Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
الذهاب إلى القناة على Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
إظهار المزيد213
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-430 أيام
أرشيف المشاركات
የወለጋ ካርድ
~
የወለጋ ካርድ ያልኩት በአማራ ፖለቲከኞችና አጋፋሪዎቻቸው ክልሉ ውስጥ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን የሚያጋልጡ ድምፆችን ለማፈን የሚጠቀሙበትን አፍ ማስያዣ ስልት ነው። እያንዳንዱ ሙስሊሞች ላይ የሚደርስ ጥቃት በተዘገበ ቁጥር "ወለጋ ውስጥ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲፈፀም የት ነበራችሁ?" ይላሉ።
* በጎንደር ሙስሊሞች ላይ የደረሰ ጥቃት ሲዘገብ "ወለጋ ..." ይላሉ።
* በባህርዳር ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲወራ ይህንኑ የወለጋ ካርድ ይመዛሉ።
* የሞጣ ግድያ ቢዘገብ "ወለጋ ..." ይላሉ።
* የእንፍራንዝ ደረሶች ግድያ ቢዘገብ የተለመደውን የወለጋ ካርድ ይመዛሉ።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች፣ ዝርፊያዎች፣ እገታዎች፣ ማሳደዶች፣ መስጂዶችን ማቃጠል በተዘገቡ ቁጥር ያለ መታከት ይህንኑ ካርድ ይመዛሉ። ሂሳባቸው አጭር ነው። ወለጋ ላይ የደረሰው ጥቃት በቂ ሽፋን ስላልተሰጠው እኛ ስንገድልም፣ ስናፈናቅልም፣ ስናግትም፣ ስንዘርፍም ተቃውሞ ቀርቶ ኮሽታ ሊሰማ አይገባም ነው። እንዲያውም እንደ ተበዳይ ነው የሚተውኑት። "የኛ ማጥቃት ለምንድን ነው የሚራገበው? ደመ መራራ ነን። ነገር ይገንብናል" አይነት ነው ጨዋታው። "አማራ ክልል ኮሽ ሲል ይራገባል" ይላሉ። ያ ሁሉ በጎንደር፣ በደባርቅ፣ በእንፍራንዝ፣ በእስቴ ፣ በቢቸና፣ በሞጣ፣ በባህር ዳር፣ ... የደረሰው መስጂዶችን ማቃጠል፣ የበርካታ ሙስሊም ግድያ፣ እገታ፣ ... ሁሉ ጢኒኒጥ ኮሽታ ብቻ ናት። መስጂድ እንደ ደመራ አንድደው መጨፈራቸው ራሱ እዚህ ግባ የማይባል ተራ ነገር ነው ፣ እንዲሁ ኮሽታ ብቻ። የትኛውም ነገር ይድረስ "አማራ ክልል ውስጥ ኮሽ ሲል... " እያሉ ጥቃቱን ተራ ኮሽታ አድርገው ነው የሚገልፁት። አላህ አናታቸው ኮሽ ያድርገውና።
ከዚያ እኛ ብንበድልም የወለጋው ከኛ ስለሚበልጥ የኛን ብዙም አታስጩሁት ነው የሚሉት። በክልሉ ሙስሊሞች ያነጣጠሩ ጥቃቶች በተዘገቡ ቁጥር ይህንን ካርድ መምዘዝን በቃ ንቃት አድርገውታል። አላማው የተቃውሞ ድምፆችን ማፈን ነው። ሳይወራ፣ ሳይዘገብ መጨረስ። በዚህ አይነት የማንሰማቸው ስንት በደሎች እንደሚኖሩ ማሰብ ይቻላል።
በነዚህ መሰሪዎች ለተሸወዳችሁ ሙስሊሞች ሁሉ! ለመሆኑ በደሉ ምን ሲደርስ ነው "አሁንስ በዛ!" የምትሉት? ነው ወይስ እንዲሁ እያሉ ሁሉንም በየተራ ቢጨርሱም አትነቁም? ለይቶ ማራገብ አለ ካላችሁ የጎደለውን በመሙላት ላይ ስሩ እንጂ በሙስሊም ደም ቁማር ለሚሰራ እባብ ለምን ትወግናላችሁ? የኦሮሚያው ችግር ሽፋን ካላገኘ እናንተ ዘግቡት። "ለምን የኦሮሚያ ሲሆን ...?" የሚላችሁ ሲኖር ነው "ምነው የአማራ ብቻ..." የሚባለው። እንጂ እንዴት በዘር መሰላል ተንጠላጥላችሁ እምነታችሁን ለሚያረክስ፣ ወገኖቻችሁን ለይቶ ለሚያጠቃ አካል ጠበቃ ትሆናላችሁ?! ወላሂ ይሄ የሞኝነት ጥግ ነው።
= Ibnu Munewor
+4
Friday prayer today from the blessed Al-Aqsa Mosque, may Allah protect our brothers and sisters there and everywhere around the world
⭕️ የተጨነቀች ብዕር ጥያቄ አለኝ ትላለች። የጥያቄዋን መልስ የሚያውቅ ካለ ይንገራት!!
ወንድም እህቶቻችሁ ስህተት ላይ ሆነው፣ የሚጎዳቸውን ነገር እያደረጉ.....
እናንተ ከስህተታቸው ለመመለስ ስትታገሉ፤ አይ አሻፈረኝ ብሏችሁ ያውቃሉ!?
የነሱ ህይወት አሳስቧችሁ ግን እነሱ ህይወታቸው ሰያሳስባቸው ስህተት ላይ ሲወድቁቧችሁ ከፍቷችሁ ያውቃል⁉️ ..... አዝናችሁ ታውቃላችሁ!?
▮ ባይተዋርነት ተሰምቷችሁ ያውቃል⁉️
◆ በነዛ አህት ወንድሞቻችሁ ተስፋስ ቆርጣችሁስ ታውቃላችሁን!?
➤ ሰው ከስህተቱ ተመለስ ስትሉት እሱ ደግሞ ስህተት መሆኑን እያወቀ ስህተቱ ላይ የሙጥኝ ሲሉ፤ የእውነት ግን አያስከፋም⁉️ ..... በአላህ ግን ልብ አይሰብርም!?
ummalife.com/ReshadMuzemil
ሃሺም ብን ኡርዋ - አላህ ይዘንላቸውና- ስለ ፈጠራ እና ስሜት ተከታይ ሰዎች ሁኔታ ሲገልጹ፡-
“ሰዎችን በዲን ውስጥ ስለፈጠሩት አዲስ ነገር አትጠይቃቸው፣ ለዛ መልስ አዘጋጅተዋልና። ነገር ግን ስለ ሱና ጠዩቋቸው፣ ሱናውን አያቁትምና።”
قال هاشم بن عروة- رحمه الله - في وصفه لأحوال أهل البدع والأهواء: "لا تسألوا الناس عما أحدثوه في الدين، فقد أعدوا لذلك جواباً، ولكن سلوهم عن السنة فإنهم لا يعرفونها"
🔖"…ሸዋል ስምንተኛው ቀን የአብራሮችም(የጥሩዎች) ሆነ የፋጂሮች(የጠማማዎች) በዓል አይደለም።ይህንኑ ቀን በዓል ነው ብሎ ማንም ሊያስበው አይገባም። ከዲን መገለጫዎች አንዱንም ቢሆን በዚሁ ቀን መተግበር አይገባም።"
📚【ኢኽቲያራት አልፊቂሂያ ሊኢብኑ ተይሚያ ገፅ :199】
ጠያቂ፦ «እንደት ነው ወደ እናንተና ወደነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ የዒልም ደረጃ የምንደርሰው?»
መልስ፦ «እኔ ዒልም የለኝም፤ እንደናንተው ነኝ። ሸይኽ ኢብኑ ባዝ አዎ ዓሊም ናቸው። ነገር ግን መማር አለብን።»
ይህን የሚሉት የዘመናችን ታላቁ ዓሊም በቂየቱ-ስ'ሰለፍ ሸይኽ ዶ/ር ሷሊሕ ፈውዛን ኢብኑ ዐብዱ-ል'ሏህ አል-ፈውዛን ናቸው አላህ እድሚያቸውን ከመልካም ሥራ ጋር ያርዝመውና!
አንዳንዱ ተራ አስተማሪውን ኡስታዝ ካላልከው፣ ሸይኽ ካላልከው፣ ኡስታዝ ተብየው ራሱ "ኡስታዝ" የሚለው ስያሜው ሳይጨመር በስሙ ከተጠራ የተናቀና ክብሩ የጎደለበት የሚመስለው፣ የሆነ ፈታዋ ሲጠየቅ የማያውቀው ከሆነ አላውቅም ብሎ መመለስ የሚከብደው፣ አለፍ ሲል በድፍረት የመሰለውን የሚናገር… ስንትና ስንት ራሱን አካባጅ ባለበት ተጨባጭ፤ ትክክለኛ ዐሊሞች እንዲህ ናቸው። የሚገባቸው ቢሆን እንኳ ራሳቸውን ያስተናንሳሉ።
||
t.me/MuradTadesse
ግጥም ስለ ዘመናችን ሙሓዲሥ አል-ዐለማህ ሸይኽ ሙሐመድ ናስሩዲን አል-አልባኒይ (ረሒመሁ-ል'ሏህ)
||
t.me/MuradTadesse
ኢስቲቃማ💌💌💌💌💌💌💌
ለኢስቲቃማ የሚረዱ ነገሮች..........................
አጭር ምክር በኢስላም ጥላ ስር ላሉ ወንድሞችና እህቶች
በሸይኽ_ኢልያስ_አህመድ(ሀፊዘሁላህ)
ቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ይበሉ
https://t.me/yeilyaswedaje
ወገንተኛ መሆን ለዲን እንጂ ለሀገር አይደለም .. ነብያችን ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም ለዲናቸው ሲሉ እሳቸው ዘንድ ትልቅ ቦታ ያለውን ሀገራቸውን መካን ትተው ወደ መዲና ተሰደዋል ..
ለሰዎች አዘኔታህን ስታሳያቸው እነሱ ያስባሉ እየለመንካቸው እንደሆነ!
እሺታህ ባበዛህ ጊዜ ጅል መስለህ ትታያቸዋለህ።
ወዳጄ አንተ በምታደርገው ነገር ከሰዎች መልካም ምላሽን ከጠበቅክ እጅጉኑ ትጎዳለህ፣ ታዝናለህ፣ ክፉኛ ትቆስላለህ!
ስለዚህ ሰዎችን ተወት አድርጋቸውና የጌታህን ነገር አደራ!
ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
