ar
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram
917
المشتركون
-124 ساعات
+27 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመድረኩ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የህዝብን ተሳትፎ ማሳደግ ለፖለቲካ ባህል ግንባታ መሰረት የሚጥል መሆኑ ተቀምጧል። በመደመር መንግስት የተፈጸሙ አስደናቂ የልማት ስኬቶችም የኢትዮጵያን ብልጽግና መፃኢ ዕድል የተሻለ የሚያደርጉ መሆናቸውን ተገልጿል። ህዝባዊ የውይይት መድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንትና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፈ ፣ እንደዚሁም የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ ፣በሚኒስተር ማእረግ የብልጽግና ፓርቲ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር አብድልዋስ አብዱልዋሂ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ እየመሩት ይገኛል። በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል፣የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ ፣የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ጨምሮ የዞን ፣የከተማ አመራሮችና የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በእለቱም "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ፅሁፍ በሚኒስተር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር አብድልዋስ አብዱልዋሂ እና በወልቂጤ ከተማ የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በከተማው ከንቲባ በአቶ ሙራድ ከድር ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም በፍትህ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የዓቃቢያን ህጎችን አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ለገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዓቃቢያን ህጎች በፍታብሔር ችሎት ክርክር ፣የኮንስትራክሽን ውሎች እና ሰነድ ማረጋገጥ ዙሪያ በዛሬው እለት ስልጠና ሰጥቶል። ዓቃቢ ህጎች በስራ ላይ ለሚያጋጥማቸው ሙያዊ ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችል እንዲሁም የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት የተዘጋጀ ስልጠና መድረክ መሆኑ ተመላክቷል። በእለቱ በጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ዓቃቢ ህግ የፍታብሔር ጉዳዮች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ግሩም ገብሩ እንዳሉት የፍትህ ተቋማት የአገልግሎት ስርዓቱ በማሻሻል ማህበረሰቡን የዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል። በፍትሃብሄር ስነ ስርዓት ህግ እና አጠቃላይ መርሆች እና የኮንስትራክሽን ውሎችና ሠነድ ማረጋገጥ ላይ ያተኳረ ሠነድ አቅርበው ውይይትና ምክክር ተደርጎበታል። በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ዓቃቤያን ህጎች ስልጠናው የክህሎት ክፍተቶችን ለመፍታት የሚረዳ፣ ቀጣይ በተግባር ሂደት የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እንደሚያግዛቸው በመግለፅ መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው ቢቀጥሉ የሚል አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ አባላት የ4ኛ ዙር ስልጠና ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስትወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨ በወረዳው "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሀሳብ በየማህበራዊ መሰረቱ ለሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት የሚሰጠው አራተኛ ዙር ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት በዛሬው እለት ተገመገመ። በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ እንዳሉት በስልጠናው የአባላችንን ዕውቀትና ክህሎት በመገንባት የተጀመረው ብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተናግረዋል። ስልጠናው "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሀሳብ የፊታችን ሠኞ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ለሁሉም አባላት የሚሰጥ እንደሆነ አብራርተዋል። አቶ አ/ሂም አክለውም አስቀድሞ በሁሉም አደረጃጀት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ከስልጠናው ቀን ቀደም ተብሎ ሁሉም ቅድመ ዝግጅቶች እንዲጠናቀቁና ስልጠናው በታቀደለት መልኩ በዲሲፕሊን እንዲሰጥ፤ እንዲሁም በከተሞችና በቀበሌዎች የሚኖሩ የአባላት መድረኮች ስኬታማ በሆነ መልኩ እንዲከናወኑ የወረዳው የስልጠና አብይ ኮሚቴ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል። በመድረኩ ላይ የወረዳው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ጠቅላላ አመራሮች ተሳትፈዋል።

ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የታቀደውን 60 በመቶው በተያዘው ታህሳስ ወር ለማሳካት በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨ ቢሮው ከወቅታዊ የገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ ከወቅታዊ የገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት በክልሉ በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የታቀደውን 23 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በሁሉም የገቢ አማራጮች ላይ በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል ። በተለይም ክልሉ አሁን ላይ እያሳየ ያለውን ፈጣን የልማት እድገት ቀጣይነቱን ለማረጋገጥና አዳጊ የልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ሀብት በሚጠበቀው ፍጥነትና ቅልጥፍና ገቢን አሟጦ መሰብሰብ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አለመሆኑን ነው ኃላፊዋ በመግለጫቸው ያብራሩት። በክልሉ እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ 60 በመቶ ገቢ ለመሰብሰብ እንዲቻል በተቋሙ ልዩ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ መገባቱን አመላክተዋል ። በየደረጃው የገቢ አማራጮችን ከተለምዷዊ አሰራሮች በማላቀቅ ዘመናዊና ተዓማኒነት ያለው ሁሉን አቀፍ አሰራሮችን ለመዘርጋት በቢሮ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። በቀሪ ጊዜያቶች ያልተሰበሰቡ የገቢ አማራጮችን በመለየት ሁሉም በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ሰራተኞች በቅንጂት በመስራት የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት መትጋት እንደሚጠበቅ ያመላከቱት ወ/ሮ ቀመሪያ የገቢ ስራ እንቅፋት የሆኑ ብልሹ አሰራሮችን ማረምና ማስተካከል ተገቢ ነው ሲሉም ገልፀዋል ። በመደበኛ የገቢ ስራዎች በተለይም የደረሰኝ ክትትል፣የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር የኢንቨስትመንት መሬት ኪራይና የማዕድን ገቢ ትኩረት መስጠት ፣ የሊዝ ኪራይና የዴስክ ኦዲት እንዲሁም ሌሎችም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የገቢ አማራጮቾን በመጠቀም በሙሉ አቅም ገቢ መሰብሰብ እንደሚገባ ጠቁመዋል ። በገቢ ስራ 40 በመቶውን ያህል ማሳካት የሚቻለው ከገቢ ደረሰኝ ጋር ተያይዞ ያሉ ስራዎች ናቸው ያሉት የቢሮ ኃላፊዋ በክልሉ የተጀመሩ ጥብቅ የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል ። እንደ ወ/ሮ ቀመሪያ ገለፃ ህብረተሰቡም ደረሰኝ ጠይቆ የመቀበል ባህልና ልምዱን ሊያጎለብት እንደሚገባና የንግዱ ማህበረሰብም የሚጠበቅበትን ተግባር በኃላፊነት ሊወጣ ይገባል ሲሉም ማሳሰባቸውን ከክልሉ ገቢዎች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ 4ተኛ ዙር ሀገረ አቀፍ የፖሊዮ ክትባት በተቀናጀ መልኩ መስጠት ተጀመረ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከ22 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጥ የጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ። በወረዳው ከታህሳስ 3 እስከ 6 ድረስ ቤት ለቤት የሚሰጠውን የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን፣የዞን ጤና መምሪያ ባለሙያዎች እና የወረዳው ጤና ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት በመሃል አምባ ከተማ መዋለ ህጻናት በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል። ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ህፃናት የመከተብ መብት አላቸው ወላጆች ልጆቻቸውን በማስከተብ ከልጅነት ልምሻ በሽታ በመጠብቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ክትባቱ በሁሉም ቀበሌዎች የሚሰጥ እንደሆነ አቶ ሚፍታ ሁሴን ገልጸው ባለድርሻ አካላትና መላው ማህበረሰብ ይህን ዘመቻ በማገዝ ጥራቱን የጠበቀ ክትባት ተደራሽ ሆኖ የህጻናት ጤና እንዲጎለብት የድርሻቸውን እንዲወጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አብራር በበኩላቸው በዚሁ ወቅት በወረዳ ደረጃ ለ4ኛ ዙር የሚሰጠው የቤት ለቤት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በሁሉም ቀበሌዎች ከ22 ሺህ በላይ የሚሆኑ ህጻናት ተደራሽ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል። በክትባት ዘመቻው ከፖሊዮ ክትባት ባሻገር ሌሎችም የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ፣የቆልማማ እግር ችግር ያለባቸው በመዘመቻው የሚለይ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የማርበርግ ቫይረስ ግንዛቤና ምልክት የደም መፍሰስና ትኩሳት ያለባቸው የመለየት ስራ የሚሰራ ይሆናል።

ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም በጉረጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጠይባ ቀበሌ የለማ የገብስ ማሳ በምስል በከፊሉ፦

ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም በሁሉም ዘርፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የጀመርናቸው የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) የ20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አፈጻጸም በጽ/ቤታቸው ገምግመዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) የ20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አፈጻጸም በጽ/ቤታቸው በገመገሙበት ወቅት እንደገለጹት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፍ የጀመርናቸው የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የክልሉ ልማት እንዲፋጠን የፈጠረው መነቃቃት ከፍተኛ እንደነበር ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ የቤተ መንግስት ፣የቢሮ ፣የአዳራሽ ግንባታ እና በከተሞች የኮሪደር ልማት ስራዎችን በአብነት ጠቅሰዋል። በዓሉ ስኬታማ እንዲሆን መላው የክልሉ ህዝብ የነበረው ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ ሊደገም እንደሚገባም አመላክተዋል። በየደረጃው ያለው አመራር ተጨባጭ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባቱን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ለስራዉ የሚሆን በቂ አደረጃጀት በመፍጠር የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል። ተከታታይነት ያለው ድጋፍና ክትትል ተደርጓል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ባዛርና ኤግዚቢሽን ፣የአዳራሽ ሲምፖዚየም ጨምሮ ሌሎች በዓሉን ለማድመቅ የተዘጋጁ ፕሮግራሞች ውጤታማ እንደነበሩም ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት፣ኢትዮ ቴሌኮም የውሃ ተቋማት እና ግለሰቦች ለበአሉ ድምቀት የነበራቸው አበርክቶ የላቀ እንደነበርም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል። ከሚጠበቀው በላይ ህዝብ የተሳተፈበት በዓል እንደነበር የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መከበሩንም አስታውሰዋል። በትብብር እና በቅንጅት በመሰራቱ በዓሉ ደማቅ ተናፋቂና በህብረተሰቡ ዘንድ ትውስታን ጥሎ እንዲያልፍ አድርጓል ብለዋል። በክልሉ ግንባታቸው በመካሔድ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ማስቀጠል እና አገልግሎት መስጠት የጀመሩትን ደግሞ መንከባከብ ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። በክልሉ በገቢ እና በስራ እድል ፈጠራ ላይ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የላቀ ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

ህዳር 30/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና የግብርና ገቢ ግብር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች በይፍ መጀመሩን የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የተሻሻለው የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር ወቅቱ የሚጠይቀውን የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ግብርን በወቅቱና በታማኝነት መክፈል ከራስ ወደ ራስ እንደሆነ የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል። በሁሉም ቀበሌ አርሶአደሮች ግብራቸውን ከዛሬ ህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚጠናቀቅ ሲሆን አርሶ አደሮች ወለድና አስተዳደራዊ ቅጣት ውስጥ ሳይገባ ተተምኖ የወረደለትን ገቢ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ክፍያውን ማጠናቀቅ እንዳለበት የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።