917
المشتركون
-124 ساعات
+27 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና የግብርና ገቢ ግብር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች በይፍ መጀመሩን የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የተሻሻለው የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር ወቅቱ የሚጠይቀውን የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲሁም
በሁሉም ዘርፍ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ግብርን በወቅቱና በታማኝነት መክፈል ከራስ ወደ ራስ እንደሆነ የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል።
በሁሉም ቀበሌ አርሶአደሮች ግብራቸውን ከዛሬ ህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚጠናቀቅ ሲሆን አርሶ አደሮች ወለድና አስተዳደራዊ ቅጣት ውስጥ ሳይገባ ተተምኖ የወረደለትን ገቢ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ክፍያውን ማጠናቀቅ እንዳለበት የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት 4ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ ለጤና
ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ከታህሳስ 3 እስከ 6/2018 ዓ.ም እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ያሉ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ቤት ለቤት እንደሚሰጥ መሆኑን የወረዳው ጤና ጽ/ቤት አክሎ አስታወቋል።
በመደበኛው የክትባት መርሃ ግብር ክትባት ያልጀመሩና ፣ክትባት ጀምረው ያቋረጡ እድሜያቸው ከ1 አመት በላይና ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት የመለየት እና የመከተብ አገልግሎት በዘመቻው የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል።
የልጅነት ልምሻ በሽታ ለመከላከል እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት ክትባት ክትባቱ ቤት ለቤት የሚሰጥ እንደሆነ በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ በፊት የትኛውም ክትባት ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ ህጻናት አድሜያቸው ከአንድ አመት በታች የሆኑ ህጻናቶች በመደበኛነት ክትባት የሚሰጥ እንደሆነ ተገልጿል።
በዘመቻው ከፖሊዮ ክትባት ባሻገር ሌሎችም የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ፣የቆልማማ እግር ችግር ያለባቸው በመዘመቻው የሚለይ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የማርበርግ ቫይረስ ግንዛቤና ምልክት የደም መፍሰስና ትኩሳት ያለባቸው የመለየት ስራ የሚሰራ ይሆናል።
መረጃው የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ነው።
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሀል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የውስጥ ገቢ ለማሳደግ ከ2.5 ሄክታር በላይ በግቢ ውስጥ የተዘራው የገብስ ምርት በኮምባይነር በመታገዝ ምርቱን መሰብሰብ ተችሏል።
የጉራጌ ክትፎ - ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጣዕሙ ነው
✅ የአፋር ዳጉ - ለዳውሮ ኩራቱ
✅ የሲዳማው ጫምባላላ - ለአማራ ሀሴቱ
✅ የኦሮሞ ገዳ - ለሐረሪ ምቾቱ
✅ የአክሱም ሐውልት - ለሀዲያ ታሪኩ
✅ የጀጎል ግንብ - ለቤንሻንጉል ቅርሱ
✅ የፋሲል ቤተመንግሥት - ለሀዲያ ሀብቱ
✅ የሶማሌው ዳንቶ - ለጋሞ ባህሉ
✅ የጉራጌ ክትፎ - ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጣዕሙ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ህዳር 28/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ " ከተረጂነት ወደ ምርታማነት " በሚል በወረዳ ደረጃ ደነብ ቀበሌ በመኸር የተዘራ 7 ሄክታር የስንዴ ምርት በኮምባይነር በመታገዝ ምርት መሰብሰቡን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የአደጋ ስጋት ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ መኪያ ነጋሽ በምርት አሰባሰቡ ወቅት ተገኝተው እንዳሉት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገርና አቅመ ደካሞችን በራስ አቅም ለመደገፍ በመኸር አዝመራ በደነብ ቀበሌ የተዘራው ስንዴ ምርት አሰባሰብ ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ወ/ሮ መኪያ ነጋሽ አክለውም በወረዳው በዘንድሮ መኸር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ሃሳብ በሁለት ቀበሌዎች 10.5 ሄክታር ስንዴና ጤፍ መልማቱን ጠቅሠው በደነብ ቀበሌ ዛሬ ምርት እየተሠበሠበ የሚገኘው 7 ሄክታር ስንዴ እንዲሁም አንበልታ ቀበሌ 3.5 ሄክታር ጤፍ እንደለማ አስታውቀዋል።
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ በበኩላቸው በሜካናይዜሽን የታገዘ የምርት አሰባሰብ ሂደት የምርት ብክነቶች እንዳያጋጥም የሚያግዝና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በመሆኑን አስታውሠው በወረዳ ደረጃ አርሶ አደሩ በሜካናይዜሽን ተጠቅሞ የደረሱ ሰብሎችን ፈጥኖ በመሰብሰብ የምርት ብክነትን መቀነስና መከላከል እንዲችል በኮምባይነር ምርት የመሰብሰብ ስራ ተጠናክሮ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
ህዳር 29/2018 ዓ.ም
🎤 የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት የሚደረግ ዘመቻ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በደነብና ቦኔ ቀበሌ በኮምፓይነር ምርት አሰባሰብ ስራ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን እቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት የማዕጤመ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መገምገሙን አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 ያለፉት ሁለት ዓመታት ጉዞ አድካሚ ቢሆንም በርካታ ያጋጠሙ ችግሮችን ማስተካከል በመቻሉ ክልሉ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆኑን ተገንዝበናል :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 ጥራት ያለውና ቀልጣፍ የጤና አገልግሎትን በብቃት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ገለፁ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 ፍትሃዊና ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም ማህበረሠብ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሃል አምባ ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት ተግባር አፈፃፀምና አገልግሎት አሰጣጥ የቦርድ አባላት በተገኙበት ተገመገመ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኢንጌ ጤና ጣቢያ ስራ አመራር ቦርድ አባላት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የፖሊስ ሰራዊት አባላት ሀገርን እና ህዝብን በተሻለ ቁመና ማገልገል እንደሚገባ ተገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ህዳር 28/2018 ዓ.ም
የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት የሚደረግ ዘመቻ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በደነብና ቦኔ ቀበሌ በኮምፓይነር ምርት አሰባሰብ ስራ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የግብርና ሜካናይዜሽን ለሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ማፋጠን ከቤተሰብ ብልፅግና ወደ ሀገር ብልፅግና ለማሸጋገር የሁሉም ዜጋ ትብብርና ትጋት ይጠይቃል።
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በደነብ ቀበሌ ውድማ ልማት ቡድን እና ቦኔ ቀበሌ ጎራ ልማት ቡድን በኮምፓይነር ምርት አሰባሰብ ስራ ተካሄዷል።
የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ሲሆን በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል።
የበሽታው ምልክቶች ለቫይረሱ በተጋለጥን ከ2 እስከ 9 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚታዩ ሲሆን፤ ምልክቶቹ:-
👉 ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ስር ደም መፍሰስ፣
👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፣
👉 የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣
👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፣
👉 ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ ናቸው።
የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች
👉 ከበሽተኛ ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ንክኪ፣
👉 በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች (እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣ መርፌ እና ሌሎች መገልገያዎች) ጋር በሚኖር ንክኪ፣
👉 በተጨማሪ በበሽታው ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል።
የበሽታው መከላከያ መንገዶች
👉 የተዘረዘሩት ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ፣
👉 ከታመመ ሰው ጋር ንክኪ ካለዎት እና ትኩሳት ካለ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ፣
👉 ሞት በሚከሰትበት ጊዜ አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀት እና መቅበር፤ አላስፈላጊ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ፣
👉 ከታመመ ሰው ደም እና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፣
👉 ለታመመ ሰው እንክብካቤ በምናደርግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን ማለትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የእጅ ጓንት መጠቀም፣
👉 እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውሃ በአግባቡ መታጠብ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
