cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

𝐈𝐛𝐧𝐮𝐨𝐮𝐦𝐞𝐫𝐨𝐟𝐟𝐢𝐜𝐢𝐚𝐥𝐜𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

በዚህ ቻናል የተለያዩ የሸኾች የኡስታዞች • ቁም ነገር አዘል ፅሁፎችን •ፈትዋዎችን •መረጃዎችን እና ኢስላምን የሚጠቅሙ ነገራቶች ይለቀቁበታል: : ብቻ ተቀላቀሉ @ibnuomer አስተያየት ካላቹ @ibnuoumerrr

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
737
المشتركون
-324 ساعات
-97 أيام
+1130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ሀጅ ለማድረግ ከእንግሊዝ ወደ መዲና በብስክሌት የተደረገ ጉዞ! … (ሀሩን ሚድያ ፦ግንቦት 23/2016) … ሁለት ሁጃጆች ከአውሮፓዊቷ ሀገር እንግሊዝ ወደ አረበ ሀገረዋ ሳዑዲ አረቢያ በብስክሌት ጉዞ በማድረግ በርካታ ወራቶችንና ኪሎሜትሮችን በማቋረጥ ሀጅ ለመፈፀም በዛሬው ዕለት መዲና ገብተዋል። … ሁጃጆችም መዲና ከተማ ሲደረሱ የተሰማቸውን ደስታ የገለፁ ሲሆን በመዲና ህዝብም አቀባበል ተደርጎላቸዋል። … ©ሀሩን ሚድያ
إظهار الكل...
💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
እንዲህ ናት ዱንያ‼ ============== ✍ «ልክ በአሁኗ ሰዓት ነገ ማታ ለሐጅ በረራ የነበራቸዉን የአንድ ትልቅ ሰው መቃብር እየቆፈርን ነው። ድንገት ነው ሕልፈታቸው። ዱንያ እንዲህ ናት። እኛ ብዙ እናስባለን፣ እናቅዳለን፤ አላህም የራሱ መሻት አለው፣ የሚሆነው ግን አላህ የሻው ብቻ ነው። ለሐጅ ቲኬት ቆረጥክ ማለት ሄድክ ማለት አይደለም ። ከቆረጥከው ቲኬት የአኺራ ጥሪ ቲኬት ቀድሞ ሊመጣ ይችላል ። ለዚህም ነው ሞትን ልክ የሆነ አገር ሊሄድ ብሎ ቲኬት ቆርጦ እንደሚጠባበቅ ሰው ሁሌም ዝግጁ ሆነን መጠበቅ የሚገባን። ሰው ከንቱ!!» ©: ሙሐመድ ሰይድ
إظهار الكل...
💯 3
Photo unavailableShow in Telegram
እንዲህ ናት ዱንያ‼ ============== ✍ «ልክ በአሁኗ ሰዓት ነገ ማታ ለሐጅ በረራ የነበራቸዉን የአንድ ትልቅ ሰው መቃብር እየቆፈርን ነው። ድንገት ነው ሕልፈታቸው። ዱንያ እንዲህ ናት። እኛ ብዙ እናስባለን፣ እናቅዳለን፤ አላህም የራሱ መሻት አለው፣ የሚሆነው ግን አላህ የሻው ብቻ ነው። ለሐጅ ቲኬት ቆረጥክ ማለት ሄድክ ማለት አይደለም ። ከቆረጥከው ቲኬት የአኺራ ጥሪ ቲኬት ቀድሞ ሊመጣ ይችላል ። ለዚህም ነው ሞትን ልክ የሆነ አገር ሊሄድ ብሎ ቲኬት ቆርጦ እንደሚጠባበቅ ሰው ሁሌም ዝግጁ ሆነን መጠበቅ የሚገባን። ሰው ከንቱ!!» ©: ሙሐመድ ሰይድ
إظهار الكل...
00:25
Video unavailableShow in Telegram
የቀልብ መረጋጊያ 🫀 #ቁርአን @ibnuomer
إظهار الكل...
3
Photo unavailableShow in Telegram
ሀቅ ነው!!
إظهار الكل...
3👏 1
كيف لا يكون لك وقت لمن خلق ازمن እንዴት ዘመንን ለፈጠረው ፈጣሪ ጊዜ አይኖርህም የቴሌግራም ቻናል : @ibnuomer
إظهار الكل...
3
ጤነኛው "እብድ" በሐሩን አልረሺድ ኸሊፋ ዘመን በህሉል የተሰኘ አንድ ''እብድ'' ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ''እብዱ'' በህሉል መቃብር ላይ ተቀምጦ ኸሊፋው ሐሩን አልረሺድ በአጠገቡ አለፈ። ከዚያም ሐሩን ለበህሉል በንቀት ንግግር እንዲህ አለው፡ "አንተ እብድ ሆይ! መቼ ይሁን ጤነኛ የምትሆነው?" በህሉልም ከተቀመጠበት ተነሳና ረዥም ዛፍ ላይ ወጣ። ከዚያም ጮኽ ብሎ ፡ "አንተ ሐሩን ሆይ! አንተ እብድ ሆይ! መቼ ይሁን ጤነኛ የምትሆነው?" አለው መልሶ ወዲያው ሐሩንም በቅሎው ላይ እንደተቀመጠ ወደ ዛፉ መጣና " እኔ ነኝ እብድ ወይንስ መቃብር ላይ የምትቀመጠው አንተ?" አለው ለበህሉል በህሉልም ፡ " ጤነኛውማ እኔ ነኝ" አለ "እንዴት ሆኖ?" ብሎ ጠየቀ ሐሩን በህሉልም ወደ ሐሩን ሕንፃዎች እያመላከተ፡ "እኔኮ ያኛው (ሕንፃ) ጠፊ መሆኑን አውቃለሁ።" ደግሞ ወደ ቀብሩ አመላከተና ፡ " ይህ ደግሞ (ቀብር) ዘውታሪ መሆኑን አውቃልሁ።" ካለ በኃላ '' ከዚያ (ከዱንያ) በፊት ይህን (አኼራዬን) ገነባሁ። አንተ ግን ያንን (ዱንያን) ገነባህና ይህንን (አኼራህን) አፈረስክ። ስለዚህ ከገንባሀው ወደ አፈረስከው መዘዋወርን ትጠላለህ። መቅረት የሌለው ጉዞ መሆኑን ከማወቅህ ጋር። " ከዚያም አስከትሎ . . " እንደው ንገረኝ እስኪ ታዲያ እብዱ ማን ነው?" ሐሩንም በሰማው ነገር ተርገፈገፈ ፤ ፂሙ እስኪረጥብ ድረስም አለቀሰ። ከዚያም እንዲህ አለው ፡ " በአላህ ይሁንብኝ! እውነት ተናገርክ!" ከዚያም አስከትሎም " በህሉል ሆይ! እስኪ ጨምርልኝ" አለው በህሉልም ፡ " የአላህ መፅሃፍ (ቁርአን) በቂህ ነውና እሱን ጠበቅ አድርገህ ያዘው!" ሐሩንም ፡ "የማስፈፅምልህ ጉዳይ ይኖርሃልን?" በህሉልም ፡ "አዎን! ሶስት ጉዳዮች ይኖሩኛል። እነዚህን ጉዳዮች ከፈፀምክልኝ አመሰግንሃልሁ" አለው ሐሩንም፡ "ጠይቀኝ" ሲለው በህሉል ፡ "እድሜ ልትጨምርልኝ ትችላለህን?" ሐሩን፡ "አልችልም" ብሎ መለሰ በህሉል፡ " ከሞት መላዕክት ልትከላከልልኝ ትችላለህን?" "አልችልም" አለ ሐሩን " ጀነት ልታስገባኝና ከእሳት ልታርቀኝ ትችላለህን?" ብሎ ሲጠይቅ ሐሩን፡ "አልችልም" ብሎ መለሰ በህሉልም እንዲህ አለ ፡ " እወቅ! አንተ ተገዢ እንጂ ንጉስ አይደለህም። በመሆኑም አንተ ዘንድ ምንም ጉዳይ የለኝም።" አለው ። (ምንጭ ፡ ዑቀላኡል መጃኒን) @ibnuomer
إظهار الكل...
5👍 2
ሰላቱል-ፈጅር ደስታና አጅር 💥ሰላት የኢማንና ክህደት መለያ ታላቅ ዒባዳህ ነው፤ሰላት የማይሰግድ ሰው ኢስላም ላይ ቦታና ድርሻ የለውም። 💥ሁሉም ሰላቶች በአግባቡ ከተሰገዱ ወደ አላህ የሚያቃርቡና ብዙ ዱንያዊም ኣኼራዊም ጥቅሞችን የሚያስገኙ ከመሆናቸውም ጋር ፈጅር ሰላት ግን ደረጃና ጥቅሙ ይበልጥ ላቅ ያለ ነው። 🔅ፈጅር ሰላትን በሰዓትና በስርዓቱ መስገድ ከሙናፊቅነት ያርቃል፣ በአላህ ጥበቃ ስር ያደርጋል። 🔅ፈጅርን በጀማዓህ መስገድ ሌሊቱን በሙሉ የለይል ሰላት ሲሰግድ ያደረን ሰው ምንዳ ያስገኛል። 🔅 ፈጅርን በስርዓቱ የሚሰግድ ሰው ቀኑን ሙሉ ልቡ ተረጋግቶ፣ በአላህ ተጠብቆ፣ ድብርትና ሸይጣን ከሱ ርቆ፣ ሌሎች ሰላቶችንም በአግባቡ ለመስገድ ታድሎ ይውላል።   🔅በተቃራኒው ደግሞ ፈጅር ሰላትን በአግባቡ የማይሰግድ ሰው ቀኑን ሙሉ ተጫጭኖትና ደብሮት፣ ደስታ ርቆት፣ ሌሎች ሰላቶች ላይም እየተዘናጋ ይውላል። 🔅ገና ከመንጋቱ ፈጅር ሰላት ላይ ቁርኣን መቅራትና መስማት የሙእሚን የቀን ሙሉ የልብ ቀለብ፣ የትም የማይገኝ ደስታ፣ ልዩ የንቃትና የጉልበት ምንጭ ነው። 🔅ፈጅር ሰላትን በአግባቡ በመስገድ እነዚህንና መሰል ጥቅሞችን ማግነት እየተቻለ ፍራሽና እንቅልፍን አስበልጦ በስርዓቱ መስገድንና ጀማዓን መተው ትልቅ ኪሳራና ሞኝነት ነው። አላህ መልካሙን ሁሉ ካገራላቸውና የዒባዳህ ጣዕምን ከታደሉ ባርያዎቹ ያድርገን። -ኣሚን!! ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ረቡዕ 25/2/1444 ዓ.ሂ @ibnuomer
إظهار الكل...
👍 2 2💯 2
ራሀቱል ቀልብ ❤️‍🩹 هذه هي ادنيا لعب ولهو @ibnuomer
إظهار الكل...
4
ደስታን አላህ ሀራም ባደረገብክ ነገር ላይ አትፈልገው :: ወንጀል ጊዜያዊ ደስታ የዘላለም ፀፀት ነው : :
إظهار الكل...
3