ar
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

الذهاب إلى القناة على Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

إظهار المزيد
213
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-430 أيام
أرشيف المشاركات
ባለ ነገር መብቃቃት! ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿والذي نَفْسِي بيَدِهِ، لَأَنْ يَأْخُذَ أحَدُكُمْ حَبْلَه، فيَحْتَطِبَ على ظَهْرِه؛ خَيْرٌ له مِن أنْ يَأْتيَ رَجُلًا، فيَسْأَلَه، أعْطاهُ أوْ مَنَعَه.﴾ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! ከናንተ አንዳችሁ ሌላ ሰው ከሚለምን ይልቅ ሰጠውም አልሰጠውም እስር እንጨት በጀርባው እየተሸከመ (ኑሮን ቢገፋ) ይመረጣል።” 📚 ቡኻሪ (1480) ሙስሊም (1042) ዘግበውታል በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

"ትክክል_መሆኑን_እያወቀ_ክርክርን (ጭቅጭቅን) ለተወ ሰው በጀነት ቤት እንደሚኖረው እኔ ዎስትና እሆነዎለሁ::" ነብያችን(ﷺ) (አቢ ዳውድ:4800)

#የተዋለልህን_ፀጋ_እንድታመሰግን… "በዱኒያ ጉዳይ ከበታቻችሁ ያሉትን ተመልከቱ:: ከበላያችሁ ያሉትን አትመልከቱ::ከበታቻችሁ ያሉትን መመልከት የተሻለ ነው::ያን ግዜ አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ ለመመልከት ያግዛችኋልና::" ረሱል (ﷺ) (ሙስሊም ዘግበውታል:2963) اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد صلى الله عليه وسلم

ድንቅ ሽልማት ~ ነፍል ወይም ግዴታ ያልሆኑ ሶላቶችህን ደበቅ አድርጋቸው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- "አንድ ሰው ሰዎች ሳያዩት የሚሰግዳት ግዴታ ያልሆነች ሶላት ከሰዎች እይታ ስር ሆኖ ከሚሰግዳት ሶላት ሃያ አምስት (እጥፍ) ትስተካከላለች።" አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል። [ሶሒሑልጃሚዕ: 3821]

የሰደቃ ትሩፋት! ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَنْ أنفقَ نفَقةً في سبيلِ اللهِ كُتِبَت لهُ بسَبعِمائِة ضِعفٍ﴾ “በአላህ መንገድ ላይ ከገንዘብህ አንዲትም ወጪ
የሰደቃ ትሩፋት! ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَنْ أنفقَ نفَقةً في سبيلِ اللهِ كُتِبَت لهُ بسَبعِمائِة ضِعفٍ﴾ “በአላህ መንገድ ላይ ከገንዘብህ አንዲትም ወጪ አታወጣም፤ ላንተ ደግሞ ሰባት መቶ እጥፍ ተደርጎ የሚመዘገብልህ ቢሆን እንጂ።” 📚 ሶሂህ አተርጊብ፡ 1236 ⭐️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ ⚡️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ ⚡️፦ https://bit.ly/486xnrS ⚡️፦ https://bit.ly/41zEZkk ⚡️፦ https://bit.ly/4arMbTx ⚡️፦ https://bit.ly/41tIUPv ⚡️፦ https://bit.ly/3UTTSwh

The Person Of Bid'ah (Innovation) In Reality Implies This Tremendous Thing Against The Prophet ﷺ Al-'Allaamah Ibnul-'Uthaymeen, may Allaah have mercy upon him Join the telegram channel: t.me/FruitsOfKnowledge

ተመልከት ይህንን ነጥብ‼ ================== ✍ ውዱ ነቢይ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦ "አላህ ለሙሳ እንዲህ የሚል ወሕይ አወረደለት፦ «…يَا مُوسَى قُلْ لِلْمُذْنِبِينَ النَّادِمِينَ : أَبْشِرُوا ، وَقُلْ لِلْعَامِلِينَ الْمُعْجَبِينَ : اخْسَرُوا) «ሙሳ ሆይ! ለነዛ ወንጀል ሠርተው ለተፀፀቱ "አብሽር" በላቸው። መልካም ሥራ ሠርተው ግን በነፍሳቸው ለተገረሙ (በራሳቸው ለተደነቁ) "ክሰሩ" በላቸው።»" [" الحلية " (5/45 و7/127) ] ♠ ዾዒፍ ነው የሚሉ ቢኖሩም መልዕክቱን ግን አስተውለው! ወንጀል'ኮ አልሠሩም፣ እንዳውም መልካም የሚባል ሥራ ሠርተዋል። ግን ጉራና ኩፈሳ ስላለበትና ኢኽላስ ስለሌለው ክሠሩ ተባሉ። ለዛምኮ ነው ኢብኑ-ል-ቀይ'ዩም «ኢኽላስ ከሌለህ አትድከም!» የሚለው። እነዚህኞቹ ደግሞ መልካም ሥራ አልሠሩም'ኮ፣ እንዳውም ወንጀል ሠርተዋል። ግን ከልባቸው ተፀፀቱና ወደ አላህ ተመለሱ። ከዚያስ ምን ተባሉ? "አብሽሩ!" አላሁ አክበር‼ «የውስጤን እሳት ለማጥፋት ፥ ወደ ዓይንህ ባ'ላይም፣ ነፍሴም ልቤም ወዳንተ ፥ ማማተሩን አይተውም።» አላህ "አብሽር!፣ ምንም ማዘንና መተከዝ የለባችሁም!" ከሚባሉት ባሮቹ ያድርገን፣ ኢኽላስንም ይወፍቀን። ||

ልብ በሉ! እንዲህ የሚንደፋደፉት ለጀይላኒይ ያላቸው የተጋነነ ቦታ እና የጀይላኒይ ብርቱ ፀረ አሽዐሪያ አቋም አልጣጣም ብሎ ስላስቸገራቸው ነው። ከቅርቃሩ መውጫ መንገድ እውነቱን መቀበል ብቻ ነበር። ግን በራሱ ላይ ቆልፎ ስለ ተቀመጠ አካል ምን ማለት ይቻላል?! = (ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዋል 16/1444 (ሚያዚያ 28/2015))

አሕ ^ባሽ እና ዐብዱል ቃዲር አልጀይላኒይ (561 ሂ.) ~ ተስፈንጣሪው የአሕ ^ ባሽ አንጃ "አላህ ከፍጡራን ሁሉ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን ከኢስላም በማስወጣት (በማ^ ክ^ ፈ^ር) የታወቀ ነው። የቡድኑ ቁንጮዎች በዚህ ፅንፈኛ አቋማቸው የተነሳ እነ ኢማሙ ዳሪሚይን፣ እነ ኢብኑ ኹዘይማን፣ እነ ኢብኑ መንደህን እስከማብጠልጠል ደርሰዋል። ይሄ አጉል የሆነ አካሄዳቸው ግን ሳያስቡት ቅርቃር ውስጥ ሲከታቸው ይታያል። "እናከብራቸዋለን" ከሚሏቸው ዑለማዎች ውስጥ የአላህን ከፍጡራን በላይ መሆን የሚያፀድቁ ያጋጥሟቸዋልና። ጀይላኒይ ረሒመሁላህ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን አንዴ ሳይሆን ደግመው ደጋግመው አስረግጠው ገልፀዋል። ይህንን እውነት የማይቀበሉትን ኮንነዋል። ከዚህም አልፈው አሻዒራን በስም ጠቅሰው አብጠልጥለዋል። ይሄ ለአ^ ሕ^ባሾች ከባድ ራስ ምታት ነው። አይቀበሏቸው እነሱ ዘንድ የማይሆን ነገር ነው። ሌሎችን እንደ - ሚያ* ከ^ ፍሩ እንዳያከ * ፍ- ሯ ^ቸው በሱፊያው ዓለም ያላቸው ቦታ እጅግ የገዘፈ ነው። ሌሎችን በሚያ* ከ^ ፍሩበት ጉዳይ እሳቸውን ሲያልፉ ደግሞ አጭ በርባሪነታቸው ገሃድ ይወጣል። ምን ይሻላል? ሽምጥጥ አድርገው መዋሸትን እንደ ዘዴ መርጠው ነበር። ችግሩ ግን ውሸቱም የነሱን ዝቅጠት ከማጋለጥ ባለፈ የሚፈይድ አለመሆኑ ነው። ቀጥሎ ጀይላኒይ የአላህን ከ0ርሹ በላይ መሆን ያፀደቁባቸውን ንግግሮች እጠቅሳለሁ፦ [1ኛ]:- وأن الله تعالى خلق سموات بعضها فوق بعض، وسبع أرضين بعضها أسفل من بعض، ومن الأرض العليا إلى السماء الدنيا مسيرة خمسمائة عام، وبين كل سماء وسماء مسيرة خمسمائة عم، والماء فوق السماء السابعة، وعرش الرحمن فوق الماء، والله تعالى على العرش “የላቀው አላህ ሰማያትን ከፊሎቹን ከከፊሎቹ በላይ፣ ሰባት ምድሮችን ደግሞ ከፊሎቹን ከከፊሎቹ በታች አድርጎ ፈጥሯል። ከላይኛዋ ምድር እስከ ታችኛዋ ሰማይ ድረስ አምስት መቶ አመት የሚያስኬድ ርቀት አለ። ከእያንዳንዱ ሰማይ እስከ ቀጣዩ ሰማይ ድረስ እንዲሁ የአምስት መቶ አመት ጉዞ ርቀት አለ። ውሃው ከሰባተኛው ሰማይ በላይ ሲሆን የአረሕማን ዐርሽ ከውሃው በላይ ነው። ከፍ ያለው አላህ በዐርሹ ላይ ነው።” [አልጉንያ፡ 1/123] [2ኛ]:- وَهُوَ بِجِهَةِ العُلُوِّ، مُسْتَو عَلَى العَرْشِ، ... واللهُ تَعَالَى عَلَى العَرْشِ وَلاَ يَخْلُو منْ عِلْمِهِ مكانٌ، وَلاَ يجوزُ وصفهُ بأنَّهُ فِي كلِّ مكانٍ، بلْ يقالُ: إنَّهُ فِي السَّمَاءِ عَلَى العَرْشِ “እርሱ በላይ አቅጣጫ ከዐርሹ በላይ ከፍ ብሎ ነው። … የላቀው አላህ በዐርሹ ላይ ነው። ከእውቀቱ የሚራቆት ቦታ የለም። ‘እርሱ ሁሉም ቦታ ነው’ ብሎ መግለፅ አይፈቀድም። ይልቁንም እርሱ በሰማይ በዐርሹ ላይ ነው።” [አልጉንያ፡ 1/121] [3ኛ]:- وهو باين من خلقه، لا يخلو من علمه مكان، ولا يجوز وصفه بأنه في كل مكان، بل يقال: إنه في السماء على العرش “እርሱ ከፍጡሩ ተለይቶ ነው ያለው። ከእውቀቱ የቱም ቦታ አይራቆትም። ‘በሁሉም ቦታ ነው’ ብሎ እሱን መግለፅ አይፈቀድም። ይልቁንም በሰማይ በዐርሹ ላይ ነው ይባላል።” ይህን ካሉ በኋላ የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃዎችን ዘርዝረዋል። አለፍ ብለውም “የኢስቲዋእን መገለጫ ያለ ‘ተእዊል’ (ቁልመማ) በዐርሹ ላይ ከፍ ማለት ነው ብሎ ያለ ገደብ መረዳት ይገባል” ካሉ በኋላ ከርራሚያ፣ #አሽዐሪያና ሙዕተዚላን ከነ ተሳሳተው ትርጓሜያቸው ጋር በስም ጠቅሰው አውግዘዋል። [አልጉንያ፡ 1/124] [4ኛ]:- كَوْنُهُ عزَّ وجلَّ عَلَى العَرْشِ مذكورٌ فِي كلِّ كتابٍ أُنزلَ عَلَى كلِّ نبيٍّ أُرسلَ بلا كَيْفٍ “አሸናፊውና የላቀው - ያለ አኳኋን - በዐርሹ ላይ መሆኑ በሁሉም የተላከ ነብይ ላይ በተወረደ መፅሐፍ ውስጥ ሁሉ ተጠቅሷል።” [አልጉንያ፡ 1/125] [5ኛ]:- وأنه تعالى ينزل في كل ليلة إلى سماء الدنيا، كيف شاء وكما شاء، فيغفر لمن أذنب وأخطأ وأجرم وعصى لمن يختار من عباده ويشاء، ... لا بمعنى نزول رحمته وثوابه على ما ادعته المعتزلة والأشعرية “የላቀው (አላህ) በየሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ በሚሻው ሁኔታ፣ እንደ መሻቱ ይወርዳል። ሃጢአት ለፈፀመ፣ ለተሳሳተ፣ ለወነጀለ፣ ላመፀ ይምራል፤ ከባሮቹ ለመረጠውና ለፈለገው። እንጂ ሙዕተዚላና #አሽዐሪያ እንደሞገቱት የእዝነቱና የምንዳው መውረድ አይደለም።” [አልጉንያ፡ 1/125] በጀይላኒይ ላይ ወሰን በማለፍ ለሚታወቁት በርካታ ሱፊዮች ይሄ እጅግ አስደንጋጭ ነገር ነው። በቁርኣንና በሐዲሥ ላይ እንደለመዱት አይቆለምሙት፣ አይመችም። ጭራሽ “አሽዐሪያ” እያሉ በስም ጠርተው ነው ደጋግመው ያብጠለጠሏቸው። ምን ይሻላል? ቢጨንቃቸው ሁለት ዓይነት ማምለጫዎችን ዘይደዋል። [ማምለጫ አንድ]፦ አንዳንዶቹ: “ሌሎች ሰዎች በኪታባቸው ውስጥ አስገብተውባቸው እንጂ እሳቸው ይህን አላሉም” በማለት አይናቸውን በጨው አጥበው የተከራከሩ አሉ። ለምሳሌ ሀይተሚይ (974 ሂ.)። [አልፈታወል ሐዲሢያህ፡ 145] ግና ከሀይተሚይ በፊት ያለፉ ታላላቅ ዑለማዎች - ሱፊዮች ጭምር - ያረጋገጡት ሐቅ በእንዲህ አይነት ድንጋጤ በወለደው ባዶ ሙግት አይፈርስም። ሲጀመር ሀይተሚይ በመሰል ጉዳዮች ላይ ሚዛናዊነት የለውም። እንደ ኢብኑ ዐረቢይ ላሉ አፈንጋጮች እየተሟገተ እነ ኢብኑ ተይሚያን በሃሰት የሚወነጅል ነው። [ማምለጫ ሁለት]፦ “ጀይላኒይ ከዚህ ዐቂዳቸው ኋላ ተመልሰዋል” የሚል ነጭ ውሸት ነው። ያፊዒይ (768 ሂ.) እዚህ ላይ ተጠቃሽ ነው። ያፊዒይ ከላይ የተዘረዘሩትን ንግግሮች የጀይላኒይ መሆናቸውን ይመሰክራል። ይሄ ለሀይተሚይ ምላሽ ይሁንልን። ነገር ግን በህይወታቸው መጨረሻ ላይ “ዐቂዳቸውን ቀይረዋል” ይላል። “ማስረጃው” አስቂኝ ነው። የጀይላኒይ “አላህ ከዐርሽ በላይ ነው” ብሎ ማመን ለኢብኑ ደቂቀል ዒድ ሲደርስ በጀይላኒይ “አፈንጋጭነት” ይገረማሉ። ጀይላኒይም ይሄ ነገር ሲደርሳቸው በህይታቸው ፍፃሜ ላይ ዐቂዳቸውን ቀየሩ ይላል። ያፊዒይ ይቀጥልና ታሪኩን የነገረኝን ነጅሙዲን አልአስፈሃኒይን አልጠረጥረውም። ምክንያቱም እሱ የከሽፍ (መገለጥ) ባለቤት ነውና ይላል። [ሚርኣቱል ጂናን፡ 3/272] ሱፊያ ሰፈር እንዲህ አይነት በሬ ወለደ ወሬ ብርቅ አይደለም። ያፊዒይም በዚህ የታወቀ ነው። ለማንኛውም ጀይላኒይና ኢብኑ ደቂቀል ዒድ ዘመናቸው አይገናኝም። ኢብኑ ደቂቅ የተወለዱት ጀይላኒይ ከሞቱ ከ64 ዓመት በኋላ ነው። ምኑን ከምኑ እንደሚያገናኝ ተመልከቱ። ባለ ከሽፉ እንዲህ አይነት መክሹፍ (የተጋለጠ) ውሸት ነው የዋሸው። ታሪኩ ቅጥፈት እንደሆነ ሌሎች ነጥቦችን መጨመር ቢቻልም በዚህ ደረጃ ላለ ቅጥፈት ደክሜ ማድከም አልፈለግኩም።

💻 አውፍ በይን አቅሳ 🇵🇸 አንቺ እየቆሰልሽ - እኛ ፈገግ እንላለን፤ አንቺ እያለቀስሽ - እኛ እንስቃለን፣ በማይረባ ነገር - እርሰበርስ እንባላለን፤ ትላንት አዝነንልሽ - ዛሬ ጨክነናል፤ ባለፈ
💻 አውፍ በይን አቅሳ 🇵🇸 አንቺ እየቆሰልሽ - እኛ ፈገግ እንላለን፤ አንቺ እያለቀስሽ - እኛ  እንስቃለን፣ በማይረባ ነገር - እርሰበርስ እንባላለን፤ ትላንት አዝነንልሽ - ዛሬ ጨክነናል፤ ባለፈ ዱዓ አድርገን - ዛሬ ዘግተናል፤ አውፍ በዪን ፈለስጢን - እኛ ጨክነናል፤ ይህ ሁሉ ሳያንሰን- በወንጀል ተዘፍቀናል፤ አወይ የኛ ክፋት - ምንኛ ጨካኝ ነን⁉️፤ ለወንድሞቻችን ወድቀት - ቀመር እንቀምራለን፤ በእህቶቻችን አይብ - እንሳለቃለን፤ ሰዎችን ለመጣል - ሴራ እናሴራለን፤ በዚያ ግን ትቀጠፋለች - የኛዋ ፈለስጢን። አቅሳ፣ ፈለስጢንን እያየን - ለሰዎች አናዝንም⁉️፤ አላህ ነስሩን እንዲሰጠን - ማመፅ አናቆምም⁉️፤ ወደ ጌታችን ተመልሰን - የአላህ አንልም⁉️፤ አረ ይበቃናል - በቁማችን ሞትን፤ መቃብር ሳንገባ - አፈርም ለበስን፤ ህይወት አላቸው እንዲሉ - እየተንቀሳቀስን፤ ክፋታችን ከፍቷል - ረሳናት ፈለስጢንን፤ ልባችን ጨከነ - ዘነጋናት አቅሳን። ለአላህ ስትይ - አቅሳ አውፍ በይን፣ አንቺ እየቆሰልሽ - እኛ ፈገግ እንላለን፤ አንቺ እያለቀስሽ - እኛ  እንስቃለን፣ ትላንት አዝነንልሽ - ዛሬ ጨክነናል፤ ባለፈ ዱዓ አድርገን - ዛሬ ዘግተናል፤ አውፍ በይን ፈለስጢን - እኛ ጨክነናል፤ አውፍ በይን አቅሳ - እኛ ጨክነናል። 🇵🇸  🇵🇸  🇵🇸  🇵🇸   🇵🇸  🇵🇸   🇵🇸  🇵🇸 📙 በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል 🕤 ቀን:- ማክሰኞ/ የካቲት 26/2016 ዓ.ል ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Tikto: tiktok.com/@secretsof_truth Instagram: Instagram.com/secretsof_truth Telegram: t.me/Secretsof_Truth Facebook: Fb.com/SecretsofTruth1 Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil

🔅المسلم لا يعجب بعمله !!
🔅ሙስሊም በስራው አይደነቅም! !
ምንም ቢሰራ ሁሌም ራሱን ከአላህ ሀቆች ያጓደለ አድርጎ ነው የሚያስበው ነፍሱን አያወድስም! አላህ እንዲህ ይላል فلا تزكوا أنفسكم هو أعلم بمن اتقى ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡
🎙 الشيخ صالح الفوزان حفظه الله

〽️ እንኖራለን በሀሴት ኢንዲ ስትል ፃፈች - ያረገዘችው ብዕሬ ለእጄ እንዳይከብደኝ - ክዳኗን ወርውሬ እናም መፃፍ ጀመርኩ - እንዲህ ስል ጀምሬ ግን ገንፍላለችና - ቀለሟ እንዳያልቅ እውነቱን ላውጣው - ልቤ እንዳይጨነቅ በሀቅ ትደሰት - ብዕሬ ትቦርቅ። እስቲ ልሞነጫጭር - ሀሳቤን ልግለጥ ግን አልችልም - ውብ ቃሎችን መምረጥ አጣዳፊ ነውና - ያረገዘቺው የብዕሬ ምጥ። የዕድሜችን ጉዞ ሽሽት የተስፋችን ቅዠት የመኖራችን ሚስጥር የህይወት ቁም ነገር የኑሮ ስንክሳር እንጨነቃለን ይሀው - ምንም ላንፈጥር በሆነ ጊዜና - ስትጠልቅ ጀምበር ድቅድቁ አይሎ - ጨለማው ሲደራ እኛም ረስተን - ሰባዓዊ ፉጥርነታችንን ፍንትው ብሎ ወጣ - ይሀው ጭካኔያችን ልብሳችን ሸፍኖት - ያን ትምኪት አንደበት ስንኖር አምሮብን - ኑሮን ግን የውሸት ሰው መች ይህን አወቀ - የእኛነታችንን እውነት ፀሃይ ማብራት ስትጀምር - ለሰው ልጅ በተራ ፍርድም ሲጓደል - እውነት ሲሆን ተራ ከፋፍለን ስንጨርስ - ሰዎችን በጎራ እናም አስተዛዘበን - የአስተሳሰባችን ስፍራ። ጊዜም ሚስጥር ሆነ - እንደ ስልክ ኮድ ሚከፍተውም የለም - አወይ የኛስ ጉድ ወይስ በኮፒ እንክፈተው - በዘረፍነው ፓስዎርድ⁉️ ቀኑ ቶሎ መሸ - ለሊቱ ረዘመ ልባችን ታመመ - እኛን እያከመ ሀሴት መበፈለግ - ውስጣችን ከሰመ እንቅፋት በዝቶበት - ደስታን ሚቀማ ግራ ገብቶን አለን - በጭንቀት አላማ። አርብን እየጠበቅን - ቅዳሜ ደረሰ ቀናት ተፈራረቁ - ወርም ተጋመሰ ጨለማው ረዝሞ - ብርሃን  ታመሰ ደስታም እንደ ቤት - ተሰርቶ ፈረሰ ቀኑ 24 ሰዓት - እኛ ግን ዜሮ ማሳለፍ ለምደን - ጭንቀትን በጓሮ ለውጥ ላናመጣ - አሰማን እሮሮ ይሀውና አለን- እንደአምናው ዘንድሮ ይሀውና አለን- እንደአምናው ዘንድሮ። ደግነት ይፃፍበት - በጥላቻ ሰነድ እውነት ይስፈርበት - በጨለማው መንገድ እስቲ ደግ እንሁን - በቃ ሰው እንውደድ በቃ ሰው እናክብር- ውስጣችን እንዳይናድ ለውዴታችን ግን - ምላሽ አንጠብቅ በሚመስጥ ትህትና - ከእውነት እንታረቅ ተስማምተው ከሄዱ - እምነትና ተስፋ ሃቅ ገኃድ ከወጣ - የሰው ልጅ ካልከፋ እውነት ሚስጥር ካልሆነ - ካወጣነው ይፋ ይሄኔማ ሰው እንሆናለን - ደግነት ያቀፈ ሁሉም ለበጎ ይሆናል - ይጠፋል ብስጭት መመኘት እንጀምራለን - እውነተኛ ምኞት በደስታ ያበበ - ውብ ማራኪ ጊዜያት እርሰበርስ ተገዳግፈን - እንኖራለን በሀሴት እርሰበርስ ተገዳግፈን - እንኖራለን በሀሴት። ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 YouTube: youtube.com/@SharpSwords1 Instagram: Instagram.com/sharp_swords1 Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil

መጥፎ ተግባር ወዳጅ ያሳጣል! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنّ شرَّ الناسِ منزلةً عند اللهِ يومَ القيامةِ من تركه الناسُ اتِّقاءَ فُحشِه﴾ “ከሰዎች መ
መጥፎ ተግባር ወዳጅ ያሳጣል! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنّ شرَّ الناسِ منزلةً عند اللهِ يومَ القيامةِ من تركه الناسُ اتِّقاءَ فُحشِه﴾ “ከሰዎች መጥፎ ሆኖ በትንሳዔ ዕለት አላህ ዘንድ የሚመጣው፤ ከመጥፎ ስራው ለመጠንቀቅ ሲሉ ሰዎች የተዉት ሰው ነው።” 📚 ቡኻሪ (6032) ሙስሊም (2591) ዘግበውታል

ይሄ ከባድ ንፅፅር ነው።

የአላህ ዲን በክርክር ላሸነፈ ሰው አይደለም!!
ከአማርኛ የፅሁፍ ትርጉም ጋር
ሸይኽ ዶ/ር ዐብዱ-ር'ረዛቅ ኢብኑ ዐብዱ-ል-ሙሕሲን አል-ዐባድ አል-በድር አላህ ይጠብቃቸው

ሟቹ "ጌታ!" ~ ወሎ ውስጥ ነው። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል። · * ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ። – "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት። · ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ። · ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው። * "እሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ። – "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ። · አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል። · * "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው። – "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት። * "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ። – "አዎ" አሉት። · ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:– "እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!!" … የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው። … መወለድ፣ ማደግ፣ መሞት ለፈጣሪ የማይመጥኑ የደካማ ፍጡሮች መታወቂያ ናቸው። እባካችሁ ያገሬ ሰዎች ቆም ብላችሁ አስቡ። "ፍፁም ሰው፣ ፍፁም አምላክ" እያሉ "ተጨፈኑ እናሙኛችሁ" ሲሉ እጅ አትስጡ። "ሁሉን ምርምሩ። መልካሙን ያዙ።" በአባቶች የውርስ ጋቢ ተጠቅልላችሁ፣ በይሉኝታ ጆሯችሁን ደፍናችሁ፣ በምስጢረ ሥላሴ ትብታብ ታስራችሁ እንጂ ህሊናችሁን ፋታ ሰጥታችሁ በእርጋታ ብታዳምጡት የሚነግራችሁ ሐቅ አለ። "ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ ይነግርሀል አንዳች እውነት" ይላል ገጣሚው። · ዳሰሳ ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 12 ቁ 29 እስከ 34። ---------- "ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። #ከትእዛዛቱ_ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ #ጌታ_አምላካችን #አንድ_ጌታ ነው፥" (የማርቆስ ወንጌል 12:29) · ማነው ይህን ያለው? እየሱስ እራሱ!! "ጌታ አምላካችን" ማለቱን አስምርበት። እየሱስ ፍጡር እንጂ ጌታ እንዳልሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ጥቅስ ነው። ይሄ ቀዳሚ ትእዛዝ ግን በክርስቲያኖች ተገፍቷል። እንቀጥል። "አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።" (የማርቆስ ወንጌል 12:30) · ልብ በል! በዚህ መልኩ "ጌታህን ውደድ" እያለ የሚያስተምረው እየሱስ እራሱ ነው። ይህም እሱ አስተማሪ እንጂ ጌታ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው። እንቀጥል። "ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም። ጻፊውም። መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ #አንድ_ነው። #ከእርሱም_በቀር_ሌላ_የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ፤" (ማርቆስ 12:31–32) እያስተዋልክ ነው?! እውነት የምትፈልግ ከሆንክ "አምላክ አንድ ነው። ከርሱ በቀር ምንም የለም" ብለህ በልብህ ዝከር። በምላስህ አስተጋባ። በተግባር ኑር። ይሄ በኢስላም "ላ ኢላሀ ኢለላህ" ("ከአላህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ የለም") ከሚለው ምስክርነት ጋር መሳ ነው። እንቀጥል። "በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው።" (ማርቆስ 12:33) ይህን ነው የምልህ። ስላሴ፣ ቅብጥርሴ የሚባለውን ወደ ኋላህ አሽቀንጥረህ ጣልና ለመፅሐፋዊ መልእክቱ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም አእምሮህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ እደር። ሥላሴ ልብ ወለድ እንጂ እውነታ አይደለም። ሥላሴ ጤነኛ ጭንቅላት የማይፈታው እንቆቅልሽ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም። "ያልገባህ መንፈስ ቅዱስ ስላላደረብህ ነው" እያሉ አይሸውዱህ። ይሄ ምእመኑ እንዳይመረምር የሚያስተኙበት የእንቅልፍ ክኒን ነው። በክኒኑ እራሳቸውን ያስተኙበት። አንተ ግን ንቃ። ይህን ስታደርግ፣ ወደ አእምሮህ ስትመለስ "ለመንግስተ ሰማያት" ትቀርባለህ። አብረን እናንብብ። "ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ። አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።" (ማርቆስ 12:34) (ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 11/2011) የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor