ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 321
المشتركون
-124 ساعات
+67 أيام
+14430 أيام
أرشيف المشاركات
ሃቢታት ፎር ሂውማኒቲ ኢትዮጵያ (Habitat For Humanity Ethiopia) የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ስናይ ድርጅት ከድሬደዋ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ድርጅቱ ለገሃሬ አካባቢ ባስክፊ ሁኔታ (informal settlement) እኖሩ ለነበሩ 28 ኣባውራዎች በመልካ ደረጃውን የጠበቀ መኖሪ ቤት የገነባላቸው ሲሆን በነዚህ ወላጆች ስር ለሚገኙ ሀምሳ አንድ የቤተሰብ ኣባላት (ወጣቶችና ሴቶች) ከሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር አቅማቸውን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በማጎልበት ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጣሪ ሆነው የኑሮ መሰረታቸውን እንዲያሻሽሉ (sustainable livelihood) በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአጫጭር ስልጠና ዕድል ተመቻቸላቸው። ድርጅቱ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሰው ተኮር የሆኑ የመኖሪያ ቤት ግንባታ እና እድሳት እነዲሁም የመጠጥ ውሃ የመሳስሉ ስራዎችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ (highly vulnerable and low-income group) ላይ ለሚገኙ እና በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ኣደጋዎች ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+8

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በአስተዳደሩ ስር ከሚገኙ የከተማ እና የገጠር አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ማስተባበሪያ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የ2018 በጀት ዓመት ለወረዳዎቹ የተሸነሸነ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡ በዚህም የውይይት መድረክ ላይ ማዕከላቱን የሚመለከቱ ሥራዎችን በመቁረስ በከተማና በገጠር ለሚገኙ አንድ ማዕከላት ማውረድ የተቻለ ሲሆን በቀጣይም በመናበብ የአስተዳደሩን ነዋሪ ተደራሽና ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን በተጨባጭ ለመስራት አስፈላጊውን ምችችት እንደሚደረግና የሚታይ ውጤትና ለውጥ ለማምጣት ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ገልጸዋል፡፡ ዕቅዱን ወደ ታች ሸንሽኖ ከማውረድ ስራው ጎንለጎን በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ በ2018 ዓ.ም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በተለይም በቀጣይ በአገራዊና በዘርፉ አዲስ ዕሳቤዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ይዞ የተናበበና የተቀናጀ ሥራ መስራት እንደሚገባ የተመላከተ ሲሆን በዋናነት የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ንግድ፤አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ማደራጀት፤ ከኢ-መደበኛ ወደ መደበኛ የሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት አንዲሁም የማደግ አቅም ያላቸው ኢንተርፕራይዞች መለየት እና መደገፍ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

ለሥራ ፈላጊዎች የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት በተለያየ የሥራ ዘርፍ በቋሚነት፣ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት በዝውውር እና በኮንትራት የቅጥር አይነት፤ ከዜሮ ዓመት እስከ አስር
ለሥራ ፈላጊዎች የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት በተለያየ የሥራ ዘርፍ በቋሚነት፣ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት በዝውውር እና በኮንትራት የቅጥር አይነት፤ ከዜሮ ዓመት እስከ አስር ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸውን 237 ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። በዚህም መሰረት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በለማው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) በመጠቀም ምዝገባው ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የዚህ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን lmis.gov.et ላይ በመመዝገብና አቅራቢያችሁ ባለ ወረዳ/ቀበሌ የአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሠራተኛነት መለያ ቁጥር/ labor ID/ ማግኘት ይኖርባችኋል፡፡ የተሰጣችሁን የሠራተኛነት መለያ ቁጥር/ labor ID/ በመጠቀም በዚህ ማስፈንጠሪያ (https://forms.gle/AMm2LCHBvdqMwW5AA ) ላይ በመገባት ትክክለኛ የትምህርት፣ የሥራ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎቻችሁን በማሰገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። ምዝገባው ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ይካሄዳል፡፡ ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: t.me/fdre_mols TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 ዓ.ም መሪ እቅድ ለኮሌጁ የቦርድ አባላት አቀረበ፡፡ በበጀት አመቱ የተቋሙን አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ሪፖር
+9
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 ዓ.ም መሪ እቅድ ለኮሌጁ የቦርድ አባላት አቀረበ፡፡ በበጀት አመቱ የተቋሙን አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለቦርዱ የቀረበ ሲሆን በዚህም ኮሌጁ ከዝግጅት ምእራፍ አንስቶ በበጀት አመቱ የነበረውን የእቅድ አፈፃፀምና አጠቃላይ በኮሌጁ የተሰሩ የለውጥ ስራዎችን እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን ለቦርዱ ሪፖርት አቅርበው ገለፃ ያደረጉ ሲሆን አያይዘውም በቀጣይ በተቋሙ ሊሰሩ በእቅድ የተያዙ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን የሚያመላክት የ2018 ዓ.ም መሪ እቅድ ለቦርድ አባላቱ በዝርዝር አመላክተዋል፡: በመድረኩ የቀረበውን ሪፖርትና መሪ እቅድን መነሻ በማድረግም የቦርድ አባላቱ ግብረ- መልሳቸውን የሰጡበት ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በቀጣይ በሚኖረው የስራ እንቅስቃሴ ላይ ምክረ-ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል:: በመጨረሻም የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በቀረበው የኮሌጁ አጠቃላይ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ማጠቃለያ እንዲሁም የቀጣይ ስራ አቅጣጫና መመሪያን በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ነሃሴ 7/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በአስተዳደሩ ለሚገኙ ወጣቶች የክረምት ወቅት የሙያ ስልጠና በኮሌጁ መስጠት ተጀመረ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በክረምት ወቅት አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ በሚል መርሃ-ግብር በአስተዳደሩ እረፍት ላይ ለሚገኙ የአጠቃላይ የ1ኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ ስልጠናዎችን መስጠት ጀምሯል:: ለወጣቶቹ በተዘጋጀ ኦረንቴሽን ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ለወጣቶች ባስተላለፉት መልዕክትም የዚህ የክረምት ወቅት ስልጠና የተዘጋጀበት ዋና አላማ ወጣቶች እረፍታችሁን ቁምነገር ላይ በማዋል ቢያንስ በክረምቱ የአንድ ሙያ ባለቤት እንድትሆኑ ለማስቻል ነው ያሉ ሲሆን አክለውም የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክረምቱን በኮሌጃችን በሚኖራችሁ ቆይታ ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት የምትገነዘቡ በመሆኑ በቀጣይ ምዕራፋችሁ ለሙያ ተኮር ስልጠናዎች ቅድሚያ እንድሰጡ ያግዛችኃልም ብለዋል:: የአንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ የክረምት ስልጠና ላይ ለመሳተፍ ወደ ኮሌጁ የመጡ ወጣቶች በቅድሚያ የህይወት ክህሎት ስልጠና ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚወስዱ ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናው ወጣቶች የቀጣይ ህይወታቸውን የመምራት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ክህሎት እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቶችን እንደሚያገኙበት የተገለፀ ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናውን እንዳጠናቀቁ በቀጣይ በመረጡት የሙያ ዘርፍ ላይ ስልጠናቸውን የሚጀምሩም ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ነሃሴ 7/12/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የውጭ ተጓዦች ተጠቃሚነት

ለሥራ ዕድል ፈጠራ የፋይናንስ አቅርቦት

ባለብዙ ተሰጥኦው አሰልጣኝ መምህር!!!

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በዛሬው ዕለት የብልጽግና ፓርቲ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ጸጋዬ፣ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የኮሌጅ ዲኖች፣ አሰልጣኝ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት የ2017 የክረምት በጎፈቃድ ስራዎች ማስጀመሪያ እና የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ። የዛሬው ችግኝ የመትከል መርሐ-ግብር  በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጊቢ ውስጥ በስሩ ከሚገኙ ኮሌጆች ጋር በጋራ በመሆን የተከናወነ ሲሆን ለትውልድ ተሻጋሪ በሆነው በዚህ ተግባር ላይ በመሳተፋቸው ተሳታፊዎች የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን ይህ ተግባርም በቢሮው የሚተገበረው የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች መጀመሪያ መሆኑና በቀጣይም ለአቅመ ደካሞች ቤቶችን በመስራት፣ በደም ልገሳ እንዲሁም ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶችን በማገዝ የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል፡፡ በመትከል ማንሰራራት! ፎቶ፦ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት ዘገባ፦ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+5

photo content
+9

የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉን ለማጠናከር በአስተዳደሩ ገጠር ቀበሌዎች ተደራጅተው የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት(LLRP) አጠቃላይ አፈጻጸም እና ቀጣይ ዕቅድ ላይ ከቴክኒካል ኮሚቴዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ በዚህም በ2017 ዓ.ም ትግበራ አስራ አምስት በግብርና ዘርፍ እያንዳንዳቸው አምስት መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው የተለዩ ስራ ፈጣሪ በሴቶችና በወጣቶች የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችን ተደራሽ ማድረጉ በአፈጻጸሙ ተመላክቷል፡፡ በውይይቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ከዚህ ቀደም በአጠቃላይ የሥራና ክህሎት ስራዎች ተደራሽነት ጋር በተያያዘ ተቀናጅቶ እና ተናብቦ የገጠሩን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በሚሰሩበት አግባብ ላይ ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረዋል። በተለይም በገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ትኩረት በመስጠት  የገጠር ስራ ዕድልን ስርዓትን ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን ማረምና መለወጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ፕሮጀክቱ በተለያዩ ዘርፎች የተደራጁ አርባ ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች ለእያንዳዳቸው ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ ድጋፍ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ማወቅ ተችሏል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+5

#|ዜና በኮሌጁ ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘው የEASTRIP ፕሮጀክት ተቋሙን learning factory እንዲሆንና ለአካባቢው ብሎም ለኢንዱስትሪዎቹ ግብአት መሆን የሚችል ሰልጣኞችን በማብቃት ረገድ ትልቅ ስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ፡፡ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስር መተግበር ላይ ያለው የEASTRIP ፕሮጀክት ከአለም ባንክ፣ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ከIUCA የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የEASTRIP ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዩኒት እንዲሁም ከኬንያ እና ከታንዛኒያ የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች የልህቀት ማዕከሉን አጠቃላይ የፕሮጀክት ሂደት ለመመልከትና ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ያለመ የስራ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው እለት በኮሌጁ በመገኘት አከናወኑ፡፡ ለግምገማው የመጣውን ልኡክ ቡድን የተቀበሉትና የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እንዲሁም የኮሌጁን ሁኔታ ለልኡክ ቡድኑ ያብራሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም እንኳን ወደ ትንሿ ኢትዮጵያ እና ሁሉን አቀፍ ከተማ ወደ ሆነችው ድሬዳዋ ከተማ በደህና መጣችሁ ፡፡ በኮሌጁ እየተተገበረ የሚገኘውየEASTRIP ፕሮጀክት ተቋሙን learning factory እንዲሆንና በኮሌጁ እየሰለጠኑ የሚገኙ ሰልጣኞች ለኢንዱስትሪውን እና ለአካባቢውን ማህበረሰብ ግብአት መሆን የሚችሉ ሰልጣኞችን ማፍራት እንዲችል በርካታ ስራዎችን መስራት ተቸሏል ያሉ ሲሆን አያይዘውም መምህራንን በማብቃት እንዲሁም ለኢንዱስትሪዎች ግብአት መሆን የሚችሉ ስራዎችን በመስራት ለውጦችን ማምጣት እንድንችል አድርጎናል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም ንግግር ያደረጉት በIUCA የምስራቅ አፍሪካ የEASTRIP ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዩኒት መሪ የሆኑት ዶ/ር ኮሳም እንዳሉት የፍቅር ከተማ ወደሆነችው ድሬዳዋ ከተማ በመምጣቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ያሉ ሲሆን አያይዘውም በኮሌጁ እየተሰራ እና እየተጠናቀቀ የሚገኘው ይህ የልህቀት ማእከል ግንባታ ከዚህ በፊት ከነበረው አፈጻጸም በላቀ ሁኔታ ለፍጻሜ ደርሶ በመመልከቴ በጣም ደስታ ተሰምቶኛል ይህ ውጤት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩና የኮሌጁ ማኔጅመንት እንዲሁም የፕሮጀክቱ ሰራተኞች በጋራ በመስራት የመጣ ውጤት ነው ብለለዋል፡፡ ከአለም ባንክ፣ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ከIUCA የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የEASTRIP ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዩኒት እንዲሁም ከኬንያ እና ከታንዛኒያ የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች የልህቀት ማዕከሉን እና አጠቃላይ የኮሌጁን እንቅስቃሴ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከመስክ ጉብኝቱ በኋላ በአቶ መሳይ ጥላሁን በቀረበው አፈጻጸም ላይ ልኡክ ቡድኑ የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም በፕሮጀክቱ የስራ አፈጻጸም እጅግ እንዳስደመማቸው እና ለፕሮጀክቱ መሳካት እየተሰሩ ያሉ ድጋፎችን አድንቀዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ነሀሴ 05/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ ስለ ኮሌጁ ትኩስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት Facebook: facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute Telegram: t.me/diredawapolytechniccollege YouTube: youtube.com/diredawapolytechniccollege