cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኑሩል-ሂላል

👇በዚህ ቻናል ላይ👇 👉ከቁርዐን ፣ከሀዲስ፣ከቀደምቶች የተሰጡ ምክሮች 👉የዘመኑ ትዝብቶችና አስደናቂ እውነታ 👉ልቦነ ሚያረኩ የቁርዐን ድምፆች 👉ፈገግ የሚያስብሉ ንግግሮች 👉አፎካካሪ ጥያቄና መልሶች ......እና 👉የተለያዩ እውነታዎች ይገኙበታል ⚠️ቻናሉን ለወዳጅዎ እና ለቅርብ ዘመዶ በማጋራት የምንዳው ተቋዳሽ ይሁኑ። 👉ለአስተያየት✒ https://t.me/ihsanjema

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
771
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-2130 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
🔴  ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ በቀንዱም ይነፋል፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ (በእርሱ) የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡ إِن كَانَتْ إِلَّا صَيْحَةً وَاحِدَةً فَإِذَا هُمْ جَمِيعٌ لَّدَيْنَا مُحْضَرُونَ (እርሷ) አንዲት ጩኸት እንጂ አይደለችም፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ فَالْيَوْمَ لَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْئًا وَلَا تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ «ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንም አትበደልም፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም» (ይባላሉ)፡፡፡፡ [ሱረቱ ያሲን  : 51-54] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
330Loading...
02
Media files
570Loading...
03
ከ ጎንደር የተላከ መልእክት ሙስሊም የሆነ ሁሉ ሼር ያድርግ 😭😭😭 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
611Loading...
04
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 أَفَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا بَيَاتًا وَهُمْ نَائِمُونَ የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የተኙ ኾነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን أَوَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا ضُحًى وَهُمْ يَلْعَبُونَ የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የሚጫወቱ ኾነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋድ ሊመጣባቸው አይፈሩምን أَفَأَمِنُوا مَكْرَ اللَّهِ ۚ فَلَا يَأْمَنُ مَكْرَ اللَّهِ إِلَّا الْقَوْمُ الْخَاسِرُونَ የአላህንም ማዘናጋት አይፈሩምን የአላህንም ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር የሚተማመን የለም፡፡ [ሱረቱ አዕራፍ  : 97-99] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት❤️ https://t.me/eslamisthebasetrilgen
641Loading...
05
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 ۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡ [ሱረቱ ዙመር  : 53] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
621Loading...
06
Media files
600Loading...
07
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 قَالَ بَلْ سَوَّلَتْ لَكُمْ أَنفُسُكُمْ أَمْرًا ۖ فَصَبْرٌ جَمِيلٌ ۖ عَسَى اللَّهُ أَن يَأْتِيَنِي بِهِمْ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْعَلِيمُ الْحَكِيمُ (ያዕቆብ) «አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡ (ሠራችሁትም)፡፡ መልካምም ትእግስት (ማድረግ) አለብኝ፡፡ እነርሱን (ሦስቱንም) የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፡፡ እነሆ እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና» አላቸው፡፡ وَتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَا أَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَابْيَضَّتْ عَيْنَاهُ مِنَ الْحُزْنِ فَهُوَ كَظِيمٌ ከእነሱም ዘወር አለናኣ«በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ፡፡ እርሱም በትካዜ የተመላ ነው፡፡ قَالُوا تَاللَّهِ تَفْتَأُ تَذْكُرُ يُوسُفَ حَتَّىٰ تَكُونَ حَرَضًا أَوْ تَكُونَ مِنَ الْهَالِكِينَ (እነርሱም) «በአላህ እንምላለን፡፡ ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም» አሉ፡፡ قَالَ إِنَّمَا أَشْكُو بَثِّي وَحُزْنِي إِلَى اللَّهِ وَأَعْلَمُ مِنَ اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ . . . . [ሱረቱ ዩሱፍ  : 83-87] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
701Loading...
08
...........ፍቅር ብዙ የፍቅር አይነት አለ ። የሁሉም ፍቅር ህመም አለው ። የቁርኣን ፍቅር ሲቀር እርሱ ግን ከሁሉም ይበልጣል ሠላምና እርካታን ይሰጣል ። ቁርኣን የልብ ብርኃን ነው ። አላህ ሆይ ልባችንን በቁርኣን ፍቅር ሙላልን 🤲 🍁 የዕለቱ መልእክቴ........
631Loading...
09
...........ፍቅር ብዙ የፍቅር አይነት አለ ። የሁሉም ፍቅር ህመም አለው ። የቁርኣን ፍቅር ሲቀር እርሱ ግን ከሁሉም ይበልጣል ሠላምና እርካታን ይሰጣል ። ቁርኣን የልብ ብርኃን ነው ። አላህ ሆይ ልባችንን በቁርኣን ፍቅር ሙላልን 🤲 🍁 የዕለቱ መልእክቴ........ #የአኼራ ስኬት || نجاح آخرة ♡
10Loading...
10
Media files
620Loading...
11
ጥያቄዎች 1 በየትኛው ሰሃባ ሞት ምክንያት ነበር አርሽ የተንቀጠቀጠው ? A ሙዓዝ ኢብን ጀበል B ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ C ሰዓድ ኢብን አቢ ወቃስ D ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ(ሰይፉላህ) 2 እየፆመና ቁርአን እየቀራ ሳለ ሸሂድ ሆኖ ደሙ ቁርአን ላይ የተረጨው ታላቁ ሰሃብይ የቱ ነው ? A ዓሊይ ኢብን አቡ ጧሊብ B  ሀምዛ ኢብን አብዱል ሙጦሊብ C አቡ ቀታዳህ D ዑስማን ኢበን አፋን 3 በ 8ኛው ዓመተ ሂጅራ በረሱል ﷺ አማካኝነት የኢስላምን ጥሪ ወደ ሮሙ ንጉስ ሄረቅል እንዲያደርስ የተላከውን ሰሃባ ከተገደለ በኋላ ሙስሊሞች ሮሞቹን ሊበቀሉ ሲሄዱ ቁጥራቸው ከሮሞች ጋር በንፅፅር ምን ያክል ነበር ? A 3000 ሙስሊሞች vs 200000 ሮማውያን B 10000 ሙስሊሞች vs 20000 ሮማውያን C 100000 ሙስሊሞች vs 200000 ሮማውያን D 3000 ሙስሊሞች vs 10000 ሮማውያን 4 ረሱል ﷺ ዘይድ ኢብን ሀሪሳ ከቆሰለ ጃዕፋር ኢብን አቡ ጧሊብ ይተካ። ጃዕፈር ከቆሰለ ደግሞዓብደላህ ኢብን ረዋህ ይተካው በማለት የጦር መኮንኖች አድርገው የላኳቸው ወደ የትኛው ዘመቻ ነበር ? A ሙዕታ B ኸይበር C ኸንደቅ D እሁድ 5 ረሱል ﷺ እናታችን ዓኢሻን በምን ወር ውስጥ ነበር ያገቧት ? A ሙሃረም B ሶፈር C ሸዋል D ሻዕባን 6 ረሱል ﷺ ከመካ ወደ መዲና በምሽት ከቤታችው ሲወጡ በሳቸው መኝታ ላይ እንዲተኛ ያደረጉት የትኛውን ሰሃብይ ነበር ? A ዑስማን ኢብን አፋን B ዑመር ኢብን አል ኸጧብ C አባ በክር አሲዲቅ D ዓሊይ ኢብን አቡ ጧሊብ 7 መካ ላይ በተሰበሰቡ ሙሽሪኮች ፊት ለፊት በመቆም ለመጀመሪያ ግዜ ቁርአንን በግልፅ ያነበበው ሰሃብይ ማን ነበር ? A ዑመር ኢብን አልኸጧብ B ዓብደላህ ኢብኑ መስዑድ C ዓሊይ ኢብን አቡ ጧሊብ D አቢ ዘር አልጊፋሪ 8 ሰሃቦች ከረሱል ጋር ከመካ ወደ መዲና ከተሰደዱ በኋላ በመዲና የተወለደው የመጀመሪያው ልጅ ማን ነበር ? A ዓብደላህ ቢን ዙበይር ኢብን አዋም B ዑሳማ ኢብን ዘይድ C ዓነስ ቢን ማሊክ D ዓብደላህ ኢብን ዑመር 9 በየማማ ጦርነት ላይ ሙሰይሊመተል ከዛብን የገደለው ሰሃብይ ማን ይባላል ? A ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ B ሙስዓብ ኢብኑ ዑመይር C ዓብደላህ ኢብን አቡ ቁሃፋ D ሲማክ ኢብን ኸራሻ 10 አላህ የት ነው የሚገኘው ? A ሁሉም ቦታ B በጀነት ውስጥ C ከአርሽ በላይ D ሁሉም መልስ ነው https://t.me/eslamisthebasetrilgen
732Loading...
12
እሄን ምስል ለመላክ ከራሴ ጋር ቀኑን ሙሉ እየተጣለው ነበር ... እናንተ ለማየት ይከብዳቹወል በማለት ግን ለምን ማፈግፈጌ ራሱ ጥፋት ሆኖ ታየኝ እነሱ እየኖሩት አይደል። እኛ ማየት የከበደንን ነው እነሱ እየኖሩት ያሉት ምናልባት እሄ ትዕይንት ያነቃን ይሁን? ይህ የዛሬው የረፈህ ውሎ ነው። በደም የተለወሰው ምድር ለአላህ የሚያሰማው ብዙ ሮሮ አለ። የተሰራበትን ግፍና በደል ለአላህ ይናገራል። ያም ቀን ሳይደርስ ዛፍ ቅጠሉ ያ ሙስሊም እዚህ አይሁድ አለ ከጀርባዬ ተደብቆሀል መጥተህ ግደለው እያለ ይጣራል አንድ ቀን ኢንሻ አላህ! https://t.me/eslamisthebasetrilgen
661Loading...
13
https://t.me/eslamisthebasetrilgen
531Loading...
14
ኢትዮጵያ ኒቃብ መልበስን ልትከለክል ነው‼ ============================= (የአዲሱ ረቂቅ አዋጅ 15+ ስጋቶች!) || ✍ የኢትዮጵያ መንግስት ኒቃበ ለብሶ መማርንና መሥራትን የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለማፅደቅ በሂደት ላይ ነው። እስካሁን ድረስ በሃገሪቱ ኒቃብን በግልፅ የሚከለክል ህግ ባይኖርም፤ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊም ጠል ኃይሎች ባልተጻፈ ህግ ኒቃብ መልበስን ሲከለክሉ ነበር። ለናሙና ያክል በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በኒቃብ ሳቢያ 2000 ገደማ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የታገዱበት ሁኔታ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ለነዚህና መሰል ኒቃብን በግል ጥላቻቸው ተነሳስተው ለሚከለክሉ አካላት ሽፋን የሚሰጥ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለመፅደቅ በሂደት ላይ ነው። ከኒቃብ ጉዳይ ባሻገር በመሰል ተቋማትና አንዳንድ የህዝብ መገልገያ አካባቢዎች በጀማዓህ ሶላት መስገድን የሚከለክል ክፍልም አለው። ረቂቅ አዋጁ ከመዘጋጀቱ በፊት ለግብዓትነት የሚሆን ጥናት ቀድሞ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉ 10 አባላት መካከል ሙስሊሙን የወከለው አንድ ግለሰብ ብቻ ነበር። ግና ከጥናት ዝግጅቱ ጀምሮ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በአግባቡ ያልወከለው ሂደት፤ ጭራሽ ረቂቅ አዋጁ ላይ ግልፅ የሙስሊሙ መብት ጥሰቶች ተካተዋል። በዚህ በባለ 15 ገፅ በንድፍ ላይ ያለ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በቀጥታ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር ከሚጋጩ ነጥቦች መካከል፤ የሚከተሉት አንቀፆችና ንዑስ አንቀፆች ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር የሚያጋጩና ጥያቄ የሚያስነሱ ናቸው። 1) 13.8 "የተከለከሉ ቦታዎች ቅስቀሳ ማድረግ" ማለት የትኞቹ በታዎች ናቸው? 2) 13.9 other (ሌሎች) ማለት ምን ማለት ነው? 3) 15.1 መስጂድ ሲጠበን ከመስጅድ ውጪ መስገድ አንችልም ማለት ነው? መስጅድ በሌለበት መስገድ አይቻልም? ይህን መሠረት አድርገው ሰበብ ፈላጊዎች ከመስጅድ ውጭ መስገድን እንዲከለክሉ መንገድ ስለሚከፍት ይህን እንደማይመለከት በግልፅ ሌላ ንዑስ አንቀፅ ላይ መስፈር አለበት። 4) 15.4 ሁሉም ቦታ በሚባል ደረጃ ሶላትን ይከለክላል፡፡ 5) 17.4 "በቡድን አምልኮ" በሚል ሽፋን የጀመዓህ ሶላትን ለመከልከል ይውላል። 6) 17.7 ቅጣቶች ለመንግስት መ/ቤቶች ክፍት ሆነዋልና ሌላ ችግር እንዲፈጠር በር ይከፍታል፡፡ ምክንየተቱም የትኛውም መሥሪያ ቤት ተነስቶ የራሱን ቅጣት በጥላቻ ቢያስተላልፍ መብት አለው ማለትን ያሲዛል። 7) 19.1 "ከኃይማኖት ተፅዕኖ ነፃ መሆን" ማለት ምን ማለት ነው? እስከምን ደረጃ? 8) 19.2: የአንዳንድ ኢስላማዊ ትምህርት ቤቶችን አሠራር ለማፈን በር የሚከፍት ነገር አለው። 9) 19.5 በትምህርት ቤቶች የጀመዓህ ሶላት ተከልክሏል፡፡ 10) 19.6: "ማንነትን ለመለየት" በሚል ሽፋን  ኒቃብን ይከለክላል። በዚህ ቴክኖሎጂው ባደገበት ዘመን እንደ አሻራ ያሉ ቀላል ወጪ የሚጠይቁ ዘዴዎች እያሉ፣ በተለመደው አሠራርም በሴት የጥበቃ ሠራተኛ ማንነታቸውን መለየት እየተቻለ፣ በቢዝነስ ተቋማት ዘንድ ይህ ጥያቄ ሳይነሳ መኗኗር ሲቻል እያዬን… በዚህ ሽፋን ኒቃብን መከልከል ነውር ነው። 11) 22.2 በተለይም በሸሪዓው ውርስንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ለአንዳንድ ሙጅሪሞች በር ይከፍታል። 12) 24.1 የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ በተለይም በሙስሊሙ ዘንድ ሶደቃ የተለመደ ነውና! 13) 25.1: ይህም የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ 14) 25.3 ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ መጅሊስ በአዋጅ የተቋቋመ ራሱን የቻለ ተቋም ከሆነ በዚህ ደረጃ በሌላ የበላይ አካል control መደረግ የለበትም። 15) 25.4: ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ "በአዋጅ መቋቋም" የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ትርጉም አሳጥቶ እንደተለመደው ወደ ተራ NGO ከማውረድ አይተናነስም። 16) 26: "ከኃይማኖት ተፅዕኖ የተላቀቀ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚወስኑት የየትምርት ቤቱ ኃላፊዎች ቢሆኑ የተሻለ ይሆናል፡፡ አለበለዚያ የኢስላማዊ ት/ቤቶችን ነፃነት ያፍናል። …  ባለ 15 ገፁ ይህ ረቂቅ አዋጅ በሶፍቲ ኮፒ በዚህ ሊንክ ስለሚገኝ፤ አንብቡትና እናንተም የታዘባችኋቸውን ስጋቶችና ህፀፆች አስፍሯቸው። https://t.me/MuradTadesse/35726 ♠ ይህ አፈና ሳይጻፍ የተበደልነው አንሶን ጭራሽ ተልፎ ሊተገበርብን ጫፍ ሲደርስ በዝምታ ማሳለፍ የለብንምና ሁሉም ሰላም ወዳድና ለእምነቱ ተቆርቋሪ ከወዲሁ ጉዳዩ ሳይጸድቅ ይስተካከል ዘንድ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ግደታችን ነው። መልዕክቱን ለሌሎችም በማሰራጨት ህዝበ ሙስሊሙ እየመጣ ስላለው አዲስ አዋጅ ከወዲሁ በቂ መረጃና ግንዛቤ ኖሮት የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ እናድርግ። || t.me/MuradTadesse x.com/MuradTadesse fb.com/MuradTadesse
611Loading...
15
لازلنا ضعفاء، رغم كل هذه التكنولوجيا والعلم الا اننا لازلنا ضعفاء جداً. صدق الله القائل: ﴿وَمَآ أَنتُم بِمُعْجِزِينَ فِى ٱلْأَرْضِ ۖ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ﴾. 🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 وَمَا أَنتُم بِمُعْجِزِينَ فِي الْأَرْضِ ۖ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ እናንተም በምድር ውስጥ የምታቅቱ አይደላችሁም፡፡ ለእናንተም ከአላህ ሌላ ከዘመድም ከረዳትም ምንም የላችሁም፡፡ [ሱረቱ ሹራ : 31] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
541Loading...
16
Media files
671Loading...
17
ለሴቶች ብቻ ነው... ......ስሚኝማ እህቴ... ህይወትሽ አጭር ነው ብዙ እቅድ አታብዥ ፡ ከመጥፎ ራቂና መልካም ነገር ያዥ፡ ነብዩን ተከተይ አሏህን ታዘዥ፡ ከአሏህ ያልተሰጠን ደስታ አታሳጂ፡ መጥፎ ጥርጣሬን ፈፅሞ አትልመጂ፡ ክብርሽን ጠብቀሽ በማስተዋል ሒጂ፡ በተራ አሉባልታ ምታሳልፊያቸው፡ እነዚህ ውብ ቀኖች ዛሬ እምትኖሪያቸው፡ ልክ እንደ አንች ሁሉ ማህፀን አላቸው፡ ቀናቶች አርግዘው ያምጣሉ እንደ ሰው፡ የስራውን ውጤት ለሁሉም መልሰው፡ ከጊዜ በኋላ ይወልዳሉ መንታ፡ ያንዱ ስም ፀፀት ነው ያንዱ ስም ትዝታ!! «የዛሬ እርጉዝ ቀኖችሽ ነገ ላይ ምን እንድወልዱልሽ  ትፈልጊያለሽ?? መሪር ፀፀት ወይስ ውብ ትዝታ ምርጫው የአንች ነው።» ሴት ሁኝ እቅድ አውጭ በጥሩ ተራመጅ ከመጥፎ ነገር ራቂ ከመጥፎ ተጠንቀቂ ✍️ይልሻል ወንድምሽ ኑረዲን https://t.me/eslamisthebasetrilgen
751Loading...
18
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يَحُولُ بَيْنَ الْمَرْءِ وَقَلْبِهِ وَأَنَّهُ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ አላህም በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መኾኑን ወደርሱም የምትሰበሰቡ መኾናችሁን እወቁ፡፡ [ሱረቱል አንፋል : 24] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_284 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
750Loading...
19
ምን ነካህ ወንድሜ 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 አንድ ልታገባ አስር መጠየቅህ ከቶ ለምን ይሁን እንደዚህ መሆንህ ሁሉንም በጅምላ አገባለሁ ብለህ ውድ እህቶችህን ፊትና ላይ መጣልህ 🍡🍡🍡🍡🍡🍡🍡🍡🍡🍡 በጣም ትገርማለህ !!! ያችንም ይችንም ትላለህ ሞትኩልሽ እሽ በይኝ ብቻ ጥርጥር አይግባሽሽ አንችን ካላገኘሁ አልኖርም በጭራሽ እያልክ ለሴቶች ትቀላምዳለህ እንደማታገባ እያወቀ ልብህ ??🌹??🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 #ደግሞ የገረመኝ !!! ካንቺ ሌላ ሴቶች አላውቅም በጭራሽ ግድየለም እመኝኝ አንችን መች ስዋሽ በህይወት ዘመኔ አንችን አናገርኩሽ ስለዚህ እመኝኝ ጥርጣሬ አይግባሽ 🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥 እያለ ቀባጥሮ ብዙዎች ያጠምዳል ነገር ግን ሲታመነው ወደኋላ ይሸሻል ልክ እንደ ንብ አውራ በሴቶች ተከበህ ሴት አይቼ አላውቅም በጭራሽ ትላለህ ለሴት የማታዝን ምን አይነት ወንድ ነህ? እንደው በፈጠረህ እህት እንኳ የለህ 🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬 ተው አላህን ፍራ አትበድል ሴት ልጅን ስሜት አትከተል ቆም ብለህ አስተንትን በዱንያም በአኼራም ከሳሪ እንዳትሆን አንቺም እወቂበት ለዚህ ወሮ በላ ልብሽን አትስጪ ለአፋ ድለላ። @አብይ ወሬ https://t.me/eslamisthebasetrilgen
772Loading...
20
⚀, ምርጥ ነገር ልምከርህ: ➢የትም ብትሆን አላህን ፍራ! قال رسولِ اللَّهِ ﷺ، قَالَ: اتَّقِ اللَّهَ حَيْثُمَا كُنْتَ وأَتْبِعِ السَّيِّئَةَ الْحسنةَ تَمْحُهَا، وخَالقِ النَّاسَ بخُلُقٍ حَسَنٍ رواهُ التِّرْمذيُّ وقال: حديثٌ حسنٌ የአልላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የትም ቦታ ብትሆን አልላህን ፍራ 〰.ለወንጀልህ መልካም ነገር አስከትል ታብስልሀለችና ➰ከሰዎችም ጋር በመልካም ስነ ምግባር ኑር (ኢማሙ ቲርሚዚ) ሀዲሱ ሀሰን ◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️ ⚁, ወደ ስኬት የሚያደርሱ ጎዳናዎችን ላመላክትህ: ➢ቁርዓን እና ➢ሐዲስን አጥብቀህ ያዝ! 🔺🔻🔺🔻🔺🔻🔺🔻🔺🔻 ⚂, ምርጥ ነገሮች ይኑሩህ: ➢ዲን, ➢መልካም ስነ-ምግባር, ➢ከሰዎች የሚያብቃቃህ ገንዘብ 🔁🔁🔁🔁🔁🔁🔁🔁🔁🔁 ⚃, 4 ነገሮች ካሉህ ብዙ ነገር አለህ: ➢ኢማን, ➢የሰው ፍቅር, ➢እናት ሃገር, ➢መልካም የትዳር ጏደኛ ❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀ ⚄, 5 ነገሮች ከእጅህ ሳይወጡ ተጠቀምባቸው: ➢ወጣትነት, ➢ጤና, ➢ትርፍ ጊዜ, ➢ገንዘብ, ➢ህይወትህ ▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️ ⚅, ሀቆች እንዳሉብህ አትዘንጋ: ➢የአላህ(ሱብሀነሁ ወታዓላ) ➢የረሱል(ሰልለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ➢የራስህ, ➢የወላጅህ, ➢የሙስሊም ወንድምህ, ➢የሌሎች ፍጥረታት..." 👉እነዚህን ምርጥ ምክሮች ለወዳጅ ዘመድዎ በስጦታ መልክ ያበርክቱ!!! ➖〰➖〰➖〰➖~ይህን ያውቁ ኖሯል?~~~ ‌ ሶስቱ እጅግ በጣም አስፈሪ የጀሃነም ሸለቆዎች ‌ 1 وادي الغَّي......አል ገይ ሸለቆ 2 وادي الوَّيل......አል ዋይል ሸለቆ 3 وادي سقر......አል ሰቀር ሸለቆ! ‌ ዝርዝሩን እነሆ ፦ 1ኛ وادي الغَّي......አል ገይ ሸለቆ ............................................ ‌ [ فخلفهم من بعدهم خلف اضاعوا الصلوات واتبعوا الشهوات فسوف يلقون غياً ] ‌ ከነሱም ቦሃላ ሶላተን ያጓደሉ ፥ (የተዉ)፥ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች (ትውለዶች) ተተኩ ! (وادي الغَّي......አል ገይ ሸለቆ ) የገሃነም ሸለቆ በርግጥ ያገኛሉ ። {መርየም ፡59} ይህቺ የጀሃነም ሸለቆ (የተለያዩ ሰላቶችን አንድ ላይ ሰብስበው ለሚሰግዱ) እጅግ በጣም ምታቃጠል ከመሆኗ የተነሳ ጀሃነም እራሷ የአሏህን እርዳታ ትጠይቃለች ! የሰው ልጆች ይቋቋሙታልን ? ‌ 2ኛ وادي الوَّيل......አል ዋይል ሸለቆ ............................................ ‌ [ ويل للمصلين الذين هم عن صلاتهم ساهون ]. ‌ ወዮላቸው ፥ ለሰጋጆች ፣ ለነዝያ እነሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት (ሰጋጆች ) ። {አል-ማኡን ፡ 4-5} ይህቺ የጀሃነም ሸለቆ (ሶላትን ያለ አግባብ ለሚያዘገዩ ) የተዘጋጀች ስትሆን እጅግ በጣም ከሚያስፈሩ የጊንጥ እና የ እባብ አይነቶች የተሞላችዋ የጀሃነም ሸለቆ ነች ። አሏህ እራሱ ይጠብቀን ! ‌ 3ኛ وادي سقر......አል ሰቀር ሸለቆ .......................................... ‌ [ماسلككم في سقر ، قالوا لم نكن من المصلين ] و قال [وماأدراك ماسقر ، لاتبقي ولا تذر ] ‌ (ይሏቸዋልም)፦ በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ" ? (እነርሱም) ይላሉ ፦ ከሰጋጆች አልነበርንም ። ሰቀር ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ ? (ያገየችውን ሁሉ) አታስቀርም ፣ አትተውምም። { አል-ሙደሲር ፡27-28/42፡43} ይህቺ የጀሃነም ሸለቆ የተዘጋጀችው (ሶላትን ለማይሰግዱት) ሲሆን ሰላትማይደግዱት ገና ሲገቡባት (ከሙቀቷ የተነሳ) አጥንታቸውን ምታቀልጥ የሆነች ነች። ሶላት የማይሰግዱ ሰዎች የሚቀሰቀሱት (ለፍርድ ሚቀርቡት ) ከነ ፊርኦን ከነ ሃማን ጋር ሲሆን!የነብያችንን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሸፋእ እንዳያገኙ አሏህ (ሱ.ወ.) ያደርጋቸዋል ። አሏህ ይጠብቀን !! እባክህን !! በተቻለህ አቅም ይህቺን መልዕክት  ለምናውቀው አካል share እናድርግ   ኢኽላሳችን ካማረ በዚ ምክንያት ይመነዳን ይሆናል በሰላታቸው ላይ የተዘናጉ ንቃት ይሆናቸዋል እናም ሰላታቸውን ወቅቱን ጠብቀው በጀማዓ መስጂድ ሄደው እንዲሰግዱና ሰላታቸውም ላይ ጠንካራ እንዲሆኑ ሰበብ ትሆን ይሆናል !!ያአሏህ ያ አርሃም አልራሂሚን ከጀሃነም እና ከሸለቆዎችዋ አንተ ጠብቀን https://t.me/eslamisthebasetrilgen
661Loading...
21
Media files
550Loading...
22
የምሽት ስንቅ ለቀልቦ መልካም ምሽት አላህ ይጠብቃችሁ ይጠብቀን 🤲🤲 ☘☘❤️❤️☘☘ ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ shar የድር السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ☘☘☘☘☘❤️❤️❤️❤️❤️☘☘☘ https://t.me/eslamisthebasetrilgen
892Loading...
23
✔️  ሞትና ቀጣይ ሂደቶች   - ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣ - ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡ 1- ልብሴን ያወልቃሉ፣ 2- ያጥቡኛል፣ 3- ይከፍኑኛል፣ 4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣ 5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣ 6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣ 7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡ ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡ 8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል - ቁልፎቼ - መጽሐፎቼ - ጫማዎቼ - ልብሦቼ ….. በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ - በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣ - የዓለም  እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣ - የኢኮኖሚው  ቀውስም አልተፈጠረም፣ - በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ ይወጣል፣ - ንብረቴ የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣ - ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤ - ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል - ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤ ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! … በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ 1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ 2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣ 3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣ የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!! 1- መልክህ፣ 2- ሀብትህ፣ 4- ጤናህ፣ 5- ልጅህ፣ 6- ቪላህ፣ 7- ዝናህ፣ 8- ሚስትህ/ባልሽ ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡ እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ 1- በግዴታዎች፣ 2- በሱንና ነገሮች፣ 3- በድብቅ መፅውት፣ 4- መልካም ሥራ አብዛ፣ 5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣ ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡ መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡ አስቡ ያሄ መልእክት እናንተ ጋር ብቻ እንዲቆይ አትፍቀዱ ለሌሎችም አጋሩ ወይም ሼር አድርጉ በናንተ ምክንያት ሌላ ሰው አንብቦ ቢጠቀም እናንተ የሱ ምንዳ ተካፋይ ናችሁና። "ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ) https://t.me/eslamisthebasetrilgen
830Loading...
24
Media files
770Loading...
25
ኒቃቧን አወለቀች          (ልብ የሚነካ አስተማሪ ታሪክ) ⇛የሃይስኩል ተማሪ እያለች ነበር ኒቃብ የለበሠችው፡፡ ያውም በአንድ ቀን ዳዕዋ፡፡ ቀኑና ጊዜውን ለማስታወስ በትዝታ ወደኋላ ርቃ ሄደች፡፡ ዕለቱ ጁሙዓ ነበር፡፡ ከሶላት በኋላ ስለ ሒጃብ ዳዕዋ ያደረገው ኡስታዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ በተለይ ሴቶች ጆሮ እንዲሠጡት ይወተውታል ‹ሴት ልጅ ዐውራ ናት፣ ፈፅሞ ፊቷ መታየት የለባትም፣ ፊት ያልተሸፈነ ምን ሊሸፈን!፣ ኒቃብ ግዴታ ነው፤ ሴቶቻችን አላህን ፍሩ፣ ኒቃብ ልበሱ፤ ወላጆችም እንድታለብሱ …› እያለ ይመክራል፡፡ ⇛እዚያው እያለች ወሠነች፡፡ ወደ ቤቷ ገባች፡፡ ለወላጆቿ ነገረች፡፡ ኒቃብ መልበስ አለብኝ አለች፡፡ ከብዙ ክርክር በኋላ አሳመነቻቸው፡፡ ትምህርት ብትጨርስም ዉጤት አልመጣላትም፡፡ በግል ኮሌጅ አካውንቲንግ ተማረች፡፡ ዉጤቷ ጥሩ ነበር፡፡ ሥራ ፈለገች፡፡ ግና በኒቃቧ ምክንያት ተገፋች፡፡ ተቆጨች፣ ተናደደች …. ↳ዕድሜዋ ሲገፋ ይታወቃታል፡፡ ከአሥራ ቤት ወጥቶ ሀያ ገብቶ ወደ ሰላሳም ተጠግቷል፡፡ በዚህ በኩል የሥራ ማጣት፣ በወዲያ ከትዳር መዘግየት አስጨነቃት፡፡ ወንድ አትቀርብም፤ ወንዶችም ሊቀርቧት ይፈራሉ፡፡ የለበሠችው በልጅነት በመሆኑ ቀይ ትሁን ጥቁር፤ ቆንጆ ትሁን መልከ ጥፉ በአካል አያውቋትም፡፡ ብቻ በሩቅ ይሸሿታል፡፡ አንድም ኢማናቸውን ንቀው አሊያም ታጠብቃለች፣ አክራሪ ናት ብለው በመፍራት፡፡ ሁለት ፈተና በአንድ ጊዜ ወጥሮ ያዛት፡፡ የለፋችበት ትምህርት ቆጫት፤ የምትመኘው ትዳር ራቃት፡፡ ብዙ ጓደኞቿ ሥራ አገኙ፡፡ በዕድሜ ታናሾቿ ተራ በተራ አገቡ፡፡ ሒጃብን ለሥሙ ብቻ ጣል የሚያደርጉት ጥሩ ትዳር ያዙ፡፡ ⇨አላህ እሱን ለማይፈሩት ነው እንዴ የሚያደላው! አለች፡፡ ጥሩዎች ሲጎዱ መጥፎዎች ሲጠቀሙ አየች፡፡ ታዘበች፣ አሰበች፡፡ ኢማኗ እየደከመ መጣ፣ በራስ መተማመኗ ቀነሰ፣ ሌሎች የሚያወሩላት ወሬ ሸረሸራት፡፡ ከራሷ ጋር ታገለች፡፡ ኡስታዞችንና ዓሊሞችን ጠየቀች፡፡ ‹ልጅ ሆኜ ስለ ዲን ብዙም ሳላውቅ ነበር በችኮላ የለበስኩት፤ አሁን ማውለቅ እችላለሁ ?› አለች፡፡ አውልቂ የሚላት ጠፋ፡፡ ወደ ራሷ ተመለሰች፡፡ ከሁለት ያጣች እንደሆነች ታወቃት፡፡ ኒቃብ ከሥራም ከትዳርም እየከለከላት እንደሆነ ሸይጧን ሹክ አላት፡፡ ደስ እያላት ባለመልበሷ ምክንያት ምንም አጅር እንደማታገኝም ነገራት፡፡ ወረደች፣ ተጠራጠረች፣ ግራ ተጋባች …. በጥርጣሬ ዉስጥ ከምዋልል ለምን አላወልቀውም አለች፡፡ ከብዙ ትግል በኋላ ....... አወለቀች፡፡ የመጀመሪያ ሰሞን እርቃኗን የሆነች ያህል ተሰማት፡፡ ግና አንዴ አድርጌዋለሁ ብላ ራሷን አበረታታች፡፡ ያዩዋትና የሚያውቋት ሰዎች ደነገጡ፡፡ እሷ ናት ወይስ ሌላ? አሉ፡፡ እሷነቷን ሲያረጋግጡ ብዙ አወሩ፣ ተሳለቁ፡፡ በወሬያቸው ይበልጥ ባሰባት፣ እልህ ተጋባች፡፡ በዚያው ሄደች፡፡ ወደ ቀደመ ቦታዋ አልተመለሠችም፡፡ እሷ የድሮ ኒቃቧን ረሣች፡፡ እነርሱም አውርተው ሲደክሙ ዘነጓት፡፡ ☞ኒቃብ የለበስሽ እህቴ ሆይ! ① ስለተነገረሽ ሳይሆን አውቀሽና አምነሸበት በዝርዝር አጥንተሸና አገናዝበሽ ልበሺ፣ ②ኒቃብ ስትለብሺ ዒባዳ መሆኑን አስቢ፤ ኒያሽ ቀጥ ያለና የተስተካከለ ይሁን፣ ③- በአንድ ልብ ኑሪ፤ ሁለት ሀሳብ መሆን ላውልቅ አላውልቅ ምንዳ የለውም፤ ④ጊዜው ቢረዝምም፣ ቀኑ ቢቆይም አላህ መልካም ባሮቹን ጥሎ አይጥልም፡፡ ⑤ኒቃብ በማውለቅና ፎቶ በመለጠፍ የሚገኝ ትዳር የለም፤ ⑥በአላህ መመካትሽ እንደ ወፍ ይሁን፣ ባዶ ሆዷን ወጥታ ሆዷን ሞልታ ትገባለች፣ ⑦ በአላህ አምኛለሁ በይና ቀጥ በይ፣ ⑧- ጥሩ መጨረሻ አላህን ለሚፈሩና ለጥንቁቆች ነው፡፡ ⑨- አላህ በመልካም ነገር ላይ ፅናት ይስጠን፡፡ [منقول] =የተወሰደ https://t.me/eslamisthebasetrilgen
931Loading...
26
ወደየት እያመራን ይሆን⁉️ ================= የነ ሮበርትስ (Oral Roberts) የብልፅግና ወንጌል (The Prosperity Gospel (PG)) ወደየት ይወስደን ይሆን? || ✍ እነሆ በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ከተማ በሚገኘው ኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ በተማሪዎችና በመምህራን እንዲሁም ከጀርባ በመንግስት አካላት ድጋፍ ባለው መልኩ ባለ 32 ገፅ የፕሮቴስታንት እምነትን የሚሰብክ፣ እስልምናን የሚያንቋሽሽ፣ ውዱን ነቢይ ﷺ የሚሳደብ መርዘኛ ጽሑፍ ታትሞ በተማሪዎች ዘንድ እየተሰራጨ እንደሆነና ሙስሊም ተማሪዎች በግደታ ጭምር እምነታቸውን እንዲቀይሩ እስከማስገደድ ድረስ የዘለቀ ጽንፈኝነት መከሰቱን እየሰማን ነው። ይሄ ነገር በየቦታው ትንኮሳው በዛና ወደየት ልናመራ ይሆን? ምንድን ነው መፍትሄው? መጅሊስ በዚህ ጉዳይ ከምሁራን ጋር ቁጭ ብሎ በሩን ዘግቶ ተነጋግሮ አንድ ቆፍጠን ያለ አቋም መያዝ የለበትም ትላላችሁ? አላህ ከሴራቸው ይጠብቀን! በተለይ የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ በዚህ ጉዳይ ያለውን ነገር በአስቸኳይ አናግሮ ጉዳዩን ለህዝብ ማሳወቅ ይጠበቅበታል። || t.me/MuradTadesse
771Loading...
27
🚨warning🚨 ⛔ ቀዩ መስመር ሊታለፍ ነው⛔ ========================== ✍ ካስታወሳችሁ ከአንድ ወር በፊት ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችና ከተለያዩ የኃይማኖት ተወካዮች ጋር በተናጠል ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በተለይ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ከኛ ከእስልምና ኃይማኖት መሪዎቻችን ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች መንግሥት በቅርቡ ኃይማኖትን የተመለከተ ሕግ እንደሚያወጣ መናገራቸው ይታወሳል። በተለይ ከመጅሊስ መሪዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት መስጂዶች የሚያደርጉት የአዛን ጥሪ፣ እንዲሁም በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚከናወኑ ቅዳሴና አስተምህሮዎች ሌላውን ሰው ማወክ ስለሌለባቸው አስቡበት በማለት ስለሚወጣው ሕግ ይዘት ፍንጭ ሰጥተው ነበር።  መንግሥትና ሃይማኖት አንዱ በአንዳቸው ተግባርና እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ፣ መንግሥት ከኃይማኖት ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ በፍትሕ ሚኒስተር በኩል ተዘጋጅቶ አሁን ላይ በሰላም ሚኒስተር አስተባባሪነት ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት መደረግ ተጀምሯል። ይህ አዲሱ አዋጅ በርካታ ክልከላዎችን የያዘ ሲሆን፤ የሙስሊሞችን በጀማዓህ ሶላት መስገድ፣ የእህቶችን ጂልባብና ኒቃብ መልበስ፣ ጀለቢያ፥ አማኢምና ኮፍያ መልበስና የመሳሰሉትን ለማገድ በር የሚከፍት ህግ ተካቶበታል። የነርሱ እሳቤ የሌላውንም እምነት ተከታይ ኃይማኖታዊ አለባበሱንና በቡድን ማምለክን ስለምንከለክል፤ ሙስሊሞችንም «እናንተን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ነው የከለከልነው!» በሚል ሽፋን በመሞገት መከልከል አስበዋል። እዚህ ላይ ያልገባቸው ነገር የእያንዳንዱ እምነት ዶክትሪን የተለያዬ መሆኑን አለማወቅ ነው። በተለይም የእስልምና እምነት ህግጋት በየትኛውም ታዕምር ቢሆን በሰው ሠራሽ ህግ የሚሻሩ አለመሆናቸውን መረዳት ተስኗቸዋል። እነርሱ ሲጀመር ከፊሎቹ ራቁታቸውን መሄድ ነው የቀራቸው። እንኳን ተከልክለው በፈቃደኝነትም እየተገበሩት አይደለም። ታዲያ እነርሱ ከተዘናጉ እኛም አብረን መታፈን አለብን? በጭራሽ! አይደለም ኢትዮጵያ አዲስ የምታዘጋጀው ህግ፤ የዓለም መንግስታት ተባብረው አዋጅ ቢያወጡ፤ እስልምናችንን ከተቃረነ ማንም አይሰማቸውም።  የራሳቸውን እንደፈለጉ ያድርጉ። የኛን ግን እንዳያስቡት። በተጨማሪም 24 ሰዓት በካሴት ሳይቀር ተከፍቶ የሚለቀቅን የቤተ ክርስቲያን ቅዳሴና መዝሙር በቀን 5 ጊዜ 5 ደቂቃ ለማትሞላ አጋጣሚ የሚደረግን የአዛን ጥሪ አወዳድሮ አብሮ ጨፍልቆ ለመከልከል መጋጋጥ በየትም ተሰምቶ አይታወቅም። መንግስት አዛን ከከለከለን በተለይም በዐረቡና በሙስሊሙ ዓለም በኩል ያለውን ግንኙነት እንደሚያበላሽ ጠንቅቆ ይወቀው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሆነ መከራ እንዲለብስ ነው የሚሆነው። ቀድሞ ከሙስሊሙ ተወካዮችና ምሁራን በኩል የተሰጣቸውን ሃሳብ ወደ ጎን በተመው፤ ይህን ረቂቅ የሚያዘጋጁ አካላት።ሙስሊሙን የሚጨፈልቅ ህግ ማውጣታቸው አላማቸው ምን እንደሆነ ግራ ያጋባል። ባለማወቅ ነው እንዳይባል ቀድሞ መረጃ ተሰጥቷቸዋል፤ ግን ወደ ጎን ብለውት በራሳቸው አካሄድ መሄድን መርጠዋል። በርግጥ ፍትሕ ሚኒስተር ውስጥ እነማን እንደሆኑ እናውቃለን። ከአሁን በፊትም ኡማውን ከወያኔ ጀምሮ ሲጨቁኑ የነበሩ አካላት አሉበት። በአጭሩ እየመጣ ያለው ረቂቅ አዋጅ የእምነት ነፃነትን የሚጋፋና ኃይማኖቶች ከእምነታቸው አስተምህሮ ይልቅ በሃገሪቱ መንግስት ቁጥጥር እንዲዳኙ የሚያደርግ አደገኛ አዝማሚያ ያለው ነውና ከወዲሁ እንዲስተካከል ማድረግ አለብን። እኛ በደፈናው ባልተጻፈ ህግ ሲጨቁኑን የነበረውን ጉዳይ ጽፈው በግልፅ አስተካክለው ይመጣሉ ስንል፤ ጭራሽ በግልፅ ከልክለውና ሌላም ዱብእዳ አክለው መጡ። ማንም አይሰማቸውም! ህዝብ መረጃ ይኑረው። በደንብ መረጃዎችን አንሸራሽሩ። ረቂቅ አዋጁ ነገ ከኃይማኖት ተቋማት ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሏል። እዛም ላይ የኛ ተወካዮች በደንብ ጉዳዩን ያንሱት። አላህ የደነገገው ሸሪዓህ በተራ ሰዎች ህግ በፍፁም አይሻርም፤ አይሻሻልም። ሸሪዓን የሚቃረን ህግ ካለ ራሱ ይቀየር እንጂ ሸሪዓህ አይቀየርም። እኛ ሸሪዓን አልደነገግነውም፤ የደነገገው አላህ ነው። ያልደነገግነውን አናሻሽልም።
721Loading...
28
🌹 የጀነቷ እንስት ሑረል = ዐይን 🌹 ~ ክፍል አንድ ~ ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡ ~ ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡ ~በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡ አል-ዋቂዓህ - 22 = 24 ሑረል ዐይኗን ፈላጊ ሆይ! ================ በኢራቅ ሀገር ውስጥ አላህን አብዝቶ በመገዛቱ ይታወቃል። በእስልምና አስተምህሮት የታነፀ ፣ ኢማን ወደ ልቡ የገባ ድሃ ወጣት ነበር። የእርሱን አይነት ባህሪና ጥንካሬን ሁሉም ይመኛል። አንድ ቀን ከጓደኛው አቡ ሱለይማን ዳረኒ ጋር ወደ መካ ጉዞን ሊያደርጉ ወስነው የሚያደርሳቸውን ቅፍለት መምጣት ይጠባበቁ ይዘዋል። ቀፍላው ደረሰና ጉዞአቸውን ወደ መካ ጀመሩ። በጉዞአቸው መሃል ላይ የኢራቁ ወጣት የሚያሳያቸው ዒባዳ አስደንቋቸዋል። እነርሱ ሲበሉ እርሱ ይፆማል። ሲተኙ ለሊቱን ወደ ጌታው በመዞር ቂያመ ለይል ያነጋል። ሁኔታው ቢያስገርማቸውም ቀርቦ ምክንያቱን ለመጠየቅ ግን ማንም አልደፈረም። መካ ደርሰው ጉዳያቸውን ፈፅመው በመመለስ ላይ ሳሉ ጓደኛው አቡ ሱለይማን ከጓደኞቹ እርሱን ነጠል አድርጎ ‹ወንድሜ ሆይ! ለዚህ ሁሉ ዒባዳ ያነሳሳህን ነገር ንገረኝ? ለማወቅ ጓጉቻለሁ› በማለት ጠየቀው። እሱም እንዲህ ሲል መለሰ… ‹አንድ ቀን ተኝቼ በህልሜ ከወርቅና ብር የተገነቡ በሉልና በአልማዝ ያሸበረቁ ህንፃዎችን ተመለከትኩ። ከበሩ ደጃፍም ላይ ዓይኗን የነፃ ፀጉሯን የለቀቀች ውብ እንስት ቆማ አየሁ። የለበሰቺው ቀሚስ ከሀር የተሰራና አዝራሩም በወርቅ የተለበጠና ያማረ ልብስ ነበር። እሷን በተመስጦ በመመልከት ላይ ሳለሁ ደስ የሚል  ቀልብን የሚማርክ አንደበቷ «እኔን ለማግኘት ከፈለግክ በዒባዳህ ላይ ፅና። በአላህ እምላለሁ እኔ አንተን ለማግኘት በዱኣ እየለፋሁና እየለፋሁና እገኛለሁ። የእኔ መህር የለይል ሶላትና ፆም ነው› አለችኝ አስከተለና ወንድሜ ሆይ! በዚህ በምታየው ዒባዳ እሷን ለማግኘት በመጣጣር ላይ ነኝ። አቡ ሰለይማን ይህንን ታሪክ ሰምቶ ካበቃ በኋላ «ይህ ሁሉ ትግል ሑረል ዐይን ለማግኘት ከሆነ ከሑረል ዐይን በላይ የሆነው ጀነት ለማግኘት የሚፈልግ ምን ያህል ይለፋ ይሆን? በማለት ተናገረ። ውቧን ሑረል አይንን ለማግኘት የሚጓጉትን ሰዎች በተስፋ መርከብ ላይ ጭነን ያማረ ጉዞ ማድረግ ጀምረናል። ኑ ተከተሉን… መንገዳችንን እንቀጥል…! ይቀጥላል… ኢንሻ አላህ 💚 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
780Loading...
29
አህባብ አንድ መረጃ ላካፍላቹ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ነገ ማብራት ከ ጠዋቱ 12:00_ምሽቱ 12_00 ማብራት አይኖርም እና ቀድማቹ ተዘጋጁ
700Loading...
30
Media files
1010Loading...
31
በአንዲት እርምጃ ብቻ የ 1 አመት አጅር!!!...                  አንብቡትማ....     አላህ ለነቢ صلى الله عليه وسلم ኡመቶች ከሰጣቸው ፀጋዎች አንዱ ጁሙዓ ነው። ☀️ጁሙዓ የቀኖች ንጉስ ነው።አይሁዶች ቅዳሜን ነሳሮች እሁድን ልዩ ቀናት ብለው እንደሚያክብሩት   እኛ ሙስሊሞች በዒባዳ ወደ አላህ በመቃረብ እንድናከብረው ከአላህ የተሰጠን ስጦታ ነው።ጁሙዓ ውስጡ ላይ ብዙ ቱሩፎቶችን ይዟል። ☀️ጁሙዓ ቀን ላይ ሙሉ ሰውነቱን የታጠበ ንፅህናውን የጠበቀ፣በመጓጓዣ ሳይሆን በእግሩ እየተራመደ ወደ መስጂድ የሄደ፣ከኢማሙ ቅርብ ሆኖ(አወል ሶፍ ወይም ሁለተኛው ሶፍ ላይ)የተቀመጠ፣ኢማሙ ኹጥባ ሲያረግ ያላወራ ሀሳብ ሚሰርቅ እንቅስቃሴ ያላደረገ ከቤቱ ተነስቶ መስጂድ እስኪደርስ ድረስ በተራመደው በእያንዳንዱ እርምጃ የ 1 አመት ዒባዳ አጅርን ያሰጠዋል ብለዋል ረሱል صلى الله عليه وسلم ። 🔴የ1 አመት ዒባዳ አጅር ሲባል: ልክ 1 አመት ቀኑን ሲፆም ምሽቱን ሲሰግድ እንዲሁም ሌሎች ኸይር ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር ተቆጥሮ ሙሉ የ1 አመት አጅር ይሰጠዋል ማለት ነው።ታዳ ይሄ የፀጋዎች ፀጋ አደለምን???አስቡት እስኪ በአንድ እርምጃ ብቻ የአንድ አመት አጅር!!! እርምጃችን በበዛ ቁጠር ደሞ ምንዳውም ይበዛል! ይህን ለደነገገልን አላህ ምስጋና ይገባው! ሁሌ ማድረግ እንኳ ቢያቅተን ንያችንን አሳምረን ባገኘነው አጋጣሚ ይሄን አጅር ለማግኘት መስፈርቱን ማሟላት እና በጊዜ መስጂድ ለመገኘት መጣር ይጠበቅብናል።ምክንያቱም ምንዳው ቀላል አደለም እና።በአንድ እርምጃ የአንድ አመት አጅር!!!.... መቶ የተራመደ ሰው የ100 አመትን የፃም የሰላት የሌሎችም ኸይር ስራዎች አጅር ያገኛል ማለት ነው!!! እርምጃው የበዛ  በዛው ልክ አጅሩም ይበዛለታል። አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሰውን  ልዩ አጅር ማግኘት ሚችለው የጁሙዓ አደብን ከጠበቀ ነው። ➡️ሙሉ ሰውነትን መታጠብ (ከፀጉር እስከ እግር ጥፍር ውሀን በማዳረስ ከታጠበ) ➡️በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ ➡️ሲሄዱ በእግር መሄድ ➡️አወል ሶፍ መሆን ወይም ሁለተኛው ሶፍ ላይ መሆን ➡️ኹጥባ ላይ አለማውራት  አብረው የተቀመጡ ሰዎችን አለመለየት የሰውን ሀሳብ ሚሰርቅ ነገርን አለማድረግ እና መሰል የሆኑ አዳቦችን መጠበቅ ያስፈልጋል። ➡️ንፁህ ነጭ(ለወንዶች) ልብስ መልበስ፣ጥፍርን መቁረጥ፣መነሳት ያለባቸውን የብብት እና የብልት አካባቢ ፀጉሮችን ማንሳት፣ለወንዶች ሽቶ መቀባት፣መፋቂያ መጠቀም፣ሰለዋት ማውረድን ማብዛት፣ሱረቱል ከህፍን መቅራት፣መስጂድ በጊዜ መግባት፣ኢማሙ ወደ ሚንበር እስኪወጣ ባለው ክፍት ጊዜ 2 2 ረከዓ መስገድ ጁሙዓ ቀን ሚሰሩ ልዩ ዒባዳዎች ናቸው። ☀️ከዚህ በተጨማሪም ጁሙዓ በሁለት የጁሙዓ ጊዜያት መሀከል ያለን ትንንሽ ወንጀል ያስምራል ትልልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቅን።ትልልቅ ወንጀሎች በተውበት ነው ሚማሩት። አንድ ሰው የጁሙዓን አጅር ሚያገኘው መስጂድ በጊዜ ሄዶ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከመውጣቱ በፊት የደረሰ ከሆነ ነው።ኹጥባ ያመለጠው ሰው ጁሙዓ የለውም (የጁሙዓን አጅር አያገኝም) ☀️በጁሙዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ የሆነ ሰው በሁለቱ ጁሙዓዎች መሀከል የሚያበራለትን ብርሀን ያገኛል ተብሏል በሀዲስ።ይህ ማለት  በጁሙዓ ቀን ሱረቱል ከህፍ በመቅራት የሚገኘው ልዩ ብርሀን *ስራ ተቀባይነት ማግኘት ማለት ነው *በመልኣክት መከበብ ማለት ነው *ከሸይጣን  መጠበቅ ማለት ነው *ዱኒያ ላይ ጥሩና መጥፎን ለይቶ ማወቅ የሚችሉበትን የልብ ብርሀን አኼራህ ላይ ደግሞ ሲራጥን መሻገር የሚችሉበት የመንገድ ብርሀን መታደል ማለት ነው የተፈለገበት ተብሎ ተተርጉሟል። አላህ ይህንን የመሰለ በቀላሉ ብዙ ምንዳን ምናገኝበት የሆነ ነገር አመቸችቶልናል።አላህ ከሚጠቀሙበት ባሮቹ ያድርገን!!!
990Loading...
32
Media files
761Loading...
33
ሱረቱል ካህፍ የቻለ ይቅራ 📚📖 ያልቻለ ያዳምጥ ⏸🎧 •_🌺ፏ ያለ ጁማአ ይሁን ላችሁ 🌺_• ✅ የጁመዓ ቀን ሱናዎች ➖➖➖➖➖➖➖ ↩️ ‏سنن يوم الجمعة ➊ الغسل ➋ الطيب ➌ السواك ➍ لبس الجميل ➎ قراءة سورة الكهف ➏ التبكير لصلاة الجمعة ➐الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➊ መታጠብ ➋ ሽቶ መቀባት ➌ ሲዋክ መጠቀም ➍ ጥሩ ልብስ መልበስ ➎ ከህፍን መቅራት ➏ ለጁመዓ ሶላት መጣድ ➐ በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ⏮لقولهﷺ أكثروا من الصلاة عليَّ ليلة الجمعة وىوم الجمعة فإنَّ صلاتكم معروضة عليَّ ✅ እንዲሁም ብለዋል ﷺ የጁመዕ ሌሊትና  ቀኑ ለይ በኔ ሰለዋትን  አብዙ። ሶለዋታችሁ እኮ ለኔ ይቀርብልኛል። اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِكْ على نَبِيِّنَـــا مُحمَّد ┄┄┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉🌴
960Loading...
34
#የጁመዓ ቀን ሱናዎች እና አዳቦች            🗣ሱረቱ  ከህፍን  ማንበብ፣            🚿ሻወር  መውሰድ፣            🚰መፋቅያ  መጠቀም፣            🥋ጥሩ  ልብስ  መልበስ፣            🧴ሽቶ  መቀባት (ለወንድ)            🕗በጊዜ  መስጂድ  መሄድ፣            👉በሀቢቡና  (ሰዐወ)  ላይ  ሰለዋት                           ማውረድ፣                            🤲ዱዓ  ማብዛት። ✅ኹጥባን በዝምታ ማዳመጥ🙊 ውብ ጁምዓ 🤍    ❤️‍🩹https://t.me/eslamisthebasetrilgen
841Loading...
35
የምሽት ስንቅ❤️❤️❤️
160Loading...
36
Media files
990Loading...
37
ያጀምዓ ልብ አንጠልጣይ እንዲሁም አዝናኝና ቁምነገር አዘል ታሪክ በተከታተይ ክፍል ለመልቃቅ አስበናል እናም የናንተን ሀሳብ መቀበል አስፈላጊ ሆኖ ስለታየን እናንተ ምን ትላላችሁ ሀሳብ አስታየታችሁን ጉሩፑ ላይ አሳውቁን ። https://t.me/theihsan
931Loading...
38
#እቺን_ሴት_አትሁኝ . 1. በቴሌግራም ሀይ አለሽ 2. ሳትመልሺ ወደ profilu አቀናሽ 3. አለባበሱም ሆነ አቁዋሙ ያምራል 4. በድጋሜ ሀይ አለሽ 5. አሁን ግን በደስታ መለሽለት 6. መልክት መለዋወጥ ተጀመረ.. 7. በአካል ለመገናኘት ቀጠሮ ተያዘ 8. ጥሩ ልብስ ለበሰሽ ሽቶ ተቀብተሽ አምሮብሸ ሄድሽ 9. ውድ የሆነ መዝናኛ ቦታ ወሰደሽ 10. ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ጀመራቹ 11. እጆችሽን በፍቅር ያሻሽሻል በቀልዱ ያስቅሻል 12. አይኖችሽን በፍቅር አይን ተመልክቶ ፈገግታ ይመግብሻል 13. ብዙ ትውውቅ ያላቹ ያህል ተሰማሽ 14. ክፍል እንድትይዘ ጠየቀሽ ተስማማሽ 15. ምቾት እንዲሰማሽ አደረገ 16. በፍቅር በስሱ ከንፈርሽን መሳም ጀመረ 17. ትክክል አለመሆኑ ቢገባሽም ደስታ ተሰምቶሻል 18. በእርጋታ ወደ አልጋ ወሰደሽ 19. ለመቃወም አቅሙን አጣሽ 20. ሌለዉ ቢቀር መከላከያ ለመጠቀም ሀሳብ አቀረብሽ 21. በስሜት ጦፎ ሰለነበር ሊሰማሽ አልቻለም 22. ፍልሚያውን ወደድሽው እርካታም አገኘሽ 23. ከፍሪጅም ቀዝቃዛ ዉሀ አምጥቶ እራሱ አጠጣሽ 24. የሚያሳይሽ ክብር እጅጉን ማረከሽ 25. ራስሽን እድለኛ አርገሽ ቆጠርሽ 26. የምትፈልጊውን ወንድ እንዳገኘሽ ተሰማሽ 27. ልብሰሽን ለባበስሽ 28. ወደ ቤት አቅፎ ሸኘሽ 29. ጉንጮችሽን ስሞ የደሰታ ጊዜ ማሳለፉን ገለፀልሽ 30. ለጉዞሽም ገንዘብ በእጅሽ አስጨበጠሽ 31. ከልብሽ ፈገግ በማለት ነገ እንገናኝ ፍቅር አልሽው 32. እሱ ግን መልስ አልሰጠሽም 33. በደስታ ፈገግ እንዳልሽ ተጉዘሽ እቤት ደረሰሽ 34. በሰላም እቤት እንደደረሽ ሜሴጅ ላክሽለት 35. online ቢሆንም መልስ አልመለሰልሽም 36. ግራ ተጋብተሽ ድጋሜ ፃፍሺለት 37. አሁንም መልስ የለም 38. ከደቂቃዎች ብሀላ ስታይው ቴሌግራም ላይ ብሎክ ተደርገሻል 39. ብሎክ መደረግሽ ታወቀሽ 40. ቀናት ሳምንት ወራት አለፉ 41. ህመም ይሰማሽ ጀመር ድካም ክብደት መቀነስ.. 42. ወደ ሆስፒታል በመሄድ ምርመራ አደረግሽ 43. ከቆይታ ቡሀላ ነርሷ ውጤት ይዛ መጣች 44. HIV ፖዘቲቭ እና እርጉዝ እንተመኘሽ ተነገረሽ 45. እንዴት??? 46. ከእውነቱጋ ተጋፈጥሽ 47. ጭንቀት ነገሰብሽ በፍርሀት ተዋጥሽ 48. ተስፋ ቢስነት ስሜት አልባነት ተሰማሽ 49. ሞት ወደ አንቺ መቃረቡ ተሰማሽ 50. ሁኔታዎች ወደ ኃላ ተመልሰው ብታድሻቸው ተመኘሽ 51. ግን ምን ዋጋ አለው እረፍዶል 52. ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ፀሎት አደረስሽ😢😥😥🙏 • እቺን ሴት አትሁኝ • በስሜት አትመሪ • በሀቡት በንዋይ ሰውን አትመዝኚ • ሴት ልጅሽ እንድትሆንልሽ የምትመኚውን አይነት ሴት ሁኚ ለሴቶች የሚሆን ምክር ያንብቡት። አንብበው ሲጨርሱ ሼር ማረግ😁 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
842Loading...
39
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته بسم الله الرحمن الرحيم { زُیِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ ٱلشَّهَوَ ٰ⁠تِ مِنَ ٱلنِّسَاۤءِ وَٱلۡبَنِینَ وَٱلۡقَنَـٰطِیرِ ٱلۡمُقَنطَرَةِ مِنَ ٱلذَّهَبِ وَٱلۡفِضَّةِ وَٱلۡخَیۡلِ ٱلۡمُسَوَّمَةِ وَٱلۡأَنۡعَـٰمِ وَٱلۡحَرۡثِۗ ذَ ٰ⁠لِكَ مَتَـٰعُ ٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَاۖ وَٱللَّهُ عِندَهُۥ حُسۡنُ ٱلۡمَـَٔابِ } [Surah Âl-`Imrân: 14] ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆችም፣ ከወርቅና ከብር፣ ከተካመቹ ገንዘቦችም፣ ከተሰማሩ ፈረሶችም፣ ከግመል ከከብትና ከፍየልም፣ ከአዝመራም የኾኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመ፡፡ ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም መመለሻ (ገነት) አለ፡፡ የማለዳ ስንቅ ለቀልቦ❤️❤️ በታዳጊው ኣንደበት🥰🥰🥰 ያጀምዓ ቀጣይ በማን ቃሪዕ ይዘጋጅ??
730Loading...
🔴  ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ በቀንዱም ይነፋል፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ (በእርሱ) የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡ إِن كَانَتْ إِلَّا صَيْحَةً وَاحِدَةً فَإِذَا هُمْ جَمِيعٌ لَّدَيْنَا مُحْضَرُونَ (እርሷ) አንዲት ጩኸት እንጂ አይደለችም፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ فَالْيَوْمَ لَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْئًا وَلَا تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ «ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንም አትበደልም፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም» (ይባላሉ)፡፡፡፡ [ሱረቱ ያሲን  : 51-54] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
إظهار الكل...
00:49
Video unavailableShow in Telegram
ከ ጎንደር የተላከ መልእክት ሙስሊም የሆነ ሁሉ ሼር ያድርግ 😭😭😭 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
إظهار الكل...
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 أَفَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا بَيَاتًا وَهُمْ نَائِمُونَ የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የተኙ ኾነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን أَوَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا ضُحًى وَهُمْ يَلْعَبُونَ የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የሚጫወቱ ኾነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋድ ሊመጣባቸው አይፈሩምን أَفَأَمِنُوا مَكْرَ اللَّهِ ۚ فَلَا يَأْمَنُ مَكْرَ اللَّهِ إِلَّا الْقَوْمُ الْخَاسِرُونَ የአላህንም ማዘናጋት አይፈሩምን የአላህንም ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር የሚተማመን የለም፡፡ [ሱረቱ አዕራፍ  : 97-99] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት❤️ https://t.me/eslamisthebasetrilgen
إظهار الكل...
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 ۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡ [ሱረቱ ዙመር  : 53] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
إظهار الكل...
00:21
Video unavailableShow in Telegram
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 قَالَ بَلْ سَوَّلَتْ لَكُمْ أَنفُسُكُمْ أَمْرًا ۖ فَصَبْرٌ جَمِيلٌ ۖ عَسَى اللَّهُ أَن يَأْتِيَنِي بِهِمْ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْعَلِيمُ الْحَكِيمُ (ያዕቆብ) «አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡ (ሠራችሁትም)፡፡ መልካምም ትእግስት (ማድረግ) አለብኝ፡፡ እነርሱን (ሦስቱንም) የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፡፡ እነሆ እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና» አላቸው፡፡ وَتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَا أَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَابْيَضَّتْ عَيْنَاهُ مِنَ الْحُزْنِ فَهُوَ كَظِيمٌ ከእነሱም ዘወር አለናኣ«በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ፡፡ እርሱም በትካዜ የተመላ ነው፡፡ قَالُوا تَاللَّهِ تَفْتَأُ تَذْكُرُ يُوسُفَ حَتَّىٰ تَكُونَ حَرَضًا أَوْ تَكُونَ مِنَ الْهَالِكِينَ (እነርሱም) «በአላህ እንምላለን፡፡ ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም» አሉ፡፡ قَالَ إِنَّمَا أَشْكُو بَثِّي وَحُزْنِي إِلَى اللَّهِ وَأَعْلَمُ مِنَ اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ . . . . [ሱረቱ ዩሱፍ  : 83-87] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 https://t.me/eslamisthebasetrilgen
إظهار الكل...
...........ፍቅር ብዙ የፍቅር አይነት አለ ። የሁሉም ፍቅር ህመም አለው ። የቁርኣን ፍቅር ሲቀር እርሱ ግን ከሁሉም ይበልጣል ሠላምና እርካታን ይሰጣል ። ቁርኣን የልብ ብርኃን ነው ። አላህ ሆይ ልባችንን በቁርኣን ፍቅር ሙላልን 🤲 🍁 የዕለቱ መልእክቴ........
إظهار الكل...
...........ፍቅር ብዙ የፍቅር አይነት አለ ። የሁሉም ፍቅር ህመም አለው ። የቁርኣን ፍቅር ሲቀር እርሱ ግን ከሁሉም ይበልጣል ሠላምና እርካታን ይሰጣል ። ቁርኣን የልብ ብርኃን ነው ። አላህ ሆይ ልባችንን በቁርኣን ፍቅር ሙላልን 🤲 🍁 የዕለቱ መልእክቴ........ #የአኼራ ስኬት || نجاح آخرة ♡
إظهار الكل...
00:18
Video unavailableShow in Telegram