cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Amhara Revolution

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
6 265
المشتركون
+2624 ساعات
+637 أيام
+52430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ትኩረት ለጎጃም አባይ በርሃ ! /////                            \\\\ ከሰሞኑ በደምብ ቀምሶ የተመለሰው የጁላ ሰራዊት አሁንም በሌላ አቅጣጫ ለመግባት እየሞከረ ስለሆነ ትኩረት እንዳይለየን ለማሳሰብ እንወዳለን። ጠላት የፋኖ ዋና ቤዝ ሆኖ የቆየውን የአባይ ሸለቆ ዙሪያ ገባ ቀበሌዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መስዕዋት ከፍሎ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዝግጅት ያደረገበትን ኦፕሬሽን ጀምሯል። ለዚህ ኦፕሬሽን በተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች በለብ ለብ አሰልጥኖ ያስመረቀቸውን ከ20ሺ በላይ ሰራዊት ጨምሮ  ከሁሉም ክልሎች የተውጣጣ ልዩ ሀይሉን አግተልትሎ በአጠቃላይ ያለ የሌለ ኃይሉን ይዞ  ለአንድ ዙር ውጊያ ቢያንስ ለዘጠኝ ቀናት እየተዋጋ የሚያቆየውን ስንቅ እና በቂ ተተኳሽ ይዞ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከኦሮሚያ ክልል በሚያዋስነው ደጀን ወረዳ በኩል አባይ በርሃ/ሸለቆ ገብቷል፡፡ ጠላት የያዘው  እቅድ ሰፊ ነው፡፡ በአሳለፍነው አንድ አመት ካየነው ሁሉ የተለየ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል።  ይህን ኦፕሬሽን የተለየ  የሚያደርገው በደጀን ጉብያ በርሃ ተጀምሮ ወደ ደጋማ ስፍራዎች ለመስፋፋት ከፍተኜ ፍላጎት መኖሩ ነው። አገዛዙ የአባይን ሸለቆ ለመቆጣጠር ዛሬ ሰኔ 19/2016 የጀመረው ኦፕሬሽን ከተሳካለት በሁለት አቅጣጫ ውጊያውን አስፋፍቶ ህዝብ እየጨፈጨፈ ለመቀጠል አልሞ እየሰራ ነው፡፡ ይኸውም፦ 1ኛ.  ከደጀን ጉበያ ቀበሌ ተነስቶ ወደ ሸበል በረንታ-ለምጨን (እነማይ) -ገደብ (እናርጅእናውጋ) - ሶማ (እናርጅ እናውጋ) - ወሪያ መስቀል (እነብሴ ሳርምድር) - የጎንቻ፣ሁለትእጁ እነብሴ እና ጎንጅ ቆለላ ወረዳዎችን አካሎ ጭስ አባይ ይደርሳል። በዚህ ቀጠና የወሎ እና  ቤጌምድር አባይ ሸለቆ አዋሳኝ ወረዳዎችንና ቀበሌዎችን ያካትታል። 2ኛ. ከደጀን ጉብያ ተነስቶ ወደ አዋበል - (ኮርክ) ባሶሊበን - አነደድ - ሞተራ (ጎዛምን) - ስላሴ( ደብረ ኤሊያስ) - ዋድ እየሱስ (ደንበጫ) - መንዝ (ጃቢጠህናን) - ቁጭ(ቡሬ) ያጠቃልላል። የአምሐራ ፋኖ በጎጃም ሁሉም ክፍለጦሮች፣ ብርጌዶች፣ሻለቃዎች በተጠንቀቅ ቆመው፣ በአንድ ትንፋሽ ፣ በአንድ ተናባቢ እቅድ፣ በሆታ፣በእልልታ፣ በጥሩንባ ተጠራርቶ መራራው ክፉ ቀን በድል ሊሻገረው ይገባል። ጠላት የጀመረው የመጨረሻ ዙር የማጥቃት እንቅስቃሴ ከእስካሁኑ ሁሉ የተለየ ባህሪ ስላለው በተቀናጀ ክንድ መክቶ በመልሶ ማጥቃት ማደባየት ያስፈልጋል ፡፡ አገዛዙ በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ እና ባህርዳር ከተሞች ሆዳም አምሐራዎችን ከየወረዳው ሰብስቦ ያደረጋቸው ስብሰባዎች በህዝባችን ላይ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ለመፈጸም  አመላካች ነበር። አገዛዙ ለሰላም እጃችንን ብንዘረጋም ሰሚ አጥተናል፣ ተው ብለን ብናስተምርም፣ብንመክርም ሰሚ አጥተናል ከዚህ በኋላ እምቢ አልገዛም ያለውን ህዝብ በሀይል፣በጉልበት ለማንበርከክ ወደ እርምጃ ገብተናል የሚል አቅጣጫ ተይዞ የገቡበት ነው።  ህዝባችን በዚህ ጨካኝ አገዛዝ የታቀደለትን የጭካኔ  ጥግ አውቆ በነቂስ ወጥቶ የድርሻውን አስተዋጽኦ የማድረግ የሞራል ግዴታ ላይ ነን።  ለዚህ ጊዜ ያልሆነ ትጥቅ፣ ለዚህ ጊዜ ያልሆነ ጉልበት ለዚህ ጊዜ ያልሆነ እውቀት ለዚህ ጊዜው ያልሆነ ሀብት  በአፍንጫችን ይውጣ።  @ጃዊሳ ሚድያ
إظهار الكل...
👍 6
ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ መግለጫ ድርጅታችን ከ19/10/16 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ተዘግቶ የነበረው መንገድ ወደ መደበኛ ስራው እንዲመለስ ክፍት የተደረገ መሆኑን እየገለጽን በነዚህ መንገድ በተዘጋባቸው ቀናቶች የተሳካ ኦፕሬሽን ተካሂዷል። ከነዚህ መካከልም ፦ 1. ከባህርዳር ስምሪት ተሰጧቸው የደህንነት ኦፕሬሽን ሊሰሩ ወደተለያዬ አካባቢ ሊሄዱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። 2. የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር አዴትና ባህርዳር ከተማ የደፈጣና ልዩ ኦፕሬሽን ተሰርቷል። 3. የአማራ ፋኖ በጎጃም በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ጉበያ እና ደብረወርቅ ላይ ልዩ ኦፕሬሽን ተሰርቷል ። 4. የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ ክፍለ ጦር ኮርክ ገብቶ የነበረውን የጠላት ጦር ተመትቶ እንዲወጣ ማድረግ ተችሏል። 5. የአማራ ፋኖ በጎጃም የመብረቁ ተፈራ ክፍለ ጦር፤  የደጋ ዳሞት ብርጌድ የተሳካ የማጥቃት ኦፕሬሽን ተደርጓል በተጨማሪም ሙሉ የሚሊሻ ሃይሉን ማፍራረስ ችሏል። 6. ልዩ ተልዕኮ ተሰጦት ሲያደራጅ የነበረው የባንዳው አረጋ ከበደን ወንድም ጨምሮ የአገዛዙ ምንጣፍ ጎታች  ካድሬዎችንም በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። 7. የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ደብረ ማርቆስ በመግባት በርካታ ጠላትን መምታት እና መማረክ ተችሏል። 8. የአማራ ፋኖ በጎጃም: ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ፣ ግዮን ብርጌድ  ሰከላ ላይ ባለው የጠላት ሃይል ልዩ የማጥቃት እርምጃ መውሰድ ተችሏል። 9. የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክፍለ ጦር ገረመው ወንድ-አውክ ብርጌድ ብራዳማ ላይ ጠላትን አይቀጡት ቅጣት መቅጣት ችሏል 10. በአዋበል መብረቁ ብርጌድ በየሰንበት ቀጠና ጠላትን ከሁለት ጊዜ በላይ ያጠቃ ሲሆን : ከ12 በላይ ሚሊሻዎች ከጠላት ወደ ፋኖ የተቀላቀሉ ሲሆን አገዛዙ በግዳጅ የዘረፈው ከ600,000 ብር በላይ ይዘው ወጥተዋል። በአምበር ተድላ ጓሉ ብርጌድና የቦቅላ ዓባይ ብርጌድም  ልዩ ልዩ  የተሳካላቸው ኦፕሬሽኖችን ማካሄድ ተችሏል። በዚህ የተናደደው የጨፍጫፊው አገዛዝ ስልጣን አስጠባቂ ቡድን ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ በተደጋጋሚ ባሳየበት መልኩ ዛሬም እንደትናንቱ ንጹሃንን በደጀን ጉበያ ህፃናትና እና እናቶችን ከቤት እያስወጣ ረሽኗል። የተከበርከው የአማራ ህዝብ፤ የድርጅታችን አባላት፤ ደጋፊዋችና አጋር አካላት  አገዛዙ የአማራን ሕዝብ ተቋማዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈፀሙን የቀጠለ ሲሆን ድርጅታችንና አመራሩ በሚሰጠው የትግል አቅጣጫ መሰረት በተለመደው የአንድነትና የቆራጥነት ወኔ ተላብሳችሁ ከበፊቱ በጠነከረ መንገድ ዝግጅታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ስንል እናሳስባለን ። ጦርነት በመጥመቅና የኢትዮጵያን ሕዝብ በማጋጨት የግፍ ስልጣኑን ለማራዘም እየተጋ ያለው በተለይ ደግሞ የአማራነት ጠላት የሆነው አናርኪስቱ የአብይ አህመድ ስብስብ የራሱን ስውርና ግልጽ አባላት ሰብስቦ ሲያሰለጥን ከሰነበተ በኋላ "የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል" በሚል እራሱን በማደራጀት ስለአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች፣ ስለሰላምና ድርድርን የተመለከተ የተኩስ አቁም ስለማድረግ መግለጫ ሰጥቷል። ጠላት የራሱን ፍላጎትና ዓላማ "የገለልተኝነት ስም ሰጥቶ ባደራጀው የራሱ ኮሚቴ" ስም መግለጫውን ከማስነበቡ በስተቀር የተለየ አቋም አልወሰደም። የስብሰባው ተሳታፊዎችም ሆነ ከመካከላቸው የወከሏቸው 15 አባላት ማንነታቸውን ጠንቅቀን የምናውቃቸው መሆናቸውን እናሳውቃለን። በዚህም የተደራጀው ካውንስል "የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ለጦርነት አያበቁም" ሲል የራሱን ማንነት ያጋለጠና የካውንስሉን ባለቤት ማንነት ማጋለጡን ተመልክተናል፤ በአማራነትና በፍላጎቱ ላይ ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ቁስልና ደም ላይ ተሳልቋል። ይህ አስተሳሰብ የአናርኪስቱ ብልጽግና ስርዓት መሆኑ ስለሚታወቅ ማንንም የማደናገር አቅም የሌለው ከንቱ ሙከራ መሆኑን እንረዳለን። ጠላት በየአቅጣጫው ዘመቻውን አጠናክሮ የቀጠለና ያለውን ሙጣጭ የሠራዊት ኃይል በተጨማሪ እያሰማራ ነው። በሌላ በኩል ደጋግሞ ስለድርድር የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ከመንዛት አልፎ አባላቱንና ደጋፊዎቹን በገለልተኛ ሰላም ካውንስል ስም በማደራጀትና የሚዲያ ዘመቻ በመክፈት ለማጭበርበር እየሞከረ ይገኛል። የአማራ ሕዝብ ትግል ወዳጅም ሆነ ጠላት በሚያውቀው በአደባባይ የተገለጠ በፍትሐዊ ምክንያት ላይ የቆመ እና ሕዝባዊ ዓላማ ያነገበ በመሆኑ በኢትዮጵያ ስርነቀል ለውጥ በማምጣት ሕዝባዊ መንግስት ከማቋቋም መለስ ሊያቆመው የሚችል ማጭበርበር አይደለም የጠላት ኃይልም የለም። በድላችን ደጃፍ ላይ ቆመን ለአፍታ የማንዘናጋ መሆናችንን የወንጀለኛው አብይ አህመድና ተቀላቢዎቹን ስልጣን ለማራዘም ንፁኃንን በግፍ እየጨፈጨፈና በምላሹ ዋጋውን እየሰጠነው የሚገኘው በምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ የሚመራው የአገዛዙ ሠራዊት በቂ ምስክር ነው። ጠላት የሕዝብን ትግል ለመጥለፍና እድሜውን ለማራዘም ለምድ የለበሱ አባሎቹን ማሰማራቱ የዛሬ ብቻ ሳይሆን የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ስለሆነ በዚህ የሚጭበረበር እንደሌለ እሙን ነው። ጀግናው ፋኖ ሠራዊታችን፣ የተከበረው የጥላቻ በትርን እየመከተ ያለው ሕዝባችንና ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ደጋፊዎቻችንና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ መሰል የማወናበድ ፕሮፓጋንዳዎችን በመረዳት ጆሮዎቻችንን እና ዐይኖቻችንን የትኩረት አቅጣጫዎቻችን ላይ ብቻ እንድናደርግ እያሳሰብን በድርጅታችን በኩል በጽናት ወደዓላማችን ጫፍ የምንገሰግስ መሆኑን እንገልፃለን።     ድል ለአማራ ህዝብ!      ድል ለፋኖ!                                                           አዲስ ትውልድ፤ አዲስ ተስፋ፤ አዲስ አስተሳሰብ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
إظهار الكل...
👍 23🔥 2😁 1
إظهار الكل...
[Episode 3 ] Amhara Property Confiscation Law

Throughout history, dictators, including the Nazis, have exploited laws to justify their actions. Today, governments like that of Aby and the Oromo Prosperity Party use legal mechanisms to confiscate property from perceived enemies, such as the Amharas and Diasporas. These laws are crafted to facilitate a significant wealth transfer from one ethnic group to another. Be a Member to our channal

https://www.youtube.com/channel/UCeO6Cwa_piOXYazOJwcEhfg/join

👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
ትግላችን << የአማራን ጦርነት >> የማስቆም ሳይሆን የመጨረስ ነው። ሠራዊቱ የብልጽግና ፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ የጦር ወንጀል ፈጽሟል። እናም በየትኛውም አግባብ አደራዳሪም ሆነ የሰላም ሀሳብ አቅራቢ ገለልተኛ ሀይል አይደለም። መሆንም አይችልም።
إظهار الكل...
👍 19😁 3👎 1
➩ አማራን ለማፅዳትና ለማጥፋት ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸው አካላት ትርክትም፣ ሕጋዊ ሥርዓትም፣ አሠራርም አበጅተው በአገሪቱ ክፍሎች እያጠቁት እና እያፀዱት የመቀጠላቸው እውነት ዛሬ በከፍተኛ ደረጃ እየተፈፀመ መሆኑ ግልፅ ነው። "ከተጣልኩበት አነሳኝ፤ ማዕረግም አንበሸበሸን፣ መሬት ገንዘብና ሀብትም ሰጡን"  ያሉ የጠላት ፈረሶችም በአስፈፃሚነት መሰለፋቸው በእኛ ዘመን የምናየው ባንዳነት ነው። ➩ አበባው የአማራ ታጋይን እናፀዳዋለን እናጠፋዋለን ያለው አማራን ነው። "እናፀዳዋለን" የተባለው የአማራ ትግል የስለት ጫፍ ፋኖ የአማራ ሕዝብ ነው። ይሔንን እሱም ያውቃል።  "እናጠፋዋለን" ብሎ አመት ሙሉ የዘመተውና የጨፈጨፈው እና ዛሬ ለሕልውናው እየታገለ ያለው አማራ "ሽፍታና ዘራፊ" እያለ ሊያጣጥል የሚሞክረው አይደለም። "እናፀዳዋለን" ፥ "እናጠፋዋለን" የተባለው ፦    ▪ በአራቱም አቅጣጫ "ድረስልን" ተብሎ በራሱ ሠልጥኖ ትጥቅ አሟልቶ፣ ትጥቅ ማርኮ የተዋጋውን የአማራ ወጣት ፋኖ ነው !!    ▪በአንድ ወቅት ቁጥሩ በ18 ክፍለጦር ተደራጅቶ ፥ በትግሉ ወንበራቸውን ያተረፈላቸው፣ በሴራ የበተኑትና ዛሬ "አታለው ወሰዱት" የሚለው ልዩ ኃይልን ነው።    ▪ ከመደበኛ ፖሊስነት ወጥቶ ወንድሞቹን የተቀላቀለውን የፖሊስና አድማ በታኝ ኃይል ነው።    ▪ ራሱ አበባው ከሚመራው ተቋም ከፍተኛ ኮለኔሎች ሳይቀሩ የወገን ጥቃት አንገብግቧቸው የሕዝቡን ትግል የተቀላቀሉ በ10ሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን እና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን ነው።    ▪የአገዛዙን ጠላትነትና ፀረ-አማራነት ተረድቶ እየታገለ ያለውን አርሶአደር ነው    ▪ የወገኑ ጥቃት አንገብግቦት ከዩኒቨርሲቲዎችና ከፍተኛ ተቋማት ወጥቶ ሕዝቡን የሚያታግለውን ዶክተር ፣ ኢንጅነር ፣ ሲቪል ሠርቫንት ነው   ▪የአበባው ሠራዊት የሚፈፅመውን ግፍ አይቶ በረሃ የገባውን የአማራ ወጣት ነው። በአጠቃላይ አበባው ታደሰ "እናፀዳዋለን" ፥ "እናጠፋዋለን" ያለው የአማራን ሕዝብ ነው ‼ አበባው ይሔንን ካለ አመት ሆነው ፤ የሚችለውን እየጨፈጨፈ ነው ፤     ➩ በማጀቴ፣ በደብረኤልያስ፣ በባሕርዳር፣ በመርዓዊ፣ በሳሲት፣ በደብረማርቆስ፣ በጋይንት፣ በእስቴ፣ በሸዋሮቢት .... ጨፍጭፏል ፥ አፅድቷል !!     ➩ የአማራን ባለሀብት ከአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ አፅድቷል፣ አጥፍቷል።     ➩ የአማራን ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ከፖለቲካ መድረኩ አፅድቶ በየማጎሪያው እያሰቃየ ነው፣ በየአገሩ እንዲሰደዱ እያደረገ ነው። ከትግል ሚናቸው አፅድቷል፣ አጥፍቷል።    ➩ የአማራ ቤተሰቦች ከ'ሸገር' ፣ ከወለጋ፣ ከአዲስአበባ ፣ ከልዩ ልዩ አካባቢዎች እና ሥራቸው አፅድቷል፥ አጥፍቷል፥ ቀጥሏል ‼ የአማራ ሕዝብም አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኖ  እየታገለ አመት ሆነው። እስከድል ጫፍ ከጠላት ጋር ይፋለማል ‼ ድል ለአማራ ትግል !! #AmharaRevolution
إظهار الكل...
👍 1
00:16
Video unavailableShow in Telegram
4.94 MB
🤪 2
ፖለቲካችንን ከስደት መልሶ መትከል ❗️ - የፋኖ አብዮታዊው ትግል አንደኛው መገለጫ ትግሉን ከፖለቲካዊ ስደት መመለስ ነው። በዚህም ትግሉን በዋነኝነት በህዝቡ እና በመሬቱ ላይ መትከል ነው። | ትግሉ በህዝብ መካከል እና መሬት ላይ እየተደረገ ነው። የትግል መርሁም ሆነ ትግል የሚደረግበት አግባብ ከዚህ አንጻር የተቃኘ ነው። የመብት፣ የጥቅም እና የፍላጎት መለኪያው እንዲሁም የልከኝነት ማነጸሪያዎች <<ህዝብ እና መሬቱ>> ላይ በመትከል ይመሠረታል። | በአንድ ህዝብ እና መሬት ውስጥ የሚኖረው አንድ ድርጅት ነው። ያልተከፋፈለ ጥያቄ፣ ያልተከፋፈለ መብት፣ ያልተከፋፈለ ጥቅም በአንድ ህዝብ እና መሬት ላይ ይደረጋል። የአማራ ህዝብ በተለያዬ ስፍራ እና ቅርጽ ውስጥ መገኘቱ እውነት ነው። ሆኖም በፖለቲካ ዲስኩራችን ውስጥ " የአማራ ህዝብ " የምንለው ፖሊቲ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነው። ይህ ፖለቲ ትግሉ በቀዳሚነት ተቀብሎ እና አላማውን ተሸክሞ የያዘ በመሆኑ ትግሉን ከፖለቲካዊ ስደት መልሶ በህዝቡ ውስጥ መትከሉ አስፈላጊ፣ ተገቢ እና ጠቃሚ ነው። አሁን ያለው የፋኖ አደረጃጀትም ይህን መሠረት ያደረገ ነው። የአደረጃጀቶች በአንድ መሪ እና ጥላ ድርጅት ውስጥ መግባት የዚህ መትከል አካል እና የሂደቱ ውጤት ነው። | ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ በቀድሞው መስመር ውስጥ ያሉ ስብስቦች አሉ። እነዚህ አካላት የስደተኛው ፖለቲካ ፈረሶች በመሆን ከአብዮታዊው የትግል መስመር አፈንግጠዋል። ስደተኛው ፖለቲካ አንዱ መሠረታዊ ችግሩ የአማራን መሠረታዊ ጥያቄ በሚገፉ እና መሻቱን በሚያሳንሱ "ኢትዮጲያኒስት" ሀይሎች መያዙ ነው። ቡድኑ የአማራ ብሄርተኝነት ጠላት እንደ መሆኑ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ መግባት የአማራን ጥያቄ፣ መብት እና ጥቅም ማነወር ነው። የአማራ ፖለቲካ ለረጂም አመታት የዚህ ፖለቲካዊ ስደት ተጠቂ ሆኖ ከርሟል። | ሆኖም የወቅቱ አብዮታዊ ትግል የአማራ ፖለቲካ ከዚህ ክፉ ዕስራት ተፈቶ ትግሉ የአማራን ጉዳይ ብቻ ያስቀደመ የማድረግ ነው። በዚህ ወቅት ትግሉ የፖለቲካዊ ስደት ተጠቂ እንዲሆን የሚያደርግ አደረጃጀት፣ አሰላለፍ እና ስብስብ የትግሉ ጠላት ነው። | #ስድስቱ የፋኖ አደረጃጀቶች፤ የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በወሎ፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ እና የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ዕዝ የአብዮታዊ ትግሉ መሪ ቡድኖች ናቸው። በዚህ ወቅት ከዚህ ውጭ ያሉት ስብስቦች በጸረ አብዮታዊ መርህ የተሰለፉ አደረጃጀቶች ናቸው። ይህን አይነት አደረጃጀት እና ስብስብ ኢ አማራዊ እና ትግል ቀልባሽ አሰላለፍ ነው። ይህ ጠላትነት ነው። እናም ቀልባሽነትን መከላከል፣ አንጃ መቺነትን ማነወር ብሎም መሠል ስብስቦችን በጥንቃቄ መነጠል ይገባል። ይኸው ነው ! #AmharaRevolution
إظهار الكل...
👍 3
የአማራ ትግል የተላላኪ ፈረሶች መነሀሪያ አይደለም፤ አይሆንም'ም❗️ - የፋኖ አብዮታዊው ትግል አንደኛው መገለጫ ትግሉን ከፖለቲካዊ ስደት መመለስ ነው። በዚህም ትግሉን በዋነኝነት በህዝቡ እና በመሬቱ ላይ መትከል ነው። | ትግሉ በህዝብ መካከል እና መሬት ላይ እየተደረገ ነው። የትግል መርሁም ሆነ ትግል የሚደረግበት አግባብ ከዚህ አንጻር የተቃኘ ነው። የመብት፣ የጥቅም እና የፍላጎት መለኪያው እንዲሁም የልከኝነት ማነጸሪያዎች <<ህዝብ እና መሬቱ>> ላይ በመትከል ይመሠረታል። | በአንድ ህዝብ እና መሬት ውስጥ የሚኖረው አንድ ድርጅት ነው። ያልተከፋፈለ ጥያቄ፣ ያልተከፋፈለ መብት፣ ያልተከፋፈለ ጥቅም በአንድ ህዝብ እና መሬት ላይ ይደረጋል። የአማራ ህዝብ በተለያዬ ስፍራ እና ቅርጽ ውስጥ መገኘቱ እውነት ነው። ሆኖም በፖለቲካ ዲስኩራችን ውስጥ " የአማራ ህዝብ " የምንለው ፖሊቲ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነው። ይህ ፖለቲ ትግሉ በቀዳሚነት ተቀብሎ እና አላማውን ተሸክሞ የያዘ በመሆኑ ትግሉን ከፖለቲካዊ ስደት መልሶ በህዝቡ ውስጥ መትከሉ አስፈላጊ፣ ተገቢ እና ጠቃሚ ነው። አሁን ያለው የፋኖ አደረጃጀትም ይህን መሠረት ያደረገ ነው። የአደረጃጀቶች በአንድ መሪ እና ጥላ ድርጅት ውስጥ መግባት የዚህ መትከል አካል እና የሂደቱ ውጤት ነው። | ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ በቀድሞው መስመር ውስጥ ያሉ ስብስቦች አሉ። እነዚህ አካላት የስደተኛው ፖለቲካ ፈረሶች በመሆን ከአብዮታዊው የትግል መስመር አፈንግጠዋል። ስደተኛው ፖለቲካ አንዱ መሠረታዊ ችግሩ የአማራን መሠረታዊ ጥያቄ በሚገፉ እና መሻቱን በሚያሳንሱ "ኢትዮጲያኒስት" ሀይሎች መያዙ ነው። ቡድኑ የአማራ ብሄርተኝነት ጠላት እንደ መሆኑ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ መግባት የአማራን ጥያቄ፣ መብት እና ጥቅም ማነወር ነው። የአማራ ፖለቲካ ለረጂም አመታት የዚህ ፖለቲካዊ ስደት ተጠቂ ሆኖ ከርሟል። | ሆኖም የወቅቱ አብዮታዊ ትግል የአማራ ፖለቲካ ከዚህ ክፉ ዕስራት ተፈቶ ትግሉ የአማራን ጉዳይ ብቻ ያስቀደመ የማድረግ ነው። በዚህ ወቅት ትግሉ የፖለቲካዊ ስደት ተጠቂ እንዲሆን የሚያደርግ አደረጃጀት፣ አሰላለፍ እና ስብስብ የትግሉ ጠላት ነው። | #ስድስቱ የፋኖ አደረጃጀቶች፤ የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በወሎ፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ እና የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ዕዝ የአብዮታዊ ትግሉ መሪ ቡድኖች ናቸው። በዚህ ወቅት ከዚህ ውጭ ያሉት ስብስቦች በጸረ አብዮታዊ መርህ የተሰለፉ አደረጃጀቶች ናቸው። ይህን አይነት አደረጃጀት እና ስብስብ ኢ አማራዊ እና ትግል ቀልባሽ አሰላለፍ ነው። ይህ ጠላትነት ነው። እናም ቀልባሽነትን መከላከል፣ አንጃ መቺነትን ማነወር ብሎም መሠል ስብስቦችን በጥንቃቄ መነጠል ይገባል። ይኸው ነው ! #AmharaRevolution
إظهار الكل...
የአዲስአበባ ሕዝብ በኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች እንዲዳኝ ... ይሔን የሚደነግገው አዋጅና ሌሎችም ሰሞኑን እየወጡ ያሉ አዋጆች ከፋሽስታዊው ዘረኛ አገዛዝ የሚጠበቁ የጥቅለላ አላማዎች አካል ናቸው። እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ነዋሪ ከከተማው እና ከዙሪያው አፈናቅሎ ቀጥሏል። ብልጭልጭ የዐይን እርካታ ( "Something that has nothung to do with the peoples stomach") ፕሮጀክት የዘረኛ አላማውና የአዲስአበባ ጥቅለላ አካል ነው። ይሔ ሕግም የዚያ አካል ነው። ነፃነትን የመረጡ ኬንያውያን አገዛዝን ታግለው ተደመጡ ፣ ባርነትን የመረጡ ኢትዮጵያውያን አፓርታይድም ፋሺዝምም ናዚዝምም እየረገጣቸው አሉ !!
إظهار الكل...
🔥 5
በሲሳይ ሙሉ የተፃፈ ስለ ችግራችን ምልክቶች (Symptoms) እያወራን መሰረታዊ ችግራችን (Underlying cause) እንዳንረሳው፡፡ መሰረታዊ ችግራችን እነዚህ ሶስቱን ማጣታችን ይመስለኛል፡፡ 1⃣የጋራ ተቋም (Institution) 2⃣የጋራ አቋም (Position) 3⃣የጋራ መርህ (Principle) ተቋም (Institution) ተቋማዊ በሆነ አሰራር በስሌት እና በጥናት ተደግፎ ጥቃት ሚደርስበት ህዝብ ተቋማዊ በሆነ አሰራር በስሌት እና በጥናት ተደግፎ ተመጣጣኝ ምላሽ ካልሰጠ ምንም ጠብ ሚል ነገር አይኖርም፡፡ በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ አሰራር በግልሰቦች አቅም ልክ የሚወስን ስራ ነው ሚሰራው፡፡ ሰዎች በጎ ሀሳብ ኖሯቸው እንኳን በአቅም ውስንነት ምክንያት ማድረግ የፈለጉትን ላያደርጉ ይችላሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውም ግልሰብ ሁልጊዜም በጣም ጥሩ ስራ ቢሰራም የአይኑ ውሃ አላማረኝም ብሎ ሚቃወመው አለ፡፡ ክፉ ስራ ቢሰራም ከአንተ ወዲያ ማንም የለም ብሎ የሚያንገሰው የራሱ ቡድን አለ፡፡ አሰራራችን ተቋማዊ እስካልሆነ ድረስ ይሄ trend ይቀጥላል፡፡ አንድ አሰራር ተቋማዊ ሆነ ማለት የትኛውም ስራ ሚሰራው መተዋወቅን ፤ ጓደኝነትን ወይም ሌላ አይነት ግንኙነትን መሰረት  አድርጎ አይደለም ማለት ነው፡፡ ሁሉም እንደችሎታው እና ስጦታው አስተዋጽኦ የሚያበረክትበት መድረክ ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ በአጭር ደቂቃ በግልጽ ቋንቋ የአማራን ችግር ለዓለም አቀፉ ማ/ሰብ ማሰማት በሚፈልግበት መድረክ ማን ቢሄድ ይሻላል ብለን በችሎታቸው ብቻ መዝነን ምንልካቸው ይኖሩናል ማለት ነው፡፡ አንድ ጥናት መስራት ቢያስፈልግ “የምናውቀው እክሌ ይስራው ሳይሆን የሚችለው እክሌ ይስራው” እናላለን ማለት ነው፡፡ ሁሉም ስራውን በሚጠበቀው ልክ መስራት እና አለመስራቱን የምንመዝንበት ሁሉንም ሚያስማማ መመዘኛ መስፈርት ይኖረናል ማለት ነው፡፡ ከዚያ ስንተችም ስናመስግንም መመዘኛ መስፈርቱን ብቻ መሰረት አድርገን ይሆናል ማለት ነው፡፡ አቋም (Position) በየትኛውም መድረክ አንድ የአማራን ጉዳይ እወክላለሁ ሚል ግልሰብ/ቡድን ጉዳዩን Passionately ሊያምንበት እና በኩራት ሊቀበለው ይገባል፡፡ አንተ ያቀለልከውን አሞሌ ማንም አይቀበልህም፡፡ አንተ ያላመንክበትን አማራነት ማንም አይገዛህም፡፡ አንተ በደንብ ያልገባህን ነገር ለሌላው ማስረዳት አትችልም፡፡ በዚህ ላይ የማያወላዳ አቋም መያዝ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው፡፡ ተቋም ሲኖር የሚመራበትን ግልጽ አቋም ስለሚያስቀምጥ ነገሩን ያቀለዋል፡፡ መርህ (Principle) ሁለት ሰዎች/ቡድኖች ተመሳሳይ ስህተት ሲሰሩ ለአንዱ ከራራን መርህ የለንም ማለት ነው፡፡ ጥራ ሲሰሩ አንዱን ብቻ ለይተን ካሞገስንም ያው ነው፡፡ መርህ ከሌለን ሁሌም Reactive የሆነና በግልሰብ አስተያየቶች ዙሪያ ሚያጠነጥን Opinion-based የሆነ ደካማ ስራ እንሰራለን፡፡
إظهار الكل...
👍 17
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.