ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

الذهاب إلى القناة على Telegram
1 331
المشتركون
+124 ساعات
+97 أيام
+8030 أيام
أرشيف المشاركات

ሁለተኛው ዙር ብቃት_የወጣቶች_የስራ_ላይ_ልምምድ_ፕሮጀክት ትግበራ የመጀመሪያ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት" ተጠቃሚ ለመሆን በአስተዳደሩ የወረዳ አንድ ማዕከላት የተመዘገቡ ወጣቶችን በዛሬው ዕለት  በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና  በኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና መስጠት ጀምሯል። በዛሬው ዕለት በኮሌጆቹ ስልጠናቸውን መውሰድ የጀመሩትም በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ወረዳ-1 አንድ ማዕከል፣ በወረዳ-2 ዋናው አንድ ማዕከል፣ በወረዳ-2 ቅርንጫፍ-1  አንድ ማዕከል እንዲሁም በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ በወረዳ-2 ቅርንጫፍ-2  አንድ ማዕከል፣ በወረዳ-4  አንድ ማዕከል የተመዘገቡ ስምንት መቶ ሰልጣኞች ናቸው። በዚህም ሰልጣኞች ስልጠና ከመጀመራችው በፊት አስፈላጊውን ኦሬንቴሽን የተሰጣቸው ሲሆን ስልጠናውን ለቀጣይ 10 ቀናት በኮሌጆቹ እየወሰዱ የሚቆዩ ይሆናል እንዲሁም ህፃናት ልጆች ያላቸው ሰልጣኞች ከስልጠናቸው እንዳይስተጓጎሉ በማሰብ በኮሌጆቹ የህፃናት ማቆያ በማዘጋጀት ሰልጣኞች ልጆቻቸውን አምጥተው እንዲያቆዩ መመቻቸቱን በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ተናግረዋል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት  ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

ሁለተኛው ዙር ብቃት_የወጣቶች_የስራ_ላይ_ልምምድ_ፕሮጀክት ትግበራ የመጀመሪያ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት" ተጠቃሚ ለመሆን በአስተዳደሩ የወረዳ አንድ ማዕከላት የተመዘገቡ ወጣቶችን በዛሬው ዕለት  በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና  በኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና መስጠት ጀምሯል። በዛሬው ዕለት በኮሌጆቹ ስልጠናቸውን መውሰድ የጀመሩትም በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ወረዳ-1 አንድ ማዕከል፣ በወረዳ-2 ዋናው አንድ ማዕከል፣ በወረዳ-2 ቅርንጫፍ-1  አንድ ማዕከል ሲሆን በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ በወረዳ-2 ቅርንጫፍ-2  አንድ ማዕከል፣ በወረዳ-4  አንድ ማዕከል የተመዘገቡ ስምንት መቶ ሰልጣኞች ናቸው። በዚህም ሰልጣኞች ስልጠና ከመጀመራችው በፊት አስፈላጊውን ኦሬንቴሽን የተሰጣቸው ሲሆን ስልጠናውን ለቀጣይ 10 ቀናት በኮሌጆቹ እየወሰዱ የሚቆዩ ይሆናል፤ እንዲሁም ህፃናት ልጆች ያላቸው ሰልጣኞች ከስልጠናቸው እንዳይስተጓጎሉ በማሰብ በኮሌጆቹ የህፃናት ማቆያ በማዘጋጀት ሰልጣኞች ልጆቻቸውን አምጥተው እንዲያቆዩ መመቻቸቱን በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ተናግረዋል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት  ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

photo content
+6

"አስተዳደሩ የክህሎት ልማቱ በአመራሩ የቅርብ ክትትልና አመራር ሰጪነት ለቀጣይ ውጤት አምጪ የኢንደስትሪ ኮሪደርነት ጉዞ መደላድል ለመፍጠርና ዜጎችን  ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ።" ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በድሬዳዋ አስተዳደር የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጉብኝትና  ድጋፍና ክትትል ማጠቃለያ መርሃግብር በዛሬው ዕለት ተደርጓል። ከመርሃግብሩ መጠናቀቅ በኋላ ክብርት ሚንስትሯ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በመገኘት በአጠቃላይ በክህሎት ልማት፣ በአሰሪና ሰራተኛ እንዲሁም በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ በምልከታ የታዩ እና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የአስተዳደራችን ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፣የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ ሻኪር አህመድ፣ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋን ጨምሮ የኮሌጅና የአንድ ማዕከላት አመራሮች በተገኙበት  ምክክር አድርገዋል፡፡ ክብርት ሚንስትሯ በአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር የሚመራው አመራር ባለፉት አመታት የአስተዳደሩን ገጽታ የቀየሩ ሥራዎች ምስጋና የሚቸራቸው መሆናቸውና በዚህም ውስጥ የሥራና ክህሎት ዘርፉን ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ የሚገባ መሆኑና እና በቀጣይ ጥራትና ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር በተለይ የአስተዳደሩን የገጠር ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ላይ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት  ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 15/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

"አስተዳደሩ የክህሎት ልማቱ በአመራሩ የቅርብ ክትትልና አመራር ሰጪነት ለቀጣይ ውጤት አምጪ የኢንደስትሪ ኮሪደርነት ጉዞ መደላድል ለመፍጠርና ዜጎችን  ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ።" ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በሐረሪ ክልል የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጉብኝትና  ድጋፍና ክትትል ማጠቃለያ መርሃግብር በዛሬው ዕለት ተደርጓል። ከመርሃግብሩ መጠናቀቅ በኋላ ክብርት ሚንስትሯ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በመገኘት በአጠቃላይ በክህሎት ልማት፣ በአሰሪና ሰራተኛ እንዲሁም በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ በምልከታ የታዩ እና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የአስተዳደራችን ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፣የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ ሻኪር አህመድ፣ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋን ጨምሮ የኮሌጅና የአንድ ማዕከላት አመራሮች በተገኙበት  ምክክር አድርገዋል፡፡ ክብርት ሚንስትሯ በአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር የሚመራው አመራር ባለፉት አመታት የአስተዳደሩን ገጽታ የቀየሩ ሥራዎች ምስጋና የሚቸራቸው መሆናቸውና በዚህም ውስጥ የሥራና ክህሎት ዘርፉን ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ የሚገባ መሆኑና እና በቀጣይ ጥራትና ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር በተለይ የአስተዳደሩን የገጠር ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ላይ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት  ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 15/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+6

በብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን በአስተዳደሩ የወረዳ አንድ ማዕከላት የተመዘገባችሁ ሰልጣኞች ከመጋቢት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና የምትወስዱ ሲሆን ሰኞ ከጠዋቱ 2:00  የምትጀምሩ ይሆናል። በዚህም 👉 በወረዳ-1 አንድ ማዕከል 👉 በወረዳ-2 ዋናው አንድ ማዕከል 👉 በወረዳ-2 ቅርንጫፍ-1  አንድ ማዕከል የተመዘገባችሁ ወጣቶች ስልጠናችሁ በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሲሆን፤ ---------------------------------------------------------- 👉 በወረዳ-2 ቅርንጫፍ-2  አንድ ማዕከል 👉 በወረዳ-4  አንድ ማዕከል የተመዘገባችሁ ደግሞ በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ተገኝታችሁ ስልጠናውን የምትወስዱ ይሆናል። ማሳሰቢያ፡- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ  እና 2 ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ እንድትገኙ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ

photo content

ኢ-መደበኛ አንቀሳቃሾችን ወደ መደበኛ ኢንተርፕራይዝ እንዲሸጋገሩ ከድሬ ብድርና ቁጠባ ጋር በመተባበር በቀጣይም ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ይህን የስልጠና መድረክ ለኢ-መደበኛ አንቀሳቃሾች ሲያዘጋጅ የሥራን ጠቀሜታ በመረዳትና ለሥራ ያላቸውን ተነሳሽነት በመጨመር የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት እንዲለውጡ አስፈላጊና ጠቃሚ የሆኑ መሠረታዊ የንግድ ክህሎቶች እንዲጨብጡ ታሳቢ ያደረገ ነው፤ የኢንተር ፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ከፈለኝ እንደገለጹት አንቀሳቃሾቹ ይህን ስልጠና ከወሰዱ በኋላ በሥራ ፈጠራና ሥራ ፈጣሪነት ላይ ግንዛቤያቸውን የሚጨምር ሲሆን በንግዱ ሙያ ውስጥ ውጤታማ ሊያደርጉ የሚያስችላቸውን ባህሪ በመላበስና ብቃቶችን እንዲገነዘቡ የሚያስችላቸው እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት  ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 14/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+6

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብርት ወ/ሮ ሙፈርሃት ካሚል  እና በከተማችን ክቡር ከንቲባ ከድር  ጁሀር  የተመራው የፌደራል እና የከተማችን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የሥራ ጉብኝት አካሂዷል። የሱፐቪዥኑ ቡድን በ ኮሌጁ ሲደርስ በኮሌጁ አመራሮች እንዲሁም ሠራተኞች ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በነበራቸው ቆይታም በተቋሙ የተከናወኑና እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ስራዎችን እንዲሁም በሰልጣኝ ተማሪዎች የተሰሩ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል:: በመሥክ ጉብኝቱ  መሠረት ልኡክ ቡድኑ በኮሌጁ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ የለዉጥ ስራዎች እንዲሁም በአስተዳደሩ ለኮሌጁ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በተጨማሪም የፕሮጀክት የማስፈጸም ተግባራቶች በሙሉ ለሌሎች እንደ ተሞክሮ የሚወሰድ ሲሆን ካለው አቅም አንጻር ከዚህ በላይ መስራት እንደሚጠበቅበት አቅጣጫ ተሠጥቷል:: ድሬዳዋ  ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 14/2016 ዓ.ም

photo content
+6

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብርት ወ/ሮ ሙፈርሃት ካሚል እና በከተማችን ክቡር ከንቲባ ክቡር ጁሀር የተመራው የፌደራል እና የከተማችን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በዛሬው ዕለ
+6
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብርት ወ/ሮ ሙፈርሃት ካሚል  እና በከተማችን ክቡር ከንቲባ ክቡር  ጁሀር  የተመራው የፌደራል እና የከተማችን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የሥራ ጉብኝት አካሂዷል። የሱፐቪዥኑ ቡድን በ ኮሌጁ ሲደርስ በኮሌጁ አመራሮች እንዲሁም ሠራተኞች ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በነበራቸው ቆይታም በተቋሙ የተከናወኑና እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ስራዎችን እንዲሁም በሰልጣኝ ተማሪዎች የተሰሩ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል:: በመሥክ ጉብኝቱ  መሠረት ልኡክ ቡድኑ በኮሌጁ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ የለዉጥ ስራዎች እንዲሁም በአስተዳደሩ ለኮሌጁ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በተጨማሪም የፕሮጀክት የማስፈጸም ተግባራቶች በሙሉ ለሌሎች እንደ ተሞክሮ የሚወሰድ ሲሆን ካለው አቅም አንጻር ከዚህ በላይ መስራት እንደሚጠበቅበት አቅጣጫ ተሠጥቷል:: ድሬዳዋ  ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 14/2016 ዓ.ም

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት ለኮሌጁ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ፣ EASTRIP GRM ኮሚቴ እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ማህበረሰብ ተወካዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። የግንዛቤ ማስጨበጫ
+5
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት ለኮሌጁ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ፣ EASTRIP GRM ኮሚቴ እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ማህበረሰብ ተወካዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የተሰጠው በፌዴራል 1ኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የተከበሩ አቶ ባይሳ ጅሩ ሲሆን የዚህ የኮሌጁ ማህበረሰብ ቅሬታዎች ከመነሻቸው እንዴት እንደሚፈቱ፣ ችግሮቹ ወደ ውጭ አካላት ከማደጉ በፊት በጊዜ በውስጥ አቅም በመጠቀም እንዴት መፍታት እንደሚቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዋና አላማዎች ሲሆኑ ሁሉም የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ከኮሌጁ ማህበረሰብ እና ከግንባታ ፕሮጀክት የሚነሱ ማናቸውንም ቅሬታዎች ለመፍታትና ለመቆጣጠር የአለም ባንክ ቅሬታ አፈታት መርሆዎችን ተከትሎ መፍታት እንዴት እንደሚቻል በስልጠናው ወቅት ለተሳታፊዎች ለማስገንዘብ ተችሏል ። በመዝጊያ መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የEASTRIP ፕሮጀክት አስተባባሪ ወ/ሪት አሽረፊያ አብዲ እንደተናገሩት ሁሉም ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ከባለድርሻ አካላት የሚነሱ ቅሬታዎችን ከኮሌጁ ቅሬታ እና የ EASTRIP GRM ኮሚቴ ጋር በጋራ ለመፍታት በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። የኮሌጁ ኮምኒኬሽን መጋቢት 13/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብርት ወ/ሮ ሙፈርሃት ካሚል የተመራው የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በዛሬው ዕለት በኮሌጃችን የመስክ ምልከታ አካሂዷል።     የሱፐቪዥኑ ቡድን በ ኮሌጁ ሲደርስ በኮሌጁ አመራሮች ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በነበራቸው ቆይታም በተቋሙ የተከናወኑና እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል:: ኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 13.2016 ዓ.ም

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች እና አመራሮች የግማሽ ምርጫ ዘመን የልማት የሰላምና መልካም አስተዳደር አፈጻጸምና የቀሪ ምርጫ ዘመን ቀጣይ አቅጣጫዎችን ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡ ለውይይት በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ባለፉት ሁለት አመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር መስራት፣ በንቅናቄ የተሰሩ ስራዎች ተፋሰስ፣ ስንዴ ልማት፣ የደንጊ እና የችኩጉኒያ ወረርሽኝ ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች፣ የጤና መድን ሽፋን ለማስፋት የተሰሩ፣ የክረምትና በጋ በጎ ፍቃድ ስራዎች፣ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገትና መዋቅራዊ ሽግግርን ያመላከቱ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡ በተለይ ከ30ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩ እና በሰላምና ጸጥታ ረገድ ወደ ከተማዋ በተለያዩ ዘርፎች በኢንቨስትመት ለመሰማራትም ሆነ ለተለያዩ ጉዳዩች ተመራጭ መሆኗና የታየው የኢኮኖሚ እድገትም በተሳታፊዎች ምስጋና የተቸረውና በዚሁ እንዲቀጥል የተጠየቀ ሲሆን ሌሎችም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በመድረክ መሪዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት  ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 12/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9