ar
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram
917
المشتركون
-124 ساعات
+27 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ የመምህራንና የፐብሊክ ሰርቫንት አባላት ስልጠና መድረክ ተጀምሯል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ስልጠናው "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬን ጨምሮ ተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም "በመደመር መንግስት እይታ፣የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለፓርቲ አባላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ‎ "በመደመር መንግስት እይታ፣የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለኢንተር ፕራይዞች፣ለከተማ ነዋሪዎች እና ለአርሶ አደር የፓርቲ አባላት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረወ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል። የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ እና የወረዳው ደጋፊ አመራር የሆኑት አቶ አብዶ ሀሰን ስልጠናው ማጠቃለያ አስመልክተው እንዳሉት "በመደመር መንግስት ዕይታ ፤ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ በየደረጃው የሚገኘው አመራርና አባላት በግብርና ፣ በአምራች ኢንደስትሪ ፣ በከተማ ልማትና በቱሪዝም ዘርፎች የተዘጋጁ ሰነዶች በዝርዝር የቀረቡበት ስልጠና መሆኑን በመግለፅ ለነዚህ ዘርፎች መንግስት የሰጠውን ትኩረት በመረዳት የመደመር መንግስት የአመራርና የአባላት ባህሪን በመላበስ የተጀመረውን ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ በውጤታማነት መምራት የሚያስችል አቅም እንዲፈጥር ያለመ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው ስልጠናው በመደመር መንግሥት እይታ የግብርና እና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ፣የቱሪዝም እና የከተማ ልማት እምርታ በሚሉ በተመረጡ ርእሰ -ጉዳዮች ዙርያ ለአባላቱ የግንዛቤ መስጠቱን ገልጸው የተቀመጡ አቅጣጫዎች በተገቢው ተገንዝቦ በመተግበር ሁለንተናዊ ብልፅግና የተረጋገጠባትን ታላቅ ሀገር በመፍጠር ሂደት የፓርቲው አባላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሚገገባ እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል። ስልጠናው በአመራርና አባላት መካከል የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በመፍጠር አመራሩና አባላቱ የብልፅግና እሳቤን በተጨባጭ እንዲተገብር ስለሚያስችል ሰልጣኝ አባላት በወሰዱት ስልጠና መሰረት ወደ ተግባር መቀየር እንዳለባቸው አቶ ሚፍታ ሁሴን አስገንዝበዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ በሁለት ቀናት የስልጠና ቆይታ አስመልክተው እንደገለጹት "የመደመር መንግስት እይታ ፣ የግብርና ፣ የኢንዱስትሪ፣ የከተማ ልማት እና የቱሪዝም ዘርፎች እምርታ" በሚሉ ርዕሶች ስልጠና የተሰጠ መሆኑን ጠቅሠው በስልጠናውም የመደመር መንግስት የሀገርን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በተለዩ ዋና ዋና ዘርፎች ያስቀመጣቸውን የልማት ትልሞችንና የትግበራ አቅጣጫዎችን በተመለከተ የብልፅግና ፓርቲ አባል በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ያለንን ፀጋ በመጠቀም እንዴት ማደግና መበልፀግ እንደሚቻል የእይታ ለውጥ የሚያመጣ እና የአባሎቻችን ትጋት የሚጨምር እና ለለውጥ የሚያነሳሳ ስልጠና እንደነበር ተናግረዋል። አቶ አ/ረሂም በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት የመጀመሪያው ዙር ለኢንተር ፕራይዞች፣ለከተማ ነዋሪዎች እና ለአርሶ አደር የፓርቲ አባላት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እንዲሳካ ከቅድመ ዝግጀት ጀምሮ በርካታ ስራዎች መፈጸማቸውና ስልጠናውም ስኬታማ መሆኑን ጠቅሠው ሁለተኛ ዙር ስልጠና ማለትም የመንግስት ሠራተኞች እንዲሁም የመምህራ አባላት ስልጠና ነገ እሮብ ታህሳስ 08 ከጥዋቱ 2፡30 ጀምሮ በተዘጋጁ ማስልጠኛ ማዕከላት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ‎"በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ የአርሶ አደር፣የከተማ ነዋሪዎች እና ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በዛሬው እለትም በመደመር መንግስት እይታ የከተማ ልማትና የቱሪዝም ዘርፍ እምርታ በሚል ርዕስ ስልጠናው እየተካሄደ ይገኛል። የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ የስልጠናውን ሂደት በመከታተልና መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ።

ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ''በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሃሳብ 4ኛ ዙር የአባላት ስልጠና እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው እለት የግብርናና ኢንዱስትሪ ዘርፍ እምርታ ለአባላት በሁሉም ቀበሌዎች የስልጠና መድረክ ተካሄዷል። የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና በነገው እለትም የበሌሎች ርስሠ ጉዳዮች እንደሚቀጥል የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ''በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሃሳብ ከነገ ታህሳስ 6 ጀምሮ 4ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አባላት የሚሰጠው ስልጠና አስመልክቶ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ''በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሃሳብ ከነገ ታህሳስ 6 ጀምሮ በሚሰጠው የአባላት ስልጠና ከ19 ሺህ በላይ የብልጽግና ፓርቲ አባላት በ91 የማሰልጠኛ ማዕከላት ስልጠና እንደሚወስዱ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታውቋል። ስልጠናውን አስመልክቶ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ እንዳሉት የስልጠና ዋና ዓላማ የፓርቲያችን አባላት ያለንን የፖለቲካ ራዕይን ከተግባራዊ የትኩረት ዘርፎች አመራር ክህሎት ጋር እንዲያስተሳስሩ በማድረግ እንደፓርቲ ቅድምያ የሰጠናቸው ዘርፎች መሳካት የሁሉም አባላት ግንዛቤና ሚና እንዲኖር በማስቻል የብልፅግና ጉዟችንን በክህሎት ተኮር አመራር ማፋጠን የሚያስችል በአባሎቻችን ዘንድ መነሳሳትና ቁጭት እንዲፈጠር በማድረግ ትጋትንና ውጤታማነትን ማሳደግ ሲሆን ስልጠናውን ወደ ተግባር በመቀየር የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በመፍጠር እንደ ሀገር የተጀመሩ የልማት ግቦችን ለማሳካት ድርሻው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል። በመደመር መንግስት ዕይታ ፤ የዘርፎች ዕመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚሰጠው ስልጠና ከታህሳስ 6 እስከ 09/2018 በየማህበራዊ መሰረቱ የሚሰጥ ስልጠና ሲሆን የአርሶ አደር አባላት ፣ የከተማ ነዋሪ አባላትና ኢንተርፕራይዝ አባላት ከታህሳስ 06 እስከ 07/2018 ዓ.ም ከነገ ጀምሮ የሚሰጥ ሲሆን ከታህሳስ 08 እስከ 09 የመንግስት ሠራተኞችና የመምህራን አባላት ስልጠና እንደሚቀጥል ጠቅሠው ስልጠናው እንደ ሀገር እና ወረዳ ያለንን የመልማት አቅም በተገቢው የምናይበት እና ለተግባር የሚያነሳሳ አቅም የሚፈጥር ስልጠና እንደሆነ የፓርቲ ኃላፊው አክለው ገልጸዋል። አቶ አ/ረሂም በመጨረሻም እንደገለጹት በሁሉም የስልጠና ማዕከላት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ስልጠናው እንዲሳካ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተገቢው መሰራታቸውን ገልፀው በሁሉም ቀበሌ ነገ ሠኞ ታህሳስ 06 ከጥዋቱ 2:00 ጀምሮ ስልጠናው እንደሚጀመር አስገንዝበዋል።

ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መንግስት በትኩረት ይሰራል፦ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሲካሄድ የነበረው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተጠናቋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንትና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ፣እንደዚሁም የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል ዶክተር አበባየሁ ታደሰ በውይይት መድረኩ ልዩነቶቻችንን በማጥበብ አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ አትኩረን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። ወልቂጤ ከተማ የታታሪ ህዝቦች መኖሪያ፣ ህብረ- ብሔራዊነትን የሚገለፅባት፣ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በፍቅርና በሰላም የሚኖሩባት ከተማ እንደመሆኗ መጠን ለኑሮ አመቺና የበለጸገች ከተማ እንድትሆን ይበልጥ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል። የበለፀገች ኢትዮጵያና ወልቂጤ ለመፍጠር አንድነት፣ ገዢ ትርክት፣ መቻቻል እና ኢትዮጵያዊነትን ማጽናት ያስፈልጋል ነው ያሉት። ከተማዋ የብዙ ክልሎች መሸጋገርያ መሆኗን የገለፁት ዶ/ር አበባየሁ ለኢንቨስትመንት፣ ለንግድ፣ ለቱሪዝም እና በሌሎችም ዘርፎች የመልማት አቅም ያላት ከተማ በመሆኗ ሁሉም በትብብር እንዲያለማትና ሰላሟን እንዲያስጠብቅላት መክረዋል። የወልቂጤ የድንበር ጣልቃ ገብነት የክልሉ መንግስት በጥናት እንደሚፈታው አመላክተው ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መንግስት በትኩረት ይሰራል ብለዋል። በዛሬው እለት በውይይቱ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል በአግባቡ ተደራሽ እንደሚደረግም አስታውቀዋል። በሚኒስተር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አብድልዋስ አብዱልዋሂ በበኩላቸው እንደሀገር አምስት የኢኮኖሚ ምሶሶዎችን መሠረት በማድረግ የሀገሪቱን እድገት ፈጣንና ቀጣይነት ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመጠቀም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሻገር የሚያስችሉ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል። ዶክተር አብድልዋስ አክለውም አንድነትና መተሳሰብን የዕድገት መሳሪያ አድርጎ በመጠቀም ሁለንተናዊ ለውጥ ለማስመዝገብ በጋራ መስራት ይጠበቃል ብለዋል። በስራ ፈጠራ፣ የኑሮ ውድነት በመቀነስ፣ ቱሪዝሙን፣ ከተሜነትን ማዘመን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ እንደሚጠበቅ ገልፀው በአገልጋይነት መንፈስ በመስራትና መልካም አስተዳደርን በማስፈን በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ዶክተር አብድልዋስ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ በዚህ ወቅት እንዳሉት የጉራጌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበ ያለው ውጤት እንደ ሃገር የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ የተያዘውን እቅድ ስኬታማ በማድረጉ ላይ የራሱን አሻራ እያኖረ ነው። ይህም የግብርና ምርቶችን በብዛት በማቅረብ የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ሚናው የጎላ ነው ያሉት ሃላፊው ከዚህ በተጨማሪም ከሰንበት እስከ ሰንበት ሳምንታዊ የገበያ አገልግሎት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። ከዚህ ባለፈ እንደ ክልልም ጉራጌ ዞን በኢትዮ ኮደርስ፣በስራ እድል ፈጠራ ፣በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች በግንባር ቀደምት ተሸላሚ መሆኑን ገልጸው በቴክኖሎጂው ዘርፍም እንደ ሀገር ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎች በማበርከት የድርሻውን ሚና እየተወጣ መሆኑንም ጠቁመዋል። በወልቂጤ ከተማም የተጀመሩትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እጅግ ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አሳስበዋል። ከከተማው ወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ በአጥኚዎች ቡድን ተጠንቶ የተጠናቀቀ መሆኑና ውጤቱ ይፋ እስኪደረግ ማህበረሰቡ በትእግስት እንዲጠብቅም አስገንዝበዋል በውይይቱ የተሳተፉ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ብልጽግና በየጊዜ እያመጣቸው ያሉ ለውጦች እጅግ አመርቂ መሆናቸውና ሰው ተኮር ፓርቲ በመሆኑ በሰዎች ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ጠቅሰዋል። እነሱም መንግስት ያወረዳቸው ኢኒሼቲቮች በአግባቡ በመተግበርና ብልጽግናን በማረጋገጥ የበኩላቸው እየተወጡ መሆኑን ገልጸው በኮሪደር ልማት፣ በግብርና፣ በጤናና በሌሎች የልማት ስራዎች ከመንግሥት ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። የጉራጌ ማህበረሰብ ከሌሎች ብሔር-ብሔረሰቦች ተዋዶና ተፈቃቅሮ የመኖር እሴቱን ይበልጥ በማጠናከር የወልቂጤ ከተማ ልማት ለማረጋገጥ በአብሮነትንና በመቻቻል እሴት ለከተማው ልማት በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ በከተማው የወሰን ጣልቃ ገብነት መኖሩ የከተማው ሰላም እና ልማት በተፈለገው ልክ እንዳይረጋገጥ እያደረገው በመሆኑ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው ጠይቀዋል። በየጊዜው የከተማው ሰላም እንዳይረጋገጥ ጽንፈኛ አካላት ሰው በመዘርፍ እና በመግደል ተደጋጋሚ ወንጀሎች መፈጸማቸው ያስታወሱት ነዋሪዎቹ እነዚህ አካላት በህግ እንዲጠየቁና የከተማው ሰላም ዘላቂነት እንዲኖረው መንግስት አበክሮ እንዲሰራ አንስተዋል። መረጃው የጉራጌ ዞን ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።