ar
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

الذهاب إلى القناة على Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

إظهار المزيد
213
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-430 أيام
أرشيف المشاركات
https://www.instagram.com/haramainarchive/ The microphones for the mihrab of Masjid Al Haram, made by the Austrian company AK
https://www.instagram.com/haramainarchive/ The microphones for the mihrab of Masjid Al Haram, made by the Austrian company AKG. مايكرفون المحراب المسجد الحرام صنع من شركة ⁦ AKG ⁩ النمساوية

Lightning in Makkah! ⚡️ ⛈️
+1
Lightning in Makkah! ⚡️ ⛈️

አግራሞቴን በብዕር የራስህን ህይወት ስታስተካክል የሌሎችን ህይወት አታበላሽ! የራስህን መንገድ ስትጠርግ የሌሎች መንገድ አታቆሽሽ የራስህን እንጀራ ለማብሰል የሌሎችን ሊጥ አትድፋ! በራስህ መንገድ ጣ
አግራሞቴን በብዕር የራስህን ህይወት ስታስተካክል የሌሎችን ህይወት አታበላሽ! የራስህን መንገድ ስትጠርግ የሌሎች መንገድ አታቆሽሽ የራስህን እንጀራ ለማብሰል የሌሎችን ሊጥ አትድፋ! በራስህ መንገድ ጣልቃ እንዲገቡ እንደማትፈቅደው ሁሉ የሌሎችንም መንገድ አትዝጋ! ↪️ ሰዎችን መጥቀም ባትችል አትጉዳቸው! ↪️ ሰውች አንገት ሲደፉ፣ ዝም ሲሉ ሞኝ ሆነው ሳይሆን ከመናገር ይልቅ መስራትን ስለሚያስቀድሙ ነው። አዎ በዝምታቸው እያወዛገቡህ በተግባራቸው ሊያስደምሙህ ስለፈለጉ ነው “ዝምታና ኢሽታ የሚመርጡት”። ❗️[[Confuse them with your silence and Amaze them with your actions]] ❗️ ⭕️ ወዳጄ አትሸወድ! አንተም መልካም ነገር ላይ በርታና ሌሎችን ለአላህ ስትል በመልካም ነገር መካሪያቸውና አጋዣቸው ሁን! ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 YouTube: youtube.com/@SharpSwords1 Instagram: Instagram.com/sharp_swords1 Ummalif: ummalife.com/ReshadMuzemil

*ተከፍተው ይሁን* ብለህ ትጨነቃለህ ለካ እነሱ አንተ ላይ ፊታቸውን አዙረውብህ ነው። እኮ ብቻ ጌታ ፊቱን አያዙርብህ፤ የሰውስ ነገር ቀላል ነው። ummalife.com/ReshadMuzemil
*ተከፍተው ይሁን* ብለህ ትጨነቃለህ ለካ እነሱ አንተ ላይ ፊታቸውን አዙረውብህ ነው። እኮ ብቻ ጌታ ፊቱን አያዙርብህ፤ የሰውስ ነገር ቀላል ነው። ummalife.com/ReshadMuzemil

👆👆👆 🔖 አላህ ይወድላችኋል ..... ይጠላላችኋል ሙስሊም አቢ ሁረይራን አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በመጥቀስ እንደዘገቡት "አላህ ሦሥት ነገሮችን ይወድላችኃል እንዲሁም ሦሥት ነገሮችን ይጠላላችኃል... " የሚለውን ሐዲሥ አጠር ባለ መልኩ የተብራራበት ትምህርት። 🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ 🔗 ድምጽ ፋይሉን ከቴሌግራም ሊንክ ማንግኘት ይችላሉ https://t.me/ustazilyas/1110 ____ 🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አህመድ የትምህርት መድረክ https://www.facebook.com/ustathilyas @ustazilyas

"መካሪ ባልሆኑ ህዝቦች ውስጥ መልካም ነገር የለም። ምክርን በማይወዱ ህዝቦች ውስጥም መልካም ነገር የለም::" (ኡመር ኢብኑል ኸጣብرضي الله عنه)

ያአላህ እንደ ወንጀላችን ሳይሆን እንዳንተ እዝነት ማረን! ያ*ረህማን የልባችን ጌታ አንተነህ ልባችንን ከመጥፎ ነገር አንፃልን። ጌታችን ያአላህ ማረን!፣ እዘንልን፣ ሲሳይን ለግሰን፣ ጠቃሚ እውቀትን
ያአላህ እንደ ወንጀላችን ሳይሆን እንዳንተ እዝነት ማረን! ያ*ረህማን የልባችን ጌታ አንተነህ ልባችንን ከመጥፎ ነገር አንፃልን። ጌታችን ያአላህ ማረን!፣ እዘንልን፣ ሲሳይን ለግሰን፣ ጠቃሚ እውቀትን ጨምርልን። 😭 የአላህ ነብሶቻችንን በዳይ ነን ይቅር በለን። ድንበር አላፊ ነን ማረን! @ReshadMuzemil

የወራሪዋ እስራኤል የሴኩሪቲ ሚኒስቴር የሆነው ጠማማው ቤን ግቪር (Itamar Ben-Gvir) ላይ በምስሉ ላይ የሚታየው ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደርሶበታል። አላህ ጨርሶ ይውሰደው!

ሸይጣን ያልቅሳል! ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إِذَا قَرَأَ ابْنُ آدَمَ السَّجْدَةَ، فَسَجَدَ اعْتَزَلَ الشَّيْطَانُ يَبْكِي يَقُولُ: يَا و
ሸይጣን ያልቅሳል! ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إِذَا قَرَأَ ابْنُ آدَمَ السَّجْدَةَ، فَسَجَدَ اعْتَزَلَ الشَّيْطَانُ يَبْكِي يَقُولُ: يَا وَيْلِي، أُمِرَ ابْنُ آدَمَ بِالسُّجُودِ، فَسَجَدَ، فَلَهُ الْجَنَّةُ، وَأُمِرْتُ بِالسُّجُودِ، فَأَبَيْتُ، فَلِي النَّارُ﴾ “የአደም ልጅ ሱጁድ ሲያደርግ ሸይጣን እያለቀሰ ይሄዳል። እንዲህም ይላል፦ ወይኔ! እሱ ሱጁድ እንዲያደርግ ታዘዘ ሱጁድ አደረገ፤ በመሆኑም ጀነት የሱ ሆነች። እኔ ግን ሱጁድ እንዳደርግ ታዘዝኩ እምቢ አልኩ ስለሆነም ጀሀነም እጣፋንታዬ ሆነ።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 81 ✅ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ 📱፦ https://bit.ly/486xnrS 📱፦ https://bit.ly/41zEZkk 📱፦ https://bit.ly/4arMbTx 📱፦ https://bit.ly/41tIUPv 📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

ራስህን ለማሻሻልህ ⑧ ምልክቶች ብዙና ጥቅም የሌላቸው ወሬዎች ትኩረትህን አይስቡም ② ከማምሸት ይልቅ በጊዜ መተኛትን ትመርጣለህ ③ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር ፍላጎትህ ይጨምራል ④ ሰዎችን ይቅር ትላለህ ⑤ የሰዎችን መለያየት አምነህ ትቀበላለህ ⑥ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ አትሞክርም ⑦ በህይወትህ የሚያጋጥሙህ ችግሮችንንና ውጣውረዶችን ወደህ ትቀበላለህ ⑧ ሰዎች ላይ ፍርድ ለመስጠት አትቻኮልም --------------------- ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛

ካነበብኩት ላካፍላችሁ #2 በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጡ! “አንድ እድሜ ልኩን ማየት የተሳነው ሰው አይኑ ሲበራለት መጀመሪያ የሚጥለው እድሜ ልኩን ምርኩዝና ምሪት ሆኖ ያገለገለውን በትር (ዱላ) ነው”
ካነበብኩት ላካፍላችሁ #2 በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጡ!አንድ እድሜ ልኩን ማየት የተሳነው ሰው አይኑ ሲበራለት መጀመሪያ የሚጥለው እድሜ ልኩን ምርኩዝና ምሪት ሆኖ ያገለገለውን በትር (ዱላ) ነው” ይባላል፡፡ “አንድ ሕጻን ጥርስ ሲያወጣ መጀመሪያ የሚነክሰው ያለፉትን ወራት ሲመግበው የነበረውን የእናቱን ጡት ነው” ይባላል፡፡ በጎ ነገር በማድረጋችሁና ጨዋ ማንነት በመያዛችሁ ምክንያት በሰዎች የደረሰባችሁ ነገር ምንም ያህል ቢጎዳችሁና ስሜቱ ደስ ባያሰኝም፣ እናንተ ላይ ብቻ የደረሰና አዲስ ነገር ግን አይደለም፡፡ ከደረሰባችሁ ሁኔታ የተነሳ ጨዋ ማንነታችሁን አትጣሉ! https://t.me/tolehaahmed

አግራሞቴን በብዕር [[ልቧ የተሰበረ ብዕር የሞነጫጨረችው ፅሑፍ]] ለሰዎች አዘኔታህን ስታሳያቸው እነሱ ያስባሉ እየለመንካቸው እንደሆነ! እሺታህ ባበዛህ ጊዜ ጅል መስለህ ትታያቸዋለህ። እነሱ ያስባሉ
አግራሞቴን በብዕር [[ልቧ የተሰበረ ብዕር የሞነጫጨረችው ፅሑፍ]] ለሰዎች አዘኔታህን ስታሳያቸው እነሱ ያስባሉ እየለመንካቸው እንደሆነ! እሺታህ ባበዛህ ጊዜ ጅል መስለህ ትታያቸዋለህ። እነሱ ያስባሉ ምንም እንደማታውቅ፣ ምንም እንዳልከፋህ!! ወዳጄ አንተ በምታደርገው ነገር ከሰዎች መልካም ምላሽን ከጠበቅክ እጅጉኑ ትጎዳለህ፣ ታዝናለህ፣ ክፉኛ ትቆስላለህ! ⭕️ ከዚህ ሁሉ የባሰ የሚያቆስለው፦ *ወንድም እህቶችህ ስህተት ላይ ሲወድቁብህ ይህ ስህተት እንደሚጎዳቸውና ከጌታቸው እንደሚያጣላቸው ደጋግመህ ነግረሃቸው ነገር ግን እነሱ ከስህተታቸው ሳይመለሱ ሲቀሩ ልብህ ስብርብሩ ይወጣል። ደጋግመህ ይህ ስህተት ነው ስትላቸው እንደ ጠላታቸው ያዩሃል። የበደልካቸው ይመስላቸዋል። በድፍረት አላህንም ሳይፈሩ እየጎዳሃቸው መሆኑን ይናገራሉ። ➤ የሚገርም ትውልድ! ➤ አንድን ነገር እንደሚጎዳው እያወቀ የሚጎዳውን ነገር የሚጨብጥ ትውልድ። ➤ እሳት መሆኑን እያወቀ እሳቱ ላይ እራሱንና ጓደኞቹን የሚወረውር ትውልድ። ➤ ወደ መጥፎ ጎዳና የሚመራውን ወዳጅ፣ ወደ መልካም መንገድ የሚያቅጣጨውን ደግሞ ጠላት አድርጎ የሚያይ ትውልድ። ✍ [[በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል]] ቀን:- ረቡዕ/ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ል ummalife.com/ReshadMuzemil

ይህ የዐቃቢ ወሒድ መልዕክት ነው ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት
ይህ የዐቃቢ ወሒድ መልዕክት ነው ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሌሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ! መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ መረጃ ለማግኘት +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ! መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom

አግራሞቴን በብዕር ▭▬▭▬▭▬ከትዝብት ማህደር ↪️ ሰውን መጥላት ምንም አይነት ጥንካሬን አይሻም። ... ነገር ግን ምንም ሳንፈልግ፣ ያለ ምንም ቅደመ ሁኔታ፤ ያለምንም ምላሽ ሰውን ለመውደድና ሰውን ለማክበር ጥንካሬን ያሻል! ▪ሰውን የሚወዱና ሰውን የሚያከብሩ ሰዎች፤ እመኑኝ እነሱ አምላካቸውን የሚፈሩ ሰዎች ብቻና ብቻ ናቸው!! ↪️ አምላካችንን ከፈራን ሰውን ያለ ምላሽ እንወደዋለን፣ ፍቅርን ሳንሰስት እንለግሰዋለን!! ↪️ አምላካችንን ከፈራን፤ ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ከደካሞች እስከ ጠንካሮች፣ ስህተት ከሚያበዙ ሰዎች እስከ ስህተታቸውን አምኖ ከሚቀበሉ ሰዎች ድረስ ማንንም ቢሆን እናከብረዋለን!! ↪️አምላካችንን ከፈራን ለሰውም ሆነ ለራሳችን የምናስበውም የምንተገብረውም ተግባር መልካምና መልካም ብቻ ነው!! ● የወንድምና የእህቶቻቻው ጭንቀት የሚያስደስታቸው ሁሉ፤ አምላካቸውን የማይፈሩ ሰዎች ብቻና ብቻ ናቸው!! ● መልካም ስራ የማያስደስታቸው ሁሉ፤ አምላካቸውን የማይፈሩ ሰዎች ብቻና ብቻ ናቸው!! ● በወንድምና እህቶቻቸው ስህተት የሚቦርቁ ሁሉ፤ አምላካቸውን የማይፈሩ ሰዎች ብቻና ብቻ ናቸው!! ● ለግል ስሜታቸውና ለግንፈልተኝነታቸው ብለው ሰውን የሚጎዱ ሁሉ፤  አምላካቸውን የማይፈሩ ሰዎች ብቻና ብቻ ናቸው!! ● የውንድምና የእህቶቻቸውን አይብ(ሚስጥር) የሚያወጡ ሁሉ፤ አምላካቸውን የማይፈሩ ሰዎች ብቻና ብቻ ናቸው!! ▬▬ግን ቆይ! ደረጃው ይለያይ እንጂ፣ አምላኩን የማይፈራ አለን!? ___። [[መልሱን ለናተው]] ▬▬ግን እኮ አምላካችንን የምንፈራ ቢሆን ከምንናገረው ጀምሮ ምንመገበው ሁሉ ሀቅና ሀቅ ብቻ በሆነ ነበር! ➛ወንድምና እህቶቻችንን ባልበደልን ነበር....! ➛ለራሳችንና ለራሳችን ስንል ብቻ ባልኖርን ነበር....! ➛ብንበደልም በደሉን ለአላህ ብለን እንረሳው ነበር..! ➛እርሰበርስ ባልተባላንና ባልተናናቅን ነበር ....! ➛ህሊናችንን ሽጠነው በሰው ሰራሽ ህግ ባልኖርን ነበር..! ➛የምንሰራው ስራ ለአላህ ብለን ሳይሆን ለብርና ለብር ብቻ ባልሆነ ነበር...! ▬▭▬▭▬ ▪አምላካችንን እንፍራ..... 📶 ምናልባት ልብ አላልነው ይሆናል እንጂ፤ በኛ ምክንያት እየተጎዳ ያለው ብዙ ነው!! ▬▭▬▭▬ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ አስታየት፣ ጥያቄ ወይም ጥቆማ ✏️✏️ t.me/ReshadMuzemil Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 YouTube: youtube.com/@SharpSwords1 Instagram: Instagram.com/sharp_swords1 Ummalif: ummalife.com/ReshadMuzemil

አሕመድ ዐጅሚ ቁርኣን ግብዣ ፡ 30

ካነበብኩት ላካፍላችሁ የብቸኝነት ጎዳና አንዳንድ ጊዜ ብቻችሁን የምትሄዱባቸው ጎዳናዎች እንዳሉ አትርሱ፡፡ የብቸኝነት ጎዳና ማለት በዙሪያችሁ አብረዋችሁ ያሉ ሰዎች አብሮነታቸውን ለማሳየት የማይፈልጉበት ወይም የማይችሉበት ሁኔታ ሲከሰት ማለት ነው፡፡  እነዚህ ጎዳናዎች ሰዎች ሊገነዘቧችሁ የማይችሉት ሁኔታ ላይ ስትሆኑ፣ አንዳንድ የተሳሳተ ውሳኔ ላይ ራሳችሁን ስታገኙትና ያንን ለማስተካከል እንኳን ጊዜ አልሰጥ ሲሏችሁ፣ ለማንም የማትነግሩት አይነት ችግር ሲያጋጥማችሁ፣ ለሕይወታችሁ አዲስ ምእራፍ ፈልጋችሁ ለውጥን ማምጣት ስትጀምሩ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ምክንያቱን በማታውቁት ሁኔታ የብቸኝነትን ጉዞ እንድትያያዙት ትገደዳላችሁ፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ራሳቸሁን ስታገኙት . . . 1. ሁኔታው ጊዜያዊ ነውና የከረሩ ውሳኔዎች ውስጥ እንዳትገቡ ተረጋጉ፡፡ 2. ሰዎች ገለል የማለታቸው ምክንያት ለምን እንደሆነ መነሻ ሃሳባቸውን ተወት አድርጉትና ውሳኔያቸውን አክብሩና ለቀቅ አድርጓቸው፡፡    3. ራሳችሁን እንድትመለከቱ እድል የምታገኙበት አስገራሚ ጊዜ ስለሆነ በቂ ጊዜን ከራሳችሁ ጋር አሳልፉ፡፡ 4. ከሰዎች ጋርም ሆነ ከሰዎች ውጪ፣ ከችግር ጋርም ሆነ ከችግር ውጪ መኖር የምትችሉበት አቅማችሁ የሚፈተሸበት ጊዜ መሆኑን አትርሱ፣ ያንንም አዳብሩ፡፡ 5. ሁል ጊዜ ፈጣሪያችን ከእናንተ ጋር እንደሆነና ሁሉን ነገራችሁን እንደሚገነዛባችሁ በማሰብ ወደ እሱ የምትጠጉበት አጋጣሚ በማድረግ ተጠቀሙበት፡፡ አይዟቸሁ! አላህ አለ! https://t.me/tolehaahmed