918
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
ጥር 05/2018 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኢንጌ ከተማ ላይ ሳምንታዊ ሙሉ ገቢያ ጥር 05/2018 ዓ.ም ማክሠኞ
በዛሬው እለት ተቋቋመ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ሻጭ እና ገዢ የየፍላጎታቸውን ጥያቄ መመለስ ከሚችሉባቸው ስፍራዎች መካከል ገቢያ ትልቁን ድርሻ ገብያ ይወስዳል!!!
በገብያ ስፍራ በኑሮ ዝቅተኛ ከሆነው የህብረተሠብ ክፍል ጀምሮ እስከ ከፍተኛው ድረስ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከመፍጠሩም በተጨማሪ ማህበራዊ መስተጋብር የሚጠናከርበት መድረክ ሆኖም ያገለግላል።
ገብያ ለመንግስት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆን፣ ለሴቶችና ወጣቶች አማራጭ የስራ እድልን ይፈጥራል፣ የባህል ትስስር በህብረተሠብ ዘንድ ይፍጥራል እንዲሁም የከተሞችን እድገት ያፋጥናል።
በእለቱ የቁም እንስሳት፣የእህልና ጥራጥሬ ፣ፍራፍሬና አልባሳት፣ሸቀጣ ሸቀት እንዲሁም ሁሉም አይነት ምርቶች ቀርበዋል።
የበደረዘር 04/2018 ኢቶብየ ዘማን ሂልቅ
በጉቲ ኢቶብየ ክልል በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ በትረሾት ደር ያለይ ጉደርነትከ 120 ሜትር የሆነይ ያዞ ሚዴ ዘራመ በትፍጆት ደር ሁኖትከ ቴወደ።
ጥር 4/2018 ዓ.ም
የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር የስራ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።
መምሪያው ከጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመሆን የሴቶች ልማት ህብረት ለማጠናከርና የተጀመረው የዳታ ቤዝ አፈጻጸም ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።
የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊና የሀይል ጥቃቶች ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተገልጿል።
በመሆኑም በዛሬው እለትም በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከእምድብር ሀገረ ስብከት ጋር በመሆን እነዚህ ችግሮች ለመቅረፍ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩም የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ አህመድ ጨምሮ የመምሪያው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር የጽ/ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኢንጌ ከተማ ላይ ሳምንታዊ ሙሉ ገቢያ የፊታችን ጥር 05/2018 ዓ.ም እለተ ማክሠኞ ለማቋቋም በዛሬው እለት ቀንቴሮ ገብያ ላይ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ተካሄዷል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በገ/ጉ/ወ/ወረዳ የኢንጌ ከተማ ላይ ሳምንታዊ ሙሉ ገቢያ የፊታችን ጥር 05/2018 ዓ.ም ማክሠኞ እለት ይቆቆማል!!!
ገብያ ሻጭ እና ገዢ የየፍላጎታቸውን ጥያቄ መመለስ ከሚችሉባቸው ስፍራዎች መካከል ትልቁን ድርሻ ገብያ ይወስዳል!!!
በገብያ ስፍራው ከቁም እንሰሳት ጀምሮ ጥራጥሬ፣ አልባሳት፣ ፍራፋሬና አትክልት፣ ሸቀጣ ሸቀጥ እንዲሁም አይነት መፈቶች በኢንጌ ሳምንታዊ ሙሉ ገቢያ ያገኛሉ።
በኢንጌ ሳምንታዊ ሙሉ ገቢያ የፊታችን ማክሰኞ ነጋዴዎች ሽጠው የሚያተርፉበት ሸማቾች ሸምተው የሚደሰቱበት የተሟላ ሳምንታዊ ገብያ በመሆኑ ሁሉም ነጋዴዎች እንዲሁም ሸማቾች የፊታችን ጥር 05/2018 ዓ.ም ማክሠኞ እለት እንዲገኙ ሲል የኢንጌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ጥሪውን ያስተላልፋል።
ጥር 03/2018 ዓ.ም
የተማሪዎች ስነ ምግባር እንዲሁም የውጤት ስብራት ለማሻሻል የመምህራን ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለፀው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መምህራን ማህበር የ2018 ዓ.ም የመምህራን ቀን እና 29ኛው የማህበሩ ምክር ቤት ከትምህርት ቤቶች የመምህራን ተወካዮች ጋር በድምቀት አክብሮ በዋለበት ወቅት ነው።
የገ/ጉ/ወ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ሚፍታ ሁሴን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው
የተማሪዎች ስነ ምግባር እንዲሁም የውጤት ስብራት ለማሻሻል የመምህራን ሚና ከፍተኛ መሆኑ ገልፀው በቀጣይ ለሚሰጡ ዞናዊ፣ክልላዊ እና ሀገር አቀፋ ፈተናዎች ላይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መምህራን ተግተው መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰው ፤መንግስት የመምህራን መብት እና ጥቅማ ጥቅም ለማስጠበቅ ከማህበሩ ጋር በትኩረት እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ት/ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለማሁ ኬኔ በመድረኩ ተገኝተው እንደገለፁት የመምህራን መብት ከማስከበር ጎን ለጎን የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
እንደ ሀገር የገጠሙንን የትምህርት ሰብራቶችን ለማሻሻል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደምገኙ እና ጥራቱን የጠበቀ ብቁ፣ ታታር ዜጋን ለማፍራት መንግሰት እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚደነቅ እንደሆነ አቶ አለማየሁ ገልፀው
ትምህርት ለሀገር ሁለተናዊ እድገት መሠረት በመሆኑ በሀገራችን የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
በመምህራን ማህበር በኩል የተሰሩ ስራ አበረታች እንደሆነና የመምህራን ማህበር ከመምህራን ጋር በቅርብ መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል ።
የገ/ጉ/ወ/ወ መምህራን ሊቀመንበር በአቶ የዚህ አለም ደስታ አማካኝነት የማህበሩ የአመቱ ሪፖርት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።
ከውይይቱ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ፦ሴት መምህራን ከወሊድ ፍቃድ ጋር ያለው የፍቃድ ሁኔታ መታየት እንዳለበት ፤ለተማሪዎች ውጤት መውረድ የመምህራን ድርሻ አይነተኛ ሚና እንዳለው ፤የመምህራን ተወካዮች የመምህራን መብት ከማስከበር አንፃር ቀሪ ስራዎች መኖራቸው ፤የመምህራን ዝውውር ወቅቱን ያልጠበቀ መሆኑ ፤የመጽሐፍ እንረት መኖሩን ፤በት/ቤቶች የመምህራን እጥረት ፤በማህበር የተደራጁ መምህራን የቤት መስሪያ መሬት ከማቅረብ ጋር መዘግየት እንዳለ ከመድረኩ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።
ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄና አስተያየት የጉራጌ ዞን መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አግዛ ግርማ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ መምህራን ማህበር ሰብሳቢ ምላሽ እና ማብራሪያ ስጥተዋል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን መምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚዎች የት/ቤቶች መምህራን ተወካዮች ተገኝተዋል ።በአሉ ምክንያት በማድረግ የመሀል አምባ መዋለ ህጻናት ተማሪዎች የተለያዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ግጥም አቅርበዋል።
በመጨረሻም ለቀጣይ የማህበሩ ትኩረት አቅጣጫዎች እና የአቋም መግለጫ በማውጣት ቀሪ ሥራዎች ላይ የጋራ መግባባት ተደርሶ መድረኩ ተጠናቋል።
በ46ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳልያ አገኘች
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨
በ46ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳልያ አገኘች።
በሻምፒዮናው አትሌት ማርታ አለማየሁ በ18 ደቂቃ 52 ሰኮንድ በመግባት የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።
በውድድሩ ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት ወሰኔ አሰፋ 2ኛ ስትወጣ የኔነሽ ሽመክት 5ኛ በመውጣት አጠናቅቀዋል።
FMC
