cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

TUBA ISLAMIC ASSOCIATION

(عن ابي هريرة رضي الله عنه،قال قال رسولﷺ :- "بدأ الاسلام غريبا وسيعود كما بدأ غريبا فطوبى للغرباء.")

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
254
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼ ================== ✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ። ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35708 * ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት። https://t.me/MuradTadesse/35742 ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር! አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር። የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35632?single ከተቋማችንም ጎን እንቁም። የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
إظهار الكل...
በኒቃብሽ ኩሪ ! በሱረቱል አህዛብ በደማቅ ተከትቧል፤ ከአንገትሽ ቀናበይ  ታሪክሽ ተውቧል፤ ድንቅ ነው ኢስላምሽ ከአምላክ የተሰጠሽ፤ ቅይጥ የሌለበት ጥርት ያለ ሀብትሽ፤ እስኪ መለስ በይ እልፍ አመታትን፤ ትእዝዛ ሲመጣ ወህይ ከአምላካችን፤ እንዴት ነበረ እስኪ ድንቁ ታሪካችን፤ የሂጃቡ አያህ ሲወርድ ለአለማት፤ ያኔ ሲታዘዙ እኒያ ሶሀቢያት፤ ሀገሩን አስዋቡት በጥቁር ቀለማት፤ በኒቃብ በጅልባብ አበሩ በውበት። 〰〰〰〰〰〰〰〰〰 አንቺስ ምንሽ ሞኙ ማማር የምትጠይው፤ በሂጃብ ተውበሽ አምላክሽን ታዘዢው፤ አዎ ታዘዢው ሀያሉን ህልምሽ እንዲሳካ፤ በዱንያም በአኼራም እንድትይ ፈካ፤ አትስጊ በፍፁም ባል ይጠፋል ብለሽ፤ እዝነቱን ፈልገሽ ኒቃብ በመልበስሽ፤ አንቺ ጀግና ሆነሽ ለትእዛዙ ካደርሽ፤ ቤትሽን ያንኳኳል ይቆማል ከበርሽ። 〰〰〰〰〰〰 እውነቱን ልንገርሽ የኒቃብን ዋጋ፤ ሊያናግርሽ ያፍራል ካንቺ የተጠጋ፤ መናቅኮ አይደለም ክብር ስላለው ነው፤ ሊቀርብሽ ያልቻለው በሩቁ የሸሸው፤ አንቱታን አተረፍሽ በ15 አመትሽ፤ ድል አጎናፀፈሽ ኒቃብ በመልበስሽ፤ ወለም ዘለም አትበይ ፅኚ በሂጃብሽ፤ ምድር ሁኝ ለባልሽ ሰማይ እንዲሆንልሽ፤ ክብርን አጎናፅፊው እሱም እንዲያከብርሽ። 〰〰〰〰〰〰〰〰 ደሞ ሴቶች አሉ ፀጉር የሚቆልሉ፤ ሂጃብ ለበስን ብለው የሚንቀዋለሉ፤ ረሱል ተራግመዋል ብለሽ ስትነግሪያቸው፤ አቦ አታጠባብቂ እነሱን ተያቸው፤ ገና አልሰለጠኑም ኃላ ቀር ናቸው፤ ብለው ያሾፋሉ ሞኛ ሞኝ ናቸው፤ ፀጉር መቆለሉ ደሞም መወጣጠር፤ ቅርፅን ማሳየቱ ሂጃብን መወርወር፤ ይሄ አይደል መስፈርቱ ለትዳርሽ መስመር፤ ይልቅማ አዳምጪኝ ለትዳርሽ ማማር፤ ዘላቂው መፍትሄ በሰላም ለመኖር፤ ሁሌ ለመወደድ ሁሌም ለመፈቀር፤ ሂጃብ ነው ሚስጥሩ ልቀቂው ከላይሽ፤ ሀያእም ተላበሽ አርጊው ጎረቤትሽ፤     Dekam አትሁኝ ማስረጃን ሰንቂ፤ ለምትሰሪው ስራም ደሊሉን እወቂ፤ ይህንን ካደረግሽ እህቴ እወቂ፤ ፍፁም አትወድቂም የለሽም ነቅናቂ። ©ለሙስሊሟ እህቴ
إظهار الكل...
surat Al-muminun 84-87
إظهار الكل...
የመጨረሻው ክፍል ክፍል 5... የሰላት አበላሾች 1.አውቆ/ሆን ብሎ መናገር 2.መሳቅ 3.መመገብ 4.መጠጣት 5.የሀፍረተ ገላ መገለጥ 6.ከቂብላ ብዙ የሆነ መዘንበል 7.ከሰላት ውጪ የሆነ ተከታታይ እንቅስቃሴ 8.ጦሀራ አለመሆን •እነሆ በ5 ክፍሎች ስለ ሰላት ሹሩጥ,አርካን,ዋጂብ,ሱና እና የሰላት አፍራሾችን አይተናል:: ኢንሻአላህ በpdf መልክ ሰብሰብ ተደርጎ የሚለቀቅ ይሆናል:: ●እነዚህ ፅሁፎች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አስተዋፅኦ ያላቸውን እና አንባቢያንም ጭምር አላህ ኢኽላሱን ሰጥቶ በጀነተል ፊርደውሱ ይሸልማቸው!!! ሱብሀነከላሁመ ረበና ወቢሀምዲክ አሽሀዱ አነ ላኢላሀ ኢላ አንተ አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይክ © https://t.me/tubajemea
إظهار الكل...
TUBA ISLAMIC ASSOCIATION

(عن ابي هريرة رضي الله عنه،قال قال رسولﷺ :- "بدأ الاسلام غريبا وسيعود كما بدأ غريبا فطوبى للغرباء.")

🌥🌥اذكار الصباح 🌥🌥 اصْبَحْنا وَأَصْبَحَ المُلْكُ لله وَالحَمدُ لله، لا إلهَ إلاّ اللّهُ وَحدَهُ لا شَريكَ لهُ، لهُ المُلكُ ولهُ الحَمْد، وهُوَ على كلّ شَيءٍ قدير، رَبِّ أسْأَلُكَ خَيرَ ما في هذا اليوم وَخَيرَ ما بَعْدَه، وَأَعوذُ بِكَ مِنْ شرِّ ما في هذا اليوم وَشَرِّ ما بَعْدَه، رَبِّ أَعوذُ بِكَ مِنَ الْكَسَلِ وَسوءِ الْكِبَر، رَبِّ أَعوذُ بِكَ مِنْ عَذابٍ في النّارِ وَعَذابٍ في القَبْر. اللّهُمَّ بِكَ أَصْبَحْنا وَبِكَ أَمْسَينا، وَبِكَ نَحْيا وَبِكَ نَمُوتُ وَإِلَيْكَ النُّشُور أَصْبَحْنا عَلَى فِطْرَةِ الإسْلاَمِ، وَعَلَى كَلِمَةِ الإِخْلاَصِ، وَعَلَى دِينِ نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، وَعَلَى مِلَّةِ أَبِينَا إبْرَاهِيمَ حَنِيفاً مُسْلِماً وَمَا كَانَ مِنَ المُشْرِكِينَ اللّهُمَّ إِنِّي أَصْبَحْتُ أُشْهِدُك، وَأُشْهِدُ حَمَلَةَ عَرْشِك، وَمَلَائِكَتَكَ، وَجَميعَ خَلْقِك، أَنَّكَ أَنْتَ اللهُ لا إلهَ إلاّ أَنْتَ وَحْدَكَ لا شَريكَ لَك، وَأَنَّ مُحَمّداً عَبْدُكَ وَرَسولُك قراءة الآيتان 285-286 من سورة البقرة آية الكرسي سورة الإخلاص، سورة الفلق، والناس @tubajemea @tubajemea