ግጥም
الذهاب إلى القناة على Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
إظهار المزيد4 828
المشتركون
+824 ساعات
+657 أيام
+21630 أيام
أرشيف المشاركات
4 827
ትኩረት ማረግ አለብሽ
መምህርት: የኢራቅ ፕሬዝዳንት ማን ነው ?
.
አቤ: አላቀውም
.
መምህርት: ጥናት ላይ ትኩረት ማድረግ አለብህ !
.
አቤ: ቲቸር ጥያቄ ልጠይቅሽ
.
መምህርት: ይቻላል
.
አቤ: ፍቅርተን ታውቂያታለሽ ?
.
መምህርት: አላውቃትም ምነው
.
አቤ: ባልሽ ላይ ትኩረት ማረግ አለብሽ !
4 827
#መቼ_ስጠን_አልንህ?
እኛን የናፈቀን ጥላቻን ሰባሪ
ፍቅርን አንግሦ ሀገር አሻጋሪ
ከዘር ዛር የራቀ እውነተኛ መሪ
ለፍትሕ አድልቶ ሰላም ዘማሪ
መቼ ስጠን አልንህ? ጌታ ነገር ሰሪ
ቂም እያረገዘ የሰው ዘር ቆጣሪ
ወይስ ከዙፋኑ ከወንበሩ ማርጀት
የታላቅ ህዝብ ሀገር ሁሌ መሪ ማጣት
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
/// " አፋቅሮ ያስማማን "///
በጥላቻ ኖረን ዘርን ከምንቆጥር
አፈር ያስማማናል ሞተን እንፋቀር
መግባባት ከአቃተን በህይወት እያለን
ሞታችን ይምጣና አፋቅሮ ያስማማን።
አሁን በዚህ ዘመን መኖሮ ለማን ሊበጅ
የተጣላ ሁሉ በአፈር ፍቅር ይወዳጅ።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
#ችግር_የለም_አትበል
የሀገር ካዝና ጎድሎ ያንተ ስለሞላ
ሚሊዮን ጦም አድሮ ግለሰብ ቢበላ
እንዴት ይመዘናል በጥቂቶች ጥጋብ
ይፋለስ የለም ወይ በብዙዎች ራብ
ህዝብ ተቸግሮ አንተ ሽህ ብትከምር
አይሆንህም ጤና አትዝረፍ ከሀገር
ችግር የለም አትበል ቤትህ ስለሞላ
ሚሊዮን ጦም ያድራል እራቱን ሳይበላ
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
#አብረህ_አትርመጥመጥ
ከትርምስ ዓለም ጋጋታ ከሞላው
እየተጋፋፋ ከሚዘላለፈው
ጥቂት ፈቀቅ በል እራስህን አድምጥ
የአንተነህ ዋጋ በሌሎች አይዋጥ
ጡዘቱ ከናረው ጠብቆ ከከረረው
መናገር ብቻ እንጂ ማድመጥ ከሰለቸው
ጥቂት ፈቀቅ በል ጥቂት እፎይ ምረጥ
ከሚተራመሰው አብረህ አትርመጥመጥ
ከልብህ ዋጋ ጋር እራስህን አድምጥ
ከተፈጥሮ ጋራ ሀሳብ ተለዋወጥ!!!
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
#አልቻለም_ሊወለድ
የእናት ውለታዋን መጣኝ ቃል ፍለጋ
ሊቃውንት ተማክረው ቢሉ ቆላ ደጋ
አዲስ ዜማ ቅኔ ገላጭ ቃል የላቸው
እናት ከማለት ውጭ መጥራት ተሳናቸው
ሽህ ዘመናት መጥቶ ሽህ አዋቂ ቢሄድ
ከእናት በላይ ቃላት አልቻለም ሊወለድ
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
መኖር ትርጉም ካጣ ከተብከነከነ
ከህይወት ተኳርፎ እዲው ከመነነ
አለም ባዶ ሁና ከቆረጥክ ተስፋ
ከጎንህ ሰው ካጣህ አዝነህ ስትከፋ
ዛሬ ነገ አደለም አለው አዲስ ተስፋ
ብትወድቅም ጠንክረህ ለመነሳት ልፋ
የእውነት ቀን ላንተ አለ የብርሀን መንገድ
በመውደቅም መሀል መነሳትን ልመድ
ሰው እንደው ጥፍር ነው የሰውነት ባዳ
ስሞ የሚሸጥህ ልክ እንደ ይሁዳ።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
" ነጎደ!!! በረረ!!! "
ዙፋኑ ተሰርቶ በቂም ውርስ ጥላቻ
መሪው ቢቀያየር ወጥ ላይሆን ጉልቻ
የሚጣፍጥ ፍትህ የሚያረካ ሰላም
ሁሌም እንዳማረን የመቻቻል ቀለም
እንኳንስ በጥንቱ ታሪክ በሰነደው
በእኛ እድሜም ብዙ አየን ወጥቶ በወረደው
ስንቱን ስንሾም ስንሽር ትውልድ ተገብሮ
መኖር እያቃተን አብሮ ተከባብሮ!!!
ከጥንቱም እያነስን የጥንቱን እየናቅን
ሙት ወቃሽ ሙት አንጋሽ ሁለት ሀሳብ ይዘን
ይኸው የእኛ እድሜ እንኳን ነጎደ በረረ
ለውጥም ሳናመጣ ቅሉም ተሰበረ!!!
ስንት መሪ ቆጥረን ስንት ትውልድ ቀብረን
ዛሬም የማንማር መላው የጠፋን ነን።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
#ማን_ያስተምረናል?
ገድሎ መፈክርን ተክነንበታል፣
ታግሶ ማለፍን ማን ያስተምረናል?
ምህረት እንጂ ለሰው የቸገረው ዛሬ፣
ገድሎ ሸላይማ መቺ አጣች ሀገሬ።
የበደለን ምረን ይቅርታ አለማወቅ፣
ውርሳች ነው ዛሬም በግፍ መተላለቅ።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
/// " ምግባር ባይኖረኝም "///
ጌታ ቶሎ ምጣ አምላክ ቶሎ ድረስ
ዓለም ብሶባታል የንጹህ ደም ማፍሰስ
ለጽድቅ የሚያበቃ ምግባር ባይኖረኝም
ይምጣ የፍርድ ቀን አሁን ግድ የለኝም
የግፍ ዘመን ሆኗል ግዜው እጅግ ከፍቶ
የበደል ጽዋችን ገደብ አልፎ ሞልቶ!!!
ሀገር የደም መሬት አኬልዳማ ሆና
ሰው እድሜ ይመኛል ዛሬም እንደገና
ምን ሊበጀኝ መኖር ምን ሊረባኝ እድሜ
የግፍ ግፍ ለመቁጠር በግፍ ዓለም ቆሜ
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
#የከንቱ_ከንቱ_ነው
ስንት ነው ሂሳቡ? የነፍሳችን ዋጋ
የጌታ ቀን ደርሶ ሲመጣ ፍለጋ
በየትኛው ሚዛን በየቱ ተሰፍሮ?
ይከፈለን ይሆን ዋጋው ተደምሮ?
ህይወታችን ሙሉ በበደል ሲጣፋ
የግፋችን ስፍረት ቀን በቀን ሲሰፋ
የትኛው ቅንነት የትኛው ሰው ይሆን?
አምላክ ፊት ለመቆም እኔ አለሁ የሚለን?
ፈራሁ በበኩሌ ዋጋዬን ሳሰላው
የስራዬን ክብደት ቆሜ ዝመዝነው
አጣሁ ጥሩ ነገር ለአምላክ የሚነገር
የከንቱ ከንቱ ነው ህይወቴ ሲሰፍር።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
" በተራ ልጠጣው"
ስከር ስከር አለኝ ያሻህን ተናገር
ሰው መቸም ጀግና ነው በጠላው ሲሰክር
ከጠጁም ደጋግም አንጋጥ በብርሌ
በፔንድሎም ዜማ ይደንስ አካሌ
ሆድ ያባውን ጌሾ ፈንቅሎ ካወጣው
ከጠላው ከጠጁ በተራ ልጠጣው።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
#መነሳቴ_ላይቀር ❤
ከትላንት ውድቀቴ ከአለፈው ተምሬ
ልበል ዳዴ ዳዴ ችዬ ልቁም በእግሬ
ጠላቴ አትደሰት ወድቆ ቀረ ብለህ
የእኔ ከስር መቅረት አንተን ለማይጠቅምህ
በእግዚአብሔር እርዳታ መነሳቴ ላይቀር
አብዝተህ አትሳቅ እንባባል ይቅር!!!
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
4 827
#የእኔና_አንቺ_ታሪክ
ከሽህ ጦር አለቃ ከሽህ መውዜር ጓንዴ
የእኔና አንቺ ፍቅር ይማርካል ውዴ ❤
ዘርሽን ሳልጠይቅ ዘሬን ሳታጣሪ
በልቤ ውሰጥ ገብተሽ ፍቅርን ስታበሪ
በሰውነት ሚዛን አክብረሽ ስትከብሪ
ስወድሽ ስቶጅኝ ሳኮራሽ ስትኮሪ!
ከሽህ ታንክ ጋጋታ ከሽህ መድፍ ማጓራት
እኔና አንቺ ውዴ ማርኮናል ሰውነት ❤❤
ከዘር ዛር እርቀን በልባችን ጀልባ
ቀጥፌ ስሰጥሽ የፍቅርን አበባ
ሰውነቴ ገዝቶሽ ሰው መሆንሽ ገብቶኝ
እኔነቴ ማርኮሽ አንችነትሽ ገዝቶኝ!!!
በእቅድ ከሚመራ ከብዙ ጦር ልቆ
የእኔና አንቺ ታሪክ ይነበባል ደምቆ
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
