ar
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram
917
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
ጥር 03/2018 ዓ.ም በ2018 ዓ.ም ባለፉት 6 ወራት ከ132 ሚሊዮን 520 ሺህ 443 ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የተያዘውን ዕቅድ 115.84 በመቶ ተፈፃሚ ማድረጉን በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ረመዳን ከድር ግብር ለአንድ አካባቢና ሃገር ሁለንተናዊ ብልፅግና አይነተኛ ሚናን ይጫወታል ሲሉ ገልፀዋል። በ2018 አጠቃላይ በጀት ዓመት 265 ሚሊዮን 040 ሺህ 886 ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅደው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን የጠቀሱ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በበጀት ዓመቱ ባለፉት 6 ወራት 153 ሚሊዮን 521 ሺህ 097 ብር ከ79 ሳንቲም ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ገለፃ ከሆነ በ6 ወራት ከመደበኛ ገቢ 116 ሚሊዮን 985 ሺህ 212 ብር ለመሠብሰብ በማቀድ 138 ሚሊዮን 687 ሺህ 136 ብር ከ62 ሳንቲም ገቢ በመሰብሰብ የተያዘውን ዕቅድ 118.55 በመቶ ተፈፃሚ ማድረግ ስለመቻሉ አብራርተዋል። ከማዘጋጃ ቤት ገቢ 15 ሚሊዮን 535 ሺህ 231 ብር ገቢ ለመሠብሰብ የታቀደ ሲሆን 14 ሚሊዮን 833 ሺህ 962 ብር ከ17 ሳንቲም ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 95.48 በመቶ ተግባራዊ ማድረጋቸውን በመግለፅ በአጠቃላይ ባለፉት ስድስት ወራት ከመደበኛ እና ከማዘጋጃ ቤት 132 ሚሊዮን 520 ሺህ 443 ብር ገቢ ለመሰብሰብ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ሠፊ ጥረት መደረጉን ተከትሎ 153 ሚሊዮን 521 ሺህ 097 ብር ከ79 ሳንቲም ገቢ በመሠብሰብ የተያዘውን ዕቅድ 115.84 በመቶ ተግባራዊ ተደርጓል ሲሉ ኃላፊው ገልፀዋል። ገቢው ከለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር 26 ሚሊዮን 568 ሺህ 791 ብር (20.04%) ብላጫ እንድለው ገልጸዋል። በተያያዘም የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና የግብርና ስራ ገቢ ግብር አሰባሰብ በ2018 በጀት አመት ከ39 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰ መታቀዱን የገለጹት አቶ ረመዳን ከድር እስካሁን 28 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ጠቁመው የማስከፈያው ጊዜ ሊጠናቀቅ በመሆኑ አርሶ አደሮች ወለድና አስተዳደራዊ ቅጣት ውስጥ ሳይገባ ተተምኖ የወረደለትን ገቢ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ክፍያውን ማጠናቀቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል። በመጨረሻም አቶ ረመዳን ከድር ባስተላለፉት መልዕክት በቀሪ ጊዜያቶች ያልተሰበሰቡ የገቢ አማራጮችን በመለየት ሁሉም በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ሰራተኞች በቅንጅት በመስራት በበጀት አመቱ የሚጠበቀውን ውጤት ለማሳካት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ጥር 01/2018 ዓ.ም የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የየዘርፉ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ የፓርቲው የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ጥልቅ ግምገማና ውይይት ይካሄዳል። በመድረኩ ላይ በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ የፖለቲካ፣ የአደረጃጀት ሥራዎችና የማህበራዊ ልማት ተግባራት በዝርዝር የሚቀርቡ ሲሆን፣ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ በትኩረት ውይይት ይደረጋል። በመድረኩ የጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል፣ የዞኑ የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናስር ሀሰን፣ የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን ጨምሮ የፓርቲው የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ረገድ የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) እንደገለጹት የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ረገድ የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል። በክልሉ በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ተግባራትን ስኬታማ ለማድረግ በትብብርና በቅንጅት መስራት ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። በበጀት ዓመቱ ተግባራዊ ለማድረግ የታቀዱ ስራዎችን በመለየት የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ለላቀ ስኬት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም አስረድተዋል። የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ውጤታማ ለማድረግ መፍጠን መስራት እና መወሰን ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። በክልሉ በንጹህ መጠጥ ውሃ ፣በመስኖ፣በመንገድ እንዲሁም በማዕድን ዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የአመራሩን ልዩ ትኩረት ያሻል ብለዋል። በተለያየ ጊዜ የሚስተዋሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ረገድ የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። መላውን ህዝብ በማስተባበር በልማት ስራ ላይ ማተኮር እንዲችል ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ነው።

"ምሁራንን ማሳተፍ የመደመር መንግስት የፖሊሲ አቅጣጫ ነው"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2018 ዓ .ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ቅ/ዝግጅት እና የክህሎት ስልጠና በሶዶ አይብ ገረን ቀበሌ ዋቤ ንኡስ ተፍሰስ ላይ ለኢንጌ አገልግሎት ለሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች መስጠቱን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በሶ/አይብ ገረን ቀበሌ ዋቤ ንኡስ ተፍሰስ ላይ የኢንጌ አገልግሎት ባለሙያ እና በንኡስ ተፍሰሱ ስም ለተደራጁ የስራ አመራር ኮሚቴዎችና ለባለድርሻ አካላት የ2018 የተፍሰስ ልማት ስራች በጥራትና በመጠን መስራት የሚያስችል የክህሎት ስልጠና በዛሬው እለት መስጠቱን ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል። በወረዳው ግብርና ጽ/ቤት የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ከድር ሞሼ በዘንድሮ 2018 ዓ.ም በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች 10400 ሄ/ር መሬት በላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ለማከናወን ታቅዶ የቅድም ዝግጅት ስራዎች እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አቶ ከድር ሞሼ አክለውም በሁሉም ንኡስ ተፍሰስ የሰው ሀይል ልየታ፣የመሳሪያ ልየታ፣ ሊለማ የሚችል የተፋሰስ ቦታ ልየታ እና የቀያሽ አርሶ አደር ስልጠና ዝግጅትና ልየታ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሠው በዛሬው እለትም በዋቤ ን/ተፍሰስ ለአገልግሎቱ ባለሙያዎች የተግባር የክህሎት ስልጠና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በጥራትና በመጠን ለመስራት የሚያግዝ እንደሆነ አስገንዝበዋል። በመጨረሻም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የተጎዱ መሬቶችን መልሶ ለማልማትና ምርታማነታቸውን ለማሻሻል ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ በዘንድሮ አመት የጥራት ጉዳይ መሰረታዊ እንደሆ የገለጹት አቶ ከድር ሞሼ ከስልጠናው የሚገኘውን እውቀት በቀጣይ በቀበሌቸው በተግባር ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል። የክህሎት ስልጠናው በቀጣይ በሁሉም አገልግሎቶች እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፁ፡፡ ዋና አሰተዳዳሪው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት የገና በዓል የፍቅር ፣የእርቅ እና የአንድነት እንደሆነ የክርስትና ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ያስገነዝበናል ብለዋል። በዓሉ ሁሉም የሚደሰትበት ፣ የተጣላ የሚታረቅበት ፣ያዘነ የሚፅናናበት የደስታ በዓል ነው፡፡ በሀገራችን ህብረተሰብ ከጥንት ጀምሮ ለዘመናት በዓላትን በጋራ በማክበር፣ በመጠያየቅ ፣ሐዘን እና ደስታን በመካፈል አብሮ የመኖር የደረጀ ጥበባዊ የሆነ ትውፊት ያለው ነው፡፡ የገና በዓልን ስናከብር አቅመ ደካሞችን በመጎብኘት እና የታመሙትን በመጠየቅ ደስታችንን የጋራ በማድረግ የቆየ እሴታችንን ልንጠብቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም አቶ ሚፍታ ሁሴን የ2018 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የሰላም የጤናና የብልፅግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም የሊዝ ጫረታ ማስታወቂያ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ካሉት ማዘጋጃ ቤቶች ውስጥ የጅማ ወለኔ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አንዱ ሲሆን በአዋጅ በተሠጠው ተግባርና ሀላፊነት ለንግድና ለመኖሪያ የሚውሉ ቦታዎች በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ዝግጁቱ አጠናቆ ተወዳዳሪዎችን ማወዳደር ይፈልጋል። ጅማ ወለኔ ማዘጋጃ ቤት  የሊዝ የመሬት ጨረታ  ይመለከታል፦ 1.የንግድ ብዛት 11 የጨረታ ሰነድ መግዥያ ዋጋ 600 የሊዝ መናሻ ዋጋ 570 2.የመኖራያ  ብዛት 11 የጨረታ ሰነድ መግዥያ ዋጋ 500 የሊዝ መናሻ ዋጋ 107.5 ብር ሲሆን $.ጨረታው የሚጀመርበት በቀን 27/ 04/2018 ዓ.ም .ጨረታው የሚዘጋበት /የሚያልቅበት በቀን 12/05/2018 ዓ.ም እስከ 11:00 ሰዓት ነው። $.የጨረታው አሸናፊ የሚከፈትበት /የሚለይበት 13/05/2018 ዓ.ም 3:00 ሰዓት የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን!!! ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በምስሉ ላይ መመልከት ይችላሉ ሲል መረጃው ያደረሰን የጅማ ወለኔ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ነው።

ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ከኢሎ ማዞሪያ - መሀል አምባ ከተማ የአስፖልት መንገድ በፍጥነትና በጥራት እየተገነባ እንደሚገኝ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን አስታወቁ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ከኢሎ ማዘሪያ -መሀል አምባ ከተማ ድረስ 8.5 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የአስፖልት መንገድ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባ ይገኛል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ግንባታውን አስመልክተው እንዳሉት መንገድ የመሠረተ ልማት አውታር ዝርጋታ ሁሉን ዓቀፍ ዕድገት ለማረጋገጥ ቁልፍ ድርሻ ያለን መሆኑን ጠቅሠው ከዚህ አኳያም የመንገድ ልማት የሃገራችንና የወረዳችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚጫወተው ሚና በእጅጉ ከፍተኛ ስለመሆኑ አቶ ሚፍታ ሁሴን ገልፀዋል። የወረዳው ህዝብ ለረጅም ጊዜያት ሲጠይቃቸዉ ከነበሩ የልማት እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መካከል ከኢሎ ማዞሪያ - መሃል አምባ ከተማ ድረስ ያለው የአስፓልት መንገድ ዝርጋታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው አሁን ላይ በብልጽግና መንግስት ግንባታው በፍጥነትና በጥራት እየተገነባ እንደሚገኝ ተናግረዋል። አቶ ሚፍታ አክለውም የመንገዱ ግንባታ በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው በተለይ የአፈር ጠረጋ ስራ፣ የድልድይና የውኃ መውረጃ ዲች ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ጠቅሠው እስካሁን 1.5 ኪሎ ሜትር ኮንኪሪት አስፓልት ግንባታ መጠናቀቁን አስገንዝበዋል። የመንገድ ግንባታ ሲጠናቀቅ በአከባቢው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ መሰረተ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ሲሆን በአካባቢው በስፍት የሚመረቱ የግብርና ውጤቶችን ወደ ማዕከላዊ ገብያ ለማጓጓዝ ኢኮኖሚያዊ ፍይዳው የጎላ መሆኑን እንዲሁም መንገዱን ለሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች ጊዜንና ጉልበት በመቆጠብ ማህበራዊ ትስስሩን ያሳልጣል በማለት የወረዳው ህዝብ የመንገድ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ እየደረገ የሚገኘውን ድጋፍ እንዲሁም አስፈላጊውን እገዛ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ አሳስበዋል። በመጨረሻም አቶ ሚፍታ ሁሴን ከኢሎ ማዘሪያ -መሀል አምባ ከተማ ድረስ 8.5 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የአስፖልት መንገድ ግንባታ ከፍተኛ አስታዋጾ ላደረጉ የፌደራል መንግስት፣የማዕከላዊ ክልል፣የጉራጌ ዞን መንግስት እንዲሁም የወረዳው መንግስትና ተወላጅ ባለሃብቶች ከፍተኛ እገዛና ድጋፍ መኖሩን ገልጸው በወረዳው መንግስትና ህዝብ ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።