Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 326
المشتركون
+224 ساعات
+87 أيام
+9730 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
+9
ወጣቶች የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ርብርብ ጉልህ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ተገለፀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ ዲፖርትመንቶች ለተወጣጡ ሰልጣኝ ተማሪዎች የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::
በመድረኩ ለሰልጣኞች መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ በንግግራቸው ይህን ስልጠና መስጠት ያስፈለገው በሀገራችን በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ የመጣው የቫይረሱን ስርጭት አስመልክቶ በተቋሙ ወጣት ሰልጣኝ ተማሪዎች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራት በማስፈለጉ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን አክለውም ሰልጣኞች የተፈጠረላቸውን ግንዛቤ በየአካባቢያቸው መረጃውን በማካፈል የተሻለ ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባልም ብለዋል::
በእለቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን ለሰልጣኞች የሰጡት አቶ ፈቲ መሀመድ የተዘጋጀውን ሰነድ ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም "የስሜት ብልህነት" በሚል ርዕስ ራስን ስለማወቅ እንዲሁም ራስን ስለመምራትና ስለመቆጣጠር ለመድረኩ ተሳታፊዎች ስልጠና ተሰጥቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 27/2017 ዓ.ም
ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው ድጋፍ ውጤታማነት እና ቀጣይነትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ ተቋማት ቅንጅትና ትብብር ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለጸ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ለጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ እየተሰጠ ያለውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በተመለከተ የሱፐርቪዥን ሪፖርት ድጋፉን ለሚያደርጉ አሰልጣኝ መምህራኖች በማቅረብ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
ዳይሬክቶሬቱ በተለያዩ ዘርፎች ለተደራጁ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ በዋናነት ኢንተርፕራይዞች ምርትና ምርታማነት እንዲጨምርና የስራ እድል እንዲፈጥሩ ማስቻል መሆኑን በመረዳት ከአሰልጣኝ መምህራኑ ጋር የጋራ ስምምነትና መግባባት በመፍጠር ውይይት ማካሄድ ተችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 26/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
እንኳን ደስ አላችሁ!!
#የድል_ዜና
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች በተሳተፉበት የቴክኖሎጂ ውድድር አሸናፊ ሆኑ::
በክልል/በአስተዳደር ደረጃ በተካሄደው የቴክኖሎጂ ውድድር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ወክለው የተወዳደሩ ቴክኖሎጂዎች ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቀቁ::
ለቴክኖሎጂ ጥራት መሻሻል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ታምኖበት በየሁለት አመቱ የሚዘጋጀው የቴክኖሎጂ ውድድር ዘንድሮም በደማቅ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን በክልል ደረጃ በሁለቱ ፖሊቴክኒኮች መካከል በተደረገው ውድድር ኮሌጃችንን ወክለው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች መሳተፍ የቻሉ ሲሆን ውድድሩንም በአሸናፊነት አጠናቀዋል::
በውድድሩ አጠቃላይ ውጤትም በኮሌጃችን አሰልጣኝ መምህራን የተሰሩ ቴክኖሎጂዎች 1ኛ እና 2ኛ በመውጣት ውድድሩን በፍፁም የበላይነትና አሸናፊነት ማጠናቀቅም ችለዋል::
በውድድሩ 1ኛ በመሆን ያሸነፈውና በኮሌጃችን አሰልጣኝ መ/ር ያሬድ ሁሉአለም አማካኝነት በሀገራችን የሚስተዋለውን የነዳጅ ችግር መነሻ በማድረግ የተሰራው ከእፅዋትና ከተለያዩ ግብአቶች የተመረተ የነዳጅ ዘይት የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል::
በውድድሩ 2ኛ በመሆን ያጠናቀቀው ደግሞ በኮሌጃችን አሰልጣኝ መ/ር ሲሳይ ምንዳ፣ አሰልጣኝ መ/ር አበበ ተረፈ እና አሰልጣኝ መ/ር ያሬድ ሁሉአለም የተሰራውና የአርሶ አደሩን ችግር በዘላቂነት የሚፈታ የእርሻ ማረሻ መሳሪያ ውድድሩን በ2ኛ ደረጃ አጠናቋል::
በተጨማሪም በውድድሩ ኮሌጁን ወክሎ የተወዳደረውና በአሰልጣኝ መምህር ግሩም ታምራት እንዲሁም አሰልጣኝ መምህር አበበ ተረፈ የተሰራው ዘመናዊ የእንቁላል ማስፈልፈያ ኢንኩቤተር በውድድሩ 5ኛ በመውጣት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብም ችሏል::
በዚህም መሰረት የውድድሩ አሸናፊ ቴክኖሎጂ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄድው የቴክኖሎጂ ውድድር ላይ አስተዳደራችንን ድሬዳዋን በመወከል በሚደረገው የቴክኖሎጂ ውድድር ላይ የሚሳተፍም ይሆናል::
በክልል ደረጃ ኮሌጃችንን በመወከል አሸናፊ የሆናችሁ የቴክኖሎጂ ባለቤቶች እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን እያልን በሀገር አቀፍ ደረጃ ድሬዳዋን ወክላችሁ የምታደርጉት ውድድርም በውጤት የታጀበ እንዲሆን ኮሌጁ መልካም ምኞቱን ይገልፃልም::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 26/2017 ዓ.ም
በድሬዳዋ አስተዳደር የተዘጋጀው፥ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድር ዛሬም ቀጥሎ ተካሄደ።
ይህ ውድድር በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ እንዲሁም በሳይንስ፥ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ነው።
የተለያዩ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማበልፀግ በአስተዳደሩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ፥ ይህ የፈጠራ ስራዎች ውድድር ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ይሆናል።
እየተካሄደ ባለው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድር ላይ ከአስተዳደሩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎችና መምህራን እየተካፈሉ ይገኛሉ።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 25/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
+5
#ዜና| የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በዛሬው እለት በቢሾፍቱ ተፈራረመ::
የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ በዋነኝነት ሁለቱ ተቋማት በምህንድስናው ዘርፍ ለሚያደርጉት ቀጣይ ግንኙነት መሰረት የሚጥል መሆኑን በዩኒቨርሲቲው በኩል የስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ረጋሳ ገልፀዋል፡፡
ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ አያይዘውም በቴክኖሎጂ እና ምህንድስናው ዘርፍ በጋራ የፈጠራ ስራን የሚያዳብሩ ትብብሮችን ስምምነቱ ከመፍጠሩ ባሻገር፤ የዩኒቨርሲቲው መምህራን የሰሯቸው የምርምር ስራ ውጤቶች ለፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ በአማራጭ ግብዓትነት እንዲቀርቡ የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ይህም ለሁለቱም ተቋማት የገበያ ትስስርን እንደሚፈጥርም ኮማንዳንቱ ጠቁመዋል፡፡
የኢንጅነሪንግ ኮሌጅ አዛዥ ኮሎኔል ኢዶሳ ቱፋ በበኩላቸው በኮሌጁ በምርምሩ ዘርፍ በርካታ የምርምር ስራዎችን ያበረከቱ መምህራን የሚገኙበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ በሁለቱ ተቋማት ያለውን ሀብት በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው ሲሉም አዛዡ አክለዋል፡፡
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኩል የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በጋራ ለመስራት ላሳየው መልካም ፈቃድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ተግባር ተኮር ለሆኑ የምህንድስና ዘርፍ የትምህርት መስኮች ዩኒቨርሲቲው አስተዋፆው የጎላ እንደሆነም የኮሌጁ ዲን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
እንኳን ደስ አላችሁ!!
በድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ በኩል በአስተዳደር ደረጃ ከተማ አስተዳደሩን ሊወክሉ የሚችሉ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፤
በዚህም ውድድር ላይ በተለይም በኮሌጆች ላይ በአሰልጠኝ መምህሩ የሚነሱ ጥያቄዎች እና በሰልጣኝ ተማሪዎች ላይ የሚስተዋሉ መፍትሄ የሚሹ ጉዳዮች ማለትም አውቶሜትድ የተማሪዎች አቴንዳንስ ማኔጅመንት ሲስተም፣ ከጤና እና ደህንነት አጠባበቅ፣ የቢዝነስ ፕላን ጥራትና ውጤት ማሻሻል፣ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ምርመራ(ቦሎ) እና የማህበረሰብ ድጋፍ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ጥናቶች ቀርበው ውድድር የተካሄደ ሲሆን በዚህም ውድድር የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን የወከሉት ተወዳዳሪዎች 1ኛ እና 2ኛ እንዲሁም 4ኛ ደረጃን በማግኘት ውድድሩን በአሸናፊነት ጨርሰዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በትናንትናው እለት ሲካሄድ በነበረው በከተማ አስተዳደር ደረጃ የከተማ አስተዳደሩን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ በተዘጋጀው የክህሎት ውድድር ኮሌጃችንን በመወከል የተሳተፉ ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ልቀው በመገኘት በአንደኛ ደረጃ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡ በዚህም የከተማ አስተዳደሩን በመወከል አዲስ አበባ በሚደረገው ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ይሆናል፡፡
ኮሌጁን በመወከል ይህን አመርቂ ውጤት ላመጡትና ውጤቱ እንዲመጣ ቀን ከሌት ለሰሩት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
የኮሌጁ ኮምኒከሽን
መጋቢት 24/2017 ዓ.ም
+9
በድሬዳዋ አስተዳደር ''የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች!'' ህዝባዊ የውይይት መድረክ በምስል።
Mariin Paanaalii Jijjiiramaa Ji'a Bitootessaa fi Abdii Boruu Mata-duree jedhuun Gaggeefamaa jiru suuraan
Madal halku dhig looga dhigay mudhihii isbedelka iyo rajooyinka ee ka curtay bisha cuur ama megabit aya lagu qabtay ismamulka Dir dhabe
የኩባንያ ውስጥ ስልጠና የኢንዱስትሪዎችን አቅም ከመገንባት ባሻገር በተቋማቱ መካከል መልካም ግንኙነትና ትብብርን ማጠናከሩ ተገለጸ፤
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴ/ሙያ/ት/ስ ኤጀንሲ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ከመንግስት ኮሌጆች ጋር በመተባበር የኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን የአሰራር፤ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን በመለየት በስራ ቦታቸው ላይ ለማብቃት የሚያስችል የኩባንያ ውስጥ ስልጠና መሰጠቱን አስታወቀ።
በዚህም በአስተዳደሩ ከሚገኙ ለትብብር ስልጠና መስጫነት በተመረጡ ኩባንያዎች በ3 የሙያ ዘርፎች ፤በማኑፋክቸሪንግ፤ ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ፤ እንዲሁም በአውቶሞቲቭ ዘርፎች በተመረጡ አሰልጣኞች በ4 ኩባንያዎች (ኒው ዌቭ ኢንዱስትሪያል ፒ ኤል ሲ፣ አርከን የጆንያ ፋብሪካ፣ ፍሬህይወት ጋራዥ፣ እንዲሁም አብሬ ጋራዥ) በድምሩ 60 ሰራተኞች ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በመለየት በስልጠና የማብቃት ስራ ተሰርቷል፡፡
የኩባንያ ውስጥ ስልጠና ዋና አላማ በኢንዱስትሪ ውስጥ ተሰማርተው የሚገኙ ባለሙያዎች በተሰማሩበት የስራ መስክ ያሉባቸውን የሙያ ክፍተት በመለየትና በማብቃት፤ የቴክኖሎጂ ክፈተቶችን በመሙላት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ሲሆን በተጨማሪም በትብብር ስልጠና ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጥራት ችግሮችን ከወዲሁ ለመፍታት ማስቻል ነው ሲሉ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጀማል አደን ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ ሲካሄድ የቆየው የክህሎት ውድድር ተጠናቀቀ፤
በአገር አቀፍ ደረጃ የክህሎት በዘርፉ ሰልጣኞች ዘንድ የውድድርና የተነሳሽነት መንፈስ ለመፍጠር የዘርፉን ገጽታ ለመገንባት ማስፈጸሚያ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ማዕከላት ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪ የሚያደርግ ምርጥ ቴክኖሎጂ በማቅረብና በማሽጋገር ምርታማ የሆነ ዜጋ በመፍጠር በአጠቃላይ የዘርፉን ተዋናዮች በማነቃቃት እና በገጽታ ግንባታ ረገድ የክህሎት ውድድር ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ በአስተዳደሩ የሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች፤ በክላስተር ደረጃ እንዲሁም በክልል ደረጃ አስተዳደሩን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎች የተለዩበት ሆኖ ተጠናቋል፤
በፌደራል ደረጃ ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የተለዩ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከሚያገኙት ማበረታቻ በተጨማሪ የአጠቃላይ አሸናፊዎች በአህጉር እና በአለምአቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ሀገርን ወክለው የመሳተፍ ዕድል እንደሚመቻች ተገልጿል፡፡
በውድድሩ ማጠናቀቂ የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ ውድድሩን ተመልክተው ተወዳዳሪ ሰልጣኞችንም ያበረታቱ ሲሆን በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች የተሰሩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
