ ሰማሁኝ
አሁንም ተስፋ አልቆረጥኩም
ቃልሽን ስመላልሰው
አመትህ ተባርኳል ብለሽ
የላክሺኝ እንደ ሞኝ ሰው
ስታገል ከማይሽር ህይወት
መቀመቅ ነፍሴን ሲውጣት
ወደፊት ፈቀቅ እያልኩኝ
ሞት ልቤን እንዳይለውጣት
"አበባ አየሆሽ" አትበዪኝ
አበባ አልቸገረኝም
ዘፈንሽ አንገሽግሾኛል
ጨዋታሽ አይሰማኝም
በያመት ደምቀሽ ስትመጪ
ህፃን ልጅ ለምትመስዪው
ግጥሙን በምነግርሽ ቃል
ስትዘፍኚ አስተካክዪው
"የሀገሬ ልጆች ውጡ በተራ
ቅስም ሰብሬ ሰው እስክሰራ
እንኳን ሰውና የለኝም እድል
ሁሌ መጣለው አመት ላጎድል
አመት አጉድዬ ስገባ ቤቴ
ደስታ ይሰማታል የእንጀራ እናቴ"
አደዪ
የሞት ጉዳዪ
"ኡኡ" በዪ
እንደዚህ ብለሽ ዝፈኚ
ግጥሙን አስተካክለሽው
በቃ አንቺም እንዳገሬ ሰው
ጊዜን ነው የተማመንሽው?
"ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ
ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ"
ሆሆሆሆ!
አታፍሪም ደግሞ
ልክ እንደ ንፁህ እንዳልበደለ
ተስፋሽ ምስኪኑን እየገደለ
ከዘመን ዘመን ማትለወጪ
ጉድ ያዘለ አመት አቅፈሽ ምትሰጪ
ሆ ብለሽ መጣሽ?
ሆ ብለሽ ውጪ!
ለተድላ ሳይሆን
ለሞት ዋዜማ ፡ እያስጨፈርሺኝ
በመጣሽ ቁጥር
ሆ የምልልሽ ፡ ሞኝ አደረግሺኝ?
አሁን ንገሪኝ
ስለ አመትሽ
ይብስብኛል ወይስ ድናለው?
ዘፈኑን ተዪ ፡ ያንቺን ስሞታ ለምጄዋለው
ባለእንጀሮችሽ በተራ ገቡ
አዝማች አባትሽ ሌላ አገቡ
እንጨቱን ሰብረሽ ቤት እስክትሰሪ
ለእንጀራ እናትሽ ሳትናገሪ
እድጅ አድረሻል ኮከብ ስትቆጥሪ
እኔ ምስኪኑ
ምን ያገባኛል ስላንቺ ኮከብ
ምን ያገባኛል የእንቅልፍሽ ማጠር
የኔ ችግር ነው ወሰን የሌለው
የኔ ስቃይ ነው የማይቆጠር
እህት አበባ ፡ እህት አበባ
እህት አበባ ስትልሽ ከርማ፤
ጥላሽ ብትሄድም በሀምሌ ጭለማ
እኔ ላይ "አዬዬ".. አትበዪብኝ፡
ለኔ አመቱ ነው የጨለመብኝ።
ተይ ባለጊዜ..
ተይ እንቁጣጣሽ..
ሀገር ጉድ አቅፈሽ ፥
ሁሌ እየመጣሽ፦
እንኩ አትበዪን፡
ሀዘን ቁስላችን ፡ ድኖ ሳይገግም፤
ካምናው የሚብስ
ሌላ አዲስ አመት ..አንፈልግም!
@mikiyas_feyisa
@mikiyas_feyisa
