ar
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram
918
المشتركون
+124 ساعات
+27 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
ባለፉት 6 ወራት የክልሉን እምቅ የመልማት አቅም ያገናዘብ እቅድ ተዘጋጅቶ የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በሚያስችል አግባብ የተቀናጀ ርብርብ ተደርጓል !! ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ጥር 25/2018 ዓ.ም የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል። ምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን  ነው የሚያካሂደው። ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታው በዋናነት በክልሉ አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የክልሉን መንግስት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ለምክር ቤቱ አቅርበው ውይይቱ የሚቀጥል ይሆናል።

ጥር 24/2018 ዓ.ም በዞኑ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ መንግስት ማህበረሰቡ፣ ተወላጅ ባለሀብቶችና አጋሮችን በማስተባበር በየአመቱ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶች ደረጃ የማሻሻል ስራ እየተሰራ ነው፦ አቶ ላጫ ጋሩማ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ኢንተርናሽናል ኮል ኦርጋናይዜሽን የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የገሬኖ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመርቋል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በምረቃ ስነስርአቱ ተገኝተው እንዳሉት እንደ ሀገር በትምህርት ላይ ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን ፖሊሲ ተቀርጾ በዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ለዚህም አብዛኛው ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ባለመሆናቸው ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ ለማድረግ በባለፉት ሶስት አመታት በጠቅላይ ሚስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በማወጅ እንደ ሀገር በዘርፉ በርካታ ስራዎችን እየተከናወነ ይገኛል። በዞኑ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ መንግስት ማህበረሰቡ፣ ተወላጅ ባለሀብቶችና አጋሮችን በማስተባበር በየአመቱ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶች ደረጃ የማሻሻል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የወረዳው መንግስት ባለፉት 3 አመታት ማህበረሰቡና ተወላጅ ባለሀብቶችና አጋሮችን በማስተባበር ከ2 መቶ አስር ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ በ14 ትምህርት ቤቶች 20 ብሎኮችን በመገንባትን ሰማኒያ የመማሪያ ክፍሎችን በማመቻቸት የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል እየሰራው ያለው ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል። ተማሪዎች በተገቢው መጽሀፍት አግኝተው መማራቸው ለትምህርት ጥራት አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ ላጫ ለዚህም እያንዳንዱ ተማሪ የሁሉም የትምህርት ዓይነት መጽሀፍት እንዲያገኝ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ባለፉት 2 አመታት ከ1መቶ 50 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ተወላጅ ባለሀብቶች፣ ማህበረሰቡና የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት በማስተባበር የመጽኃፍት አቅርቦት ለማሻሻል የተሰራ መሆኑን አንስታውሰው፣በቀራይም ይበልጥ በማጠናከር ይሰራል ብለዋል። የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥና ጉራጊኛን ቋንቋ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አስተዳዳሪው በዚህም በዞኑ ከባለፉት 4 አመታት ጀምሮ ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ መደረጉን አስረድተዋል። ከዚህም ባለፈ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር ማስተማር ስራ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ለዚህም በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። በወረዳው በሁሉም ዘርፍ የተጀማመሩ የልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመቀናጀት እየሰሩት ያለው ስራ በቀጣይም አጠናክረው እንዲያስቀጥሉም አስገንዝበዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው በወረዳው በባለፉት 3 አመታት በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ማህበሰቡ፣ ተወላጅ ባለሀብቶችና አጋሮችን በማስተባበር ከ2መቶ 10 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ 20 ብሎክ፣ 80 የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት ተችሏል ብለዋል። ከዚህ ባሻገር ከ21 ሚልዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ግብአት የማሟላት ስራዎችን መሰራቱንም አስረድተዋል። በዛሬው ዕለት በኢንተርናሽናል ኮል ኦርጋናይዜሽን የበጎ አድራጎት ድርጅት፣በመንግስትና ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ተገንብቶ  የተመረቀው የማስፋፊያ ፕሮጀክት 2 ብሎክ፣ 9 የመማሪያ ክፍሎች፣ 3መቶ ዴስኮች፣ ከ2መቶ 50 በላይ ማጣቀሻ መጽሀፍትና 5 የመማሪያ ክፍሎችን ጥገና እንደሚገኝበትም አንስተዋል። ለትምህርት ተደራሽነት በተሰራው ልክ የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ስራ ይበልጥ ለማጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚገባም ገልጸዋል። የኢንተርናሽናል ኮል ኦርጎናይዜሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሪስ በሽር ድርጅቱ፣መንግስትና ማህበረሰቡ በመተባበር ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የትምህርት ቤቱ ደረጃ ማሻሻል መቻሉን አንስተው ለዚህ ግንባታ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት አመስግነዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ከዚህ ቀደም ትምህርት ቤቱ ለመማር ማስተማር ምቹ ባለመሆኑ በተማሪዎች ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሮ እንደነበር አስታውሰዋል። ለትምህርት ቤቱ ግንባታ በገንዘብና በጉልበታቸው ድጋፍ ማድረጋቸውን አንስተው ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ በመመረቁ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። በቀጣይ ተማሪዎች ደረጃውን በጠበቀ ትምህርት ቤት መማራቸው የተማሪዎች የመማር ፍላጎት ከመጨመር ባለፈ ውጤት በማሻሻል ረገድ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ጥር 24/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ኢንተርናሽናል ኮል ኦርጋናይዜሽን የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የገሬኖ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት የምረቃ ስነ-ስርአት እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በዞኑ በየዓመቱ የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥና የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል መንግስት ማህበረሰቡ፣ ተወላጅ ባለሀብቶችና አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ የትምህርት መሰረተ ልማት ለማሻሻል በርካታ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል። በዚህም የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተገልጿል። በወረዳው በዛሬው እለት እየተመረቀ ያለው የማስፋፊያ ፕሮጀክት 2 ብሎክ፣ 9 የመማሪያ ክፍሎች፣ 3መቶ ዴስኮች፣ ከ2መቶ 50 በላይ ማጣቀሻ መጽሀፍትና 5 የመማሪያ ክፍሎችን ጥገና ይገኝበታል። ለትምህርት ተደራሽነት በተሰራው ልክ የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ስራ ይበልጥ ለማጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል። በምረቃ ፕሮግራሙም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ኸይሩ መሀመድ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል፣ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ጨምሮ የዞንና የወረዳው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የኢንተርናሽናል ኮል ኦርጎናይዜሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሪስ በሽር፣ የአካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶችና  ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ እንደሚያስቀጣ ያውቃሉ? *** ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ ያስቀጣል። ታዲያ ለገበያ ምን ይዘን እንውጣ? ከቤትዎ ሲወጡ የጨርቅ ከረጢት ወይም ዘላቂ የሆኑ የሸመታ ከረጢቶችን መያዝዎን ያረጋግጡ። ይህ አዲስ መመሪያ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ትልቅ እርምጃ ነው። የፕላስቲክ ከረጢቶች በአካባቢ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት የሚደነቅ ቢሆንም፣ የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ፍላጎት ለማሟላት በቂ ተኪ ምርቶች ተዘጋጅተው ይሆን? በዚህ ጉዳይ ምላሽ የሰጡት በፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የከተማ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ክትትል ዴስክ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን አለሙ እንደገለጹት ፤ መንግሥት እና የግል ባለሀብቶች ፕላስቲክ ከረጢትን ተኪ ምርቶች ላይ እየሰሩ ስለመሆናቸው ነው ከኢቢሲ ዶት ስትሪም ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሱት ። ያቀረቧቸውን ነጥቦች መሠረት በማድረግ፣ ስለ ተኪ ምርቶቹ እና ስለ ሕጉ አፈጻጸም ዝርዝር መረጃዎችን በሚከተለው መልኩ ማጠቃለል ይቻላል፦ ✅ ከጥጥ ጨርቅ የሚሰሩ ከረጢቶች፦ እነዚህ ከረጢቶች ታጥበው ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ በመሆናቸው ለዘላቂነት ተመራጭ ናቸው። ✅ ከካኪ (ወረቀት) የሚሰሩ ምርቶች፦ በተለይ ለደረቅ ዕቃዎች እና ለምግብ ነክ ግብይቶች ውጤታማ ናቸው። ✅ የማምረት አቅም፦ በአሁኑ ወቅት ሶስት ትላልቅ ተቋማት በቀን እስከ 55,000 የሚደርሱ የጨርቅ ከረጢቶችን እያመረቱ ሲሆን፣ በርካታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም በስፋት እየተሳተፉ ይገኛሉ። የመንግሥት ድጋፍ እና ማበረታቻ ሕጉን ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት የሚከተሉትን ማበረታቻዎች እያቀረበ ይገኛል፦ ✅ከቀረጥ ነፃ መብት፦ ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ ማሽኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከቀረጥ ነፃ መብት ተሰጥቷል። የፋይናንስ ድጋፍ፦ አምራቾች ካፒታል እንዲያገኙ ከባንኮች እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር የውይይት መድረኮች ተመቻችተዋል። ጥሬ ዕቃ፦ ምንም እንኳን በጥሬ ዕቃ ላይ የተወሰነ ቀረጥ ቢኖርም፣ ምርቱን ለማሳደግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። ✅ሊታረሙ የሚገባቸው የተሳሳቱ አመለካከቶች ባለሙያው እንደገለጹት፣ "ያልተሸመነ ጨርቅ" (Non-woven fabric) ከፕላስቲክ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው እና ለረጅም ጊዜ ስለማያገለግል፣ አምራቾችም ሆኑ ሸማቾች ከዚህ ምርት ይልቅ ዘላቂ የሆኑ የጨርቅ ከረጢቶችን እንዲጠቀሙ ይመከራል። ✅የሸማቹ ሚና ሕጉ ውጤታማ እንዲሆን የሸማቹ ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ✅ከቤት ይዞ መውጣት፦ እያንዳንዱ ሸማች ለገበያ ሲወጣ የራሱን ዘላቂ ከረጢት (Reusable bag) የመያዝ ልምድ ማዳበር ይኖርበታል። ✅ግንዛቤ፦ ፕላስቲክ የሚያስከትለውን የጤና እና የአካባቢ ጉዳት በመገንዘብ ሕጉን ማክበር። #EBC

ጥር 21/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በ2018 ዓ.ም ከ10 ሺህ 446 ሄክታር በላይ መሬት በተፋሰስ እንደሚለማ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለጸው በወረዳው የ2018 ዓ.ም የተቀናጀ ግብርና ልማት ወረዳ ዓቀፍ ንቅናቄና ማብሰሪያ መድረክ ዛሬ በተካሄደበት ወቅት ነው። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ሚፍታ ሁሴን በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የተቀናጀ የግብርና ሥራዎችን በማጠናከር የማህብረሰባችን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ ሁሉም በየዘርፉ ትኩረት በማድረግ ሊሰራ እንደሚገባ  ተናግረዋል። ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ባለሙያዎች በግብርናው ዘርፍ የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ የሙያ ኃላፊነታቸውን በተገቢው በመወጣት የተሠሩ ተግባራትን በተገቢው ማሳየት አለባቸው ብለዋል።  የተሻሻሉ ዝርያዎች በመጠቀም የማድለብና ማሞከት፣ የዶሮ እርባታ፣የእንሰትና ቡና ልማት  መታወቂያችን (ብራንዳችን) የሆነው የማር ምርት በሰፊው መስራት የፍራፍሬ ዘርፍ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ሀብቶቻችን ናቸው ሲሉ ዋና አስተዳደሪው አመላክተዋል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ የባለፈው በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የዘንድሮ ተፋሰስ እቅድ ባቀረቡበት ወቅት የበልግ ወቅት የተቀናጀ ግብርና ልማት ስራዎች፣ ተፋሰስ ተግባራትን በጥራት በመፈጸም ዘላቂ ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ፣ በእንስሳት መስክ የንብ ሀብት፣ የወተትና የስጋ ምርት ማሳደግ፣ የቡና ምርታማነትን መጨመር፣ በበልግ ልማት ላይ ውጤታማ ስራ መስራት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተደርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል። በ2018 ዓ.ም ተፋሰስ ቁጥራቸው ከ54 ሺህ 414 በላይ አ/አደሮች የሚሳተፉ ሲሆን በ32 ን/ተፋሰስ ላይ 10 ሺህ 446 ሄክታር መሬት ይለማል። የዘንድሮውን የተፋሰስ ልማት ስራ ከዚህ ቀደም የነበረውን ልምድና ክህሎት በመጠቀም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው የተፈለገውን ውጤት ለማምጣት ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አሳውቀዋል ። በተያያዘም በመድረኩ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሲራጅ ደንበል በ CALM-LA ፕሮጀክት ድጋፍ በአዲሱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 32/2016 እና በመሬት መረጃን ወቅታዊ በማድረግ ላይ ትኩረት ያደረገ ግንዛቤ መፍጠሪያ ሠነድ አቅርበዋል። በቀረበው ስነድ መነሻ በማድረግ ተሳታፊዎች የተሻሻለ የእንስሳት ዝርያ አቅርቦት በቂ አለመሆን፣በአዋጁ መሰረት ባህር ዛፍን በማንሳት መሬትን ለምርት ከመጠቀም አንፃር ውስንነት መኖሩ፣በየዘርፉ የሰለጠነ ባለሙያ ድጋፍ ክትትል መደረግ እንደሚያፈልግ ፣የተፋሰስ ስራ ከተጀመረ ወዲህ በምርታቸው ላይ ለውጥ ማግኘታቸው ፣የደረቁ ምንጮች ዳግም መመለሳቸው ፣በቀበሌ ደረጃ የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱ ያነሱት ተሳታፊዎቹ በጥራትና በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ ለተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን አ/አደሩ በእርሻና ምንጮች አከባቢ ያሉ ዛፎች በማስወገድ ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ አስታውሰው የሌማት ቱሩፋት ስራዎችን በማጠናከር መስራትእንደሚገባ አሳስበዋል። በሌላም በኩል በሁሉም የወረዳው ቀበሌዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች የብሔራዊ ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ማጠናቀቅ እንዲችሉ ከማድረግና የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት መረጃ ከፋይዳ ጋር በማስተሳሰር ረገድ ለአርሶ አደሮች በቂ ግንዛቤ በመፍጠር መረጃዎችን በፋይዳ መታወቂያ ለማስተሳሰር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ሚፍታ ሁሴን በመድረኩ ማጠቃለያ ወቅት እንደገለጽት ከወቅቱ ጋር ለመሄድ እና እቅዶቻችን ለማሳካት አደረጃጀቶችን በማጠናከር ተግባሮቻችን ማከናወን እንደሚገባ ጠቅሰው የአፈር ጥበቃ፣የማይታረስ መሬት ዜሮ ማድረግ ፣የእንሰት ስራ፤በተቀናጀ መልኩ መረባረብ እንደሚገባ ገልፀው ግብርና የአርሶ አደሩ እና የሀገር ኢኮኖሚ ዋልታ በመሆኑ አርሶ አደሩን በተገቢው መደገፍ መቻል እንዳለበት አሳስበው የግብርና ባለሙያዎች አቅማችሁ እና እውቀታችሁ በመጠቀም የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ብለዋል። በመጨረሻም በ2017 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ስራ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቀበሌዎች የእውቅና ሰርተፍኬት በማበርከት መድረኩ ተጠናቋል።

ጥር 21/2018 ዓ.ም የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ተገለፀ። በመድረኩም ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ያቀረቡት የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ኤሊያስ ለማ እንደተናገሩት የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትብብርና በቅንጅት እንደሚሰራ ገልፀዋል። ‎ ‎አቶ ኤሊያስ አክለውም የምክር ቤቱ መቋቋም ዋነኛ ዓላማ ሲገልፁ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የተለያየ ስራ በሚሰሩበት ጊዜ የሚገጥማቸው ተግዳሮቶች በመቅረፍ በቀጣይነት የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል ነው ብለዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ እንደተናገሩት የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ትብብርና ቅንጅታቸው ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማምጣት የሲቭል ማህበራትና ድርጅቶች ወሳኝ መሆናቸውን ጠቅሰ በቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮዎች በብቃት ለመፈፀም እገዛቸው አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘሀራ ግራኝ በበኩላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የራሳቸው ዓላማና ግብ ስላላቸው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ስራቸው በአግባቡ መስራት እንዳለባቸው አንስተዋል። ‎በመሆኑም እነዚህ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት ዛሬ በተቋቋመው ምክር ቤት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ሳይደረግባቸው በራሳቸው ዕቅድና ዓለማ መሰረት አድርገው ከመንግስት ጋር በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። ‎ ‎የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት የጋራ ምክር ቤቱ መቋቋሙ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ በመግለፅ በቀጣይ የሚገጥሙ ተግዳሮቶች የሚቀርፍ መሆኑ አንስተዋል። ‎በመጨረሻም ለተቋቋመው ምክር ቤት 7(ሰባት) ስራ አስፈፃሚ አካላት በመምረጥ ተጠናቋል። ‎

በምርጫ ብቻ፡ የሉዓላዊነታችንና የሰላማችን መተማመኛ! በኢትዮጵያችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለመክፈትና የዴሞክራሲ ሥርዓትን በፅኑ መሰረት ላይ ለመትከል "በምርጫ ብቻ" የሚለው መርህ ብቸኛው የሰላማዊ ስልጣን ሽግግር መንገድ ነው። ይህ መርህ የዜጎችን ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥና የሀገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሕዝብ ድምፅ ለመወሰን የሚያስችል ታላቅ የድል ጎዳና ነው። ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ምድር ስልጣን በጠመንጃ አፈሙዝ፣ በኃይል ወይም በሁከት የሚያዝበት ዘመን ላይመለስ አክትሟል።ይልቁንም፣ ማንኛውም የፖለቲካ ኃይል ወደ ስልጣን መውጣት የሚችለው በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ የሃሳብ ፍልሚያ እና በነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በሚገኝ የሕዝብ አመኔታ ብቻ መሆን ይኖርበታል። ይህ ሲሆን ነው የሀገር ግንባታ ጉዟችን ትርጉም የሚኖረው፤ ይህ ሲሆን ነው የሕግ የበላይነት የሚከበረው። ለምን "በምርጫ ብቻ"? የሕዝብ ሉዓላዊነት፡ ስልጣን የሕዝብ ነው! ምርጫ ዜጎች የሚመራቸውን አካል በነፃነት በመሰየም የሀገሪቱ የበላይ ባለቤት መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት መድረክ ነው። ለዘላቂ ሰላም፡ ችግሮችን በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ እንዲሁም በውይይት ሲፈታ፣ የግጭትና የጦርነት ምንጮች ይደርቃሉ። የሃሳብ ብዝሃነት የግጭት ሳይሆን የውበት ምንጭ ይሆናል። ለሀገራዊ ብልፅግና፡ ፖለቲካዊ መረጋጋት ሲሰፍን የኢኮኖሚ እድገት ይፋጠናል፤ ኢንቨስተሮች እና ሀገር አልሚዎች በልበ ሙሉነት ይሰራሉ፤ ወጣቶችም የተሻለ ነገን ተስፋ ያደርጋሉ። ውድ ኢትዮጵያውያን! ዴሞክራሲን ለመትከልና ለማፅናት በሚደረገው በዚህ ታሪካዊ ጥረት ውስጥ የሕዝብ ሚና ከማንም በላይ የላቀ ነው። እያንዳንዱ ድምፅ የሀገርን ሕልውና የመወሰን አቅም አለው። ስለሆነም፣ ከፊታችን ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሁላችንም ለነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ራሳችንን በማዘጋጀት፣ የፖለቲካ ባህላችን እንዲሰለጥን፣ በሰለጠነ መንገድ ተሳትፎ በማድረግ የኢትዮጵያን ብሩህ ተስፋ እውን እናድርግ። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረትና በዴሞክራሲያዊ አንድነት ለዘላለም ትኑር! #EBC