መርጌታ አይነኩሉ 🇪🇹
الذهاب إلى القناة على Telegram
ለእያንዳንዱ ችግሮቻቹ መፍትሔ የምታገኙበት የጥበብ ቻናል ነው🇪🇹 ይደውሉልን ያማክሩን
إظهار المزيد1 977
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+147 أيام
+3330 أيام
أرشيف المشاركات
1 977
ለጥንቃቄ‼️
አንዳንድ ሰዎች
❓ "መምህር መንፈስ ጋር መዋረስ እፈልጋለሁ ስንት ብር ነው? "
"❓መምህር ከዚህ ቀደም ይህን ያህል ገንዘብ ለሆነ መሪጌታ ከፍዬ ያወረሰኝ መንፈስ ምንም እየሰራልኝ አይደለም።"
"❓መምህር የተዋረስኩት መንፈስ ጭራሽ አልታዘዝም አለኝ ይልቁስ እየተጋጨኝ ነው ምን ላድርግ?"
❓"መምህር የፈለኩትን የሚያረግልኝ መንፈስ ማግኘት መዋረስ እፈልጋለሁ ስንት ነው ዋጋህ ንገረኝ።"
"❓መምህር መንፈስን እንደፈለኩኝ እያዘዝኩት ነገርን ሁሉ እንዲያደርግልኝ እፈልጋለሁ በተለይ ገንዘብን ስለዚህ ሰው ገለህ እንኳን አምጣ የሚል ቢሆን አደርጋለሁ ነገር ግን አሁን ገንዘብ መክፈል አልችልም እባክህ እርዳኝ"
..... ይህንና የመሳሰሉትን ጥያቄ ከሰው ልጅ ከራሴ ወገን ስሰማ እውነት እላችሗለሁ ምን ዓይነት መታወር እና በምን ዓይነት ጭካኔ ክህደት ውስጥ የሰው ልጅ ነፍሱን በአንድ ዕቃ እንደሚለውጥና ሳይሞት የተፈረደበት የበዛበት ዓለም ውስጥ እንዳለን ያስታውሰኛል።
በመጀመሪያ ደረጃ ትልቁ ስህተት መናፍስትን ገንዘብ ብቻ ስለከፈልክ ወይም እንስሳ ስላረድክ ይዋረሰኛል ይታዘዘኛል ብሎ የሚያስብ ከቂል በላይ እራሱ የተሸጠ ያለቀለት መሆኑን አለመረዳቱ ነው። መናፍስት አንተ ወይም አንቺ የፈለጋችሁትን ከፍተኛ ብር ስለከፈላቹ በእውነት ተዋርሰው ከሚያገለግሏችሁ ይልቅ ሞኝነታችሁን ተጠቅመው በራሳችሁ ገንዘብ እራሳችሁን በፈቃዳችሁ ገዝተው ባሪያ ያደርጓችሗል ምክንያቱም አስተውሎ መጓዝ በሞኙ ዘንድ አላዩምና። ፈጣሪም አውቀህ አስተውለህ መርጠህ አመዛዝነህ በውድድር በዕውቀት እና በእውነት ይኖር ዘንድ ሜዳውን ከነፃ ፍቃድ ጋር ሰጥቷልና። እንዲያ ባይሆንማ ፈጣሪ አንድ ሀይማኖት ከሌላው ትክክል ነው አይደለም ብሎ ለእርሱ የማይሆነውን አይፈጥርም ነበር ያጠፋም ነበር።
"በፈጣሪ ዘንድ ለራሱ ለፈጣሪ ፈተና የለውም ለፍጥረታቱ እንጂ። "
የሰው ልጅ ነው ፈጣሪውን እየመረጠ ያለው እንጂ ፈጣሪ ምርጫው ፍፁም መጀመሪያ ያለመጨረሽያ የተጠናቀቀ ነው። ሰው የመረጠው ፈጣሪ ከሆነማ ያለው የሁሉ ሀይማኖት ፈጣሪ እንደፓለቲከኛ ቁንጮ ቁጥሩ የትየለሌ በነበር።
ስለዚህ ፈጣሪ ህግ ነው አንድ ህያውነት እውነት የማይቀየር የማይመረጥ ። ልጅ ከመወለዱ በፊት ሀይማኖት ሳይኖረው ህፃን ሁኖ ፈጣሪውን ያውቀዋልና። መናፍስት ሁሉ እስላም ክርስቲያን ፔንጤ ፓጋን ቡዳህ የመሆን የመምረጥ ፍቃድ አላቸው ይህ የሰው ልጅ ልኬት ነውና። ፈጣሪ ለምን ይህን ሀይማኖት ተከተልክ ብሎ ያጠፋው ፍጡር የለውም። የሰው ልጅ ግን እኔ የምከተለውን ሀይማኖት አልተከተልህም ብሎ የፈጣሪን የእጅ ስራ ያጠፋል። አያችሁ ሁለት አለም ግን አንድ እውነት። ፈጣሪ ሰዎች ከመረጡት ሳይሆን እርሱ ካወቃቸው እነርሱም ካወቁት እውነት ብቻ እንጂ ሰው ለይቶ ከመረጠልህ ፈጣሪ እራስህን ጠብቅ።
መናፍስትም እንደሰው ነፃ ፍቃድ አላቸው በህጉ መሰረት። በገንዘብ አይገዙም። በንብረትህ አትማርካቸውም። በሰዋዊ ስልጣንህም አይማረኩም ነገር ግን በእውነት እውቀትህ እና የአለሙን ገዢ የሆነውን ፈጣሪን በማወቅህ ብቻ ይዋረሱሃል ይዋሃዱሃል። መዋረስ መዋሃድ ወዳጅነት አንድ ናቸው እንጂ ማስገደድ ባርነት አይደለም። እስቲ እውነት እኔ መናፍስትን ባሪያ አገልጋይ አድርጌ አሳይሃለሁ የሚል ካለ እኔ ብቻ ሳልሆን የፈጣሪ ህግም ቆመን እንሞግተዋለን ማለት ነው።
አያችሁ ባል ማታ ማታ ሚስቱ ስትደበድበው ታድርና ለቀኑ ውሎ ባሌ ሲደበድበኝ አደረ ብላ በደለኛን እንደተበዳይ ትወቅሳለች ወንድ ልጅም ስደበደብ አደርኩ ከማለት ስረግጣት አድርኩኝ ብሎ የራሱን በድል በቅኔ ይናገራል። የሀገሬ ሰውም ከሰዎች የሚሰማው መንፈሱን ስረግጠው ጭቃ ሳስረግጠው ጎጆ ሳሰራው ነው የማድር ብሎ የራሱን ስራ በቅኔ ይናገራል። አላዋቂ ሰው ደግሞ ቀጥታ ቃሉን ሰምቶ ይስታል።
እንግዲህ አሰተዋይ ልቡና ያድለን ወዳጆቼ።
@ayne_kulu
@ayne_kulu
1 977
‼️ገንዘብ መሳቢያ ምስሃበ ንዋይ‼️
ሰላም ፍቅር ለእናንተ ይሁን ልጆቼ። ሰላም ለሀገራችን ለህዝባችን ምህረትም ይሁንልን።
ይህ ምስሃበ ንዋይ እጅጉን መልካም ነው ገንዘብ ይስብላችሗል ተጠቀሙት ጥቀሙበት።
ይህንን ከመጠቀማችሁ በፊት ለእኔ ቢጤ ሰባት ብር በጠቅላላው ስጡ ለግሱ ለጉዳያችሁ ማንገሻ ነውና።
አገባበሩ እንደሚከተለው ነው፦
፩-እሁድ ቀን ፀሀይ ከመዉጣቱዋ በፊት ወይም ፀሀይ ከገባች በሗላ የተጠቀሰውን ጠልሰም መስመር በሌለዉ ወረቀት ላይ ጠልሰሙን ከትብ። የሚከተበው በእፅዋት ወይም አልኮል በሌለው ቀለም ነው።
፪-የጠልሰሙ መሐል ላይ የብር ሳንቲም እና አንስተኛ ማግኔት ቁረጥ አረጋችሁ አስቀምጡ ከመሃሉ። ጠልሰሙን በከተባችሁበት ወረቀት ጀርባላይ ስማችሁንና የእናታችሁን ስም በመፃፍ ጠልሰሙን ከነሳንቲሙ እና ማግኔቱ እጥፍጥፍ አድርጋችሁ ቢገኝ በወርቃማ ክር ካልተገኘም በነጭ ክር ጥምጥም አድርጎ ማሰር ነው።
፫-የቋጠራችሁትን ጠልሰም ከርቤ ወይም ነጭ እጣን አጭሳችሁ ጠልሰሙን እጠኑት።
፬- ማንኛዉም መስቀለኛ መንገድ አነስ ያለም ቢሆን ጠልሰሙን ከነማግኔት እና ሳንቲሙ የሚከተለዉን ድጋም ሶስት ጊዜ ብላችሁ ቅበሩት።
"አንግላ አዶናይ ሜርሎይ ፀባኦት እንዳመንኩህ ይሁን አያቱሃ ያ ከሪም ያ ነቢላ አጂቡ።"
ቀብራችሁ ዞራችሁ ሳታዩ ነው መሄድ።
@ayne_kulu
@ayne_kulu
1 977
‼️መጠብቅ እራስን መከላከያ ‼️
ይህንን መጠብቅ መጀመሪያ በወረቀት ፅፈህ ለሶስት ቀን ጥዋት ጥዋት ምንም ሳትቀምስ ነጭ የቤተክርስቲያን እጣን እያጨስክ ወረቀቱን ፊትህ አስቀምጠህ የሚከተለውን 21 ጊዜ ድገም።
ከሁሉ ክፍ ነገር ወመናፍስት ይጠብቃል። ከሶስት በሗላ ክታቡን ሁሌም ያዘው።
1)ፊትህን ወደምስራቅ ዙር እና ይህንን ፀልይ ። የሚፃፈውም እራሱ ፀሎቱነው።
2) ታላቅ በሆነው በአብ ስም አናም በክብሩ በፊቱም በሚቆሙት
አቶናስ ሲያክ ከሳስ ሳባክ ካአብ ካይሳስ ኤኮይ
ንዓ ንዓ ንዓ መልአከ መንበር
በታላቅ ስሞችህ ፈጣሪ በሰጠህ
በምታትሮን በጎራዴህ ክፍውን አርቅልኝ
በዳይናሚስ በቀስትህ ከጠላት ጠብቀኝ
በካስዲኤል ይህንን ስፍራ አንፃልኝ
በጃኤል ጥልቁን አንፃልኝ
በያሆኤል ምስራቁን አንፃልኝ
በሜጋሜይዳን ሰሜኑን አንፃልኝ
በፓአዚኤል ደቡቡን አንፃልኝ
በናአሪኤል ምዕራቡን አንፃልኝ
በሃዳሪኤል ከፍታውን አንፃልኝ ሊተ ለገብርከ እገሌ
አሜን አሜን አሜን።
@ayne_kulu 🇪🇹
1 977
‼️ገንዘብ ከእጁ አልቆይ አልያዝ ላለው‼️
ብዙ ሰዎች ገንዘብ እጃቸው ሲኖር አሊያም ደም-ወዝ ሲቀበሉ የሚጠቅመውንም የማይጠቅመውንም ግዙ ግዙ ወጪ አውጡ አውጡ የሚላቸው የሚሸረብ መንፈስ አለባቸው። ሁሉጊዜ ገንዘብ ማውጣታቸውን የሚያቆሙት ገንዘቡ ሲያልቅ ብቻ ነው። በዚህም ብዙ ህይወት ብዙ ትዳር ቤተሰብ ፈርሷል። ለዚህም መፍትሄ በውስጥ መልእክት ብዙዎቻችሁ ጠይቃችሁኛል። እኔም እጅግ ፍቱን እና ወዲያው የሚሰምር ነው ሞክሩት
ሎሚ በተፈጥሮ ያለው ሐይል እና ጥቅም እጅግ ከፍተኛ ነው። ስለዚህ በዚህ መፍትሄም ዋናው የሚያስፈልገን አረንጓዴው ሎሚ ነው ልጆቼ።
1-መጀመሪያ ባዶ እግራችሁን ሁናችሁ ጫማ ሳትደርጉ ወደምስራቅ ዙራችሁ ሶስት ጊዜ ይህንን ድገሙ
"ሰላኢላ ወሊ ወሊ ሰላኢላ"
2-አሁን ልሚውን ለሁለት እኩል ከፍላችሁ የግራ እጃችሁን መዳፍ ሶስት ጊዜ እንዲሁም የቀኝ እጃችሁን መዳፍ ሶስት ጊዜ እያፈራረቃችሁ በሎሚው ክፋይ እሹት።
በሎሚው መዳፋችሁን በምታሹበት ሰዓት የሚከተለውን ፀልዩ
"ፈጣሪ ሆይ ከዛሬ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከእጄ ከኪሴ ከማጀቴ ገንዘብ ያለምክንያት አይወጣም። ገንዘብ በእጄ፣በኪሴ በማጀቴ ይቆያል ይበረክታል ለታላቅ ጥቅም ብቻ ይውላል ይሁን ይሁን ይሁን።"
*ሎሚው አረንጎዴው ነው የሚሆነው።
**ይህ እጅግ ቀላል የሚመስል ግና ታላቅ መፍትሄ ነው። ከዛች ሰዓት ጀምሮ ገንዘብ አውጡ አውጡ አባክኑ አባክኑ የሚላችሁ መንፈስ ይረክሳል። ይህ ወዲያው ውጤታማ የሚሆን መፍትሄ ነው ልጆቼ።
@ayne_kulu 🇪🇹
1 977
‼️ተመልሶ፡ እንዳያጠፋ፡ ይህን፡ አስተውል።
ደብተራም፡አንድ፡ሰው፡ላይ፡ክፉ፡ጥቁር፡አስማት፡ከማድረጉ፡በፊት፡የተዋረሰውን፡መንፈስ፡የሚከተለውን፡ጠይቆ፡አውቆ፡እንጂ፡እንደው፡ስለተባለ፡አሊያም፡እርሱ፡ደብተራው፡ጥበበኛው፡ጠላት፡አድርጎ፡ሰለፈረጀው፡ብቻ፡ጥቁር፡አስማት፡ምትሀት ፡ለጠላት፡አያደርግም።
ሁልጊዜ፡ለጠላት፡ክፍ፡ነገርን፡በቀል፡አስማትን፡ከመተግበር፡በፊት፡የሚከተሉትን፡ግንዛቤ፡ውስጥ፡ ማስገባት፡ተገቢ፡አስፈላጊ፡ነው። አለበለዚያ፡በእራስ፡ፈንጂ፡እራስን ፡ማጥፋት፡ይሆናል፡በእውነቱ።
1-ሁልጊዜ፡ከ18 ዓመት በታች የሆነ ሴትም ሆነ ወንድ ሙጫ ልጅ ላይ ጥቁር አስማት ብታደርግ (ብታስደርግ) ተመልሶ ወደራስህ ወደቤተሰብህ መጥቶ ያጠፋሃልና ተጠንቀቅ አለ ወዳጅ።
2-⭕️ በተለይ ከሰባት አመት በታች የሆኑ ሙጭቅላዎች ላይ ክፉ አስማት ብታደርግ ብታስደርግ ወደአንተው ቤተሰብ ሳይውል ሳያድር ክፋቱ ገብቶ ያጠፋሃልና እወቅ።
3-⭕️ቆራቢ ፣ሼህ ወንድ ወይም ሴት ላይ በእድሜ ከገፋ አይደረግም።
4⭕️-ዋናው እና የመጨረሻው ጥበበኛ ሰው ላይ ሳታውቅም ሆነ አውቀህ ጥቁር ክፋት አስማት ብታስደርግ ጥበበኛው አወቀ አላወቀ የተዋረሰው ወዳጅ እና ነገዱ ወታደሩን ይዞ ሳይውል ሳያድር ደጅህ ይመጣል አትችልም እና ተጠንቀቅ።
‼️ብዙ ሰው እኒህን ነጥቦች ሳያውቅ በስሜታውነት እራሱ ገደል ገብቷልና ወዳጅ ልጆቼ ያባትን ምክር አድምጣቹ አስተውሉ። ለዚህም ነው አንዳንድ ጥበበኛ እከሌ ላይ እንዲህ አላደርግም ነገር ግን እከሌ ላይ ይህን አደርጋለሁ ብሎ ምክንያቱን ሳይዘረዝር የሚናገረው ተግባሩን።
@ayne_kulu 🇪🇹
1 977
‼️ለገርጋሪ፣ስራይ ለተደረገበት፣መጥፎ መንፈስ ለዋለበት ይህ ፍቱን ነው
1-በእጅ መዳፍህ ሙሉ ጨው ይዘህ (ቢገኝ የአሞሌ ጨው)
2-የሚከተለውን 66ት ጊዜ ጨዉ ላይ ድገም
"መዝጀል በዝጀል"
3-የተደገመበትን ጨው ውሃ ውስጥ ጨምረህ ደባልቀህ በውሃው ለሰባት ቀን በተከታታይ ገላን መታጠብ ነው ወይም የታመመውን ሰው ማጠብ ነው።
ይህ ድንቅ ፍቱን ነው። ከየትኛውም ስራይ መፍቻ ገርጋሪ መፍቻ የላቀ ነው።
ድግምቱን ስትደግም የቃል ግድፈት እንዳይኖር እንዲሁም ቁጥሩም 66ት ጊዜ ነው እንዳትስት።
ይህንን ስታደርግ ንፁህ ሁን
ለኔቢጤ ከሰባተኛው ቀን በሗላ ሳንቲም ስጥ ምስጋና ለፈጣሪ እንዲሆንልህ።
@ayne_kulu 🇪🇹
1 977
‼️የራስ ዛር መንፈስ
ሁሉም የሰዉ ልጅ በምድር ሳለ አብሮት የሚወለድ ፣የሚኖር እና ሰዉዬዉ ሲሞት ግን አብሮት የማይሞት ቃሪን ወይም የራስ ዛር ወይም የራስ ዉቃቤ አለዉ ።ግለሰቡ ሀይማኖቱ እስላም ፣ክርስትያን ወይም ሌላ ሀይማኖት ቢኖረዉም ሀብታም ድሀ ነጭ ጥቁር ሳይል ትንሽ ትልቅ ሳይል ሳይለይ ሁሉም የሰዉ ልጅ በተፈጥሮ የራሱ ቃሪን አለዉ ።
ቃሪን (የራስ ዛር) የግለሰቡን ማንኛዉም ድርጊት ሁኔታ ሀሳብ ሚስጥር ድምፁንና የግል የሆኑቱን ሁሉ ያዉቃል። ቃሪን ለሰዉ ልጅ በጥበብ ለነቃ ብዙ ጥቅሞችን ያደርጋል። ይከላከላል ፣ይመራል ፣ሚስጥር ይናገራል፣ የተደበቀዉን ያሳያል ነገር ግን ላላወቀ እንዲሁ በከንቱ ጊዜዉ ያልፍና ይቀራል።
ብዙ ጊዜ በሀገራችን ብዙ ሰዎች አንድ ቤተሰባቸዉ ከሞተ በሗላ በተለያዩ ምክንያቶች ሙት አናጋሪ የሚባሉት ጋር በመሄድ የግለሰቡን መንፈስ ወይም ነፍሲያ አስጠርተዉ እናናግራለን ይላሉ በርግጥም ሙት አናጋሪዉ ጋር ሲሄዱ የጠቀሱት ግለሰብ በድምፅ እራሱን ሆኖ ሁሉንም ሚስጥር በመናገር እኔነኝ ይላል ሆኖም የቀረበዉ የግለሰቡ ነፍሲያ ሳትሆን የግለሰቡን ሁሉን ሚስጥር እና ህይወት የሚያዉቀዉ በግለሰቡ ድምፅ ሆኖ የሚቀርበዉ ቃሪኑ ነዉ ። የሰዉ ልጅ ነፍስያ ከአርባ ቀን ቡሗላ ወደ እዚህ ምድር በእንደዚህ መገለፅ አትመጣምና።
እናም ብዙ ሰዎች የእከሌን ሙት መንፈስ ወይም ነፍሲያ አናግሬ መጣሁ እያሉ ይታለላሉ። ብትነግሯቸውም አያምኗችሁም ምክንያቱም ቃሪኑ በግለሰቡ ድምፅ ሁኖ ሁሉንም የግለሰቡን ህይወት ስለሚያውቅ የሚላቸው ነገሮች ሁሉ ቀጥታ የግለሰቡን ነፍሲያ እንዳነጋገሩ ነው የሚመስላቸው።
ይህንን መግለፄ ለምን እንደሚጠቅም ላስተዋለው ብቻ ይገባዋል።
በእርግጥ የራስን ቃሪን ሰው በህይወት እያለ ከተጠቀመበት በጣም ታላቅ ተግባሮችን ያደርጋል ።የራስን ቃሪን በጥበብ መሰረት ከተገናኙ ይህ የራስ ቃሪን የሰዎችን ሁሉ የግል የግል ቃሪን እየጠየቀ የማንንም ሰው የልብ መሻት እና ሚስጥር ይነግርሃል ሰውዬው ምንም ሳይናገር።
ለምሳሌ አንድ ግለሰብ ወደአንተ ዘንዳ ተቸግሮ ተጨንቆ ታሞ ቢመጣ ያ ያንተ ቃሪን ወዲያውኑ የዚያን ግለሰብ ቃሪን በቅፅበት በመጠየቅ ምን ፈልጎ እንደመጣ ፣ምን እንደቸገረው፣ ምኑን እንዳመመው እና መድሀኒቱ ምን እንደሆነ እናም የት እንደሚገኝ ላንተ በቀጥታ ይነግርሃል አንተም ለግለሰቡ ትነግረዋለህ።
አየህ ቃሪን ጥቅሙ የላቀ ነው በህይወት ላለህ እስካለህ። ይህ ብዙ ጠቢባን ኡልማዎች የሚያውቁት እና የሚጠቀሙበት መንገድ ነውና።
@ayne_kulu 🇪🇹
1 977
ዕፀ ደብተራ
‼️‼️ፍቅረኛዋ ጥሏት ለሄደ ሰው
እግረ መልስ ፣ፍታህወአድኖህ
የሚከተለው ታላቅ አስማት በመጠን ትንሽ ቢመስልም ሀይሉ ግን አስደናቂ ነው።አስማት አስማትነቱ እያንዳንዱ ፊደላትና ሙሉ ስም ወይም አስማት በትክክል ያለ ምንም ግድፈት የተፃፈ ከሆነ ነዉ።ይህ የሚከተለው አስማት ያለ ምንም ግድፈት ነው። ፍፁም ፍቱን ነዉ አስማቱ ።
አስማቱ ጥቅሞቹ ወይም ገቢሮቹ የሚከተሉት ናቸዉ።
"አምዲዲክ ዲኦ ዲኦ ዬሱስ"
ገቢሮቹ፡
1-ጥሎ የሄደሰዉ ተመልሶ እንዲመጣ በቀኝ መዳፍህ ላይ አስማቱን በእኩለ ለሊት ሰባት ግዜ ወይም አርባ ዘጠኝ ግዜ ድገም እና በደገምክበት መዳፍህ የቤትህን መስኮት የታችኛዉን ክፍል መታመታ አድርግ ሰባት ግዜ ።
2-ማንኛዉንም ድግምት እርግማን ለማክሸፍ እንዲሁም የተሰማህን ህመም ለመፈወስ ለአንተም ይሁን ለሌሎች ማድረግ ብትፈልግ አስማቱን በጭንቅላት መሀል አናት ላይ ሰባት ወይም አርባ ዘጠኝ ግዜ ደግመህ እፍ እፍ በልበት ።ለአንተ ከሆነ ሌሎች እንዲያ ያድርጉልህ ።
3-እባብ ባየህ ግዜ እንዳይነድፍህ እንዳይተናኮልህ ሦስት ግዜ አስማቱን በል ወይም በመፋቂያ ወይም በአንድ ነገር ላይ አስማቱን አርባ ዘጠኝ ግዜ ደግመህ በኪስህ ያዝ።
4-ይህንን አስማት የምንጭ ውሀ ቀድተህ በቃ አድርገህ ወይም በአዲስ መስታወት ላይ አርባ ዘጠኝ ግዜ ብትደግም የጠላትህን መልክ በውሃው ውስጥ ወይም በመስታወት ላይ ያሳይሀል።
‼️**የዚህ አስማት እና ገቢሮቹ ዋና ሚስጥራዊ ቁልፍ አስማቱን በምትደግም ግዜ በማንሾካሾክ ድምፅ ብቻነው የሚደገመው።በፍፁም ከፍ ባለድምፅ ቢደገም አይሰራም።ቁልፉ በማንሾካሾክ መድገም ነው።
ይህ ጥበብ በዚህ አግኝታችሁ ስተገብሩ ለኔ ቢጤ ወይም ረደት ለሌላቸው አምስትም አስር ብርም ለግሱ።
@ayne_kulu 🇪🇹
@ayne_kulu 🇪🇹
1 977
ዕፀ ደብተራ ‼️
‼️የሰው ዓይን (ቡዳ) ማናገሪያ
አሪቲ (ጭቁኝ) ከነጭ ሽንኩርት ጋር ደባልቆ ፈጭቶ የተጨመቀውን ውህድ ውሃ የሰው ዓይን ወይም ቡዳ ለበላው በግራ አፍንጫው ቢያደርጉ ቡዳው ይናገራል ይጮሃል ገዝተህ እንዲለቅ አድርገው።
**ፍቱን ነው።
@ayne_kulu
1 977
ዕፀ ደብተራ
‼️የመቃብር ግብር
በየትኛውም የመቃብር ስፍራ ሰዎች ለተለያዪ ጉዳዮች ሄደው የመቃብር አፈር፣ ዕፅዋት ከመቃብሩ ላይ፣የመቃብሩ አናት ላይ ጠጠሮችን እንዲሁም ከፍ ሲል ከሬሳው አጥንቶችን ይወስዳሉ ለተለያዩ መንፈሳዊ ጉዳዮች ነገር ግን ብዙዎች የማይረዱት ነገር ቢኖር የትኛውንም ነገር ከመቃብር ስፍራ ለመውሰድ እና የተወሰደውም ነገር እንዲሰምር እንዳይፃረር ግዴታ ወደመቃብሩ ስትገቡ ከበሩ ላይ የነሀስ ሣንቲም "በረኛው ይሀው ግብርህ " ተበሎ በመግቢያው በግራ በኩል ጣል ይደረጋል። ይህ ሳይደረግ ቢቀር ግን የወሰዳችሁት ነገር ለናንተ እና ለቤተሰብ ከፍተኛ ጉዳት ያመጣል። በዚህ ምክንያትም ብዙ ሰዎች የደረሰባቸውን ችግር ቤት ይቁጠረው። እያንዳንዱ መቃብር ስፍራ የራሱ ጠባቂ መንፈስ አለው ስለዚህ ለእርሱ ግብሩን ሳትሰጡ ገብታችሁ ብትወስዱ የወሰዳችሁት ነገር ለናንተው ከባድ ተፃራሪ ይሆናል እና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል በዕውቀት ። በመንፈስ መስመር ሁሉ ህግ አለውና የዋህነት ብቻ ሳይሆን በዕውቀት መመራት ከታላቅ ቦታ ያደርሳል።
@ayne_kulu 🇪🇹
1 977
ዕፀ ደብተራ 🇪🇹
‼️የህቡዕ፡ስሞች(አስማት)፡ምስጢር
የአስማኡል፡ሁስና፡ የአስማተ፡መለኮት፡ወህቡዕ፡ስም፡አጠቃቀም፡ምስጢር፡ ምክር፡ለልጅ ፡ለወዳጅ፡የሚበጅ።
ስላም ፣ጤና ፣ፍቅር ይሁን ለውድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ ልጆቼ ሁሉ እመኛለሁ። ሰላም ፍቅር ለሀገራችን ይሁን ውድ ወገኖቼ ።ፈጣሪ በምህረቱ እኛንም ሀገራችንንም ይጎበኘን ዘንድ ምኞቴ ነው።
ዛሬ በተለያዩ የሐይማኖት እና ጥበብ መፅሐፍት እና ጥቅል ክታቦች በተለያዩ ፀሎቶች ተፅፈው የሚገኙ የተለያዩ አስማኡል ሁስና(የኣላህ 99 ስሞች )፣ መለኮታዊ አስማት እና ህቡዕ ስሞች በቀላሉ እናገኛለን ነገር ግን ብዙዎች እኒህን ህቡዕ ስሞች ተጠቅመው ውጤት አያገኙም የዚህም ዋናው ምክንያት ሁለት ነው። አንደኛው ከጥበበኛ አባት ፍቃድ በረካ አለማግኘት እና ሁለተኛው ደግሞ ህቡዕ ስሞቹን እንዴት መጠቀም እንዳለብን አለማወቅ ነው ልጆቼ።
ለምሳሌ፡
-አል አዚዝ---ከክፉ ጠላት ለመጠበቅ ።
-አል ጀባር---ግርማ ሞገስ ለማግኘት።
-አል ሙተከቢር---ጥሩ ተናጋሪ የሚያደርግ።
-አል ሙሰዊር---መናፍስትን ለማቅረብ።
-ብያም ድያም ልያም ልምም ድምም
-ሜላህ መልኺ
-ያህ
-ኤልሻዳይ
እኒህን እና የመሳሰሉትን አስማት ብዙ ቦታ ታገኛላችሁ ነገር ግን የራሳቸው አጠቃቀም ፣ምስጢር ፣ስነስርዓት አላቸው እንጂ እንዲሁ ተመፅሐፍ ስለተገኘ 49 አሊያም 99 ጊዜ ቢደግሙት አይሰምርም ውድ ወገኖቼ። ጥበብ የራሱ ስነስርዓት እና አካሄድ አለው ለዚያ ነው በስነምግባር ተአዋቂው ተጠግቶ የተማረው የተረዳው ብቻ የሚሰምርለት።
እነሆ የእኒህን አስማት(ህቡዕ ስሞች) አጠቃቀም እንደሚከተለው ለውድ የሀገሬ ልጆች እገልጣለሁ በፈጣሪ ፍቃድ ። በማስተዋል ተከተሉ።
*መጀመሪያ ተማንኛውም የመንፈሳዊ የጥበብ አባት ለስሞቹ በረካ ፍቃድ ጠይቁ እና ተቀበሉ።
*ሁለተኛው እና ዋናው የስሞቹ አጠቃቀም ነው።
ንፁህ ተሁኖ ከእንስሳት ተዋፅዖ ተቆጥቦ ተሴት ግንኙነት እና አደፍ ከምታይ ሴት ተቆጥቦ ያንን የሚፈልጉትን ህቡዕ አስማት ማታ ስትተኙ በቀኛችሁ አሊያም በግራችሁ ጎን ተኝታችሁ አስማቱን ያለማቋረጥ መድገም ነው እንቅልፍ በዚያው እንዲወስዳችሁ።
ይህንን ተግባር ለሰባት ቀን ከውኑ። ተሰባተኛው ቀን በሗላ ያንን አስማት ለጉዳያችሁ መጠቀም ትችላላችሁ ማለት ነው። እንግዲህ ልጆቼ እኒህ ሰባት ቀናት አስማቱን ማንገሻ መዋሃጃ ነው ማለት ነው። ማንኛውም ህቡዕ አስማት በዚህ ዓይነት ዘዴ እና ስርዓት ሳይነግስ ሳይዋሃድህ ይሰምርልኛል ማለት ጅልነት ነው ወገኖቼ።
ተላይ በገለፅኩላችሁ ምስጢር መሰረት እጅግ ብዙ አስማትን ተሌሎች ክታቦች የምታገኙትንም ማንገስ እና መጠቀም ትችላላችሁ ማለት ነው ወገኖቼ። ከነገሰ ከተዋሃደ ሗላ በገቢሩ መሰረት መጠቀም ነው።ይህ ታላቅ ስጦታ ነውና በማስተዋል እና ፈጣሪን በማመስገን ተጠቀሙ ጥቀሙበት እላለሁ እኔ መምህር ዓይና።
**አስተውሉ ህቡዕ ስሞች የክርስቲያን የእስላም ተብሎ አይለይም ሁሉም መጠቀም ይችላል መለኮታዊ ናቸውና እንደሰው በሐይማኖት እና በባለፀጋነት አይለዩም ውድ ወገኖቼ።
@ayne_kulu 🇪🇹
1 977
@debtra 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@debtra 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
መስተፋቅር‼️‼️‼️‼️‼️‼️
ብዙዎቻቹህ የመስተፋቅር ጥያቄ እየጠየቃችሁኝ ነው፡፡
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
በመጀመሪያ ትንሽ ስለመስተፋቅር እና አይነቶቹ ማብራሪያ
ልስጣቹህ፡፡
እንግዲህ መስተፋቅር ወይም መስተዋድድ ማለት የግዕዝ ቃል
ነው ትርጉሙም መፋቀር መዋደድ ወይም የሚያፋቅር የሚያዋድድ
ማለት ነው፡፡ መስተፋቅር በሁለት አይነት መንገድ ይከፈላል፡፡
ማለትም በነጭ አስማት የሚሰራና በጥቁር አስማት የሚሰራ
እያንዳንዳቸውን እንደሚከተለው እዘረዝራቸዋለው፡፡
እንግዲህ በነጭ አስማት የሚሰሩት መስተፋቅሮች
የእግዚአብሔርን ብቻ ህቡዕ ስሞች በመጥራት ወይም የአንዳንድ
ቅዱሳን መላእክትን ስም በመጥራት የማፋቀር ሀይል አላቸው
ተብለው የሚታመንባቸው ስሞች በመጥራትና በመጠልሰም
ይሰራል፡፡ ታድያ ነጭ አስማት ውስጥ ከሚመደቡት መስተፋቅሮች
መካከል የሚከተሉት ናቸው፡
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
የማይስማሙ ባለትዳሮችን ለማስማማት የሚሰራ
(በጠልሰም፣በዕጽ፣በድጋም)
ፍቅር አሊዘው ላለ ሰው ማፍቀር እንዲችል ተፅፎ የሚሰጥ
በእድሜ በጣም የተራራቁ ሰዎች ሲጋቡ ለማዋደድ የሚሰጥ
ሚስት ወይም ባል ሲሄድ ለመመለስ የሚሰራ(እግረ መልስ፣
በወዝ)
ለማይስማማ ቤተሰብ ወይም ለቤተሰባዊ ፍቅር የሚሰራ
(በድጋም፣በጥምቀት)
ከሁሉም ተግባብቶ ለመኖር የሚረዳ( በጽሑፍ
የሚሰጥ፣በድጋም ወዘተ )
የነጭ አስማት መስተፋቅሮች እንግዲህ እነዚህና እነዚህን
የመሳሰሉ ናቸው፡፡
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
በጥቁር አስማት የሚሰሩ የመስተፋቅር አስማቶች አሰራራቸው
ያው ከርኩስ መንፈስ ጋር የተገናኘ ነው ማለትም መስተፋቅሩ
የሚሰራ የአጋንንት ወይም የዛር ወይም የሣጥናኤልን አስማቶች
በመድገም ርኩስ መንፈሱ ከተሳበ በኋላ የማን ስም እንደሆኑ
የማይታወቁ ስሞችን በመጥራት የሚሰራ ነው በጥቁር አስማት
የሚሰሩ መስተፋቅሮች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
አንድን ሴት እቤት ድረስ መጥታ ተራክቦ እንድታረግ
የሚያረግ( በግብር)
በግራ እጅ ሰላም ያለው ሁሉ ተከትላው እንድትሄድ የሚሰራ
(በንቅሳት)
በስራ ቦታ በትራንስፖርት በትምህርት ቤት እንዲፈቀር
የሚያደርግ በአዩት ሁሉ እንዲወደድ የሚሰራ(በመቀባት፣በሽቶ )
ለዝሙት ስራ በተለይ ብዙ ሴቶችን ለመሳብና ለመሰብሰብ
የሚሰራ( በመፋቂያ፣በወርቅ ጥርስ ተደግሞ የሚሰጥ ወይም
በወርቅ ቀለበት የሚሰራ )፡፡
አንደን ሴት በፍቅር ለማሳበድ የሚሰራ( በሎሚ ተደግሞ
ወርውሮ በመምታት ወይም ውሀውን ተቀብቶ ሰላም በማለት)
የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡
የብዙዎቻቹህ የመስተፋቅር ጥያቄዎች በጥቁሩ አስማት ላይ
ወደዘረዘርኳቸው ያደላሉ፡፡
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
ሁላችሁም ጓደኛቻችሁን share አድርጉ
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
1 977
ለገበያ ‼️‼️‼️‼️‼️‼️
የዔሊ ዐፅም ጊዛዋ አለብላቢት ችፍርግ የፍየለ ፈጅ የፍልፈል አፈር በነጭ ደሮ ደም ተለውሶ
የሀገርህን ገብያ ፫ ጊዜ አዙርህ ከስራህ ቦታ አስቀምጥ
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@debtra ‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
1 977
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
@debtra 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@debtra 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጥቁር_አስማት_ምንድን_ነው ?
ክፍል ፩ ‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
ጥቁር አስማት (black magic) ተብሎ የሚጠራው አስማት እርኩሳን መናፍስትን
በመሳብ የሚሰራ በሰው ልጅ አካላዊ እና የሞራላዊ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ የ አስማት
አይነት ነው። እስቲ እነዚህ የ አስማት አይነቶች ከፋፍለን ለማየት እንሞክር።
1, መቅትል(ገዳይ አስማት) ምንድነው??
መቅትል የሚለው ቃል ፥ቀተለ፥ገደለ፥ነፍስ አሳለፈ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ነው።
ይህ አስማት ሰውን ለመግደል ጠንቋዮች የሚጠቀሙበት አስማት ነው ተብሎ በመናፍስቱ
አለም ይነገራል።
እግዚአብሔር አምላኩን ክዶ፥ ሰይጣንን አምኖ፥ የተዋረሰ ጠንቋይ ፥ የዲያብሎስን ስም
ደጋግሞ በመጥራት ፥ ህንፃ ስላሴን ለማፍረስ ይጥራል።
አንዳንድ ጠንቋዮች እንዲሞት የሚፈልጉትን ሰው ስም በየቀኑ 49ጊዜ ደጋግመው ችፍርግ
በተባለችው የእጽዋት ሥር ላይ ይጠራሉ። ከዛም ያቺ የተደገመባትን የችፍርግ ቁጥቋጦ
ሥሯን ወደ ግራ በመጠምዘዝ ፥ለ 7ቀናት ሲደግሙባት ከቆዩ በኋላ ሰውዬው እንዲሞት
ከፈለጉ ሥሩን ይቆርጣሉ። እንዲታመም ከፈለጉ ደግሞ ሥሩን ወደ ግራ በመጠምዘዝ
ድንጋይ ጭነው ይተውበታል።
ሌሎች ጠንቋዮች ደግሞ የሰይጣን ስም ደጋግመው በመጥራት የደገሙበትን ገዳይ
ድግምት ከምግብ እና ከመጠጥ ጋር ለሰዋች በመስጠት ሰዎችን ይገሉበታል።
ሌላም ብዙ አይነት መንገዶች አሉ .......
በዚህ ሁኔታ የተጠቃው ሰው ወደ ሆስፒታልም ሆነ ወደ ባህላዊ ህክምና ሔዶ መዳን
አይችልም። ምክንያቱም የመናፍስት አሠራር ስለሆነ። ይህ ተጠቂ ሊድን የሚችለው ከስም
ሁሉ በላይ በሆነው በአምላካችን ኢየሱስ በክርስቶስ ስም ብቻ ነው።
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
1 977
ጥቁር አስማት
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
=አሽኮኮ ወደ ጠላት ቤት መላኪያ አንደርቢ===
በስመ አብ በል
ፀሎት በእንተ አንደርብ ወብዝንቱ አሽኮኮ ቢስሚላሒ ሮሂማን ሲያን አዝቢላሂ ኢፈደደን ወዝለሂ
መዝለሂ በዝ አሽኮኮ ወበዝ አንደርቢ አስተአብድ ሸወቅ በዝ አንደርብ ወበዝ አሽኮኮ ንዒ ንዒ ቤትኪ
ወእሁር አስተናክርኪው ዘረወ ወሰላቢ ገብርከ እገሌ
ከመንፈስ አንፍስ ወከመ ከልብ አንብው
ከመ ያንፍስ ወከመ በቅሎ ወአትረድ ከመ አብራርወ ከመ ሰብ አስተዳልኢ በዝ አሽኮኮ ወበዝ
አንደርብ አስተዳልዕ ሰብ ወአንስተ ሎሌ ወጎረቤት ወበዘንጋኤ ፍፍት ከመዝ አንደርቢ ወበዝ አሽኮኮ
በአይጥ ዳኛ በመቆስ ቀማኛ አሀልኩከ በዝ አሽኮኮ ወበዝ አንደርብ ሀሌ ሀለ ሰቢታ ገብርከ እገሌ
7 ቀን ሰባት ጊዜ ድገም በዕፀ ፋርስ በአብሾ ደግመህ ጥቁር ገብስ ጨምረህ ስጨርስ በአሽኮኮ
ጉሬ አስቀምጥ
መመለሻ ቀንሰህ ከወንዝ ጣል
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@debtra ‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
1 977
@debtra
@debtra
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
ዓቃቤ ርእስ የራስ መጠበቂያ#
በስመ አብ በል
ፀሎት በእንተ ዓቃቤ ርእስ
መርዱቃኤል፯ጊዜ
መድሩቃኤል፯ጊዜ
መርዱኤል፯ጊዜ
መድሩኤል፯ጊዜ
ብሩራኤል፯ጊዜ
ሐሹናኤል፯ጊዜ
ሠውርናኤል፯
በእሉ አስማተ እግዚአብሔር በከመ ሠወርኮሙ ለሄኖክ ወለኤልያስ እምገፀ ሞት ድሩክ
ከማሆሙ ሠውረኒ እሞተ ግብት ወመቅሰፍት ወእምደ ፀላዒ ወፀር ለገብርከ እገሌ
የክርስትና ስም አስገባ
ገቢር ጠዋት ጠዋት ፯ ጊዜ ድገም አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ሀልቀ ኄርን ፯ጊዜ አብረህ
ድገም።
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@ayne_kulu 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
