ar
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

الذهاب إلى القناة على Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

إظهار المزيد
213
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-430 أيام
أرشيف المشاركات
ትንሽ ፈገግ በሉ‼ ============ ✍ «… ወሎ ውስጥ ነው አሉ። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ  ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል። * ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት። ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ። ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው። "ይሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ። አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል። * "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው። "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት። * "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ። "አዎ" አሉት። · ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:– "እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!" ©: የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው።

‍ 🔰 ተስፋ አለኝ የትላንቱ ክፍተት - የዛሬው ቀዳደ ኋሊት የሚኖር - ነገን እያቀደ የመሸ ይመስለኛል - ጎኅ እየቀደደ ብሮጥ ብሮጥ አያልቅ የህይወት ሜዳ ውስጤ ይሀው አለ - እኔን እየጎዳ ዛሬን እሰጣለሁ - ለትላንትናው እዳ ያለፈው ታሪኬ - በትዝታ ተሞልቶ ዛሬም ትላንት ሆነ - ነገን አስረስቶ ትዝታ አርጌው - ትላንት አርፍዶብኝ በተስፋ ስባንን - ዛሬ ቀደመኝ ትላንትን ትዝታ - ዛሬን ምን ልበለው? እኮ አልታየኝም - ከትላንት አንድ ነው። የትላንት ትዝታ - ታሞብኝ በጠና አሁንም ቆሰለ - ዛሬም እንደገና ነገን ደገመ - እዩ ይሀውና አለሁ እስከዛሬ - በቆሰለ ትላንትና። ዘመን ሲለዋወጥ - ጊዜም ሲቀያየር በኛ አልተጀመረ - መከፋት መቸገር እንዲህ ነው ነገሩ - የህይወት ስንክሳር ደምረን ብንቀንስ - ብንቀምር ቀመር አካፍለን ብናባዛ - ማስተዋል ብንጀምር ኮድ ሆነ ከረመ - የኑሮ ሚስጥር። በተስፋ እየኖርኩ ነው - ጠይቆኛል ፓስዋርድ ውስጤ ሆይ ቻለው - እባክህ አትናደድ ኮዱን ካገኘሁት - ላገላብጥ ሰነድ። ብንዘፈቅ በድህነት - ምንም ባይኖረንም ጠንካራ ማንነትን - ዝቅ አያረግብንም ምንም ቢሞላለት - ሀብታምም ቢሆን ከፍ አያረግም - የሰው ወራዳነትን በቃ አዲስ ነገር የለም - ህይወት እንደዚህ ናት ደስታና ሀዘን - የተፈራረቀባት ሳቅና ለቅሶ - በአንድ የኖረባት ክፋቷ ያመዘነ - ያጠፋች ደግነት በአዋጅ ፈቀደች - የክፋትን ጥግነት ታዲያ ምኑነው አዲስ - ሁሌም ይኖራላ ሀዘንና ደስታ - ይቀያየራላ ለአንዱ ሲሞላለት - ለአንዱ እየጎደለ ሳይስቅ ሳያለቅስ - የሚኖር መች አለ!? ለአንዱ ሲሞላለት - ለአንዱ እየጎደለ ሳይቸገር ሳይከፋ - የሚኖር መች አለ!? በቃ ሰው ራቅኩኝ - እንደው በደፈና ውስጤን አሳዘነው - ትዝታ መጣና ማለፍ ቢያቅተኝ - የህይወት ምዘና በቃ ሰው ጠላሁኝ - እኔም ሰው ሆንኩና ግን ስሞታ አበዛሁ - እኔም ሰውነኝና ሽሽት ሽሽት አለኝ - ግን ወዴት ይሸሻል ያው ህይወት ህይወት ነው - ይነጋል ይመሻል ሰውም እንደዘበት - ይቀርባል ይርቃል እኮ ወዴት ልሽሽ - ውስጤ ይጨነቃል አንድ ፈጣሪ ግን - መድረሻዬን ያውቃል የሰው ልጅማ - ውስጥን ያሳምማል ድህነትህን ሲዘክር - አንገት ያስደፋሃል የሰው እርዳታ አልሻም - እባካችሁ ተውኝ መኖር እችላለሁ - ምንም ሳይኖረኝ መክንያቱም ይህ ነው - በአላህ ተስፋ አለኝ መክንያትህ ላለኝ - በአላህ ተስፋ አለኝ!    âœ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል መስከረም 30/2012[Oct 11/2019] ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 YouTube: youtube.com/@SharpSwords1 Instagram: Instagram.com/sharp_swords1 Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ ማሳሰቢያ: ግጥሙ በመልዕክቱ ሰዎችን ማስተማር እንጂ የኔን የግል ህይወት (ንዴትና ቁጭቴን) ለመግለፅ የተፃፈ አይደለም!

🔰 ክፋትን አርግዞ አለን እያልን አልቀን - አለመኖራችንን ስናውቅ፣ ሀብታምነን እያልን ስኮራ - ሀብታችን ሲያልቅ፣ ህይወትም አምርራ - የምስጥር ቁጥር ስትጠይቅ፣ እኛው ሰነፍ ሆነን - ሰዓትም ሲሳ
🔰 ክፋትን አርግዞ አለን እያልን አልቀን - አለመኖራችንን ስናውቅ፣ ሀብታምነን እያልን ስኮራ - ሀብታችን ሲያልቅ፣ ህይወትም አምርራ - የምስጥር ቁጥር ስትጠይቅ፣ እኛው ሰነፍ ሆነን - ሰዓትም ሲሳለቅ፣ ጊዜም ሂድ ሳይባል - እሱ እየሄደ፣ ሴኮንዶችን ደማምሮ - ደቂቃ እየወለደ፣ ጊዜ ሩጥ ሳይባል - እሱ እየሮጠ፣ ደቂቃዎችን ደማምሮ - ሰዓትን እያማጠ፣ የሰው ልጅ ባያምንም - ልሹ እጅ ሰጠ። ጥፋት እያሰራው - አልሸነፍ ባይ ጅልነት፣ ሌላው አልቆ - እኔ ልኑር የሚልበት፣ ውሸትን ተላምዶ - ውስጡ ረሳ እውነት። እውነት እዛው ቆመ - በውሸት ተይዞ፣ አረ ህዝብ  አለቀ - በሴራ ተመርዞ፣ ሰውም ጨርሶ ወለደ - ክፋትን አርግዞ። ሰውም ጨርሶ ወለደ - ክፋትን አርግዞ‼️        âœ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 YouTube: youtube.com/@SharpSwords1 Instagram: Instagram.com/sharp_swords1 Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil

በፍልስጤም ቅዱስ በሆነው አልአቅሳ መስጂድ የዛሬውን የጁመአ ሰላት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መስገዳቸው ተገልጿል። … በሌላ መረጃ እስራኤል በጋዛ በፍልስጤማውያን ላይ እየፈፀመችው ባለው ጥቃት ከ10 ሺ
+2
በፍልስጤም ቅዱስ በሆነው አልአቅሳ መስጂድ የዛሬውን የጁመአ ሰላት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መስገዳቸው ተገልጿል። … በሌላ መረጃ እስራኤል በጋዛ በፍልስጤማውያን ላይ እየፈፀመችው ባለው ጥቃት ከ10 ሺህ በላይ ሴቶች መገደላቸውን የፍልስጤም የዜና ምንጮች ዘግበዋል። …

አነጋገሩ ራሱ አይከብድም? "የጌታ መቃብር"! سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ! (وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ ع
አነጋገሩ ራሱ አይከብድም? "የጌታ መቃብር"! سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ! (وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا) «እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡» [አ-ን'ኒሳእ: 157]

📹 የመሲሕ ባሮች ሆይ 1 ጥያቄ አለን? የ ኢብኑል ቀይም መካሪ ግጥም →

ለእየሱስ ባሪያዎች! ~ የመሲህ ባሮች ሆይ - አንድ ጥያቄ አለን የተረዳው ካለ - መልሱን እንሻለን ጌታ ግፍ አቅቶት - ሰዎች ከገደሉት አለቀ አከተመ - የታል አምላክነት?! ሰዎች የሰሩትን - በሱ ላይ ሲያደርሱ ጌታ ግብራቸውን - ፈቅዶ ነው በራሱ? እንዲያ ከሆነማ - ምንኛ ታደሉ?! ፍቅሩን ይቸራሉ - ፈቃዱን ሲሞሉ። ባደረሱት ሁሉ - አልፎ ከተከፋ እንግዲህ ምን ይባል? ሀይሉ ከኮሰሰ - ሀይላቸው ከሰፋ?! ግን እንጠይቃለን - ለመልስ አትንፈጉ ማለባበስ ይቅር - ይመለስ በወጉ ፈጣሪዋን አጥታ - ዐለም ስትዋትት ሰው ወደ ማን ነበር - የሚያስበው ፀሎት? ፍጡር ፈጣሪውን - ካፈር ሲያደባየው ሰባቱን ሰማያት - ማነበር ያቆየው? ምስማር ተቸንክሮ - ሲያሸልብ ፈጣሪ ዓለም ቀርታ ነበር - ያለ አስተናባሪ? የሰማይ መላእክት - ምንኛ ለገሙ?! እጁ ተቸንክሮ - ዋይታውን ሲሰሙ? እንጨቱም ታምር ነው - አቅሙ መቋቋሙ አምላክ ያክል ነገር - ችሎ መሸከሙ ስለቱስ ጭቃኔው - ብረቱ ምስማሩ አካሉን ሰንጥቆ - ስቃይ ማሳደሩ ጉድ በሉ እሄን ጌታ - በአይሁድ የሚረታ ማጅራቱን ታንቆ - ታስሮ የሚመታ ኋላስ ራሱ ነቃ - ከሞት አንሰራራ ወይስ ጌታ አገኘ - ህይወት የሚዘራ?! ጉድ በሉ ለቀብር - ጌታ አቅፎ ለያዘ የባሰም ሆድ አለ - አምላክ ያረገዘ ዘጠኝ ወር ታሽጎ - ሲኖር በጨለማ ሐይድ እየተጋተ - ደም እየተጠማ ብልት ቀዶ ወጣ - አቡሻ ህፃኑ አፉን ለጡት ከፍቶ - አቤት ማሳዘኑ! አስቡ እሄን አምላክ - ሲጠጣ ሲበላ ከዚያም ያስገባውን - ሲያስወጣ በሌላ ጌታዬ ከፍ አለ - ከነሳራ ቅጥፈት ሁሉም ይጠየቃል - ለቀባጠረበት የመስቀል ባሮች ሆይ! - ግራ ገባኝ እኔ ያሽቀነጠረው ሰው - ፅድቅ ነው ኩነኔ ማቃጠል ሰባብሮ - ፈቃጁን ጨምሮ ህሊና ከዚህ ውጭ - ይፈርዳል አምርሮ? አምላክ አቅም አንሶት - ለተጠፈረበት ሰብሮ እንደማቃጠል - ጭራሹን አምሎኮት?! እውነትም እርጉም ነው - ለምንስ ይዘንጋ? በመሳለም ሳይሆን - በእግር ይሰጥ ዋጋ! ለተዋረደበት - ጌታህ ከነነፍሱ አንተ ካመለክከው - የሱ ነህ የነሱ? ‘ጌታን ስላዘለ’ - ከሆነ አክብሮቱ አስተዋሽ ቅርፃቅርፅ - ቢሆን እንጂ እንጨቱ መስቀሉ ከጠፋ - ሺ ስንት አመታቱ?! እንዲያ ከሆነማ - ሂሳቡ ቀመሩ ለመስገድ አትቦዝን - ለየመቃብሩ ያስታውሳልና - ነገረ ስርኣቱ "ጌታህ" ካፈር በታች - ለነበረበቱ። የመሲህ ባሪያ ሆይ! - ንቃ ተረጋጋ ይሄ ነው እውነታው - ካ'ልፋ እስከ ኦሜጋ፡፡ የኢብኑል ቀዪም አልጀውዚያህ “አዑባደል መሲሒ ለና ሱኣሉን” ድንቅ ግጥም ግርድፍ ትርጉም፡፡ ግጥሙን “ኢጋሠቱል ለህፋን ኪታክ ገፅ: 2/290 ላይ ያገኙታል፡፡ የግጥሙን አሪፍ የቪዲዮ ቅንብር ደግሞ ከፍቺው ጋር ከስር ይመልከቱ፡፡ ኢብኑ ሙነወር = * ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor * ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL * ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

◆ የተጠሰኝ እድሜ ዘመን ላልሻገር - በተሰጠኝ እድሜ ለምን እኖራለሁ - ስንቱን አስቀይሜ ላለፈው በደሌ - ጠይቄ ይቅርታ በፍቅር ተክቼ - የበቀሌን ቦታ ጊዜያዊ ነውና - የምድር ቆይታ ምንም ነገር ትቼ - ልኑር በይቅርታ፡፡ ሰዎችን እያስከፋሁ - ባላሰብኩት መንገድ በስህተቴ ተክዤ - ምንም ብናደድ ስህተት ሰርቻለሁ - ሳልወድም በግድ ቃል ገባሁ ለራሴ - እውነትን ልነግድ፡፡ ሰውን ማስከፋት - ሰላምን ካሳጣ ውስጤ ከተከፋ - ከመጣብኝ ጣጣ እጅግ ተጠብቤ - ጭቀቴ ከመጣ ሰጥቼ ልረፍ - የይቅርታን እጣ፡፡ ሰው ፉፁም አደለም - እንደው አትከፉ ይቅርታን ተቀበሉ - አታስቡ ክፉ ውሸትን አባረው - ሀቅን እያቀፉ በሰላም መኖር ነው - የድሮን እየተፉ፡፡ ወዳጆቼ ስሙኝ - እንደው ልምከራችሁ እህትና ወንድም - ሰዎች የሆናችሁ ወደ ሩቅ ሀገር - ከጠርም ያላችሁ ውዶቼ ሁላችሁንም - ሰላም እያልኳችሁ ዕውቀት ባይኖረኝም - ትንሽ ልበላችሁ፡፡ ይቅርታውን እንቀበል - ስህተትን ለሳራ የኛ እንቢ ማለት - ማዶ ላያበራ ጎጆ ቀልሶልን - ቤታችን ላይሰራ ሞትም ሊደርሰን - ለሁሉም በተራ ይቅርታ ይሻላል - ቡረቃው የጋራ፡፡ ሸር በዛ አደል? - እንደው በዚህ ዘመን በቃ ቀረ አደል? - እንደው ሰውን ማመን ጊዜው ተበላሸ - ኑሮም ኮድ ጠየቀን፡፡ የዚህ ሁሉ ትምኪት - ምን ይሆን ችግሩ? ሰው ሁሉ ተነስቶ - ለውሸት *ማበሩ* እውነትን ላይችሏት - ከመንገድ ሊቀሩ ጨለማን ለማፅደቅ - ለብርኃን ሳይራሩ ወዲህ ሳይሆን አይቀርም - እንደው ቁምነገሩ ምድርን ሲያናውጧት - ቅጣትን ሳይፈሩ ይቅርታ አለማወቃቸው - ሰላምን ሰበሩ ውሸት ቆማ ሄደች - እውነቶች ተቀበሩ፡፡ ይቅርታ ባለማለታችን - ከተጎዳን እኛ እንደው ይቅርብን - አንሁን ጎጠኛ ብርኃን አይሻለም? - ይቅር ጨለምተኛ ሰላምን ብናወርስ - ባንሆን ትምኪተኛ ይቅርታ እንጠይቀ - አንሁን ነውጠኛ፡፡ የኑሮን ሰመመን - ላልችለው ቆሜ አብሬ ካልሰራሁ - ከውድ ወንድሜ ተበላሽቶ ካየሁት - የይቅታ ስሜ ለምን እኖራለሁ - ስንቱን አስቀይሜ ዘመን አያሻግረኝ - የተጠሰኝ እድሜ ዘመን አያሻግረኝ - የተጠሰኝ እድሜ ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ቀን፦ ሕዳር 19/2011 [ Nov 28/2018] ummalife.com/ReshadMuzemil

በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿الصدقةُ على المسكين صدقةٌ، وعلى القريبِ صدقتان: صدقةٌ وصِلَةٌ﴾ “ለምስኪን ሶደቃ መስጠትህ ሶደቃ ነው።
በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿الصدقةُ على المسكين صدقةٌ، وعلى القريبِ صدقتان: صدقةٌ وصِلَةٌ﴾ “ለምስኪን ሶደቃ መስጠትህ ሶደቃ ነው። ለዘመድ ሲሆን ግን ሶደቃ እና ዝምድና መቀጠል ነው።” 📚 ሶሂህ አተርጊብ: 892

ሶፊያን አስውሪ (رحمه الله) እንዲህ ይሉ ነበር፦ ﴿إذا عرفتَ نفسَك لم يضرَّكَ ما قيلَ لَكَ،﴾ “አንተ ስለራስህ የምታውቅ ከሆነ፤ ስላንተ የሚባለው የሰዎች ንግግር አይጎዳ
ሶፊያን አስውሪ (رحمه الله) እንዲህ ይሉ ነበር፦ ﴿إذا عرفتَ نفسَك لم يضرَّكَ ما قيلَ لَكَ،﴾ “አንተ ስለራስህ የምታውቅ ከሆነ፤ ስላንተ የሚባለው የሰዎች ንግግር አይጎዳህም።” [«አልሙኽለሲያት» ሊአቢ ጣኺር አልሙኽለስ (1626)] ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM

🌕 ከሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት የበለጠ ለመረዳት የሚያስችሉህ ጥያቄዎች ናቸው ። ስለራስህ ትክክለኛ የሆነውን መረጃ በመመለስ ውጤትህን ነጥቦችን በመያዝ ማወቅ ትችላልህ ። 1. የብዙ ሰዎች እይታ ወዳንተ ያተኮረ መሆኑን ስትረዳ ምን ይሰማሀል ? - እፍረት ( አንድ ነጥብ) - ምንም የተለየ ነገር አይሰማህም ( ሁለት ነጥብ) - በራስ መተማመንና ደስ የሚል ስሜት ( ሶስት ነጥብ) 2 .ብዙ ጊዜ እይታን የሚስብ አለባበስ ትለብሳለህ? - አው ሁሌም ( ሶስት ነጥብ) - በተወሰኑ አጋጣሚዎች ብቻ ( አንድ ነጥብ) - በጭራሽ ( ሁለት ነጥብ) 3. ስብስሶች የበዙበት ቦታ ላይ ስትሆን ድምፅህን ዝቅ አድርገህ ነው የምታወራው? - አው… አንዳንዴም ንግግሬ እንዲሰማ ልደግመው እችላለሁ ( አንድ ነጥብ) - አይ… ድምፄን ዝቅ አድርጌ የማወራበት ምክንያት የለም ( ሶስት ነጥብ) - አንዳንዴ ( ሁለት ነጥብ ) 4.ብቻህን ስትሆን ምን አይነት ስሜት ይሰማሃል? - ከባድ የሆነ ብቸኛነት ( አንድ ነጥብ) - በእርፍትና መረጋጋት ( ሶስት ነጥብ) - ነፃነት (ሁለት ነጥብ) 5. ሰዎች ሲተቹህ ምን ይሰማሀል ? - ቅሬታ ( ሁለት ነጥብ) - ምንም አይመስልህም ( አንድ ነጥብ) - ደስታና ራስህን ለማሻሻል ጥሩ አድል እንደሆነ ታምናለህ ( ሶስት ነጥብ) ---------------------- ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛

የላቀ ምንዳ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَن صلى الفجرَ في جماعةٍ، ثم قَعَد يَذْكُرُ اللهَ حتى تَطْلُعَ الشمسُ، ثم صلى ركعتينِ، كانت له ك
የላቀ ምንዳ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَن صلى الفجرَ في جماعةٍ، ثم قَعَد يَذْكُرُ اللهَ حتى تَطْلُعَ الشمسُ، ثم صلى ركعتينِ، كانت له كأجرِ حَجَّةٍ وعُمْرَةٍ تامَّةٍ، تامَّةٍ، تامَّةٍ﴾ “የፈጅርን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ። ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ ሙሉ! ሙሉ ! ሙሉ!” 📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 6346

ሰው መሳይ በሸንጎ ~ ዑለማኦች ከሰውነት አጥር ውጭ አይደሉም። የሰው ልጅ ላይ የሚታዩ ድክመቶች ይታዩባቸዋል። ከዒልምና ከተቅዋ አንፃር በአመዛኙ ከሌሎች ስለሚሻሉ የተሻለ ነገር እንጠብቃለን። ይሁን እንጂ "የኣደም ልጅ ሁሉ በጣም ተሳሳች ነው" ከሚለው እውነታ ውጭ እንዳልሆኑ መዘንጋት አይገባም። ስለሆነም፡ * አንዳንዴ ስሜታዊነት፣ ምቀኝነት፣ ጥቅመኝነት፣ ዝናን መሻት፣ አጉል ተጠራጣሪነት፣ ... የመሳሰሉ መጥፎ ባህሪዎች ሊፀናወቷቸው ይችላሉ። * ወይም ተቆርቋሪና ታማኝ የመሰለ የቅርብ ሰው የሚያሳስታቸው ሊኖሩም ይችላሉ። በነዚህ ወይም በሌላ ምክንያቶች አንዱ ዓሊም ሌላው ላይ ከባድ ቃል ሊናገር ይችላል። ይሄ በአየር ላይ ያለ ምናብ ሳይሆን ተጨባጭ ምሳሌዎች ሊጠቀሱበት የሚችል እውነታ ነው። ይህንን ከተረዳን አንድ ዓሊም በሌላው ዓሊም ላይ ከባድ ትችት ቢሰነዝር ሳያጣሩ ከማራገብ በፊት ጉዳዩን ቆም ብሎ ማጤን ይገባል። * ሌሎች ዓሊሞች ምን ይላሉ? ጉዳዩን ከማወቃቸው ጋር የተለየ ትንታኔ ሰጥተዋል? ተማሪዎች በጉዳዩ ላይ አርፈው እንዲቀመጡ አሳስበዋል? ዝምታን መርጠው ከሆነም ለነሱ የበቃ ዝምታ ለኛም ሊበቃን ይገባል። * ጉዳዩ በልኩ ተይዞ ይሆን? ወይስ ድንበር ባለፈ መልኩ ነው የተያዘው? * የትችቱ መነሻ ምንድነው? አሉባልታ ላይ ወይስ ተጨባጭ መረጃ ላይ የተመረኮዘ ነው? * ተወንጃዩ አካል ምን ይላል? እንደተዋሸበት ይናገር ይሆን? ንግግሩ ተቆልምሞ ሌላ ትርጉም ተሰጥቶበት ይሆን? እየተከሰሰ ያለው ከጥፋቱ ከተመለሰ በኋላ ይሆን? ይሄ ትችቱ በዑለማኦች የተሰነዘረ ከሆነ ነው። ካልሆነስ? * ሲጀመር ተቺዎቹ እነማን ናቸው? አንዳንዶቹ እዚህ ግባ የማይባሉ ከንቱ ፍጥረቶች ናቸው ከተራራ የገዘፉ ዓሊሞች ላይ አንጋጠው የሚተፉት። የሆነ ጊዜ አንዱ ጎረምሳ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድን ሲዘረጥጥ ነበር። በአደብ ቢያርርም ምንም አልነበረም። "ሁሉም አራሚና ታራሚ ነውና።" ነገሩ ግን እንደዚያ አልነበረም ያደረገው። ሸይኽ ዐብዱልሙሕሲን የሱን ብጤ ቀርቶ እሱ የሚያጣቅሳቸውን ሸይኾች ያስተማሩ የሸይኾቹ ሸይኽ ናቸው። እሱ በገለፀበት መልኩ ሸይኾቹ እንኳ አይደፍሯቸውም። ታላላቆቹ በሚያፍሯቸው ታላቅ ሸይኽ ላይ ሲዳፈር ማየት ያሳቅቃል። ይህን እንድፅፍ ያደረገኝ ሸይኽ ፈላሕ ሙንደካርን፣ ሸይኽ ሷሊሕ አሱሐይሚን፣ ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድርን የሚያብጠለጥሉ አካላትን አይቼ ነው። በቃ ብልግና ጀብድ ሆነ። ለሆነ ሸይኽ ቅርብ ስለሆኑ ወይም ከሆነ አካል ተዝኪያ ስላላቸው ራሳቸውን አይነኬ የሚያደርጉ አንዳንድ "ከተዘሩ ያልታረሙ" ዋልጌዎች አሉ። ለእንዲህ አይነቶቹ ሙጅሪሞች ቦታ መስጠት ራስን ማርከስ ነው። ምግባሩ ያቆሸሸውን የማንም ተዝኪያ አያፀዳውም። አላሁል ሙስተዓን! = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor