Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 330
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+97 أيام
+8030 أيام
أرشيف المشاركات
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰሞኑን ይፋ ከተደረጉት ሁለት ተጨማሪ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት አካል የሆኑ አገልግሎቶች መካከል የሳይኮሜትሪክ ምዘና ለክህሎት ልማት (Psychometric for Skills Development) አንዱ ነው፡፡
....ለዘንድሮም እንዳለፉት ጊዜያት በወንድማማችነት በእህትማማችነት በፍቅር አንድነት አሸብርቀን፤ ከጨለማ_ወደ_ብርሃን ላሸጋገረን ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት የሀገራችን ድንቅ ውበትና የኦሮሞ ህዝብ ውብ ባህል ደምቆ ለሚታይበት ኢሬቻ (2017) በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!
አቶ ሮቤል ጌታቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የውጪ አገር ሥራ ስምሪትና የሰራተኞች ደህንነት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ለአሰሪና ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ።
የስልጠና መድረኩ የሥራ ቦታ ማህበራዊ ምክክር በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 በሕብረት ድርድር ዙሪያ ሲሆን በይበልጥ ትኩረቱን በሥራ ቦታ ማህበራዊ ምክክር ያደረገና በአሰሪና ሠራተኛ መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቀርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሥራ ቦታ ማሕበራዊ ምክክር የሚጫወተውን ሚና ለማስገንዘብ ያለመ ነው።
በዚህም አዋጁን በመረዳት የአሰሪውንና ሰራተኛውን ግንዛቤ ማሳደግ ዓላማው አድርጎ ከዚህ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪውን ሰላም በማረጋገጥ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚኖሩ አለመግባባቶችን በመቀነስ የስራ ክርክሮችን በምክክር መፍታት የሚያስችላቸው እንደሚሆን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ኢብራሂም ተናግረዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና ኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር በጋራ በመሆን ያቋቋሙት ሥራ ፈላጊ ለሆኑ ወጣቶች ዘላቂ የገቢ ማስገኛ የሆነውን ሀርላ ጋርመንት ፕሮጀክትን ለመደገፍ የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት ቦታ በአካል በመገኘት ጎበኙ።
በዚህም ጉብኝት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑት ወጣቶች ህይወታቸው ተቀይሮ ለሌሎችም ወጣቶች ምሳሌ የመሆን ህልማቸውን ለማሳካት ሰው ተኮር አገራዊ ተልዕኮ ይዞ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የሥራና ክህሎት ቢሮ የሚጠበቅበትን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና ኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር በጋራ በመሆን ሥራ ፈላጊ ለሆኑ ወጣቶች ዘላቂ የገቢ ማስገኛ የሆነውን ሀርላ ጋርመንት ፕሮጀክትን ለመደገፍ የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት ቦታ በአካል በመገኘት ጎበኙ።
በዚህም ጉብኝት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑት ወጣቶች ህይወታቸው ተቀይሮ ለሌሎችም ወጣቶች ምሳሌ የመሆን ህልማቸውን ለማሳካት ሰው ተኮር አገራዊ ተልዕኮ ይዞ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የሥራና ክህሎት ቢሮ የሚጠበቅበትን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ የሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ዝግጅታቸውን አጠናቀው የ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ ሰልጣኞችን ለመቀበል እየተጠባበቁ መሆኑን ገለጹ፤
ይህንንም የገለጹት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ስርአት ላይ የድጋፍና ክትትል በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ማለትም በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ላይ በተደረገበት ወቅት ነው፡፡
የድጋፍና ክትትሉ የቢሮው ባለሙያዎች በቼክሊስት በተደገፈ ኮሌጆቹ አዲሱን የዘርፉን ፖሊሲና ስትራቴጂ ትግበራ ለማሳካት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በተለይ በዝግጅት ምዕራፍ ለ2017 ነባርና አዳዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን በዕቅድ የሰሯቸው ዋናዋና ጉዳዮች ላይ ምልከታ ማድረግ ተችሏል፡፡
በመሆኑም ኮሌጆቹ በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ዕሳቤዎች መሰረት ሰልጣኞችን ለመቀበልና ዘርፉን ተመራጭ በሆነ መልኩ ዜጎችን ለማገልገል እንዲያስችል ታሳቢ ያደረገ የድጋፍና ክትትል መደረጉ ታውቋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 22/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በ2017 የሥራ ፈላጊዎች ምዝገባን እና "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ ማጠቃለያን አስመልክቶ ለከወረዳ ዋናና ምክትል ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የአንድ ማዕከል እና የቢሮው ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ።
በዚህም መድረክ ለተሳታፊዎች ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በአስተዳደሩ የተፈጠሩ ዕድሎችን በተለይም የኢንደስትሪዎች መስፋፋት ተከትሎ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎችን የአስተዳደሩ ሥራ ፈላጊዎች እንዲጠቀሙ የሥራ ፈላጊዎች ምዝገባው ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የቢሮ ኃላፊው አክለውም ዘንድሮ የሚከናወነው ምዝገባ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ https://lmis.gov.et መሆኑ ከዚህ በፊት የነበረውን አሰራር ያዘመነና ለሥራ ፈላጊዎች አለምዓቀፍ የሥራ አማራጮችን ያቀረበ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ሥራ ፈላጊዎች ተቀጥሮ መስራት ላይ ብቻ ሳይሆን በግልም ሆነ ተደራጅተው ሥራ እንዲፈጥሩ የሚያበረታቱ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ወደ አስተዳደሩ መምጣታቸውን አስታውሰው በዚህም የዕድሎቹ ተጠቃሚ ለመሆን ከመስከረም 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንዲመዘገቡ ጥሪ አድረገዋል።
በመሆኑም በአስተዳደሩ የሚገኙ የከተማ ወረዳዎች ስር የሚገኙ 19, 000 ሥራ ፈላጊ ዜጎችን መመዝገብ የታሰበ ሲሆን ተመዝጋቢ ሥራ ፈላጊዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የወረዳ አንድ ማዕከላት ቀርበው ምዝገባቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት አስቀድመው https://lmis.gov.et በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።
በመጨረሻም "ብቃት" የወጣቶች ሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ ማጠቃለያን አስመልክቶ እስካሁን የታየው አፈጻጸም ሁሉም አካላት በቅንጅት በመስራታቸው የተገኘ ውጤት መሆኑ ከየወረዳዎቹ ከቀረቡ ሪፖርቶች የተመላከተ ሲሆን በቀጣይም የሥራ ላይ ልምምድ ያደረጉ ወጣቶች ቅጥር እንዲፈጸምላቸው ትኩረት ሰጥተው ሁሉም አካላት እንዲሰሩ መግባባት መፍጠር ተችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 21/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በ2017 የሥራ ፈላጊዎች ምዝገባን እና "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ ማጠቃለያን አስመልክቶ ለከወረዳ ዋናና ምክትል ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የአንድ ማዕከል እና የቢሮው ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ።
በዚህም መድረክ ለተሳታፊዎች ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በአስተዳደሩ የተፈጠሩ ዕድሎችን በተለይም የኢንደስትሪዎች መስፋፋት ተከትሎ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎችን የአስተዳደሩ ሥራ ፈላጊዎች እንዲጠቀሙ የሥራ ፈላጊዎች ምዝገባው ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የቢሮ ኃላፊው አክለውም ዘንድሮ የሚከናወነው ምዝገባ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ https://lmis.gov.et መሆኑ ከዚህ በፊት የነበረውን አሰራር ያዘመነና ለሥራ ፈላጊዎች አለምዓቀፍ የሥራ አማራጮችን ያቀረበ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ሥራ ፈላጊዎች ተቀጥሮ መስራት ላይ ብቻ ሳይሆን በግልም ሆነ ተደራጅተው ሥራ እንዲፈጥሩ የሚያበረታቱ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ወደ አስተዳደሩ መምጣታቸውን አስታውሰው በዚህም የዕድሎቹ ተጠቃሚ ለመሆን ከመስከረም 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ አድረገዋል።
በመሆኑም በአስተዳደሩ የሚገኙ የከተማ ወረዳዎች ስር የሚገኙ 19, 000 ሥራ ፈላጊ ዜጎችን መመዝገብ የታሰበ ሲሆን ተመዝጋቢ ሥራ ፈላጊዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የወረዳ አንድ ማዕከላት ቀርበው ምዝገባቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት አስቀድመው https://lmis.gov.et በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።
በመጨረሻም "ብቃት" የወጣቶች ሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ ማጠቃለያን አስመልክቶ እስካሁን የታየው አፈጻጸም ሁሉም አካላት በቅንጅት በመስራታቸው የተገኘ ውጤት መሆኑ ከየወረዳዎቹ ከቀረቡ ሪፖርቶች የተመላከተ ሲሆን በቀጣይም የሥራ ላይ ልምምድ ያደረጉ ወጣቶች ቅጥር እንዲፈጸምላቸው ትኩረት ሰጥተው ሁሉም አካላት እንዲሰሩ መግባባት መፍጠር ተችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 21/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የውጪ አገር ስራ ስምሪትና የሰራተኞች ደህንነት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሚገኙ ከስድስት የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ለተወጣጡ ሰራተኞችና የሴፍቲ የኮሚቴ አባለት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በማዘጋጀት በሙያ ደህንነትና ጤንነት ላይ ስልጠና መስጠቱ ተገለጸ።
በቢሮው የውጭ አገር ስምሪትና የሰራተኞች ደህንነት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት በዋናነት የኢንደስትሪውን ሰራተኛ ደህንነትና ጤና የማስጠበቅ ሥራዎች ትኩረት የተሰጣቸው ሲሆኑ ይህም የኢንዱስትሪውን ምርታማነት በማሳደግ የኢንዱስትሪውን ሰላም በማረጋገጥ ረገድ የሚጫወተው ሚና ቀላል አለመሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ኢብራሂም ተናግረዋል።
በመሆኑም በአስተዳደሩ በሚገኙ ኢንደስትሪዎች የሙያ ደህንነትና ጤንነት ኮሚቴ አንዲደራጅና እንዲቋቋም ድጋፍ በማድረግ ለተመሰረቱት ኮሚቴዎችም በቀጣይ በሚያከናውኗቸው ሥራዎች በማስገንዘብ በተለይ የሙያ ደህንነቱና ጤናው የተጠበቀ የሥራ አካባቢን በመፍጠር የኢንደስትሪውን ሰላም እና ደህንነት በማስጠበቁ በተጨባጭም ውጤት እያስገኘ ይገኛል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 21/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ