cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

መርጌታ አይነኩሉ 🇪🇹

ለእያንዳንዱ ችግሮቻቹ መፍትሔ የምታገኙበት የጥበብ ቻናል ነው🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 061
المشتركون
+524 ساعات
+107 أيام
-6630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ዕፀ ደብተራ ‼️ምክር ‼️ምክረ ሰብዕ ወሂቃ መናፍስት በዚህ ገፅ እኔ መምህር አይነኩሉ እና  ረዳቶቼ  መምህራን እየገለፅን እያካፈልን ያለንውን የአሀዱ አምላክ አብ ወጥበብ ዘይሆነ የአባቶቻችንን  ጥበብ ሚስጥረ አዳም ዓለመ ሐመልማል ወሌዋቲ  ሌሎች ሰዎች የተለያየ  መንፈሳዊ ገፅ ላይ በመሄድ በዛ የራሳቸው  ችግር ለመፍታት በራሳቸው ነገሮችን ይሞክራሉ ይህ ክፋት የለውም ምክንያቱም ጥበብ  የአንድ ግለሰብ ሳትሆን አሀዱ አምላክ ለሰው ልጅ ለሚያስተውል ብቻ የስጋ ዓይኑ ባዳ እንደሆነ እና የመንፈስ ህሊና ዓይኑ አውነት እንደሆነ የሚገልፅበት መንገድ ነው ጥበብ።  ያስተዋለ ጥበብ  የተለገሰችው ደግሞ ለፍቶ እንጂ የስጋ አይኑን በስጋ አለም ለስጋ ግብር አሳድሮ በቀላል አያገኘውም። ‼️  እኛ ፈጣሪ ዋሉበት ብሎ ካደለን ፀጋ ጥበብ  ለሰው ልጅ በዚህ ገፅ ስናካፍል እንደህጉ ሰዎች ጥበቡ ይሰምርላቸው ዘንድ አይፃረራቸው ዘንድ የመምህርነታችንን የመሪ አባት የኔታነታችንን ከተሰጠን ፀጋ አብነቱ ጥበቡ ለተጠቃሚው  ይሰምር ዘንድ ጥበቡን በዚህ ገፅ ስንገልፅ በስውር ፍቃድ ለተጠቃሚዎቹ እየሰጠን ነው። ነገር ግን ከዚህ ከኛ ገፅ ብዙዎች የኛንም ፍቃድ ሳይጠይቁ ገቢሮች ይፈትናሉ። በሌሎች መንፈሳዊ ገፆችም ላይ እንዲሁ ይህ ደግሞ በዛ በነሱ ገፅ ላይ ጥበቡን ያነበበ  ወይ ዝም ብሎ ያለፍቃድ ይተገብረዋል ወይም ሰዎቹ ሌላ አላስፈላጊ  ነገር ውስጥ ገብተው ጥበቡም ላይሰምርለት መናፍስትም ይጋጩታል። ‼️ ፍቃድ ከመምህሩ ከመሪው ከአስተማሪው ከየኔታው ሁሌም አስፈላጊ ነገር ነው። ባይገለፅ እንኳን  በዚህ በኛ ገፅ ለሚጠቀሙ የሀገራችን ልጆች በህቡዕ  ፍቃድ ሰተናል። ‼️ ከዚህ ከኛ ገፅ ገቢር የሚፈትኑ ስዎች ግን እባካችሁ አንድም የኛን ፍቃድ በረከት ጠይቁ ሌላ ወገንን ላለመጉዳት።  አሊያም ከዚህ ገፅ አትቅዱ መልካም አይደለምና ያለፍቃድ እባካችሁ።   ክፉ ለማድረግ ቀላል ነው ግና ቀናውን  እናደርግ ታደርጉ ዘንድ ስንጠይቅ እናንተ እኛን እንደትንሽ ብታዩን አይፈረድባችሁም ክፉውን ላሳይህና ልክህን እወቅ አይባልምና የሰው ልጅ። ‼️ እኛ ይህን  ገፃችንን share አድርጉልን ብለን እንደሌሎች ያልጠየቅነው ጥበብ  የጠራችው እንጂ ምሶ የፈለጋት አያገኛትምና በዚህ ገፅ ጥበብን የምትጋሩ እንግዲህ እንደ መርጌታ አይነኩሉ ፍቃድ የማታውቁትን ግን የተሰጣችሁን አግኝታችሁ ስለሚሆን ፈጣሪያችሁን እነደ እምነታችሁ አመስግኑት። ሳያደርግ ለሚያመሰግኑት አውቆ ቀድሞ የሚሞላ ፈጣሪ አለንና። @ayne_kulu @ayne_kulu
إظهار الكل...
👍 4
ለጥንቃቄ‼️ አንዳንድ ሰዎች ❓ "መምህር መንፈስ ጋር መዋረስ እፈልጋለሁ ስንት ብር ነው?  " "❓መምህር ከዚህ ቀደም ይህን ያህል ገንዘብ ለሆነ መሪጌታ ከፍዬ ያወረሰኝ መንፈስ ምንም እየሰራልኝ አይደለም።" "❓መምህር የተዋረስኩት መንፈስ ጭራሽ አልታዘዝም አለኝ ይልቁስ እየተጋጨኝ ነው ምን ላድርግ?" ❓"መምህር የፈለኩትን የሚያረግልኝ መንፈስ ማግኘት መዋረስ እፈልጋለሁ ስንት ነው ዋጋህ ንገረኝ።" "❓መምህር መንፈስን እንደፈለኩኝ እያዘዝኩት ነገርን ሁሉ እንዲያደርግልኝ እፈልጋለሁ በተለይ ገንዘብን ስለዚህ ሰው ገለህ እንኳን አምጣ የሚል ቢሆን አደርጋለሁ ነገር ግን አሁን ገንዘብ መክፈል አልችልም እባክህ እርዳኝ" ..... ይህንና የመሳሰሉትን  ጥያቄ ከሰው ልጅ ከራሴ ወገን ስሰማ እውነት  እላችሗለሁ ምን ዓይነት መታወር እና በምን ዓይነት ጭካኔ ክህደት ውስጥ  የሰው ልጅ ነፍሱን በአንድ ዕቃ እንደሚለውጥና ሳይሞት የተፈረደበት የበዛበት ዓለም ውስጥ እንዳለን ያስታውሰኛል። በመጀመሪያ ደረጃ ትልቁ ስህተት  መናፍስትን ገንዘብ ብቻ ስለከፈልክ ወይም እንስሳ ስላረድክ ይዋረሰኛል ይታዘዘኛል ብሎ የሚያስብ ከቂል በላይ እራሱ የተሸጠ ያለቀለት መሆኑን አለመረዳቱ ነው። መናፍስት አንተ ወይም አንቺ የፈለጋችሁትን ከፍተኛ ብር ስለከፈላቹ በእውነት ተዋርሰው ከሚያገለግሏችሁ ይልቅ ሞኝነታችሁን ተጠቅመው በራሳችሁ ገንዘብ እራሳችሁን በፈቃዳችሁ  ገዝተው ባሪያ ያደርጓችሗል ምክንያቱም አስተውሎ መጓዝ  በሞኙ ዘንድ አላዩምና። ፈጣሪም አውቀህ አስተውለህ መርጠህ አመዛዝነህ በውድድር በዕውቀት እና በእውነት ይኖር ዘንድ ሜዳውን ከነፃ ፍቃድ ጋር ሰጥቷልና። እንዲያ ባይሆንማ ፈጣሪ አንድ ሀይማኖት ከሌላው ትክክል ነው አይደለም ብሎ ለእርሱ የማይሆነውን አይፈጥርም ነበር ያጠፋም ነበር። "በፈጣሪ ዘንድ ለራሱ ለፈጣሪ ፈተና የለውም ለፍጥረታቱ  እንጂ። "  የሰው ልጅ ነው ፈጣሪውን እየመረጠ ያለው እንጂ ፈጣሪ ምርጫው ፍፁም መጀመሪያ ያለመጨረሽያ የተጠናቀቀ  ነው። ሰው የመረጠው ፈጣሪ ከሆነማ ያለው የሁሉ ሀይማኖት ፈጣሪ እንደፓለቲከኛ ቁንጮ ቁጥሩ የትየለሌ በነበር።  ስለዚህ ፈጣሪ ህግ ነው አንድ ህያውነት እውነት የማይቀየር የማይመረጥ ። ልጅ ከመወለዱ በፊት ሀይማኖት ሳይኖረው ህፃን ሁኖ ፈጣሪውን ያውቀዋልና።    መናፍስት ሁሉ እስላም ክርስቲያን ፔንጤ ፓጋን ቡዳህ የመሆን የመምረጥ ፍቃድ አላቸው ይህ የሰው ልጅ ልኬት ነውና።  ፈጣሪ ለምን ይህን ሀይማኖት ተከተልክ ብሎ ያጠፋው ፍጡር የለውም። የሰው ልጅ ግን እኔ የምከተለውን ሀይማኖት አልተከተልህም ብሎ የፈጣሪን የእጅ ስራ ያጠፋል።  አያችሁ  ሁለት አለም ግን አንድ እውነት። ፈጣሪ ሰዎች ከመረጡት ሳይሆን እርሱ ካወቃቸው እነርሱም ካወቁት እውነት ብቻ እንጂ ሰው ለይቶ ከመረጠልህ ፈጣሪ እራስህን ጠብቅ። መናፍስትም እንደሰው ነፃ ፍቃድ አላቸው በህጉ መሰረት። በገንዘብ አይገዙም። በንብረትህ አትማርካቸውም።  በሰዋዊ ስልጣንህም አይማረኩም ነገር ግን በእውነት እውቀትህ እና የአለሙን ገዢ የሆነውን ፈጣሪን በማወቅህ ብቻ ይዋረሱሃል ይዋሃዱሃል።  መዋረስ መዋሃድ ወዳጅነት አንድ ናቸው እንጂ ማስገደድ ባርነት አይደለም።  እስቲ እውነት እኔ መናፍስትን ባሪያ አገልጋይ አድርጌ አሳይሃለሁ የሚል ካለ እኔ ብቻ ሳልሆን የፈጣሪ ህግም ቆመን እንሞግተዋለን ማለት ነው። አያችሁ ባል ማታ ማታ ሚስቱ ስትደበድበው ታድርና ለቀኑ ውሎ ባሌ ሲደበድበኝ አደረ ብላ በደለኛን እንደተበዳይ ትወቅሳለች ወንድ ልጅም ስደበደብ አደርኩ ከማለት ስረግጣት አድርኩኝ ብሎ የራሱን በድል በቅኔ ይናገራል። የሀገሬ ሰውም ከሰዎች የሚሰማው መንፈሱን ስረግጠው ጭቃ ሳስረግጠው ጎጆ ሳሰራው ነው የማድር ብሎ የራሱን ስራ በቅኔ ይናገራል። አላዋቂ ሰው ደግሞ ቀጥታ ቃሉን ሰምቶ ይስታል። እንግዲህ አሰተዋይ ልቡና ያድለን ወዳጆቼ። @ayne_kulu @ayne_kulu
إظهار الكل...
👍 4 4🥰 3
‼️ገንዘብ መሳቢያ ምስሃበ ንዋይ‼️ ሰላም ፍቅር ለእናንተ ይሁን ልጆቼ። ሰላም ለሀገራችን ለህዝባችን ምህረትም ይሁንልን። ይህ ምስሃበ ንዋይ እጅጉን መልካም ነው ገንዘብ ይስብላችሗል ተጠቀሙት ጥቀሙበት። ይህንን ከመጠቀማችሁ በፊት ለእኔ ቢጤ ሰባት ብር በጠቅላላው ስጡ ለግሱ ለጉዳያችሁ ማንገሻ ነውና። አገባበሩ እንደሚከተለው ነው፦ ፩-እሁድ ቀን ፀሀይ ከመዉጣቱዋ በፊት ወይም ፀሀይ ከገባች በሗላ የተጠቀሰውን ጠልሰም መስመር በሌለዉ ወረቀት ላይ ጠልሰሙን ከትብ። የሚከተበው በእፅዋት ወይም አልኮል በሌለው ቀለም ነው። ፪-የጠልሰሙ መሐል ላይ የብር ሳንቲም እና አንስተኛ ማግኔት ቁረጥ አረጋችሁ  አስቀምጡ ከመሃሉ። ጠልሰሙን በከተባችሁበት ወረቀት ጀርባላይ ስማችሁንና የእናታችሁን ስም በመፃፍ ጠልሰሙን ከነሳንቲሙ እና ማግኔቱ እጥፍጥፍ አድርጋችሁ ቢገኝ በወርቃማ ክር ካልተገኘም በነጭ ክር ጥምጥም አድርጎ ማሰር ነው። ፫-የቋጠራችሁትን ጠልሰም ከርቤ ወይም ነጭ እጣን አጭሳችሁ ጠልሰሙን እጠኑት። ፬- ማንኛዉም መስቀለኛ መንገድ አነስ ያለም ቢሆን  ጠልሰሙን ከነማግኔት እና ሳንቲሙ የሚከተለዉን ድጋም ሶስት ጊዜ ብላችሁ ቅበሩት። "አንግላ አዶናይ ሜርሎይ ፀባኦት እንዳመንኩህ ይሁን አያቱሃ ያ ከሪም ያ ነቢላ አጂቡ።" ቀብራችሁ ዞራችሁ ሳታዩ ነው መሄድ። @ayne_kulu @ayne_kulu
إظهار الكل...
😁 6👍 2
‼️መጠብቅ እራስን መከላከያ ‼️ ይህንን መጠብቅ መጀመሪያ በወረቀት ፅፈህ ለሶስት ቀን ጥዋት ጥዋት ምንም ሳትቀምስ ነጭ የቤተክርስቲያን እጣን እያጨስክ ወረቀቱን ፊትህ አስቀምጠህ የሚከተለውን  21 ጊዜ ድገም። ከሁሉ ክፍ ነገር ወመናፍስት ይጠብቃል። ከሶስት በሗላ ክታቡን ሁሌም ያዘው። 1)ፊትህን ወደምስራቅ ዙር እና ይህንን ፀልይ ። የሚፃፈውም እራሱ ፀሎቱነው። 2) ታላቅ በሆነው በአብ ስም አናም በክብሩ በፊቱም በሚቆሙት    አቶናስ  ሲያክ ከሳስ ሳባክ ካአብ ካይሳስ ኤኮይ    ንዓ ንዓ ንዓ መልአከ መንበር  በታላቅ ስሞችህ ፈጣሪ በሰጠህ በምታትሮን   በጎራዴህ ክፍውን አርቅልኝ በዳይናሚስ  በቀስትህ ከጠላት ጠብቀኝ በካስዲኤል  ይህንን ስፍራ አንፃልኝ በጃኤል   ጥልቁን አንፃልኝ በያሆኤል  ምስራቁን አንፃልኝ በሜጋሜይዳን   ሰሜኑን አንፃልኝ በፓአዚኤል  ደቡቡን  አንፃልኝ በናአሪኤል ምዕራቡን አንፃልኝ በሃዳሪኤል ከፍታውን አንፃልኝ  ሊተ ለገብርከ እገሌ አሜን  አሜን አሜን። @ayne_kulu 🇪🇹
إظهار الكل...
👍 10
‼️ገንዘብ ከእጁ አልቆይ አልያዝ ላለው‼️ ብዙ ሰዎች ገንዘብ እጃቸው ሲኖር አሊያም ደም-ወዝ ሲቀበሉ የሚጠቅመውንም የማይጠቅመውንም ግዙ ግዙ ወጪ አውጡ አውጡ የሚላቸው የሚሸረብ መንፈስ አለባቸው። ሁሉጊዜ ገንዘብ ማውጣታቸውን የሚያቆሙት ገንዘቡ ሲያልቅ ብቻ ነው። በዚህም ብዙ ህይወት ብዙ ትዳር ቤተሰብ ፈርሷል። ለዚህም መፍትሄ በውስጥ መልእክት ብዙዎቻችሁ ጠይቃችሁኛል። እኔም እጅግ ፍቱን እና ወዲያው የሚሰምር ነው ሞክሩት ሎሚ በተፈጥሮ ያለው ሐይል እና ጥቅም እጅግ ከፍተኛ ነው። ስለዚህ በዚህ መፍትሄም ዋናው የሚያስፈልገን አረንጓዴው ሎሚ ነው ልጆቼ። 1-መጀመሪያ ባዶ እግራችሁን ሁናችሁ ጫማ ሳትደርጉ ወደምስራቅ ዙራችሁ ሶስት ጊዜ ይህንን ድገሙ "ሰላኢላ ወሊ ወሊ ሰላኢላ" 2-አሁን ልሚውን ለሁለት እኩል ከፍላችሁ የግራ እጃችሁን መዳፍ ሶስት ጊዜ እንዲሁም የቀኝ እጃችሁን መዳፍ ሶስት ጊዜ እያፈራረቃችሁ በሎሚው ክፋይ እሹት። በሎሚው መዳፋችሁን በምታሹበት ሰዓት የሚከተለውን ፀልዩ "ፈጣሪ ሆይ ከዛሬ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከእጄ ከኪሴ ከማጀቴ ገንዘብ ያለምክንያት አይወጣም። ገንዘብ በእጄ፣በኪሴ በማጀቴ ይቆያል ይበረክታል ለታላቅ ጥቅም ብቻ ይውላል ይሁን ይሁን ይሁን።" *ሎሚው አረንጎዴው ነው የሚሆነው። **ይህ እጅግ ቀላል የሚመስል ግና ታላቅ መፍትሄ ነው። ከዛች ሰዓት ጀምሮ ገንዘብ አውጡ አውጡ አባክኑ አባክኑ የሚላችሁ መንፈስ ይረክሳል። ይህ  ወዲያው ውጤታማ የሚሆን መፍትሄ ነው ልጆቼ። @ayne_kulu 🇪🇹
إظهار الكل...
👍 12 1😁 1
‼️ተመልሶ፡ እንዳያጠፋ፡ ይህን፡ አስተውል። ደብተራም፡አንድ፡ሰው፡ላይ፡ክፉ፡ጥቁር፡አስማት፡ከማድረጉ፡በፊት፡የተዋረሰውን፡መንፈስ፡የሚከተለውን፡ጠይቆ፡አውቆ፡እንጂ፡እንደው፡ስለተባለ፡አሊያም፡እርሱ፡ደብተራው፡ጥበበኛው፡ጠላት፡አድርጎ፡ሰለፈረጀው፡ብቻ፡ጥቁር፡አስማት፡ምትሀት ፡ለጠላት፡አያደርግም። ሁልጊዜ፡ለጠላት፡ክፍ፡ነገርን፡በቀል፡አስማትን፡ከመተግበር፡በፊት፡የሚከተሉትን፡ግንዛቤ፡ውስጥ፡ ማስገባት፡ተገቢ፡አስፈላጊ፡ነው። አለበለዚያ፡በእራስ፡ፈንጂ፡እራስን ፡ማጥፋት፡ይሆናል፡በእውነቱ። 1-ሁልጊዜ፡ከ18 ዓመት በታች የሆነ ሴትም ሆነ ወንድ ሙጫ ልጅ ላይ ጥቁር አስማት ብታደርግ (ብታስደርግ) ተመልሶ ወደራስህ ወደቤተሰብህ መጥቶ ያጠፋሃልና ተጠንቀቅ አለ ወዳጅ። 2-⭕️ በተለይ ከሰባት አመት በታች የሆኑ ሙጭቅላዎች ላይ ክፉ አስማት ብታደርግ ብታስደርግ ወደአንተው ቤተሰብ ሳይውል ሳያድር ክፋቱ ገብቶ ያጠፋሃልና እወቅ። 3-⭕️ቆራቢ ፣ሼህ ወንድ ወይም ሴት ላይ በእድሜ ከገፋ አይደረግም። 4⭕️-ዋናው እና የመጨረሻው ጥበበኛ ሰው ላይ ሳታውቅም ሆነ አውቀህ ጥቁር ክፋት አስማት ብታስደርግ ጥበበኛው አወቀ አላወቀ የተዋረሰው ወዳጅ እና ነገዱ ወታደሩን ይዞ ሳይውል ሳያድር ደጅህ ይመጣል አትችልም እና ተጠንቀቅ። ‼️ብዙ ሰው እኒህን ነጥቦች ሳያውቅ በስሜታውነት እራሱ ገደል ገብቷልና ወዳጅ ልጆቼ ያባትን ምክር አድምጣቹ አስተውሉ። ለዚህም ነው አንዳንድ ጥበበኛ እከሌ ላይ እንዲህ አላደርግም ነገር ግን እከሌ ላይ ይህን አደርጋለሁ ብሎ ምክንያቱን ሳይዘረዝር የሚናገረው ተግባሩን። @ayne_kulu 🇪🇹
إظهار الكل...
👍 12 2😢 1
‼️ለገርጋሪ፣ስራይ ለተደረገበት፣መጥፎ መንፈስ ለዋለበት ይህ ፍቱን ነው 1-በእጅ መዳፍህ ሙሉ ጨው ይዘህ (ቢገኝ የአሞሌ ጨው) 2-የሚከተለውን 66ት ጊዜ ጨዉ ላይ ድገም     "መዝጀል በዝጀል" 3-የተደገመበትን ጨው ውሃ ውስጥ ጨምረህ ደባልቀህ በውሃው ለሰባት ቀን በተከታታይ ገላን መታጠብ ነው ወይም የታመመውን ሰው ማጠብ ነው። ይህ ድንቅ ፍቱን ነው። ከየትኛውም ስራይ መፍቻ ገርጋሪ መፍቻ የላቀ ነው። ድግምቱን ስትደግም የቃል ግድፈት እንዳይኖር እንዲሁም ቁጥሩም 66ት ጊዜ ነው እንዳትስት። ይህንን ስታደርግ ንፁህ ሁን ለኔቢጤ ከሰባተኛው ቀን በሗላ ሳንቲም ስጥ ምስጋና ለፈጣሪ እንዲሆንልህ። @ayne_kulu 🇪🇹
إظهار الكل...
👍 6🤩 2
‼️የራስ ዛር መንፈስ    ሁሉም የሰዉ ልጅ በምድር ሳለ አብሮት የሚወለድ ፣የሚኖር እና ሰዉዬዉ ሲሞት ግን አብሮት የማይሞት ቃሪን ወይም የራስ ዛር ወይም የራስ ዉቃቤ አለዉ ።ግለሰቡ ሀይማኖቱ እስላም ፣ክርስትያን ወይም ሌላ ሀይማኖት ቢኖረዉም ሀብታም ድሀ ነጭ ጥቁር ሳይል ትንሽ ትልቅ ሳይል ሳይለይ ሁሉም የሰዉ ልጅ በተፈጥሮ  የራሱ ቃሪን አለዉ ።   ቃሪን (የራስ ዛር) የግለሰቡን ማንኛዉም ድርጊት ሁኔታ ሀሳብ ሚስጥር ድምፁንና የግል የሆኑቱን ሁሉ ያዉቃል።  ቃሪን ለሰዉ ልጅ በጥበብ  ለነቃ ብዙ ጥቅሞችን ያደርጋል። ይከላከላል ፣ይመራል ፣ሚስጥር ይናገራል፣ የተደበቀዉን ያሳያል ነገር ግን ላላወቀ እንዲሁ በከንቱ ጊዜዉ ያልፍና ይቀራል። ብዙ ጊዜ በሀገራችን ብዙ ሰዎች አንድ ቤተሰባቸዉ ከሞተ በሗላ በተለያዩ ምክንያቶች ሙት አናጋሪ የሚባሉት ጋር  በመሄድ የግለሰቡን መንፈስ ወይም ነፍሲያ አስጠርተዉ እናናግራለን ይላሉ በርግጥም ሙት አናጋሪዉ  ጋር ሲሄዱ የጠቀሱት ግለሰብ በድምፅ እራሱን ሆኖ ሁሉንም ሚስጥር በመናገር እኔነኝ ይላል ሆኖም የቀረበዉ የግለሰቡ ነፍሲያ ሳትሆን የግለሰቡን ሁሉን ሚስጥር እና ህይወት የሚያዉቀዉ በግለሰቡ ድምፅ ሆኖ የሚቀርበዉ ቃሪኑ ነዉ ። የሰዉ ልጅ ነፍስያ ከአርባ ቀን ቡሗላ ወደ እዚህ ምድር በእንደዚህ መገለፅ አትመጣምና። እናም ብዙ ሰዎች የእከሌን ሙት መንፈስ ወይም ነፍሲያ አናግሬ መጣሁ እያሉ ይታለላሉ። ብትነግሯቸውም አያምኗችሁም ምክንያቱም ቃሪኑ በግለሰቡ ድምፅ ሁኖ ሁሉንም የግለሰቡን ህይወት ስለሚያውቅ የሚላቸው ነገሮች ሁሉ ቀጥታ የግለሰቡን ነፍሲያ እንዳነጋገሩ ነው የሚመስላቸው። ይህንን መግለፄ ለምን እንደሚጠቅም ላስተዋለው ብቻ ይገባዋል።   በእርግጥ  የራስን ቃሪን ሰው በህይወት እያለ ከተጠቀመበት በጣም ታላቅ ተግባሮችን ያደርጋል ።የራስን ቃሪን በጥበብ መሰረት ከተገናኙ ይህ የራስ ቃሪን የሰዎችን ሁሉ የግል የግል ቃሪን እየጠየቀ የማንንም ሰው የልብ መሻት እና ሚስጥር ይነግርሃል ሰውዬው ምንም ሳይናገር። ለምሳሌ አንድ ግለሰብ ወደአንተ ዘንዳ ተቸግሮ ተጨንቆ ታሞ ቢመጣ ያ ያንተ ቃሪን ወዲያውኑ የዚያን ግለሰብ ቃሪን በቅፅበት በመጠየቅ ምን ፈልጎ እንደመጣ ፣ምን እንደቸገረው፣ ምኑን እንዳመመው እና መድሀኒቱ ምን እንደሆነ እናም የት እንደሚገኝ ላንተ በቀጥታ ይነግርሃል አንተም ለግለሰቡ ትነግረዋለህ። አየህ ቃሪን ጥቅሙ የላቀ ነው በህይወት ላለህ እስካለህ። ይህ ብዙ ጠቢባን ኡልማዎች የሚያውቁት  እና የሚጠቀሙበት መንገድ ነውና። @ayne_kulu 🇪🇹
إظهار الكل...
👍 3
ዕፀ ደብተራ ‼️‼️ፍቅረኛዋ ጥሏት ለሄደ ሰው እግረ መልስ ፣ፍታህወአድኖህ የሚከተለው ታላቅ አስማት በመጠን ትንሽ ቢመስልም ሀይሉ ግን አስደናቂ ነው።አስማት አስማትነቱ እያንዳንዱ ፊደላትና ሙሉ ስም  ወይም አስማት በትክክል ያለ ምንም ግድፈት የተፃፈ ከሆነ ነዉ።ይህ የሚከተለው አስማት ያለ ምንም ግድፈት ነው።  ፍፁም ፍቱን ነዉ አስማቱ ። አስማቱ ጥቅሞቹ ወይም ገቢሮቹ የሚከተሉት ናቸዉ። "አምዲዲክ  ዲኦ ዲኦ  ዬሱስ" ገቢሮቹ፡ 1-ጥሎ የሄደሰዉ ተመልሶ እንዲመጣ በቀኝ መዳፍህ ላይ አስማቱን በእኩለ ለሊት ሰባት ግዜ ወይም አርባ ዘጠኝ ግዜ ድገም እና በደገምክበት መዳፍህ የቤትህን መስኮት የታችኛዉን ክፍል መታመታ አድርግ ሰባት ግዜ ። 2-ማንኛዉንም ድግምት እርግማን ለማክሸፍ እንዲሁም የተሰማህን ህመም ለመፈወስ ለአንተም ይሁን ለሌሎች ማድረግ ብትፈልግ አስማቱን በጭንቅላት መሀል አናት ላይ ሰባት ወይም አርባ ዘጠኝ ግዜ ደግመህ እፍ እፍ በልበት ።ለአንተ ከሆነ ሌሎች እንዲያ ያድርጉልህ ። 3-እባብ ባየህ ግዜ እንዳይነድፍህ እንዳይተናኮልህ ሦስት ግዜ አስማቱን በል ወይም በመፋቂያ ወይም በአንድ ነገር ላይ አስማቱን አርባ ዘጠኝ ግዜ ደግመህ በኪስህ ያዝ። 4-ይህንን አስማት የምንጭ ውሀ ቀድተህ በቃ አድርገህ ወይም በአዲስ መስታወት ላይ አርባ ዘጠኝ ግዜ ብትደግም የጠላትህን መልክ በውሃው ውስጥ ወይም በመስታወት ላይ ያሳይሀል። ‼️**የዚህ አስማት እና ገቢሮቹ ዋና ሚስጥራዊ ቁልፍ አስማቱን በምትደግም ግዜ በማንሾካሾክ ድምፅ ብቻነው የሚደገመው።በፍፁም ከፍ ባለድምፅ ቢደገም አይሰራም።ቁልፉ በማንሾካሾክ መድገም ነው። ይህ ጥበብ በዚህ አግኝታችሁ ስተገብሩ ለኔ ቢጤ ወይም ረደት ለሌላቸው አምስትም አስር ብርም ለግሱ። @ayne_kulu 🇪🇹 @ayne_kulu 🇪🇹
إظهار الكل...
👍 9 2
ዕፀ ደብተራ ‼️ ‼️የሰው ዓይን (ቡዳ) ማናገሪያ አሪቲ (ጭቁኝ) ከነጭ ሽንኩርት ጋር  ደባልቆ ፈጭቶ የተጨመቀውን ውህድ ውሃ የሰው ዓይን ወይም ቡዳ ለበላው በግራ አፍንጫው ቢያደርጉ ቡዳው ይናገራል ይጮሃል ገዝተህ እንዲለቅ አድርገው። **ፍቱን ነው። @ayne_kulu
إظهار الكل...
2🎉 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.