cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🔮ምክር📝ለሰለፊያ ወጣቶች! وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَارْكَعُوا مَعَ الرَّاكِعِينَ

➩ኢብኑ ኡሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ፦ 📚➷ቀብር የጨለማ ሀገር ነው። ቀብር ውስጥ የሚታይ ፀሀይም ሆነ ጨረቃ የለም። ነገር ግን አንድ ሰው ከሰጋጆች ከነበረ አሏህ ቀብሩን ብርሀን ያደርግለታል። https://t.me/UMUHuzaifa2666

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
804
المشتركون
+224 ساعات
+47 أيام
+1630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

👉 ዓሹራእና ምንዳውዓሹራእ ማለት የሙሐረም ወር 10ኛ ቀን ሲሆን ከነብዩላሂ ሙሳ አስገራሚ ታሪኮች አንዱን የሚያስታውሰን ቀን ነው። ➧ ነብዩላሂ ሙሳ ፊርዓውን ህፃናቶችን በሚያርድበት ዘመን ተወልደው በራሱ ቤት እንዲያድጉ አላህ ያሻውን ሰሪ የሆነው ጌታ አደረገ። ይህም ፊርዓውን በይተል መቅዲስ አካባቢ የተነሳ እሳት የግብፅን ምድር ሲያጠፋ በህልሙ ያይና ለጠንቋዮቹና ድግምተኞቹ ሲነግራቸው ከእስራኤላዊያን የሚወለድ ህፃን የንግስናው  መጥፊያ ሰበብ እንደሚሆን ነግሩት። ፊርዓውንም ከሚወለዱት ህፃናት ሴቶቹ ቀርተው ወንዶቹ እንዲታረዱ አዘዘ።ይህ ነገር አገልጋይ እንዳያሳጣቸው የፈሩት ግብፃዊያን ፊርዓው ዘንድ ሄደው አቤቱታ ሲያቀርቡ አንድ አመት የሚወለደው ተትቶ በሌላኛው አመት የሚወለደው እንዲታረድ አዘዘ። የአላህ ፍላጎት ሆነና ነብዩላሂ ሙሳ ወንድ ህፃናቶች በሚታረዱበት አመት ተወለዱ። የእስራኢላዊያን ህፃናት መወለድ የሚጠባበቁ ሰራዊቶች በመኖራቸው የነብዩላሂ ሙሳ እናት ጊዜዋ በመድረሱና አመቱ ወንድ ህፃናት የሚታረዱበት በመሆኑ ጭንቅ ውስጥ ገባች። የተፈራው አልቀረም ህፃኑ ተወለደ። እናት ምን ይዋጣት!!!? ↪️ አላህ ሁሉን ቻይ መሆኑን ሊያሳያት በሳጥን አድርገሽ ወደ ቀይ ባህር ወርውሪው የሚል መልእክት እንዲመጣላት አደረገ። ወረወረችውም። ወደ አላህም ፍፁም ተማፀነች። አላህም ልጇን እንደሚመልስላት ቃል ገባላት። ባህሩ ሳጥኑን ወደ ፊርዓውን ቤተመንግስት እየነዳ አደረሰው። የፊርዓው አገልጋይ ሴቶች ሳጥኑን አገኙት ሲከፍቱት የሚያምር ህፃን ነው!!!። ወደ ቤተመንግስት ተወሰደ። ኣሲያ የፊርዓው ባለቤት የአይናችን ማረፊያ ይሆናል ልጅ አድርገን እንያዘው አትግደለው አለችው ተቀበላት።     ➲ ረሃብ ይዞት ሲያለቅስ የሚቀርብለት ጡት በሙሉ እንቢ አለ። ምናልባት የሚስማማው ጡት ከተገኘ ብለው ሴቶችን ሲፈለጉ እህታቸው ማንነቷን ደብቃ አንድ ህፃናት በሙሉ ጡቷን የሚጠቡላት ሴት ላመላክታችሁ ወይ ብላ ጠየቀች አው አሉ። እናታቸው ወደ ቤተመንግስት መጣች!!!። ሱብሃናላህ በፊርዓውን ቤተመንግስት በእሱ ተንከባካቢነት በእናታቸው ጡት እንዲያድጉ አላህ አደረገ። በወቅቱ እስራኤላዊያን በቂብጦች የመከራ ገፈት ይጎነጩ ነበር። አላህ በሙሐረም 10ኛ ቀን ፊርዓውንን ከነሰራዊቱ አጥፍቶ እሳቸውንና ህዝቦቻቸውን ነጃ አወጣ። የአላህ መልእክተኛ ነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ወደ መዲና ሲሄዱ አይሁዶች ይህን ቀን ሲፆሙ አገኙዋቸው። ለምንድነው የምትፆሙት ብለው ሲጠይቁዋቸው ይህ ቀንማ አላህ ፊርዓውን አጥፍቶ ሙሳን ያዳነበት ቀን ነው። ለዚህ ነው የምንፆመው አሉዋቸው። እሳቸውም ለሙሳማ እኔ ከናንተ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው መፆም ጀመሩ ተከታዮቻቸውንም እንዲፆሙ አዘዙ። ያለውንም ምንዳ ሲናገሩ እንዲህ አሉ:– "صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ"     رواه مسلم   ( 1162). "የዓረፋ ቀንን መፆም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የዓሹራእ ቀንን መፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።" ♻️ አዩዶችን ለመኻለፍ አላህ ካቆየኝ የሚመጣውን አመት ዘጠነኛውን የሙሐረም ቀን እፆማለሁ ብለው ነበር። ከዚህ በመነሳት የሙሐረምን ዘጠነኛና አስረኛ ቀን መፆም ይወደዳል። አብዛኛዎች ፉቀሃዎች ዘጠነኛ አስረኛና አስራ አንደኛውን ቀን መፆም ሱና ነው ይላሉ። ነገር ግን ከመረጃ አንፃር ዘጠነኛና አስረኛው ነው። ይህ ካልተቻለ አስረኛና አስራ አንደኛውን በመፆም አይሁዶችን መኻለፍ ይቻላል።         አላህ ይወፍቀን። ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር በድጋሚ የተለቀቀ። http://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🏝 የሴቶችን ተፈጥሯዊ ደም የተመለከተ ማብራሪያ ➶➶➶➶       ➘➘➘➘ ↪️ ክ ፍ ል 03 ↩️        ➚➚➚➚         🏝 العنوان:- ➘➴➷ ✉️ رسالة في الدماء الطبيعية للنساء 🏝 ርዕስ :- ➘➴➷ ✉️ ሪሳለቱን ፊ-ዲማኢ አጦብኢያህ ሊኒሳእ ❴የሴቶች ተፈጥሯዊ ደምን ማለትም #የወር_አበባ ደም፣ #የወሊድ ደም፣ #የበሽታ ደም፣ የምትዳስስ ጥሩ ሪሳላህ!❵ 📝  بقلم فضيلة الشيخ العلامة: محمد بن صالح العثيمين - رحمه الله 📝 አዘጋጅ፦ ታላቁ ዓሊም አሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል’ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸው!!! 🎙 በወንድም አቡ  ዒምራን 📮 የኪታቡ pdf ➴➴➴ https://t.me/AbuImranAselefy/8744 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/AbuImranAselefy/8897 https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy
إظهار الكل...
03_رِسَالَةٌ_فِي_الدِّمَاءِ_الطَّبِيعِيَّةِ_لِلنِّسَاءِ.mp321.34 MB
እንዳትወድቂ ከፈለግሽ ከማንም ፍጥረት ትከሻ ላይ አትገደፊ ሁሌም ቢሆን መመኪያሽ (መጠጊያሽ) አሏህ ﷻ ብቻ እና ብቻ ይሁን!! ✒️......................
إظهار الكل...
👍 1
(سورة الكهف)  (ሙሉ ሱራ ) የቻለ ይቅራ 📖 ያልቻለ ያዳምጥ 🌸🎧 የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል የጁመአ ቀን ሱረቱል ካህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁመዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ https://t.me/UmuAmar_UmuManas
إظهار الكل...
4_5879592791209678033.mp37.57 MB
👍 2
ልዩ እና ገራሚ ሙሐደራ 🔍🔍🔍🔍🔍🔍 እያንዳንዱ ሰው ስላለበት አማና ✅ አደራን የመወጣት አስፈላጊነት ➜ ይህ ሙሐደራ    ➧ ኡስታዝ ያለበት አደራ    ➧ ሚስት ያለባት አማና    ➧ ዶክተር ስላለበት አማና    ➧ ተማሪ ስላለበት አደራ    ➧ ሰራተኞች ስላለባቸው አማና    ➧ የሀገር አስተዳዳሪ ስላለበት አማና    ➧ በየትኛውም ሙያ፤ እድሜ ሁኔታ ወዘተ ያለ ማንኛውም ሰው ስላለበት ሀላፊነት በዝርዝር ተዳሷል።    ➹ ሌሎችም በሚገርም አቀራረብ ተካተዋል። 🎙 በተከበሩ ሸይኽ አቡ ዐብዱልሃሊም ዐብዱልሐሚድ ብን  ያሲን አል'ለተሚይ አሱኒይ አስሰ'ለፊይ አላህ ይጠብቃቸው 🏝 ይሄን ሁሉ ትንታኔ ያቀረቡት ሸይኹ በሂፍዛቸው ነው። በጣም ትልቅ ብቃት አላህ ሰጥቷቸዋል። በጣም አስገራሚ አሊም ናቸው። ▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴ ⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩ 🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣  ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy ሀሳብ  ካለዎ  ⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/AbuImranAselefybot
إظهار الكل...
የዲን አማናዎችን መጠበቅ.mp327.58 MB
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
انــشروهــا فـي قــناتكـم أيــها السـلفـيون بـــــــارك الله فــيكـم
إظهار الكل...
💯 1
ቆንጆ ምላስ ፀጋ ነው ከምትናገረው አንድ ቃል በፊት አንድ ሺህ ጊዜ ማሰብ  መቻል ከአላህ የሆነ ስጦታ ነው  የሰዎችን ተፈጥሮና የግንዛቤ አቅምን በማስተዋል የተገራ አንደበት የተባረከ ነው  አንዳንድ ሰዎች አሉ… ለንግግራቸው ለከት የሌላቸውና ሁኔታን የማያገናዝቡ  ወይ የንግግር ለዛ የላቸው ወይ  ቃላት አይመርጡ…  በቃ እንደወረዱ
إظهار الكل...
☑️ መተኛትህ ካልቀረ በሱና ላይ ሁነህ ተኛ !! ➰➰➰➰➰➰➰➰➰➰➰➰ ✅ ቻት እያደረክ ከዛም ከዚህ ትርፍ ወሬ እየተላላክ አልፎም ከአጅ ነብይ ጋር በሀራም እያወራህ ከምትተኛ፦ የመኝታ ዚክር ብለህ ውዱእ አድርገህ ወደ አላህ ተመልሰህ የበደለህን ይቅር ብለህ ↪️ በመተኛት ሱናውን ህያው አድርግ። ✅ ልብ በል እንቅልፍ ትንሹ ሞት መሆኑን አስታውስ ተኝተህ በዛው ልትቀር ትችላለህ። የውመል ቂያማ በሞትክበት ሁኔታ ነው የምትቀሰቀሰው በሀራም ተግባር ላይ ሞተህ በሚያስጠላ ሁኔታ ከምትቀሰቀስ በሱና ላይ ተኝተህ በሱና ላይ መቀስቀስን ምረጥ። ➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘ https://t.me/abushuayb1
إظهار الكل...
Abu shuayb (Channel)

القناة الرسمية للأخ أبي شعيبٍ السلفيِّ

✍በጋብቻ ዙሪያ የተደረገ ዳሰሳ 🎙 በኡስታዝ አቡ ፊርዶወስ አላህ ይጠብቃው! 🗒 ዛሬ እሁድ ምሽት ሰኔ  2016 E.C በአልፋሩቅ የሰለፍዮች መድረሳ የተደረገ ሙሐደራ ➴➘➴➘ https://t.me/alfarukmedrasa
إظهار الكل...
4_6035222576152712112.mp313.55 MB
👍 1
«ሴት እንዳትበልጥህ ከፈለክ ጠንክረህ ተማር  !    አንዳንዱ ወንድም ሴት አታስተምረኝም ይላል አቦ አትጃጃልብኝ ታዳ ሴት እንድታስተምርህ ካልፈለክ መማርነዋ ተምረህ ብለጣት ምን ሁነሃል   ጠንካራዋን ፈልገህ እንዳበልጥህ ፈርተህ እረግ ሁለት ወዶ ይሆናልን ?እረ በጭራሽ  ወይ ቀጥ ብለህ ተምረህ ማሳየት ነው ወይ  የመረጥካትን መምሰል ነው!?    #የምን መቀዋለል   ነው ?
إظهار الكل...
👍 4
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.