ar
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

الذهاب إلى القناة على Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

إظهار المزيد
213
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-430 أيام
أرشيف المشاركات
Subhana Allah Stunning nature and green carpets along the Haramain Expressway. ሱብሀን አላህ በሀረማይን የፍጥነት መንገድ ላይ አስደናቂ ተፈጥሮ እና አረ
+2
Subhana Allah Stunning nature and green carpets along the Haramain Expressway. ሱብሀን አላህ በሀረማይን የፍጥነት መንገድ ላይ አስደናቂ ተፈጥሮ እና አረንጓዴ ምስሎች።

🔍ጀግና የሚያስብልህ የቀልብህ እንጂ የአካል ጥንካሬህ አይደለም። 📍ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል። «ጀግንነት የሰውነት አካል ጥንካሬ አይደለም። አንድ ሰው በአካል ጠንካራ ሆኖ ቀልቡ ደካማ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ጀግንነት ማለት የቀልብ ጥንካሬና ፅናት ናት።» 📖[ الفَتَاوَى العِرَاقِيَّة || ١ / ٢٨٧ ] 👉ከሰዎች መካከል በአካል ጠንካራ እንዲሁም ወጣት የሆኑ ነገር ግን በአስተሳሰብና በሞራል ያረጁና የደከሙ አሉ። 👉ሌሎች ደግሞ በአካል ሲታዩ ያረጁና የደከሙ ነገር ግን በሞራልና በአስተሳሰብ ወጣት የሆኑና የጠነከሩ አሉ። ♦️አንተስ ከየትኞቹ ነህ? ➡️ ለዚህም ነው ውዱ ነብያችን ፦ ጀግና ብሎ ማለት ታግሎ የሚጥል ሳይሆን በንዴት ጌዜ ነፍሱን የሚቆጣጠር ሰው ነው ብለው ያሉት። =

🎉 የገና በአል እና ሙስሊሞች (ክሪስማስ) 🪄የገና በአል ይዘት ምንድን ነው? 🪄ክርስቲያን ወገኖቻችንንስ እንኳን አደረሳችሁ ማለት? 🪄ፅንፈኛ ወይም ወግ አጥባቂ ልኩ ምንድን ነው? 🪄የእስልምናን ዳር ድንበር ከማስከበር ጋር ከክርስቲያን ወገኖቻችን ጋር መኗኗር እንዴት እንደምንችል ምላሽ የያዘ አዲስ ቪዲዮ 💡በሸይኽ ዑስማን አል ኸሚስ 👉ከድምፅ ትርጉም ጋር ⭐ሌሎችም ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ሟር ማድረግን አትሰስቱ! 

☞አላህን በመታዘዝ ፍራው በመፍራትም ታዘዘው ☞እጆችህን ከሙስሊሞች ደም ጠብቅ ☞ሆድህን ከንብረታቸው ጠብቅ ☞ ምላስህንም ክብራቸውን ከመንካት ጠብቅ #አቡበክር_ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ። https://u
☞አላህን በመታዘዝ ፍራው በመፍራትም ታዘዘው ☞እጆችህን ከሙስሊሞች ደም ጠብቅ ☞ሆድህን ከንብረታቸው ጠብቅ ☞ ምላስህንም ክብራቸውን ከመንካት ጠብቅ #አቡበክር_ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ። https://ummalife.com/ReshadMuzemil

☞አላህን በመታዘዝ ፍራው በመፍራትም ታዘዘው ☞እጆችህን ከሙስሊሞች ደም ጠብቅ ☞ሆድህን ከንብረታቸው ጠብቅ ☞ ምላስህንም ክብራቸውን ከመንካት ጠብቅ #አቡበክር_ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ። https://ummalife.com/ReshadMuzemil

በታላቁ ፍንዳታ ውስጥ እንዲህ አይነት ሂደትና ቅደም ተከተል የለም። ፍንዳታ ውስጥ ምን አይነት ስርአትና ቅደም ተከተል ይኖራል? ደግሞም ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት በሳይንሱ ባዶ ህዋ እንጂ ሰማይ የሚባል በቁጥር 7 የሆነ አካል የለም። በኢስላም ግን ያለ ምሰሶ አላህ በቁድራው ያንጣለላቸው 7 ግዙፍ ሰማያት አሉ። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል:- { خَلَقَ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ بِغَیۡرِ عَمَدࣲ تَرَوۡنَهَاۖ} {ሰማያትን ያለምታዩዋቸው አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ።} [ሉቅማን: 10] { ٱللَّهُ ٱلَّذِی رَفَعَ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ بِغَیۡرِ عَمَدࣲ تَرَوۡنَهَاۖ} {አላህ ያ ሰማያትን የምታዩዋት አዕማድ ሳትኖር ያነሳት ነው።} [ረዕድ: 2] እነዚህን እውነቶች ይዘን ስንመለከት በአንዳንዶች የሚደረገው የቁርኣን አንቀፆችን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ እየተረጎሙ "ታላቁን ፍንዳታ" ለማስለም መንደፋደፍ ተሸናፊ ስነ ልቦና የፈጠረው የከሸፈ ልፋት ነው። ደግሞስ በቁርኣን ውስጥ የተጠቀሰው ሰማይና ምድር ቀድሞ የተጣበቁ ነበሩ ማለት እነሱ እንደሚሉት 'The whole universe is an infinite mass and nearly a zero volume matter ነበር' ማለት አይደለም። ሰዎቹ ያለ ጥርጥር ቁርኣንን ያላግባብ እየመነዘሩ ነው። የቁርኣኑ አንቀፅ የሚያወራው ስለ ሰማያትና ምድር ብቻ ነው። እንዲሁ ከbig bang ጋር ለማዛመድ ነው ሌሎች ፍጥረታትን አብረው የሚጨፈልቁት። ከሰማያትና ምድር መፈጠር በፊት ጊዜና ቦታ (time & space) አልነበረም ማለት ግልፅ ቅጥፈት ነው። ይህንን ነው ወደ ቁርኣን የምታስጠጉት? በነገራችን ላይ "ታላቁ ፍንዳታ" /The big bang/ ከበርካታ ሳይንቲስቶች ጠንካራ ትችት አስተናግዷል። የምሁራን ኢጅማዕ አለበት የሚለው ጩኸት ነጭ ውሸት ነው። ይህንን እውነታ ሌላው ሁሉ ቢቀር ጉግልን በስሱ የፈተሸም የሚያረጋግጠው ነው። ሲጀመር እነሱም ዘንድ ንድፈ ሃሳብ (theory) እንጂ ያለቀለት እውነታ አይደለም። እንዳልኩት ይሄ "ዐቂዳ" መሰረተ-ቢስ ንድፈ ሃሳብ እንደሆነ የተናገሩ ብዙ ሳይንቲስቶች አሉ። ለምሳሌ ያክል Halton Arpን እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል። በሳይንሱ ዓለም ስሙ የገነነ፣ ብዙ ዓለማቀፍ ሽልማቶችን ያገኘ ነው። ከመሆኑም ጋር የ"ታላቁ ፍንዳታ" አከርካሪ ላይ ደግሞ ደጋግሞ ብርቱ ምት አሳርፏል። ሌሎችም ብዙ አሉ። ይህን የማነሳው ሳይንሳዊ "ግኝቶችን" እንደ ወረዱ ከመቀበል፣ የተረጋገጡ እውነታዎች አድርጎ ከማመን፣ አልፎም ከቁርኣን ጋር ለማዛመድ ከመሞከር በፊት ቢያንስ እዚያው እነሱው ሰፈር ስላሉ ሙግቶች ዳሰሳ ብናደርግ መልካም እንደሆነ ለመጠቆም ነው። አንዳንዶች በሳይንስ ስም የሚቀርቡ ሙግቶችን ሳያኝኩ ለመዋጥ የፈጠኑ ናቸው። እነዚህ "ግኝቶች" በሚነቀፉ ጊዜ ይረበሻሉ። ጭንቀታቸው ይገባኛል። እነዚህን "ግኝቶች" ስለነቀፍን ሃይማኖታችን አደጋ ላይ የሚወድቅ እየመሰላቸው ነው። ይሄ የዋህነት ነው። በመጨረሻም የምለው:- 1ኛ፦ ሃይማኖታችን ከተረጋገጡ እውነታዎች ጋር ፈፅሞ አይጋጭም። ስለዚህ ስጋት አይግባን። የሚጋጭበት ቦታ ከገጠመን ወይ "ግኝቱ" fact አይደለም። ወይ ሸሪዐዊ መረጃዎችን በትክክል አልተረዳንም። 2ኛ፦ አንድ ግኝት ከተገኘ በቃ ተገኘ። ግኝት በተገኘ ቁጥር "ቁርኣንም ውስጥ ተጠቅሷልኮ" እያሉ አጉል መዘባረቅ አይገባም። የግድ እያንዳንዱ ግኝት ቁርኣን ውስጥ እንዲኖር አይጠበቅም። ቁርኣንኮ የሳይንሳዊ እውነታዎች መዘርዘሪያ መፅሀፍ አይደለም። ይሄ ቀርቶ ሶላት፣ ፆም፣ ሐጅ፣ ... ዒባዳዎች እንኳ ሙሉና ዝርዝር አፈፃፀማቸው ቁርኣን ውስጥ የለም። 3ኛ:- በሳይንስ ስም የሚነገሩ "ግኝቶች" ሁሉ ያለቁና የተረጋገጡ እውነቶች አይደሉም። ስንት "ግኝቶች" በዘመናት ውስጥ ተቀይረዋል? እነሱ በቀየሩ ቁጥር ተፍሲራችንን ልንቀያይር ነው ወይ? 4ኛ:- በሳይንስ ስም የሚነገሩ "ግኝቶች" ሲነቀፉ አርካኑል ኢስላም የተነኩ ያህል አንደግጥ። የሰዎች የምርምር ውጤቶች እንጂ መለኮታዊ ወሕይ አይደሉምኮ! እዚያው ከጎናቸው ብዙ የሚነቅፉ ሳይንቲስቶች ባሉበት ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ ሲብስ ደስ አይልም። 5ኛ፦ ከአንዳንድ ሳይንሳዊ "ግኝቶች" ጀርባ ሰዎችን ከሃይማኖት ለማራቅ የታሰቡ ያደፈጡ ሴራዎች ይኖራሉ። ችኩል ድምዳሜ ከመስራት በፊት ረጋ ብሎ ዓሊሞች ምን እንደሚሉ ማየት ይገባል። የ"ታላቁ ፍንዳታ" "ግኝት" አላማም በፈጣሪ መኖር ከነ ጭራሹ የማያምኑ ሰዎች "እና ፈጣሪ ከሌለ ፍጥረተ ዓለሙ እንዴት ተገኘ?" ለሚለው ፈታኝ ጥያቄ መሸወጃ ሆኖ የቀረበ ሰይጣናዊ እሳቤ ነው። ስለዚህ ጥንቃቄ ይኑረን። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 7/2014) የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor

"ታላቁን ፍንዳታ" - የማስለም ግብግብ =============== ሰሞኑን የአሜሪካው የህዋ ሳይንስ ምርምር ተቋም (NASA) በጀምስ ዌብ ቴሌስኮፕ የተወሰዱ የህዋ ፎቶዎች ናቸው በማለት ምስሎችን መልቀቁን ተከትሎ በሳይንቲስቶች የሚቀርበውን "ታላቁ ፍንዳታ" (The big bang) ላይ የተመሰረተውን የፍጥረተ አለም አጀማመር ንድፈ ሃሳብ ቁርኣን ውስጥ እንደተጠቀሰ አድርገው በቁርኣን አንቀፆች ላይ ደፋር ትንታኔ የሚሰጡ ሰዎችን እያየን ነው። ለዚህም መነሻ የሚያደርጉት ተከታዩዋን አንቀፅ ነው:- (أَوَلَمْ يَرَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَنَّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ كَانَتَا رَتْقًا فَفَتَقْنَاهُمَا) {እነዚያም የካዱት ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መሆናችንን አያውቁምን?} [አንቢያእ: 30] የቁርኣኑን መልእክት ያዙና ቀጥሎ ያለውን ሃሳብ ታዘቡ እስኪ። <<በጥቅሉ ሰማይ የሚለው ቃል Space/ህዋን እና Astronomical object's/ ስነ-ፈለካዊ ቁስ አካላት የሚለውን ይወክልልናል። ምድር የሚለው ቃልም Galaxy/የከዋክብቶች ክምችት እና Nebula/ድብዝ ስብስብ ከዋክብት መሬትን ጨምሮ ለተዋቀሩበት Matter መገለጫ ነው።>> ይሄንን እርስ በርሱ የሚዋጋ የተቀዣበረ ትርጓሜ ተመልከቱ። ይሄ እጅግ አሳፋሪ ትንታኔ ነው፡፡ አንድ ነገር ልጠይቅ። በአንቀጿ ውስጥ የተጠቀሰው ምድር (الْأَرْضَ) ትርጓሜው ይሄ ነው? በታሪክ የትኛው የኢስላም ሙፈሲር ነው Galaxy/የከዋክብቶች ክምችት እና Nebula/ድብዝ ስብስብ ከዋክብት ሁሉ ምድር ተብሎ ይጠራል ያለው? ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! ይሄ ብቻም አይደለም የታላቁ ፍንዳታ አማኞች ዘንድ ሰማይ ማለት ህዋ / Space እንጂ እራሱን የቻለ ግዙፍ አካል አይደለም። ኢስላማዊው ግንዛቤ ይሄ እንዳልሆነ ሁሉም የሚያውቀው ነው። ለምሳሌ ያህል እነዚህ ተሸናፊዎች ያላግባብ ከሚመነዝሯት አንቀፅ አለፍ ብሎ እንዲህ የሚል እናገኛለን፦ { وَجَعَلۡنَا ٱلسَّمَاۤءَ سَقۡفࣰا مَّحۡفُوظࣰاۖ } {ሰማይንም (ከመውደቅ) የተጠበቀ ጣራ አደረግን፡፡} [አንቢያእ: 32] አያችሁ? ሰማይ እራሱን የቻለ ግዙፍ አካል እንጂ እነሱ እንደሚረዱት ባዶ ህዋ አይደለም። በዚያ ላይ በቁጥር 7 እንደሆኑ ነግሮናል። { ٱللَّهُ ٱلَّذِی خَلَقَ سَبۡعَ سَمَـٰوَ ٰ⁠تࣲ وَمِنَ ٱلۡأَرۡضِ مِثۡلَهُنَّۖ} {አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም እንዲሁ መሰላቸውን (ፈጥሮአል)።} [ጦላቅ: 12] ሰማይንም ምድርንም ቁርኣን ውስጥ ከተረጋገጠው አውጥተን ከተረጎምን በምን አግባብ ነው ለዚህ አይነት ቅብዥርዥር ያለ 'ዐቂዳ' የቁርኣን አንቀጾችን የምንጠቀመው? የ"ታላቁ ፍንዳታ" አማኞች ዘንድ የፍጥረተ ዓለሙ መነሻ የአንዲት በአይን እንኳ የማትታይ ከatom ያነሰች እጅግ ደቂቅ ነገር ነች። ይቺ ደቂቅ ነገር እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ ታምቃ ኖራ ስትፈነዳ ጊዜ ይሄ ግዙፍ ፍጥረተ ዓለም ተገኘ ይላሉ። ከዚች ደቃቅ ነገር ምን ምን ተገኘ ይላሉ መሰላችሁ? - ብዛታቸው በቁጥር የማይገለፅ እልቆ መሳፍርት (infinite) ፍጥረተ ዓለሞች ተገኙ። - ከነዚህ ውስጥ አንዱ ፍጥረተ ዓለም (univers) ብቻ በቢሊየን የሚቆጠሩ ጋላክሲዎች አሉት። - አንዱ ጋላክሲ ብቻ (Milky Way የሚባለው) ፀሐይን፣ በርካታ ፕላኔቶችንና በመቶ ቢሊዮን የሚቆጠሩ ከዋክብት ይዟል ይላሉ። ይህን ሁሉ ጉድ ነው ከአንዲት ነጥብ እንኳ ከማታክል ነገር ፍንዳታ ተነስቶ ተፈጠረ የሚሉት። ከዚህ ፍንዳታ በኋላ ነው ጊዜና ቦታ (time & space) ተገኘ የሚሉት። ለዚህ ተረት (ኹራፋ) ነው እንግዲህ "ሰማያትና ምድር የተጣበቁ ነበሩ፤ ለያየናቸው" የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ የሚጠቅሱት። ሱብሓነላህ! ይሄ ምን የሚሉት ድፍረት ነው? አንዳንዶች ይሄ አካሄዳቸው ሲነቀፍ "እኛ ከቁርኣን ጋር ያዛመድነው የተረጋገጠን ሳይንሳዊ እውነታ እንጂ፣ ያልተረጋገጠን ንድፈ ሃሳብ አይደለም" ይላሉ። የቱ ነው የተረጋገጠው ሐቅ? * "ፍጥረተ-ዓለሙ ሁሉ በአንድነት እምቅ ብሎ የተጠቀለለ፣ የታጨቀ፣ የታፈገ አንዲት ትንሽ እኑስ ቅንጣት ነበር" የሚለው ነው የተረጋገጠው ሐቅ? * "ይህ እኑስ በውስጡ ምንም አይነት አተም መዋቅርም ሆነ ቅጥ አልነበረውም" ማለት ነው የተረጋገጠው ሐቅ? * ይሄ ግዙፍ ዓለም፣ ይሄ ፍፁም የሆነ የፈለክ እንቅስቃሴ ከዚህ ደቂቅ ነገር ድንገቴ ፍንዳታ የተገኘ ነው ማለት ነው የተረጋገጠው ሐቅ? * "ከዛሬ 13.78 ቢሊዮን ዓመት በፊት፣ ይህ ጥንጥ ጠጣር ነገር ድንገት ፈንድቶ በመበታተኑ ህዋ እና አተሞች ተፈጠሩ። አተሞቹ እየጓጎሉ ኮከቦችን ፈጠሩ" ማለት ነው የተረጋገጠው ሐቅ? * "ከፍንዳታው በኋላ የተፈጠረው ዓለም እየሰፋና እየቀዘቀዘ በመሄዱ እንደ መሬት ያሉ ፈለኮች (ፕላኔቶች) በሂደት ቀስ እያሉ ተፈጠሩ" ማለት ነው የተረጋገጠው ሐቅ? * "The black hole has an infinite density; since its volume is zero, ... የሚለው መላምት ነው የተረጋገጠው ሐቅ? ቁርኣን ውስጥ አግኝተኸው ነው የተረጋገጠ ሐቅ ነው የምትለው? ነው ወይስ በሳይንስ ስም ስለቀረበ ብቻ የነሱን ንግግር ባይገባንም እንደ ወሕይ እንመን? ከመላምት ባለፈ የትኛው መረጃ ቀርቦ ነው የተረጋገጠ ሐቅ ነው የሚባለው? ወንድሜ ሆይ! በአላህ ላይ ያለ እውቀት መናገር ከባድ ጥፋት ነው። ለነዚህ ሰዎች የምንላቸው የምትጠቅሱት አንቀፅ ውስጥ ሰማያትና ምድር የተጣበቁ ነበሩ አለ እንጂ የፍጥረት መጀመሪያ ይሄ ነው አይልም። እንዲያውም ከነሱ በፊት ሌሎች ፍጥረቶች እንደቀደሙ ነው ቁርኣን የሚጠቁመው። ሰማያትና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት የአረሕማን ዐርሽ ነበር። ዐርሹ በውሃ ላይ ነበር። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል:- {وَهُوَ ٱلَّذِی خَلَقَ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضَ فِی سِتَّةِ أَیَّامࣲ وَكَانَ عَرۡشُهُۥ عَلَى ٱلۡمَاۤءِ} {እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው፡፡ ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር፡፡} [ሁድ: 7] ከዚህ በኋላ ነው ሰማያትና ምድር የተፈጠሩት። በመጀመሪያ ምድር ተፈጠረች። ቀጥሎ ደግሞ ሰማያት። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል:- {هُوَ ٱلَّذِی خَلَقَ لَكُم مَّا فِی ٱلۡأَرۡضِ جَمِیعࣰا ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰۤ إِلَى ٱلسَّمَاۤءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبۡعَ سَمَـٰوَ ٰ⁠تࣲۚ} {እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው፡፡} [በቀራህ: 29] ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የተፈጠሩት ከዚህ በኋላ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል:- { فَقَضَىٰهُنَّ سَبۡعَ سَمَـٰوَاتࣲ فِی یَوۡمَیۡنِ وَأَوۡحَىٰ فِی كُلِّ سَمَاۤءٍ أَمۡرَهَاۚ وَزَیَّنَّا ٱلسَّمَاۤءَ ٱلدُّنۡیَا بِمَصَـٰبِیحَ} {በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፡፡ በሰማይቱም ሁሉ ነገሯን አዘጋጀ፡፡ ቅርቢቱንም ሰማይ በመብራቶች አጌጥን፡፡} [ፉሲለት: 12]

Imām Ibn Al-Qayyim رحمه الله stated: "There are three doors by which the Shaytān (Devil) enters upon the servant (of Allāh):
Imām Ibn Al-Qayyim رحمه الله stated: "There are three doors by which the Shaytān (Devil) enters upon the servant (of Allāh): •One of them is the (servant's) heedlessness. •The second is the (evil) desires. •The third is (uncontrolled) anger." 【Al-Wābil As-Sayyib (37)】

የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) አደራ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿احفظ اللهَ يحفظك، احفظ اللهَ تجده تجاهك، إذا سألت فاسألِ اللهَ، وإذا استعنت فاستعن ب
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) አደራ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿احفظ اللهَ يحفظك، احفظ اللهَ تجده تجاهك، إذا سألت فاسألِ اللهَ، وإذا استعنت فاستعن بالله،﴾ #“አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል። አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ። ስትጠይቅ እላህን ጠይቅ። ስትታገዝም በአላህ ታገዝ።” 📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 2516

ሰሞኑን ሙስሊሙን ሚሊኒዬር መሆን አለበት የሚል ዱንያዊ ጥሪ ነበር። በዲን ሽፋን ሲሆን ብዙዎችን ሊያወዛግብ ይችላል። ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን በጁሙዓህ ኹጥባቸው ላይ ጥሩ ምላሽ ሰጥተውበታል። አዳምጡት‼ ለሌሎችም አሰራጩት! ♠ ምንም እንኳ ኡማው በዱንያዊ ነገሩም ንቁ ተሳታፊ መሆን ቢገባውም፤ በዱንያ ብቻ እንዲጠመድ የሚያደርግ ሰበካ አሁን ላይ ብዙም አያስፈልገውም። ካስፈለገም በተቃራኒው በዛ አድርጎ ስለ ዱንያ መጥፎነት መሰበክ አለበት። አሁን ላይ እኮ አላህ ካዘነለት ውጭ አብዛሃኛው ህዝብ ዲኑን ረስቶ በዱንያ ተጠምዷል። ታዲያ እንደት ይባስ በዱንያ እንዲጠመድ እንገፋፋዋለን? እንዳውም አላህ ዱንያን የሰጠው ህዝባችን ዘካውን በአግባቡ እንዲያወጣ ቢነገር ኖሮ ብዙም በድህነት የሚሰቃይ ኡማ፣ መሻይኽና ኡስታዝ ባልነበረ ነበር። ሁሉም ሚዛናዊ አካሄድ ይሻል። ለሆነ አላማ ብቻ ብለን ኡማውን እንዳናጠማው። || t.me/MuradTadesse

ብስራት ለበሽተኛ! ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ إنَّ اللهَ تعالى يَبتلِي عبدَهُ المؤمن بالسَّقَمِ؛ حتى يُكفِّرَ عن
ብስራት ለበሽተኛ! ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ:  ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ إنَّ اللهَ تعالى يَبتلِي عبدَهُ المؤمن بالسَّقَمِ؛ حتى يُكفِّرَ عنهُ كلَّ ذنْبٍ﴾ “አላህ አማኝ ባሪያውን ሁሉም ወንጀሎቹ እስኪታበሱለት ድረስ በበሽታ ይፈትነዋል።” 📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 1870

✍""ጁምዓ "" #ጁሙዐ_ሙባረክ_አይባልም !!!። ሸይኽ ፈውዛን ወፈቀሁሏህ ይላሉ፡– ሰለፎቻችን ከፊል ለከፊሉ የጁሙዐ ቀን እንደዚህ የሚሉ አልነበሩም፡፡እኛም ከነርሱ ያልተገኘን ነገር አንፈፅምም" ➲«
✍""ጁምዓ "" #ጁሙዐ_ሙባረክ_አይባልም !!!። ሸይኽ ፈውዛን ወፈቀሁሏህ ይላሉ፡– ሰለፎቻችን ከፊል ለከፊሉ የጁሙዐ ቀን እንደዚህ የሚሉ አልነበሩም፡፡እኛም ከነርሱ ያልተገኘን ነገር አንፈፅምም" ➲«ሰለዋት አንርሳ !! የአላህ መልዕክተኛ  እንዲህ ብለዋል፦ ➲«በጁምዓ ለሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በኔ ላይ ሰላዋት ማውረድ አብዙ፣ በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድበታል።» 💦ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ " ሀሰን " ብለውታል። 📚 [አል ሲልሲለቱ ሰሂሃ: ቁጥር 1407 ]      ↷ ⇣🌹⇣↷

🔰 ባሮችህ ረገፉ በፈለስጢን ምድር - በአላህ ቤት በመስጂደል አቅሳ - ነብዩ ባረፉበት በካኃዲዋ እስራኤል - ረገፉ ህፃናት ቦምብ ዘነበባቸው - እንቅልፋቸውን በተኙበት ዓለምም ችላ አለው - ይህን የዘር ማጥፋት ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ ሙስሊም የሆኑ - ኢባዱ ራህማን ናቸው ሰው ናቸውና ያራሂም - ካጠፉም ማራቸው መንገድ ስተው እንደሆን - መንገድ አሳያቸው ሙስሊሞቹም ያንተ - ህፃኖች ያንተው ካንተ ውጭ ሌላ መጠጊያም ዬላቸው! አዎ ወጀለኞች ነን - ነብሳችንን በዳይ ድንበር አላፊዎች ነን - በሰጧን አታላይ ለብልጭልጭ ህይወት - በርከክ ባይ ለዚህች ለቀን ጤዛ - ደሞም ለዱንያ ላትሆነን መንገድ - ጀነትን መዝለቂያ እያጠለቀችልን - የአዛብ ሜዳሊያ ግን አንገሰፅም - ከዚህ ሁሉም ነገር በኛ ወንጀል የተነሳ - ሙስሊሙ ሲሸበር ጠላት ተጠራርተው - ሁሉም ባአንድ ሲያብር እኛ ስንባላ - በጎሳ በብሄር እኛ ስንከፋፋል - በቋንቋ በዘር አስክሬኖች በርክተው - አፈር ሲለብስ በዶዘር እኛ ቆይ የት ገባን - ቆይ የትስ አለቅን!? ቆይ ምን ዋጠን - ምንስ ላይ ሰመጥን!? ሙስሊም ረገፈ እኮ - እኛ በቁም እያለን ጂሃዱስ አይሳካ  - ያአላህ ማለት አቃተን! የሙስሊም መሣሪያው - ዱዓ ነው እየተባልን፤ ያራህማን ያራሂም - እኛስ ቀሽሞች ነን፤ ሙስሊሞች ነንና - እባክህን ማረን አዛኝ ነህና - ያአላህ እዘንልን ውስጣችን ቆሰለ - ደም ዘነበ ከዓይን ወንድሞቻችን አለቁ - በከሃዲዎች ረገፉብን እነዛ የሰው አውሬዎች - ያንተን ቤት ደፈሩብን። ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ ያአላህ ያ! ራህማን - ቤቱም ቤትህ ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ ከጭንቅ ጠብቃቸው - ከጭንቅ አውጪ ነህ ብዙዎች ቆሰሉ - ብዙዎች አለፉ በህይወት እያሉ - ባሮችህ ደም ተፉ በዘረጋሃው ምድርህ - ሙስሊሞች ተገፉ እነዛ አውሬዎች - ሬሳን አሰለፉ ሴትም አልቀራቸው - ህፃንም ቀጠፉ ገደልን እያሉ - በደስታም ደነፉ ⭕️ በባረከው ምድርህ  - *ባሮችህ ረገፉ* ። በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ቀን: ጥቅምት 20/2016 E.C [Oct 31/2023 G.C] Join:- YouTube.com/@SecretsofTruth tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 https://ummalife.com/ReshadMuzemil t.me/ReshadMuzemil