ar
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram
918
المشتركون
+124 ساعات
+27 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
ጥር 21/2018 ዓ.ም "የተቀናጀ የግብርና ልማት ጥረት ለቤተሰብ ብልጽግና ስኬት "በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት 2018 ዓ.ም የበልግ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በንቅናቄ መድረኩ ላይ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን፣የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳን ጨምሮ የወረዳ አመራሮች የቀበሌ ሊቃነመናብርት ፣ስራ አስኪያጆች ፣የሴቶች ተወካዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም በለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ። ዝርዝር መረጃ ተከታትለን እናደርሳለን

ጥር 20/2018 ዓ.ም ጉራጌ ብልፅግናዊ እሳቤና እሴት ያለው፣ፈተናዎችን እንደ እድል እየተጠቀመና እየፀና ጀምሮ በመጨረስ ልምድና ስነልቦና የታነፀ ህዝብ ነው፦ አቶ ላጫ ጋሩማ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የጉራጌ ዞን አስተዳደር እና የኦሮሚያ ብርድካስቲንግ ኔትወርክ የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ ግንባታ ለማከናወን የውል ስምምነት ተፈራርመዋል!! የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በስምምነቱ ወቅት እንደገለፁት ከአምስት አመታት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ጉራጊኛን የሚዲያ  ቋንቋ በማድረግ በዞኑ የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ካለምንም ክፍያ በሳምንት ለሶስት ሰዓታት በሚዲያው በማስተላለፉ ኦቢኤን ትልቅ ምስጋና ያስፈልገዋል፡፡ ኦቢኤን  ከሀገሪቱ አልፎ በአፍሪካ ደረጃ ከሚገኙ ሚዲያዎች ግንባር ቀደም ተቋም ለመሆን እየሰራቸው የሚገኙ ተግባራት አበረታችና ሌሎችም ሊማሩባቸው የሚገቡ ናቸው ያሉት አቶ ላጫ ድርጅቱ የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን በማቋቋም ሂደት ውስጥ አሻራው እንዲያሳርፍ መወሰናችን ተገቢነት ያላው መሆኑንም አብራርተዋል። የጉራጌ ማህበራሰብ በተቋሙ ያለው እምነት ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ ላጫ ከዚህም በመነሳት የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ ግንባታ እንዲገነባ መወሰኑን አውስተዋል፡፡ ከድርጅቱ ጋር በጋራ መስራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚያስገኝ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ ከመገንባት ባለፈ የህዝብ ለህዝብ ትስስር በማጠናከር፣ለባለሙያዎች ስልጠና  በመስጠት፣ የጥገና ስራዎች ለማከናወንና ሌሎችም በሂደቱ የሚያስፈልጉ ተግባራት ጭምር እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡ ጉራጌ ገና በጥልቀት ሊጠኑና ሊፈተሹ የሚችሉ ቱባ ባህሎችና ፀጋዎች ያሉት ህዝብ ነው ያሉት ክቡር አስተዳዳሪው የዞኑ ማህበረሰብ ቋንቋውን፣ ባህሉን፣ ታሪኩንና ሌሎች የልማት ስራዎች የሚያስተላልፍበት የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለመኖሩ ለህዝቡም ሆነ ለሌሎች ተደራሽ ማድረግ እንዳልተቻለ አብራርተዋል፡፡ ማህበረሰቡ ችግሩን በመደጋገፍ እንዲፈታ እቁብ፣ ሀዘን ሲገጥመው እድር፣ ከሀገሪቱ ባለፈ እንደ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነ የመንገድ ልማት ስራ ድርጅት በማቋቋም ፈር-ቀዳጅ ተግባራት ያከናወነ ማህበረሰብ እንደሆነ አስረድተው የቴሌቭዥን ጥያቄም ለረዥም ጊዜ ሲጠይቀው የነበረ መሆኑን አውስተዋል። ስለሆነም ይህንን ጥያቄ በመመለስ ጉራጊኛ ወደ አንድ ለማምጣት፣ ህብረተሰቡ በልማት ለማነቃቃት፣ ብዙ ያልተነገሩ፣ ጎልተው ያልወጡና ያልተዋወቁ ባህሎች በማልማት ማስተዋወቅ እንዲቻል የጉራጌ ቴሌቪዥን ሚናው የላቀ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ህዝቡን የሚመጥን የሚዲያ ተቋም ለማቋቋም ከኦቢኤን ጋር በመሆን የተጀመረው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላ ብለዋል፡፡ የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ጋዜጠኛ ፍሰሃ በላይነህ በበኩላቸው የጉራጌ ህዝብ እጅግ በጣም አኩሪ ታሪክና የስራ ባህል ያለው ነው!! ጉራጌ ብልፅግናዊ እሳቤን የያዘና በመንደር ያልታጠረ በመላ ሀገሪቱ በመንቀሳቀስ እየሰራ ያለና ያለበትንም ከተማ የሚያለማ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ኦቢኤን የህዝቡ ትልቅነትና ስፋትን በመገንዘብ እንደዚሁም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በስፋት በመኖሩ በነፃ ሰፊ የአየር ሰዓት በመስጠት በሳምንት ሶስት ቀናት በጉራጊኛ ቋንቋ እያስተላለፋ መሆኑን አብራርተዋል። ተቋማቸው ኦቢኤን በሀገሪቱ የኢዚአን ጨምሮ የተለያዩ ስቱዲዮችን መገንባቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ስቱዲዮን ደግሞ ከሌሎች ያካበተውን ልምድ በመጣቀምና ዘመኑ የደረሰበትን ደረጃ ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚገነባ ገልፀዋል!! መረጃው የጉራጌ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

ጥር 19/2018 ዓ.ም የጉራጌ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ፣ የቤት አሰራርና የመንደር አመሰራረት ጥበብ ያለው፣ እቁብ፣ እድር እና ሌሎች ባህላዊ እሴቶች የመሰረተ ጥንታዊና ኩሩ ህዝብ ነው፦አቶ ላጫ ጋሩማ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ዞናዊ የአንትሮሽት የእናቶች የምስጋና ቀን)  በልዩልዩ ክዋኔዎች በአበሽጌ ወረዳ አምበልታ ቀበሌ ተከበረ። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ የጉራጌ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ፣ የቤት አሰራርና የመንደር አመሰራረት ጥበብ ያለው፣ እቁብ፣ እድር እና ሌሎች ባህላዊ እሴቶች የመሰረተ ጥንታዊና ኩሩ ህዝብ ነው፡፡ እነዚህ ባህላዊ እሴቶች በጊዜ ሂደት  አንዳንዶቹ እየተዳከሙ፣ ጥቂቶች እየጠፉ፣ ውስኖች ደግሞ እየተበረዙ የሚገኙ በመሆናቸው ዳግም እንዲያንሰራሩ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ የአንድ ማህበረሰብ ባህል መገለጫው ቋንቋው እንደሆነ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው   የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበት የነበረው የጉራጊኛ ቋንቋ ለመታደግ መጠነ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው አስረድተዋል። ከማህበራዊ አገልግሎት ወጥተው በአማርኛ ቃላት የተተኩ በርካታ ቃላት መኖራቸው እና በአፍ መፍቻነት የሚናገሩ  ህፃናት ቁጥር መቀነሱ  በጉራጊኛ ቋንቋ እድገት ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደራቸውን አውስተዋል። ይህንን የማንነት መገለጫ የሆነው ጉራጊኛን ለመታደግ የዞኑ ምክርቤት ቋንቋው የትምህርት፣ የስራ እና የሚዲያ እንዲሆን ካፀደቀ በኋላ  አበረታች ተግባራት ማከናወን ተችሏል። በዚህም በዞኑ ከ96 ሺህ በላይ ህፃናት በአፍ መፍቻነት የሚማሩ ሲሆን በኦቢኤን ሆርን ኦፍ አፍሪካ፣ በወልቂጤ ኤፍ ኤም 89.2 ሬዲየና በዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ አስረድተዋል፡፡. ይህንን ይበልጥ ለማጠናከር የጉራጌ ቴሌቪዥን ለማቋቋም በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ነው፡ የገለፁት፡ እንደ አቶ ላጫ ገለፃ እናቶቻችንና አባቶቻችን ጠብቀው ካቆዩዋቸው ባህላዊ እሴቶች  አንዱ አንትሮሽት ሲሆን ሳይበረዝ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው። የጉራጌ ማህበረሰብ ከሰለጠነው አለም አስቀድሞ የእናት ውለታ በመረዳት ለማክበር እና ለማመስገን ቀን ተቆጥሮ በአመት አንድ ጊዜ እናትን ማክበር የጀመረ ህዝብ ነው። በዓሉ የሚከበረው እናቶች እንዲደሰቱ፣ እንዲያርፉና ልጆቻቸው ስጦታ በማዘጋጀት እንዲያበረክቱላቸው ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል። ይህን ድንቅ እሴት ይበልጥ እንዲያድግ እና ልጆች እናቶቻቸውን በሚገባ መንከባከብ እንዲችሉ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድናስር በ14ኛው ክ/ዘመን የተጀመረው የአንትሮሽት በዓል የማህበረሰቡ ቀደምት አባቶች የስልጣኔ ደረጃ ከፍታ የሚያሳይ እንደሆነ ገልፀዋል። የሰለጠነው አለም ስለ ሴቶች  ማርች 8 ብሎ ማክበር የጀመረው በ19ኛው መቶ ክፍለዘመን መሆኑ የገለፁት ኃላፊዋ የጉራጌ ማህበረሰብ ግን ቀድሞ የሰለጠነ፣ የሴቶች እኩልነትና ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል። በዓሉ ለብዙ አመታት በማህበረሰቡ ዘንድ የኖረ የመከባበር፣ የመተባበር፣ የሰላምና ሌሎች መሰል እሴቶች እንዲጎለብቱ፣ የሴቶች መብት እንዲከበሩና፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ የሚያስችል መልካም እሴት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ አንትሮሽት ሴቶች መብቶቻቸው እንዲከበር፣ ድካማቸው፣ ጥረታቸውና ልፋታቸው ወንዶች እንዲያውቁትና እንዲረዱት በጥበብና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የጠየቁበትና ያስከበሩበት ትልቅ በዓል  መሆኑ ተናግረዋል፡፡ ይህ ጥረት ዛሬ ፍሬ አፍርቶ ልጆች፣ ባለቤትና ሌሎች ዘመድ አዝማድ ስጦታ በማበርከት፣ መብል በማዘጋጀት ከእናቶቻቸው ምርቃት የሚያገኙበት በዓል ሆኖ እየተከበረ መሆኑ አስረተድተዋል፡፡ በመሆኑም በዓሉ ፆታዊ እኩልነት ለማስፈን፣ በሰላም እሴት እና በዲሞክራሲ ግንባታ፣ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና  ተጠቃሚነት ላይ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ ሚናው  የጎላ መሆኑ ኃላፊዋ አስገንዝበዋል፡፡ አክለውም ኃላፊዋ ሴቶች በዘላቂነት መደገፍና መንከባከብ ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የሴቶች ልፋትና ድካም የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን  በማስፋት ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ መሀመድ በጉራጌ ብሔር ዘንድ በወርሃ ጥር ከሚከበሩ በዓላት መካከል የእናቶች የምስጋና ቀን ’’አንትሮሽት’’ ተጠቃሽ ሲሆን በዓሉ መከበር ከጀመረ ዘመናትን መቆጠራቸውን አስገንዝበዋል። እናቶች ዓመቱን ሙሉ በስራ አሳልፈው በወርሃ ጥር በልጆቻቸውና በባለቤቶቻው ተከብረው፣ ስጦታ ተበርክቶላቸው፣ ከስራ ሁሉ አርፈው የሚውሉበት አንትሮሽት በወርሃ ጥር ከ15 እስከ ጥር 29 በልዩልዩ ፕሮግራሞች እንደሚከበርላቸው አስገንዝበዋል፡፡ እናቶች እንሰት ፍቀው የሚያጠናቅቁበት፣ ማጀታቸው በእህል የሚሞላበትና ለክብረ በዓሉ የሚመጡ እንግዶች በወግ በማዕረግ የሚሸኙበት ወቅት በመሆኑ ነው ወርሃ ጥርን የመረጡት፡፡ አንትሮሽት እናትን ማዕከል ያደረገ፣ ልጅ ሲወለድ አፍንጫ የምትጠባ (ያፉና አዶት) ጨምሮ ሌሎች የቤተሰብ አባላት እንደ ምራት፣ ወንድና ሴት ልጅ እንዲሁም ባለቤት አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ሲያከብሩላቸውቸው እንደነበር ኃላፊዋ ገልጣል፡፡ ሴት ልጆች ከያሉበት ተሰባስበው በእናታቸው መኖሪያ ቤት በመገኘት ቤት እና ግቢው በማጽዳትና በማሳመር፣ አንጋፋዋ ልጅ የእናታቸው ገላ በማጠብ፣ አዲስ ልብስ በማልበስ እንዲሁም ልዩልዩ ባህላዊ ምግቦች በማዘጋጀት እንደሚያከብሩላቸው አስረድተዋል፡፡ የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስዳዳሪ አቶ ካሱ ጁሃር የአንድ ማህበረሰብ ማንነት የሚገልፁ ምልክቶችና እሴቶች መካከል አንዱ ባህል ሲሆን የጉራጌ ማህበረሰብ በርካታ ባህላዊ እሴቶች በማዳበር ግንባር ቀደም ተጠቃሽ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ አንትሮሽት የማህበረሰቡ ቱባ እሴት መሆኑ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ከተጀመረ ዘመናት ያስቆጠረ ቢሆንም በሂደት ተቀዛቅዞ ከነበረበት ወጥቶ አሁን በየአመቱ የሚከበር ተጠባቂ በዓል መሆን መቻሉ አስረድተዋል፡፡ አንትሮሽት የጉራጌ ብሔር ያጎለበተው ጠቃሚ እሴት በመሆኑ ይበልጥ እንዲለማ፣ እንዲተዋወቅና የእናቶች ውለታ ይበልጥ እንዲታወስ ሁሉም በቅንጅት መስራት ይኖርበታል ብለዋል፡፡ አክለውም አቶ ካሱ የሀገሪቱ እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ የሁሉም ርብርብ ማድረግ የሚጠበቅበት ሲሆን በወረዳው ልማትን በማደናቀፍና የህብረተሰቡ ሰላም ለማደፍረስ እና ደህንነት የሌሎችን አፍራሽ አጀንዳ ያላቸው ግለሰቦች ተልዕኮ ማራመድን ትተው ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን የእናት ሀገራቸው እድገት እንዲረጋገጥ በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ አንዳንድ እናቶች በሰጡት አስተያየት በብዙ ውጣውረድ ወልደው ባሳደጓቸው ልጆቻቸው ዛሬ አርፈውና ተከብረው ቀኑን ማክበራቸው ወደር የሌለው ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል። መረጃው የጉራጌ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

ጥር 19/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅህፈት ቤት የከተሞች ልማትና ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስተወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ከ/ል/ኮ/ል/ፅ/ቤት በ2018 በጀት አመት በወረዳው በሚገኙ በሁሉም ከተሞች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ በርካታ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል። የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተማም አደም በ2018 በጀት ባለፉት 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም አስመልክተው እንደገለጽት በወረዳው በሁሉም ማዘጋጃ ቤት ከተሞች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ በርካታ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በግማሽ አመቱ ተጠናቀው ርክክብ የተረገባቸው ፕሮጀክቶች የመሀል አምባ የማስፋፊያ መንገድ ጠጠር የማልበስ የእስትራክቸር ስራ፣ ወ/ዲሴ መንገድ ጠጠር የማልበስ የእስትራክቸር ስራ፣የመሀል አምባ ከተማ ደረጃውን የጠበቀ የቄራ ግንባታ ተጠቃሽ መሆናቸውን የገለጹት የጽ/ቤቱ ኃላፊ የመሀል አምባ ከተማ የጌጠኛ ድንጋይ ንጠሰፍ ስራ፣ ወ/ዲሴ የማዘጋጃ ቤት ቢሮ ግንባታ ፣ የአንጌ መዋለ ህፃናት ግንባታ፣ የኢንጌ ሁለ ገብ አደራሽ ግነባታ፣ የጅማ የውሃ መስመር ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየር ስራ፣ የመሀል አምባ ከተማ የማስፋፊያ የመብራት መስመር ዝርጋታ እና ትራንስፎርመር ተከላ ስራዎች በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልጸው በቅርቡ እንደሚጠናቀቁ አቶ ተማም አደም አስታውቀዋል። ጽህፈት ቤቱ በ2018 በጀት አመት ትኩረት ሰጥቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት ሲሆን ወ/ዲሴና ጎራ ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ እና በኢንጌ መዋለ ህፃነት ግንባታ ስራው ተጀምሮ 90% የደረሰ ሲሆን የመሀል አምባ፣ ኮንበል፣ ጅማ ከተሞች አዲስ የመዋለ ህፃናት ግንባታ መሆናቸውን ጠቅሰው የዚህ አካል የሆኑት የመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ የሆስፒታል ካፌ ግንባታ እነዲሁም በሚድሮክ ኢንቨስትመነት ግሩፕ አማካኝነት ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የንጽህ መጠጥ ውሃ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በተያየዘም የመሀል አምባ ከተማ አስተዳደር /ከፈርጅ 4 ወደ ፈርጅ 3 እና የኢንጌ ማዘጋጃ ቤት ከፈርጅ 5 ወደ ፈርጅ 4 የማሰደግ ስራ በጀት አመት ትኩረት ተስጥቶት እየተሰራ እንሚገኝ የገለጽት አቶ ተማም በሁሉም ከተሞች የመሬት አቅርቦት መሬት ለመኖራያ፣ ለንግድ ፣ ለኢንቨስትመንት እና ማህበራት የቤት ባለቤት ለማድረግ ዝግጅት በማድረግ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል። በተጨማሪም በወረዳው  እየተገነቡ ለሚገኙ ካፒታል ፕሮጀክቶች የዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ከኢሎ ማዞሪያ መሀል አምባ ከተማ እየተገነባ ለሚገኘው የአሰፓልት መንገድ የመብራት እና የቴሌ እንጨቶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በወቅቱ የማስናሳት ስራ መሰራቱን አቶ ተማም አደም አስገንዝበዋል። በመጨረሻም በየከተሞች ታጠረው ብቻ የተቀመጡ ነባር የኢንቨስትመንት ቦታዎች እንዲያለሙ እና በማያለሙት ህጋው አስራር እርምጃ ለመውሰድ እየተሰራ ሲሆን ለአዳዲስ ኢንቨስትመንት የሚሆን መሬት ከይገባኛል ነፃ በማድረግ ማልማት እንዲችሉ ገልጸው ተቋማቸው አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ እንደሚሰራ ገልፅዋል።

ድሉን ለማጽናት፤ ንቃታችን አይቀንስ **** ምንም እንኳን የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝን ብንቆጣጠረውም፣ ነገም ጤናማ ሆነን ለመቀጠል፡- 💦ንጽህና፡ የመጀመሪያው መከላከያ፦ እጅን በሳሙና መታጠብን የዘወትር ልማዳችን እናድርግ። የምንኖርበትንና የምንሰራበትን ስፍራ በንጽህና በመጠበቅ ለበሽታዎች በር አንክፈት። 📢 መረጃ፡ የጥንቃቄ መሣሪያ፦ ከጤና ተቋማት የሚወጡ ወቅታዊ መረጃዎችን በጥንቃቄ እንከታተል። ለጤናችን የሚበጁ ምክሮችን በተግባር በመዋል ራሳችንንና ቤተሰባችንን እንጠብቅ - የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ (ዶ/ር)

ጥር 18/2018 ዓ.ም የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለፀው የሴቶች ማህበርና ፌዴሬሽን አደረጃጀቶች አስፈላጊነት እና ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መይሙና ሙዘይን እንደገለፁት የሴቶች ማህበርና ፌዴሬሽን አደረጃጀቶች ሴቶችን በአንድነት በማደራጀት የመብት ጥበቃ፣ የኢኮኖሚ ብቃት እና የማህበራዊ ተሳትፎ ለማጠናከር አስፈላጊ መሆናቸውን አመልክተዋል። የሴቶች ማህበራትና ፌዴሬሽኖች ሴቶች መብታቸውን እንዲያውቁ፣ በውሳኔ ሰጪነት ሂደቶች እንዲሳተፉ እና በወረዳው የልማት እቅዶች ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያግዙ መዋቅሮች መሆናቸውን ወ/ሮ መይሙና ገልጸዋል። የዕለቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በሴቶች እና ህፃናት ባለሙያ በአቶ ተስፋዬ ሻምበል እና የሴቶች ማህበራት ሰብሳቢ በወ/ሮ ቲኩ ሁሴን ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። የሴቶች ማህበራትን አደረጃጀት እስከ ቀበሌ ድረስ ማጠናከር፣ አባላትን በተከታታይ ማስተማር እና የፌዴሬሽን አደረጃጀቶችን በተግባር ማጠናከር እንዳለበት፤ የሴቶች ሚሰማሩባቸው የስራ ዘርፎች መለየት መቻል እንዳለባቸው ፤ድጋፍ እና ክትትል ስራዎች ማጠናከር እንደሚገባ የውይይቱ ተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት ሰጥተዋል። የውይይት መድረኩን የመሩተ የወረዳው የብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽን ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ አ/ዋሂድ እንደገለጹት የሴቶች ማህበርና ፌዴሬሽን አደረጃጀቶችን በመደገፍ ሴቶች በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ያላቸው ተሳትፎ እንዲጠናከር በቀጣይም ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብሮች እንደሚካሄድ እና የሴቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የሴቶች ማህራት ሰብሳቢ ወ/ሮ ቲኩ ሁሴን በበኩላቸው የስልጠናው ዋና አላማ ሴቶችን በኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ተሳትፎቸውንና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ ሚናቸውን እንዲጫወቱ ማድረግና እንደሆነገልፀዋል። በመጨረሻም የሴቶች ፐብሊክ ሰርቫንት አስፈፃሚ ኮሚቴዎች በመምረጥ መድረኩ ተጠናቋል።

ጥር 18/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት የአንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃልያ ፈተና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በአንደኛው ወሰነ ትምህርት 12 ኛክፍል ወ=158  ሴ=161 ድ=319 8ኛ ክፍል ወ=753 ሴ=753 ድ=15116ኛ ክፍል=ወ=998 ሴ=954 ድ=1952 ተማሪዎች ለፈተና የተቀመጡ ት አጠቃላይ ወ=1909 ሴ=1868 ድ=3777 ቀሪዎች የክፍል ደረጃ ተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀላቸው የማጠቃለያ ፈተና እየወሰዱ ይገኛሉ።

የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወንድማችን ሠኢድ አስፋ ይበላል በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስፈዲን ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን በቀን 07/05/2018 ዓ.ም ከለሊቱ 9:00 ሰዓት ለስራ ከአስፈዲን ቀበሌ ወደ ቡታጅራ ለንግድ እቃ ይዞ ለመምጣት እንዳሰበና ባጃጅም ኮንተራት እንደጠራ ከአካባቢው የቅርብ ጎረቤቶቹ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ብቻው ይኖር የነበረ በመሆኑ የወሰደው ባጃጅ ማን እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም። በመሆኑም ከቤት እደወጣ እስካሁን አልተመለሰም ወንድማችንን ያገኛችሁ ወይም ያያችሁ ሰዎች እንድትተባበሩን ስንል በፈጣሪ ስም በአክብሮት እንጠይቃለን ይላሉ ፈላጊ ቤተሰቦቹ። ወንድማችንን ያያችሁ ከታች በተቀመጡ ስልክ ቁጥሮች እድታሳውቁን ስንል በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን። 0911689690 ረዲ ስራጅ +251979030121 ያሲን አስፋ መረጃውን ሼር በማድረግ እንተባበራቸው!!!