Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 326
المشتركون
+224 ساعات
+87 أيام
+9730 أيام
أرشيف المشاركات
”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” በሶስተኛው ዙር ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን ወደ ትግበራ ለማስገባት እንዲያስችል ለመልማይ እና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተዘጋጀ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በዚህ ዓመት ቀበሌዎች ለሚተገበረው ”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” ውስጥ መሳተፍ ያለባቸውን ወጣት የሆኑ ነዋሪዎችን በመምረጥ በኩል የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባበቡ መወጣት እንደሚገባቸው ከየቀበሌው ለተመረጡ መልማይና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ገለጻ ተደርጓል፡፡
በሁለተኛው ዙር ”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” ተግባራዊ ተደርጎ እንደ አስተዳደር የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል ከተጠቃሚዎች ምልመላ ጀምሮ የታዩ የአሰራር ክትተቶችን በማሻሻል ወደ ምዝገባ መገባቱ ይታወቃል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የጤና መምሪያ ስር የተደራጀው የምስራቅ እዝ ደረጃ-3 ሪፈራልና ማስተባበሪያ ሆስፒታል ውስጥ የተቋቋመው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማሰልጠኛ ኮሌጅ በአዲሱ የነርሲንግ ሙያ ላይ ከደረጃ ሶስት እስከ ደረጃ አራት መደበኛ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንዲሰጥ ለአንድ አመት የሚቆይ የምዝገባ ፈቃድ ከድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ተሰጠው፡፡
የምዝገባ ፈቃዱንም በቢሮው የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ በኩል ብ/ጀ ዶ/ር ሃይሉ ከፈኔ የጦር ሀይሎች ሆስፒታል አዛዥን ጨምሮ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሰርተፍኬቱን አበርክተዋል፡፡
ብ/ጀ ዶ/ር ሃይሉ ከፈኔ የምዝገባ ፈቃድ መሰጠቱን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ሰራዊቱ ከጊዜው ጋር የሚሄድ አቅምን እንዲፈጥር ከክህሎትና ቴክኖሎጂ ጋር ያለው መስተጋብር እያሳደገ መሄድ ይገባዋል ያሉ ሲሆን ለዚህም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እውቅና መሰጠቱ የሚኖረው ፋይዳ ቀላል አለመሆኑን አስረድተዋል።
አቶ ታሪኩ ለገሰ በበኩላቸው ማሰልጠኛው ፈቃድ እንዲሰጠው በጠየቀው መሠረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከግብዓት፤ ከሰውሃይል እና ስልጠናውን ለማካሄድ የሚያስፈልጉ ምቹ ሁኔታዎች መሟላታቸውን በማረጋገጥ ለአንድ አመት የሚቆይ የምዝገባ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል አፈጻጸም ታይቶም ከአንድ አመት በኋላ ለሶስት አመት የሚቆይ የዕውቅና ፈቃድ የሚሰጣቸው እንደሚሆን ገልጸዋል።
በተያያዘ የማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ወስደው ላጠናቀቁ አሰልጣኞች ሰርተፍኬት በተመሳሳይ የተበረከተ ሲሆን አጠቃላይ የኮሌጁን እንቅስቃሴ ተዘዋውረው በመጎብኘት በቀጣይም የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ የስልጠና ተቋሙን አቅም የሚያሳድጉ ተከታታይነት ያለውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 3/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የሥራና ሠራተኛ ማገናኛ ኤግዚብሽን(Job fair) ዝግጅት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ምክክር ተደረገ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት ይህን የምክክር መድረክ ሲያዘጋጅ የሥራና ሠራተኛ ማገናኛ ኤግዚብሽኖች አሰሪውና ስራ ፈላጊው በአንድ ቦታ የሚገናኙበትና ሥራ ፈላጊው አሰሪው ላቀረበው ክፍት የሥራ ቦታ የሚያመለክትበት ቀጣሪው ቃለመጠይቅ የሚያደርግበትን ሁኔታ ማመቻቸት ትኩረት እንደተሰጠው የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ኢብራሂም ተናግረዋል፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ተሳታፊ የሆኑ ባለድርሻ አካላት በአጠቃላይ ሥራ ፈላጊውና (job seekers) እና ቀጣሪዎች (Employers) በቀላሉ መገናኘት እንዲችሉ መንግሥት ከሚሰጣቸው የስራ ስምሪት አገልግሎቶች መካከል ሥራና ሰራተኛ ማገናኘት ኤግዚብሽን (Job fair) ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በማስተካከልና በመናበብ ሊሰሩ በሚችሉበት አግባብ ላይ በሰፊው ተወያይተዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 3/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የአሰልጣኝ ልማት ቡድን የAUTOMOTIVE ዘርፍ አሰልጣኝ መምህራን በMOENCO ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ላለፉት ሁለት ወራት የቆየው የኢንዱስትሪ ላይ ተግባራዊ ስልጠና ቆይታ ማጠቃለያ በቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ምልከታ ተደረገ፡፡
በምልከታው የካምፓኒው ኃላፊዎች እና አስተባባሪዎችም ለአሰልጣኞች ያላቸውን ክህሎት እያካፈሉ መቆየታቸውንና ይህ ግንኙነትም ከፍ ብሎ ለዘርፉ አጠናቃቂ ሰልጣኞች የስራ ዕድል ምችችት በር የከፈተ መሆኑን ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን ቢሮው ከኢንደስትሪው ጋር ያለውን ግንኙነት ለአሰልጣኝ መምህራን አቅም መገንባት እና ለአጠናቃቂ ሰልጣኞች የስራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ብቻ ሳይሆን በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዮች በተለይም ከሙያ ጤንነት እና ደህንነት አኳያ የተሰሩ ስራዎችን ተመልክተው በቀጣይ ተቋማቱ በትብብር በሚሰሩበት አግባብ ላይ ከካንፓኒው ኃላፊዎች ጋር መግባባት ፈጥረዋል፤
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 2/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+6
#ዜና| በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተለያዩ ዝግጅቶችን አጠናቆ ለውድድሩ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በዘንድሮ በጀት ዓመት ለ4ኛ ጊዜ ‹‹ ብሩህ አዕምሮዎች ፣በክህሎት የበቁ ዜጎች!››በሚል መሪ ሀሳብ ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቆ ወደ ተግባር ተሸጋግሯል ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ ዲኑ አያይዘውም ውድድሩ ለሀገር የሚተርፉ ዜጎችን ወደፊት ለማምጣት የሚጠቅም ነው። ይህ የክህሎት ውድድሩ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ወደ ተግባር በመለወጥ ሂደት የበቁ ዜጎችን ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል። ለውድድሩም የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ብቃታቸውን የሚያሳድጉ ስራዎችን ስንሰራ ቆይተናል ብለዋል፡፡
በአሰልጣኞችና ሰልጣኞች እንዲሁም ኢንተርፕራይዞች ኮሌጁን ብሎም የከተማ አስተዳደሩን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመለየት በኮሌጅ ደረጃ የተለያዩ ውድድሮችን ከመጋቢት 10 ጀምሮ መካሄድ እንደሚጀምር የገለጹት ደግሞ የኮሌጁ ም/ዲንና የኢ/ኤ/ቴ/ሽግግር ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ ወ/ሮ ትግስት አያይዘውም ይህ ውድድር በኮሌጁ በአሰልጣኞች እና ሰልጣኞች መካከል የፉክክር መንፈስ በመፍጠር እና ተወዳዳሪነታቸውን በማሳደግ በቀጣይ በከተማ እና በሀገር አቀፍ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል፡፡
መጋቢት 15/2017 ዓ.ም መካሄድ የሚጀምረው የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር በ6 የሙያ ዘርፎች በኮሌጅ ደረጃ በርካታ ሰልጣኞች እንደሚወዳደሩ ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 02/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት የስርዓተ-ፆታ እና አካታችነትን ለማሳደግ በተዘጋጀው ጥናት ላይ ከፑል አመራር አባላትና ሴት አሰልጣኝ መምህራን ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ::
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት በቅድሚያ በአለም አቅፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ ለሚከበረው የሴቶች ቀን(March 8) እንኳን አደረሳችሁ ያሉ ሲሆኑ በዚህ ቀን ስርዓተ-ፆታን በኮሌጃችን ለማዳበር በተዘጋጀ ጥናት ላይ ውይይት ማድረጋችን ቀኑን ልዩ ያደርገዋልም ብለዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም በተቋማችን በስርዓተ-ፆታ እና በአካታችነት በርካታ ፍላጎቶች መኖራቸውን አስታውሰው ከዚህ ቀደም የተወሰኑ ስራዎች ቢሰሩም በሚነሱት ፍላጎቶች ልክ በአግባቡ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ እንዳልነበሩ ጠቅሰው በዚህም በስርዓተ ፆታ እና አካታችነት ላይ መስራት በሚገባን መጠን ለመንቀሳቀስ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አድርጎ መነሻ የሚሆን መመሪያ ማዘጋጀት አስፈልጏልም ብለዋል::
በተጨማሪም በሁለቱ ጉዳዮች ላይ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ለማድረግ በተመረጡ ቡድኖች አማካኝነት ጥናቱ ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው በዛሬው እለትም የጥናት ቡድኑ የደረሰበት በመድረኩ አቅርቦ በቀረበው ጥናት ላይ አስተያየት እንዲሰጥበትና መካተት የሚገባቸውን ጉዳዮች ማካተት እንዲቻል የተዘጋጀ መድረክም ነው ብለዋል::
የስርዓተ ፆታ እና እካታችነትን ለማሳደግ በEASE ፕሮጀክት በቀጣይ 5አመት ውስጥ ለሚኖረው ትግበራ መነሻ ሚሆነውን መመሪያ ለማዘጋጀት የተደረገውን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አዘጋጆቹ የደረሱበትን ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን በቅድሚያ በአካታችነት ላይ የተደረገውን የፍላጎት ዳሰሳ በአሰልጣኝ መምህር ዮናስ ሙሉጌታ ለተሳታፊዎች ቀርቦ በጥናቱ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ እንደ ተቋም የተለዩ ክፍተቶችን በዝርዝር አመላክቷል::
ቀጥሎም በስርዓተ-ፆታ ላይ የተዘጋጀውን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በወ/ሮ ራሄል እሸቱ እና ኢንጂነር ህይወት እሸቱ አማካኝነት ለመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በቀረበው ጥናትም በስራ እካባቢ ለሴቶች የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች የማሟላት ክፍተት፣ ስርዓተ ፆታ ላይ በቂ ግንዛቤ ለኮሌጁ ሰራተኞች አለመፍጠር፣ ሴቶችን የማበረታታትና ወደ አመራርነት እንዲመጡ ተገቢውን ድጋፍ ያለማድረግ እንዲሁም የማማከር አገልግሎት ሚያገኙበት አግባብ ያለመኖሩ የሚሉት በጥናቱ ከተገለፁት ውስጥ ተጠቃሽ ነጥቦችም ነበሩ::
በመጨረሻም በቀረቡት ጥናቶች መነሻነት ከተሳታፊዎ በርከት ያሉ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት የተደረገበት ሲሆን ጥናቱንም ለማዳበር ተጨማሪ ግብአቶች የተገኙበት መድረክም ነበር::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
የካቲት 29/2017 ዓ.ም
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ዋና ስራ ሂደት በተቋሙ ከሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ::
የውይይት መድረኩ የመሩት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ በንግግራቸው እንደግለፁት በአካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት የትምህርትና ስልጠናው የመጀመሪያ ተርም ተጠናቆ ሁለተኛውን ተርም ምንጀምርበት ወቅት ላይ እንደመሆናችን የነበሩ ክፍተቶችን በሚገባ ለይቶ መፍትሄ ለማበጀትና በሁለተኛው ተርም ላይ በድጋሚ እንዳይስተዋሉ ለማድረግ ይህ የውይይት መድረክ አስፈልጎናልም ብለዋል::
ም/ዲኑ አክለውም ቀደም ብለው ከአካዳሚክ አባላት ጋር ተመሳሳይ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውሰው ከዛ በተገኘው ግብዓት መነሻነት እንዲሁም ከአሰልጣኝ መምህሩ የሚነሱ ሀሳቦችንም ጨምሮ በመወያየትና መፍትሄዎችንም በማስቀመጥ ለሁለተኛው ተርም በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም ገልፀዋል::
በመድረኩ ተሳታፊ ከነበሩት አሰልጣኝ መምህራንም የትምህርትና ስልጠና ሂደቱን አስመልክቶ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን ከተነሱት ሀሳቦች ውስጥም የትምህርትና ስልጠና ማቴሪያል ውስንነት፣ ከትብብር ስልጠና ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንዲሁም በምሽት ስልጠና ላይ ያልተመጣጠነ የመምህራን ክፍያ ችግርን ጨምሮ ትምህርትና ስልጠናውን ውጤታማ እንዳይሆን መንስኤ ናቸው ያሏቸውን በርካታ ክፍተቶችን በመጥቀስና አያይዘውም የመፍትሄ ሀሳብ ይሆናሉ ያሏቸውንም በመድረኩ አቅርበዋል::
በመጨረሻም አጠቃላይ ከመድረኩ በተነሱ ሀሳቦች ላይ ውይይት በማድረግ እንዲሁም ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸው መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
የካቲት 28/2017 ዓ.ም
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሴት አመራሮችና ሰራተኞች ዘንድሮ በዓለም ለ114ኛ በሃገራችን ለ49ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው ዓለማቀፉ የሴቶች ቀንን "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ-ግብሮች አከበሩ፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በዓሉን ስናከብር የሴቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በመስራት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ አክለውም የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆኑን ጠቅሰው የሴቶችን ቀን በዓመት 1 ቀን ከማክበር ባሻገር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ቀኑን አስመልክቶም የመወያያ ሰነድ በወ/ሮ ማርታ በዛብህ የሴቶች ወጣቶችና ኤች አይ ቪ ኤድስ ባለሙያ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 28/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+5
#ዜና|የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ እና ተደራሽ እንዲሁም አካታች የሆነ ተቋም እንዲሆን እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአካል ጉዳተኞች መልካም መደላድልን ለመፍጠር ያለመ ለኮሌጁ ትምህርት ክፍል ተጠሪዎች እንዲሁም ለተለያዩ የኮሌጁ ሰራተኞች ለ10 ቀን የሚቆይ ስልጠና ተጀመረ፡፡
በሃገራችን ከሚገኙ ኮሌጆች መካከል ሁሉን አካታች ኮሌጅ የሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው ያሉት በስልጠናው ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ም/ዲንና የኢ/ኤ/ቴ/ሽግግር ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ አያይዘውም ኮሌጃችን የህብረተሰባችን ክፍል የሆኑ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰልጣኞችን ተቀብሎ እንደማሰልጠኑ መጠን መልካም መደላደል ለአካል ጉዳተኞች መፍተር ይኖርብናል ይህንንም መልካም መደላደል ለመፍጠር ደግሞ አካታች የሆኑ እቅዶችን በማዘጋጀትና ምቹ የስልጠና ቦታዎችን በማመቻቸት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት የተጀመረው ስልጠና ለሁሉም የኮሌጁ አካላት በቀጣይነት የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናው ሲጠናቀቅ ደግሞ አካል ጉዳት ያለባቸው ሰልጣኞችን ያለ አስተርጓሚ ስልጠናቸውን በጥራት እንዲከታተሉ ያስችላል ያሉት ደግሞ የኮሌጁ ልዩ ፍላጎት አስተባባሪ አቶ መሰለ ወ/ጊዮርጊስ ናቸው፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት 28/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
በአስተዳደሩ የገጠር አራቱም ክላስተሮች ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የመስክ ምልከታና ልየታ መደረግ ጀመረ።
በዛሬው ዕለትም በቢዮአዋሌ ክላስተር የተለዩ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምልከታ የተደረገ ሲሆን ቀሪ የአስተዳደሩ ገጠር ክላስተሮች ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች በተመሳሳይ ምልከታ እና ልየታ የሚደረግ ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 26/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
