ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 321
المشتركون
+224 ساعات
+87 أيام
+15130 أيام
أرشيف المشاركات
በድሬዳዋ አስተዳደር ከስደት ተመላሽ ወገኖችን እንዲሁም ወጣቶችን በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ ወደ ስራ የማስገባት ተግባር በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ ኢ
+9
በድሬዳዋ አስተዳደር ከስደት ተመላሽ ወገኖችን እንዲሁም ወጣቶችን በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ ወደ ስራ የማስገባት ተግባር በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ ኢሮፒያን ዩኒየን፣ ከእንግሊዝና ከስዊድን ኤንባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ፅህፈት ቤት የተውጣጣ ልዑካን ቡድን ከስደት ተመላሾችን መልሶ የማቋቋም አቅምን የማሳደግ ስራዎች ላይ ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር ምክክር አድርጓል። በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ስደተኛ እና ከስደት ተመላሽ ወገኞች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ እንዲሁም ስደትን በዘላቂነት ከመከላከል አኳያ በአስተዳደሩ አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ በአካባቢው የሚገኙ ወጣቶችን በእውቀትና በክህሎት የዳበሩ እንዲሆኑ የተለያዩ ሞያዎችን በማሰልጠን ከራ አልፎ ለሃገር የሚተርፍ ስራ እያከናወነ እንዳለ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል። በአስተዳደሩ እንደሁም በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ልኡክ ቡድኑ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ተዘዋውሮ ከጎበኙ በኋላ ወጣቶችን ከጠባቂነት መንፈስ ተላቀው ተወዳዳሪና ክህሎት ያለው ትውልድ እንዲሆን ብሎም የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ኢንተርፕራይዝ እንዲሆኑና በሚያገኙት ገቢም የተሸለ ነግር መፍጠር እንዲችሉ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እየተሰራ ያለው ስራ እጅግ የሚያረካና በሀገር አቀፍ ደረጃም በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን የልኡክ ቡድኑ አባላት ገልፀዋል። የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥር 27/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሰልጣኝ ልማትና የተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የአጫጭር ስልጠና እና የምዘና መሳሪያዎች ክለሳ እንዲሁም በመሰረታዊ ክህሎት ሞጁሎች ላይ ከኮሌጅ ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ፤ በዚህም መሰረት ከሁለቱ የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የተውጣጡ የዲፓርትመንት ተጠሪዎችና የስልጠና ባለሙያዎች ስራዎችን በመገምገምና ያጋጠሙ ችግሮችን በመንቀስ መሻሻል ያለባቸውን በመከለስና ተጨማሪ ቨርዥኖች ለማዘጋጀት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ መድረክ አድርገዋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኮሌጆች/ተቋማት ከዘመናዊ የኢንዱስትሪ ፍላጎቶች ጋር እንዲናበቡ በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማቀናጀት ለወደፊት የኢዱስትሪው ፍላጎትን የሚያሟሉ ምሩቃንን በጥራት በማዘጋጀት ለገበያው በማቅረብ ስራ አጥነትን ለመቀነስ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የተቋም ውስጥ የምዘና መሳሪያዎችን ባለፈው አመት አዘጋጅቶ በስራ ላይ ማዋሉን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደን አስታውሰዋል። በተጨማሪም በፌደራል ደረጃ የተዘጋጁ 5 የመሰረታዊ ክህሎት ሞጅሎች አስፈላጊነት ላይ ወቅቱን የጠበቀ ስለመሆኑ ውይይት በማደረግ ለማውረድም ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንደሚሰሩ እና አሰልጣኞችን የማብቃት ስራዎች በቀጣይ ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን አቶ ጀማል ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 26/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+8

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞችን በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች የበቁ እንዲሆኑ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ስር ላሉ የፖሊስ አባላት ሶስተኛ ዙር በመሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና በዛሬው እለት መስጠት ጀመረ፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪያ እለት በመገኘት ስልጠናውን ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም እንኳን ወደ ሁለተኛ ተቋማችሁ ወደሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን ኮሌጁ በሁሉም ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞችን ለማብቃት በርካታ የአጫጭር ስልጠናዎችን እንዲሁም ከ12 በላይ ትምህርት ክፍሎች የተለያዩ የሞያ ትምህርቶችን አዘጋጅቶ እየሰጠ ይገኛል ያሉ ሲሆን አያይዘውም የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ ቀደም ከስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ እንዲሁም ከኮሌጃችን ጋር ባለ መልካም ግንኙነት አብሮ ለመስራት ኮሌጁ ቁርጠኛ ነው፡፡የፖሊስ አባላቱንም በአዳዲስ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የበቁ እንዲሆኑ በጋራ ከጠቅላይ መምሪያው የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት የስራ መመሪያ ያስተላለፉት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የፖሊስ አካዳሚ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ጌታቸው መገርሳ እንዳሉት የፖሊስ አባሎቻችንን የቴክኖሎጂ ችሎታቸውን ለማዳበር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ያሉ ሲሆን አያይዘውም ይህንን ስራችንን ደግሞ ወደ ተግባር እንድንቀይር ትልቁን ድርሻ የሚወስደው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ ስልጠና መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱት የኮሌጁ እንዲሁ የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊዎችን አመስግነዋል፡፡ በመጨረሻም ስልጠና የሚወስዱ የፖሊስ አባላት ስልጠናውን በአግባቡ በመውሰድ የሰለጠኑትን ሙያ በመጠቀም ተቋማቸውን ሊያገለግሉ ይገባል ብለዋል፡፡ ኮሌጁ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዙር ከ127 በላይ ሰልጣኞችን በመሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና ያሰለጠነ ሲሆን ዛሬ በተጀመረው የሶስተኛ ዙር ስልጠና ከ60 በላይ የፖሊስ አባላት ስልጠናን እንደሚወስዱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥር 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

#ዜና | የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ ክህሎት መር የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ #DGC | ጥር 24/2018 ዓ.ም የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ በ 100 ቀናት ዕቅድ በምግብ ዋስትና እና በምርት ዘርፍ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ገልጸዋል። በዶሮ እርባታ፣ በማር ምርት እና በመንገድ ዳር ፈጣን ምግቦች (Street Food) ዝግጅት ላይ የሚሰማሩ አምስት ማህበራት መደራጀታቸውን አቶ ሮቤል አመላክተው በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አማካኝነት ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች፣ የዶሮ ቤቶች፣ የዶሮ መኖ ማቀነባበሪያ ማሽኖች እና የከተማዋን ውበት በሚመጥን ሁኔታ ዘመናዊ የጎዳና ላይ ምግብ መሸጫ ጋሪዎች በፈጠራ ዘምነውና እርስ በርስ ተመጋጋቢነት እንዲኖራቸው ተደርገው መሰራታቸውን ጠቁመዋል። ዘመናዊ የንብ ቀፎ በወጣቶች ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከግብርና ውሃ መአድንና ኢነርጂ ቢሮ ጋር በመሆን የሚያከፋፍል መሆኑንም አቶ ሮቤል ተናግረዋል። አቶ ሮቤል አያይዘውም ቢሮው በከተማ እርስ በርስ ተመጋጋቢ የሆኑ ሶስት እንዲሁም በገጠር ሁለት በድምሩ አምስት አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን ስራ በማስጀመር የስራ አጥነትን ቁጥር መቀነስን ትኩረት ያደረገ ስራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ያብራሩ ሲሆን ኢንተርፕራይዞቹ የሚጠቀሙባቸው ማሽነሪዎችና የፈጠራ ውጤቶች በቢሮው ስር ባሉት ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በራስ አቅም ፈጠራ ታክሎባቸው የተመረቱ መሆናቸውን አመላክተዋል። ቢሮው በስሩ የሚገኙ ሁለት የመንግስት ኮሌጆችና ስድስት የግል ኮሌጆች ውስጥ የሚሰሩ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ አርባ ስድስት ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸው በቢሮውም ሆነ በኮሌጆቹ አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ ተገልጋዮች የፋይዳ መታወቂያ መያዝ እንደሚገባቸው አመላክተዋል። በሌላ በኩል፣ የቴክኖሎጂ ክህሎትን ለማሳደግ እየተተገበረ ባለው የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) ፕሮግራም፤ በኢትዮ-ጣልያን እና በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሚገኙ ሰራተኞችና ተማሪዎችን ጨምሮ 2,600 ሰዎችን ለማሰልጠን ታቅዶ እስካሁን ከ2,500 በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ አቶ ሮቤል ተጠቁመዋል በከበደ ካሳ ፎቶ፦ ቴድሮስ ልዑልሰገድ

ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ እንደሚያስቀጣ ያውቃሉ?  *** ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ ያስቀጣል። ታዲያ ለገበያ ምን ይዘን እንውጣ? ከቤትዎ ሲወጡ የጨርቅ ከረጢት ወይም ዘላቂ የሆኑ የሸመታ ከረጢቶችን መያዝዎን ያረጋግጡ። ይህ አዲስ መመሪያ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ትልቅ እርምጃ ነው። የፕላስቲክ ከረጢቶች በአካባቢ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት የሚደነቅ ቢሆንም፣ የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ፍላጎት ለማሟላት በቂ ተኪ ምርቶች ተዘጋጅተው ይሆን? በዚህ ጉዳይ  ምላሽ የሰጡት በፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የከተማ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ክትትል ዴስክ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን አለሙ እንደገለጹት ፤ መንግሥት እና የግል ባለሀብቶች ፕላስቲክ ከረጢትን ተኪ ምርቶች ላይ እየሰሩ ስለመሆናቸው ነው ከኢቢሲ ዶት ስትሪም ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሱት ። ያቀረቧቸውን ነጥቦች መሠረት በማድረግ፣ ስለ ተኪ ምርቶቹ እና ስለ ሕጉ አፈጻጸም ዝርዝር መረጃዎችን በሚከተለው መልኩ ማጠቃለል ይቻላል፦ ✅ ከጥጥ ጨርቅ የሚሰሩ ከረጢቶች፦ እነዚህ ከረጢቶች ታጥበው ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ በመሆናቸው ለዘላቂነት ተመራጭ ናቸው። ✅ ከካኪ (ወረቀት) የሚሰሩ ምርቶች፦ በተለይ ለደረቅ ዕቃዎች እና ለምግብ ነክ ግብይቶች ውጤታማ ናቸው። ✅ የማምረት አቅም፦ በአሁኑ ወቅት ሶስት ትላልቅ ተቋማት በቀን እስከ 55,000 የሚደርሱ የጨርቅ ከረጢቶችን እያመረቱ ሲሆን፣ በርካታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም በስፋት እየተሳተፉ ይገኛሉ። የመንግሥት ድጋፍ እና ማበረታቻ ሕጉን ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት የሚከተሉትን ማበረታቻዎች እያቀረበ ይገኛል፦ ✅ከቀረጥ ነፃ መብት፦ ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ ማሽኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከቀረጥ ነፃ መብት ተሰጥቷል። የፋይናንስ ድጋፍ፦ አምራቾች ካፒታል እንዲያገኙ ከባንኮች እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር የውይይት መድረኮች ተመቻችተዋል። ጥሬ ዕቃ፦ ምንም እንኳን በጥሬ ዕቃ ላይ የተወሰነ ቀረጥ ቢኖርም፣ ምርቱን ለማሳደግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። ✅ሊታረሙ የሚገባቸው የተሳሳቱ አመለካከቶች ባለሙያው እንደገለጹት፣ "ያልተሸመነ ጨርቅ" (Non-woven fabric) ከፕላስቲክ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው እና ለረጅም ጊዜ ስለማያገለግል፣ አምራቾችም ሆኑ ሸማቾች ከዚህ ምርት ይልቅ ዘላቂ የሆኑ የጨርቅ ከረጢቶችን እንዲጠቀሙ ይመከራል። ✅የሸማቹ ሚና ሕጉ ውጤታማ እንዲሆን የሸማቹ ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ✅ከቤት ይዞ መውጣት፦ እያንዳንዱ ሸማች ለገበያ ሲወጣ የራሱን ዘላቂ ከረጢት (Reusable bag) የመያዝ ልምድ ማዳበር ይኖርበታል። ✅ግንዛቤ፦ ፕላስቲክ የሚያስከትለውን የጤና እና የአካባቢ ጉዳት በመገንዘብ ሕጉን ማክበር።

photo content
+4

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ብልጽግና ህብረት አባላት በልሳነ ብልጽግና ቅፅ 1 ቁጥር 7 መጽሔት ይዘቶችና ጠንካራ አደረጃጀት ለተሳካ ምርጫ በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ተወያዩ፡፡ በልሳነ ብልፅግና መጽሔት የተዳሰሱ ዋናዋና ነጥቦች 1, ዲሞክራሲያዊነት እና ምርጫ እሳቤያዊ ተቃርኖዎች እና የፓርቲያችን ማስታረቂያ መንገዶች። 2, ካለፉት ምርጫዎች የሚቀሰሙ ትምህርቶች ። 3, የ7ኛ ሀገራዊ ምርጫ አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች ። 4, የምርጫ ግቦቻችን እና የአመራርና አባላት ሚና ሲሆን። በአጠቃላይ በመጽሔቱ ላይ እና ጠንካራ አደረጃጀት ለተሳካ ምርጫ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን አባሉ በመጪው 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ላይ በንቃት እንዲሳተፍና ኃላፊነቱን እንዲወጣ አቅም የሚፈጥርለት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 22/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9