ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 322
المشتركون
+124 ساعات
+77 أيام
+14530 أيام
أرشيف المشاركات

በአዲስ የተዘጋጁ ሀያ ሁለት ስርዓተ ትምህርቶች ላይ ክለሳ የማድረግ ስራ መጀመሩ ተገለጸ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሰልጣኝ ልማትና የተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት በአስተዳደሩ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን በማስተባበር የኢንተርፕርነርሺፕ እና ሀገር ወዳድነትና የስራ ላይ ስነ ምግባርን አካቶ በመጨመር የዘርፉን ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ የስርዓተ ትምህርቱን የመከለስ ስራ መጀመሩ ታውቋል። ለ2018 ዓ.ም የክህሎት ስልጠናውን በጥራት ለመስጠት እንዲቻል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት አራት አመታት በስርዓተ ትምህርቱ አተገባበር ሂደት ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን በመገምገም አዳዲስና ከዘመኑ ጋር የሚሄዱ አሰራሮችን የይዘትና የምስል መጣጣም ያለባቸውን ለማጣጣም ወደ ስራ መገባቱን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደን ተናግረዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+6

ለፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን የተዘጋጀ በተግባር የተደገፈ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በሁለቱም ኮሌጆች እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በአቅም ግንባታ ስልጠናው የኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራኑ ሙያዊ ብቃታቸውን የሚያሳድጉበትና ከዚህም ባሻገር በየሙያ መስኩ በየኢንዱስትሪው ተግባራዊ ዕውቀትና ክህሎት እያገኙበት እንደሆነና የተሻለ ልምድና ተሞክሮዎችን ከአቻዎቻቸው የሚቀስሙበትን ዕድል እንደፈጠረላቸው መድረክ አሰልጣኝ መምህራኑ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የአቅም ግንባታ ስልጠና የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ተሳታፊ ሲሆኑ ገበያው የሚፈልገውን ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ ለማፍራት የአሰልጣኞችን ብቃት ተከታታይነት ባለው መልኩ ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ በሁለቱም ኮሌጅ እየተሰጠ እንደሚገኝ በቢሮው የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+8

የ2018 የቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና የመግቢያ ነጥብ መሰረት በአስተዳደሩ ባሉ ሰባት የግልና የመንግስት ኮሌጆች ሰልጣኞችን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ። የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሞያ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በሰጡት መግለጫ የ2018 የቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና የመግቢያ ነጥብ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጹ ። ሀላፊዋ እንደገለጹት በ5 የግል ኮሌጆች እና በሁለቱ የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ከ4 ሺ በላይ አዳዲስ ተማሪዎችን ለማሰልጠን ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል:: ምዝገባውም ከጥቅምት 12 ጀምሮ ይካሄዳል። በመንግስት ኮሌጆች የሚገቡት በሁለቱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የሳይኮ ሜትሪክ ምዘና እና የባዮ ሜትሪክ ምዝገባ በማድረግ ሲሆን በተመሳሳይ ወደ ግል ኮሌጆች ለመግባት ደግሞ በወረዳ አንድ ማዕከላት የባዮ ሜትሪክ ምዝገባ በማድረግ የሌበር መታወቂያ በመያዝ መመዝገብ እንደሚችሉ ጠቅሰዋል ። በ2017 ዓ.ም አስራ ሁለተኛ ክፍል ያጠናቀቁና ከዚህ በፊት 12ተኛ ክፍል አጠናቀው ወደ ኮሌጅ ያልገቡ ተማሪዎች በቴክኒክና ሞያ የመግቢያ ነጥብ መስፈርት መሰረት መግባት እንደሚችሉም በመግለጫው ተጠቅሷል። የትምህርትና ስልጠናው በመንግሥት ኮሌጆች ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 እንዲሁም በደረጃ 6 ዲግሪ ፕሮግራም የሚሰጥ ሲሆን በግል ኮሌጆች ደግሞ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4 ድረስ ይሰጣል። ኃላፊዋ አክለው እንደገለጹትም አስተዳደሩ ከአጎራባች ክልሎች ሰልጣኝ ተማሪዎችን እንደሚቀብሉም ጠቁመዋል። ©️ DireTvአማርኛ | ጥቅምት 11፥2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ

photo content
+1

photo content

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከ4 መቶ 54 ሺህ 106 በላይ ዜጎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል ክቡር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የ2018 የትምህርትና ስልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለዜጎች ተግባራዊ እውቀትና ክህሎትን በማስታጠቅ የሥራ ፈጠራ አቅምና ችግር ፈቺ አስተሳሰቦችን ያለውን ቁልፍ ሚና በመገንዘብ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራበት ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎት ምላሽ መስጠት እንዲችል የሥራ ገበያውን መሰረት ያደረገ የክህሎት ልማት አቅጣጫ ነድፎ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በመደበኛና አጫጭር ስልጠና ተደራሽ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ መሠረት 2017 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤትን፣ የሥራ ገበያው ፍላጎት እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የቅበላ አቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት የ2018 የትምህርትና ስልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት መቀበያ መቁረጫ ነጥብን ይፋ አድርጓል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የመቁረጫ ነጥቡን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ባለፉት ሦስት ዓመታት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ከ1,500 ባላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በአካባቢያቸው ያለውን ተፈጥሯዊ ፀጋ መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲደራጁና ስልጠና እንዲሰጡ መደረጉን ክቡር ሚኒስትር ድኤታው አስታውቀዋል፡፡ የተቋማቱን የቅበላ አቅም ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ የውስጥና የዲጂታል መሰረተ ልማትን የማስፋፋት ሥራ ሲሠራ መቆየቱን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው በ2017 ዓ.ም በመደበኛ ከ5መቶ ሺ በላይ፣ በአጫጭር ስልጠና ደግሞ ከ4ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከ1መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ በልምድ የሙያ ባለቤት የሆኑ ዜጎች ተመዝነው ዕውቅና ማግኘታቸውን ብሎም ከ5መቶ ሺ የሚልቁ ደግሞ ለውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ብቁ የሚያደርጓቸውን ስልጠናዎች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት መከታተላቸው ተገልጿል፡፡ በ2018 የትምህርትና ስልጠና ዘመን 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ከ4መቶ 54ሺ1መቶ ስድስት የሚሆኑ ዜጎችን ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም ለማሰልጠን፣ 4ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች አጫጭር ስልጠና በመስጠት ለሀገር ውስጥ የሥራ መስኮች ለማብቃት እንዲሁም ቁጥራቸው እስከ 8መቶ ሺ የሚሆኑ ዜጎችን ደግሞ በስልጠና አብቅቶ ለውጭ ሀገር የሥራ ገበያ ዝግጁ ለማድረግ የሚያስችል ዕቅድ መያዙንም አስታውቀዋል፡፡ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: t.me/fdre_mols TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ “Gender based Violence code of conduct “ላይ ትኩረቱን ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞች አደረገ፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ወቅት ተገኝተው ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ኢ/ኤ/ቴ/ሽግግር ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ በንግግራቸውም የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሰፊ ስራ እንደሚሰራበት መጠን ከብዙ ባለ ድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት እንዲፈጠር ያደርጋል ስለሆነም በዚህ ዘርፍ ውስጥ ተሳታሲ የሆኑ አካላት ደግሞ በህግ አግባብ ስራቸውን መስራት እንዲችሉ መደላደል መፈጠር አለበት ያሉ ሲሆን ይህ በጀንደር ዩኒትና በEASTRIP ፕሮጀክት በኩል ተዘጋጅቶ የቀረበው code of conduct ደግሞ Gender based የሆኑ የViolence ችግሮች ቢፈጠሩ እነዚህን ችግሮች በምን አይነት መንገድ መፍታት ይቻላል የሚለውን የሚፈታ ነው ብለዋል፡፡ “Gender based Violence code of conduct “በጀንደር ዩኒትና በEASTRIP ፕሮጀክት በኩል በኮሌጁ በተቋቋመው የሪሰርች ቡድን ተጠንቶ የተዘጋጀ ሲሆን ሰነዱም ሙሉ በሙሉ ከከተማ አስተዳደሩ የሰራተኞች አዋጅ ጋር ተስማሚ ሆኑ የተዘጋጀ እንደሆነ በግንዛቤ ማስጨበጫ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ You tube: Dire Dawa Polytechnic College(DDPTC) Facebook: https://web.facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute Telegram: https://t.me/diredawapolytechniccollege TikTok: tiktok.com/@diredawapolytechnicollege

በኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ትግበራ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ:: በቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ ስራ ሂደት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ክፍል ስር ለሚሰሩ ነባር እና በአዲስ ለተመቡ አሰልጣኝ መ/ራን በትግበራው አፈፃፀምና በቀጣይ የስራ እንቅስቃሴ ላይ የግብዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል:: መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ የቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ ዋና ስራ ሂደት ሀላፊና ም/ል ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ በ2017 በጀት ዓመት በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ትግበራው በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ አመርቂ ስራ ለሰሩት ነባር ባለሙያዎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን አክለውም በ2018 በጀት ዓመት ለሚኖረው የኢ/ኤ/አ ትግበራ በቅንጅትና በጥራት ለማከናውን እንዲረዳን ይህን የግንዛቤ መድረክ ማዘጋጀት ማስፈለጉንም ገልፀዋል:: የግንዛቤ ስልጠናውን የኢዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ኬዝቲም ሀላፊ በሆኑት አሰልጣኝ መ/ር አቤል ዘገየ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የተሰጠ ሲሆን በዚህም የ4ቱ የትግበራ ማእቀፎች አተገባበርን በተመለከት ሰፋ ያለ ግንዛቤ መስጠት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም በ2018 በጀት ዓመት የኢ/ኤ/አ እቅድን በተመለከተ ከፈፃሚዎች ጋር መወያየት ተችሏል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥቅምት 06/2/2018 ዓ.ም

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአፍሪካ የICT ትምህርትና ስልጠና ልህቀት ማእከል ፕሮጀክት ጅማሮ ማብሰሪያ የመሰረት ድንጋይ በክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በዛሬው የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት ተካሄደ። ይህ በዛሬው እለት ግንባታውን ለማስጀመር የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠው የG+4 ICT ህንፃ ግንባታን በተቀመጠለት ግዜ በማጠናቀቅ ከተማችን የጀመረችውን “ስማርት ድሬ” ኢንሸቲቭ እውን ለማድረግ ብቁ የሰለጠነ ዜጋ በማቅረቡ ረገድ ሚናው የጎላ እንደሆነ በእለቱ ተነግሯል። ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ አጠቃላይ 3.3 ሚሊዮን ዩሮ የተመደበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ለግንባታው የሚፈጀው 2.3 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 384 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ 2 ሚሊዮን ዩሮ የሚሆነው በጀርመን ባንክ (kfw) ድጋፍ እና 300 ሺ ዩሮ የሚሆነው በአስተዳደሩ መዋጮ የሚሸፈን እንደሆነ በግንባታ ማስጀመሪያ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህንጻው በአጠቃላይ 42 ክፍሎች የያዘ ሲሆን በዋናነት ስማርት ክፍል፣ የኮምፕዩተር ላብራቶሪ፣ የምርምር ክፍል፣ መማሪያ ክፍል፣ የዲዛይን ስቱዲዮ፣ ኮንፈረንስ ክፍል፣ ዲጂታል ቤተ መጽሃፍት እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተገልጿል።ግንባታውን ለማጠናቀቅ 14 ወራትን እንደሚፈጅ ታውቋል። የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ You tube: Dire Dawa Polytechnic College(DDPTC) Facebook: https://web.facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute Telegram: https://t.me/diredawapolytechniccollege TikTok: tiktok.com/@diredawapolytechnicollege

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት ከተለያዩ ፋብሪካዎች ለተወጣጡ አሰሪና ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በማዘጋጀት በኢንዱስትሪ ሰላም፤ በስራ ሁኔታ እና በሙያ ደህንነትና ጤንነት ላይ ስልጠና ሰጠ። በዚህም ስልጠና በዋናነት መሰረታዊ የሥራ ሁኔታ በአሰሪና ሰራተኛው መሃል ያሉ ጠቅላላ ግንኙነቶች የሰራተኛውን የቅጥር ሁኔታ፣ የስራ ሰዓት እና የሰራተኛውን ጥቅማጥቅም የሚመለከቱ ጉዳዮች በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ 1156/2011 ላይ በተደነገገው መሠረት ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ህግና ስርዓታቸው ተከብሮ  የአሰሪና ሰራተኛው ግንኙነት ጤናማ የሚሆንበትና ሰላማዊ የስራ ከባቢ እንዲኖረው ግንዛቤ የሚፈጥርላቸው ሆኗል፡፡ በተጨማሪ የሥራ ቦታዎች ምቹ፣ ጤናማና ከአደጋ የተጠበቁ እንዲሆኑ በማስቻል  ምርታማነትን ከማረጋገጥ አኳያ ከሙያ ደህንነት እና ጤንነት አጠባበቅ አንፃር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በዚህም ለግንዛቤ ያክል የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ በተመለከተው መሰረት የሙያ ደህንነትና ጤንነትን በተመለከተ አሠሪዎች፡- 🔑 ሠራተኞች የሚሰሩት ሥራ ሊያስከትልባቸው ስለሚችለው አደጋ እንዲሁም በጤንነት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለማስወገድ ስለሚያስፈልገው ጥንቃቄ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ፣ 🔑 የአደጋ ተከላካይ ሠራተኛ ይመድባሉ፤ የሙያ ደኅንነትና ጤንነት ኮሚቴ ያቋቁማሉ፣ 🔑 ለሠራተኞች የአደጋ መከላከያ መሣሪያ ልብስና ሌሎች ቁሳቁሶችን ያቀርባሉ፤ ስለአጠቃቀሙም መመሪያ ይሰጣሉ፣ 🔑 በሥራ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችንና አደጋዎችን ይመዘግባሉ፤ ለሥራ ሁኔታዎች መቆጣጠሪያ አገልግሎት ያሳውቃሉ፣ 🔑 እንደሥራው ጠባይ አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች በራሳቸው ወጪ የጤና ምርመራ እንዲካሄድላቸው ያደርጋሉ፣ 🔑 በአደገኛ ሥራ ላይ የሚሰሩ ሠራተኞች እንደአስፈላጊነቱ የጤና ምርመራ እንዲያገኙ ያደርጋሉ፣ 🔑 ሆኖም ይህ ምርመራ ኢትዮጵያ ያፀደቀችው የዓለም አቀፍ ስምምነት ካላስገደደ በስተቀር የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ምርመራን አይጨምርም፤ 🔑 የድርጅቱ የሥራ ቦታና ግቢ በሠራተኞች ደኅንነትና ጤንነት ላይ አደጋ የማያስከትል መሆኑን ያረጋግጣሉ፣ 🔑 በድርጅቱ ልዩ ልዩ የሥራ ሂደት በሚገኙ ፊዚካላዊ፣ ኬሚካላዊ፣ ባዮሎጂካዊ፣ ኢርጎኖሚካዊና ሥነ ልቦናዊ ምንጮችና ምክንያቶች ሳቢያ በሠራተኞች ደኅንነትና ጤንነት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ተገቢውን ጥንቃቄ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡ በመሆኑም የሠራተኞችን የሙያ ደህንነትና ጤንነት በማረጋገጥ ጤናማ አምራች ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት በቢሮው የአሠሪና ሠራተኛ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢብራሂም ይህ ስልጠና በብዙ መልኩ አሠሪና ሠራተኛው አዋጁ ባስቀመጠው የሙያ ደህንነትና ጤንነት መብትና ግዴታቸውን ተረድተው የሚያከብሩበትንና የሚያስከብሩበትን ብሎም የጋራ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመውሰዳቸው በቀጣይ ደህንነትና ጤንነቱ የተጠበቀ ሙያተኛ፣  ምርታማና ሰላሙ የተጠበቀ ኢንዱስትሪ መፍጠር ያስችላቸዋል ብለዋል ፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መስከረም 6/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+5