ar
Feedback
Joseph Math Tutor

Joseph Math Tutor

الذهاب إلى القناة على Telegram

Hello, welcome to Joseph Math Tutor channel! https://youtu.be/D8K0MVqynVA?si=y_uFeHG7awC1oX9Y Subscribe our youtube channel On tiktok : josephmathtutor Owner: Yosef Adefris @yosef_2580

إظهار المزيد
1 763
المشتركون
+324 ساعات
+387 أيام
+9030 أيام
أرشيف المشاركات
#ASTU #NG - Non Grade NG ምንድነው? ምን ሲሆን ነው NG የሚሰጠው?? ከጠየቃችኋቸው ጥያቄዎች መካከል ይሄ ጥያቄ ይገኛል። 👉 በአጭሩ NG የሚሰጣችሁ የ continuous assessment ጉድለት ካለባችሁ ነው። ለምሳሌ በተለያየ መንገድ Quiz ወይ ደሞ Test ካመለጣችሁ እና ከመምህራችሁ ጋር ተነጋግራችሁ ካላስተካከላችሁ ግሬዳችሁ NG ይሆናል። ምናልባት quiz አምልጧችሁ "ከ 5 ነው ይቅር" ብላችሁ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እነሱ 0/5 ሳይሆን NG ነው ሚያደርጉት።   👉 አንዳንዱ አስተማሪ quiz or test ምናምን ያልተፈተነ ወይ ደሞ assignment ያላስገባ ተማሪ ያናግረኝ ይልና ስታናግሩት ያስተካክላል። አንዳንድ አስተማሪ ደግሞ ዝም ነው ሚለው ፣ አይናገርም ፤ ከዚያ NG አድርጎት እርፍ 🫠። 👉 ስለዚህ እንደዚህ አይነት የ continuous assessment ጉድለት ያለባችሁ ተማሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ሁሉንም ነገር ካልጨረሳችሁ ተበላችሁ ማለት ነው። ከሚቀጥለው ሳምንት ውጪ አስተማሪዎችን ማግኘት ከባድ ነው። አስታውሱ ☝️: "F" Grade ከ "NG" ይሻላል።

#ASTU 📚 library 1-Central Library 2-Applied Library 3-Liberal arts library 4-Post graduate library 5-Females library

Repost from Top Students
#ASTU ለምትገቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ 🔥 ✅ ባለፈው አመት ከ675 በላይ ተማሪዎችን ሲያስጠና የቆየው Joseph Math Tutorial በዚህም ዓመት ለ2018 freshman ተማሪዎች ኮርሶች
+1
#ASTU ለምትገቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ 🔥    ✅ ባለፈው አመት ከ675 በላይ ተማሪዎችን ሲያስጠና የቆየው Joseph Math Tutorial በዚህም ዓመት ለ2018 freshman ተማሪዎች ኮርሶችን በመጨመር ለማስጠናት ዝግጅቱን ጨርሶ ምዝገባ ጀምሯል።       ✍ ለ2ኛ አመት ተማሪዎች ምዝገባው ሊጠናቀቅ 6 ቀናት ብቻ ቀርተዋል። ለ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል።      📍 ግቢ ከገባችሁ በኃላ ለምትፈተኑት FAST TRACK EXAM ለ1 ሳምንት ሙሉ Applied math I እና General physics ለማስጠናት ምዝገባ ጀምሯል።        📊  ለተጨማሪ መረጃ እና ለመመዝገብ እንዲሁም የ ASTU freshman course ሞጁሎችን ለማግኘት ከዚህ በታች ባሉት አድራሻዎች ይጠቀሙ👇👇👇 👉Group:-  @astututorials 👉User:- @yosef_2580 👉YouTube:- https://youtu.be/_4mnS1FnMpg?si=oVaxgj7aHZRRX_xV 👉 Contact Us 0911708941/0910775924 👉ቦታ:-ASTU block 515 (space-A)

መልካም ጊዜ👍👍👍

እነዚህ ሁሉ መረጃዎች ገብታችሁ እስክትወጡ ይጠቅሟችኋልና share ማድረግ አትርሱ ASTU ለሚገቡ

#FastTrack #SpecialExam 1⃣.ፈተናዉ መቼ ይሰጣል? ፍሬሾች ልክ ግቢ ስትገቡ ከሁለት ወይም ከሶስት ሳምንት ቧኃላ ፈተናዉን መፈተን ለምትፈልጉ ተማሪዎች ማስታወቂያ ይወጣል ። ከዛ fast track መፈተን የምትፈልጉትን subject ትመርጣላችሁ ከ Chemistry, Maths, Physics ሶስቱንም ተፈትኖ ያለፈ ተማሪ pre enginering ሳይማር ቀጥታ 2ኛ አመት መሆን ይችላል (በ3ቱም ያለፈ ብቻ) ። 2⃣. ሶስቱንም subject ከ80 በላይ ባላመጣስ ብያንስ በ1ንዱ ባልፍስ ?  ሶስቱንም መፈተን አልፈልግም(የፈለኩትን ልፈተን) የሚል ተማሪ ወይም ደግሞ ሶስቱንም ተፈትኖ 1ዱን ወይም 2ቱን ትምህርቶች ብቻ ከ80 በላይ ያመጣ ተማሪ አንደኛ አመት ሆኖ ግን ከ80 በላይ ያመጣዉን subject class ገብቶ መማር ሳይጠበቅበት ዉጤቱ ይያዝለታል ። 3⃣. የከዚህ በፊት ፈተናዎች አሉ ? fast track በጣም ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ነዉ የምሰጠዉ ፎቶ ለማንሳት ማንም ሰዉ አይችልም ። ስለዚህ የሉም። 4⃣. የፈተናዎቹን ይዘት ምንድናቸው? የ2015 fast track ፈተና ይዘት ልንገራችሁ 👉Applied maths • 25 ጥያቄ አከባቢ ነበር ... 13 ባዶ ቦታ መሙላት , 12 workout  .... workout part • Matrix (determinant, inverse, equations) • Proving Continuity of functions • Application of derivatives (local maxima,minima, critical numbers, rates) • Integrations (substitution, by parts... • new concept blank space lay Hyperbolic function. 👉 Chemistry • 60 የምርጫ ጥያቄዎች ነበሩ ... እንደ ማትሪክ አይነት 👉Physics • 50 የምርጫ ጥያቄ .... ግን ሙሉ ጥያቄዎች workout ናቸው ... outstanding ያልሆነ ተማሪ ሰዓት ላይበቃው ይችላል። 5⃣. ፈተናዉ ከባድ ነዉ ወይ? ብዙም ከባድ የሚባል አይደለም ! ብዙ ተማሪዎች እንደምሉት ፈተናዉ የሚሰራ አይነት ነዉ ። physics ግን ምን አልባት..... 🥶😬 6⃣. ምን አይነት ማቴሪያል እንጠቀም ? 11& 12ኛ ክፍል ስትጠቀሙበት የነበረዉን .... Astu የገባ ተማሪ ሁሉ ምያነበዉ ልቦ-ለድ አለ ደራሲዉን ካወቃችሁት Begashaw ይባላል (applied maths) እሱንም መጠቀም ትችላላችሁ። ይህ 👆 እስከአሁን የነበረው አሰራር ነው ... በዚህ አመት የሚቀየር ነገር ይኑር አይኑር አይታወቅም 🤷‍♂️

ወደ ዩኒቨርስቲው ዋና ዋና ዶክመንቶችን የኢንተራንስ ሰርተፍኬት ፣ ትራንስክሪብት እና የስምንተኛ ክፍል ካርድ የምታስገቡት ID ካርድ ስትወስዱ ነው። ለመመዝገብ temporary ሰርተፍኬት በቂ ነው። ስለዚህ አትጨናነቁ። ID ካርድ እስከምትወስዱ የተወሰነ ጊዜ ይፈጃል። በዛን ጊዜ ውስጥ የትምህርት ሚኒስቴር ሰርተፍኬት ይደርሳችኋል። ያኔ በኦርጅናሉ ሰርተፍኬት መመዝገብ ትችላላችሁ። ኦርጅናል ID ካርድ እስከምትወስዱ ድረስ የምትጠቀሙት temporary ID ካርድ ይሰጣችኋል። ካፌ ፣ ላይብረሪ የምትገቡት እሱን በመጠቀም ይሆናል። ስትመዘገቡ የምትነሱት ፎቶ ይኖራል። ዩኒቨርስቲው ነው ሚያነሳችሁ። ይህ የምትነሱት ፎቶ ግቢው እናንተን የሚያውቅበት ፎቶ ነው። በ ID ካርዳችሁ እና በፖርታላችሁ profile picture ላይ ይደረጋል።

ምን ታያላችሁ ❓ እኔ ለማዳ ነኝ ፤ አልነካችሁም። ፍሬሾች ናችሁ መሰለኝ ... እኔ ምፈልገው ተከባብሮ አብሮ መኖርን ብቻ ነው። — ከ ASTU ጅብ የተላለፈ መልዕክት 😂

በዓል ሲደርስ ከስንት ቀን በፊት ነው ምንወጣው ❓ 😅 You are about to join ASTU. But think you will celebrate your holidays. 🤔... maybe you might have listened to a motivational speaker saying "Think the impossible" 🤣🤣🤣 ምን መሰላችሁ ... ግቢው በዓል አያቅም። በእርግጥ ዝግጅት ግቢ ውስጥ ይዘጋጃል። ነገርግን ለበዓል ተብሎ የግቢው ካላንደር አይዛባም። ለምሳሌ በ 2017 ዓ.ም የሁለተኛ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስቴር ፋይናል ፈተና የሚሰጥበት ቀን በገና በዓል ላይ ይውላል። ለበዓል ብለው ትምህርት ይዘጋሉ የሚለውን አታስቡት።

Grade Calculate ማድረግ Grade እንዴት Calculate እንደሚደረግ አናውቅም post ይደረግልን ስትሉ ለነበራችሁ እንሆ አሰራሩን ይዤ ከች ብያለሁ 😊 Grade calculate ለማድረግ በመጀመሪያ 3 ነገሮችን ማወቅ ይጠበቅባችኋል:- እነሱም 1. የ እያንዳንዱን የትምህርት አይነት Crh (credit hours) In our case maths ብቻ ነው 4 crh ሌሎቹ 3 Crh ናቸው። Applied 1 ----------------- 4Crh English---------------------3Crh Physics--------------------3Crh Chemi----------------------3Crh Logic------------------------3Crh Python---------------------3Crh 2.በሁለተኛ ደረጃ ማወቅ የሚጠበቅባችሁ ነገር ደግሞ የእያንዳንዱ የ Grade ፊደላት ዋጋ ነው። ይሄም እንደሚከተለው ይሆናል A+ ---------- 4.0 A ------------ 4.0 A- ----------- 3.75 B+ ---------- 3.5 B ------------ 3.0 B- ----------- 2.75 C+ ---------- 2.5 C ------------2.0 C- -----------1.75 D ------------ 1 F ------------- 0 3. ሶስተኛ እና የመጨረሻው ደግሞ ማወቅ የሚጠበቅባችሁ ከመቶ ስንት ባመጣ እነዚህን ከላይ ነተጠቀሱትን Gradeኦች ይሰጠኛል የሚለውን ነው። ይሄም እንደሚከተለው ነው። 90 እና ከዛ በላይ = A+ 85 - 89 = A (85ትን እና 89ን ያካትታል) 80 - 84 = A- (80ን እና 84ትን ያካትታል) 75 - 79 = B+ (75ትን እና 79ን ያካትታል) 70 - 74 = B (70ን እና 74ትን ያካትታል) 65 - 69 = B-(65ትን እና 69ን ያካትታል) 60 - 64 = C+ (60ን እና 64ትን ያካትታል) 50 - 59 = C (50ን እና 59ን ያካትታል) 45 - 49 = C-(45ትን እና 49ን ያካትታል) 40 - 44 = D (40ን እና 44ትን ያካትታል) 39 እና ከዛ  በታች = F እሺ በስተመጨረሻ እንዴት አድርገን ነው Calculate ምናደርገው ❓... እሺ ለምሳሌ ተማሪ አየለች ተመስገን የሚከተለውን ውጤት አመጣች እንበል Maths 49.5 ( C- 🙆) መምህር ገነነ አዩን በጣም አበሳጭተዋታል😢 English 72 ( B  🐒) Physics 66 (B- Oops🙄) Chemi 94 ( A+...  chemoን እማ ተክናበታለች Logic 87  (A...አየሉ Logic ላይ ጥሩ ናት👏) Python 78 ( B+...Wow!) አሁን ምን እናረጋለን ... የ አዩን ውጤቶቾ በእያንዳንዱ ትምህርት Crh እናባዛቸዋለን Maths => 1.75 × 4 = 7 English => 3 × 3 = 9 Physics => 2.75 × 3 = 8.25 Chemistry => 4 × 3 = 12 Logic => 4 × 3 = 12 Pyhton => 3.5 × 3 = 10.5 ከዛ ተባዝተው የሚመጡትን ውጤቶች እንደምራቸዋለን 7 + 9 + 8.25 + 12 + 12 + 10.5 = 58.75 ተደምሮም የመጣልንን ውጤት ለ Crhኦቹ ድምር እናካፍለዋለን የ Crhኦቹ ድምር => 4 + 3 + 3 + 3 + 3 + 3 = 19 ስለዚህ 58.75/19 = 3.092 ( አየሉን እንዳይከፋት አስኪ 3.1 እንበልላት) The End 🤗 🙌

📒 ማስታወሻ/ደብተር 📔 እዚህ እንደፈለጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። እንደ high school ለእያንዳንዱ ትምህርት አንድ ደብተር ካላችሁም መብታችሁ ነው። ሁሉንም በአንድ ካላችሁም ትችላላችሁ። ዋናው ነገር የሚፃፍ ነገርን በትክክል ትፅፋላችሁ ወይ በቂ የሆነ ማስታወሻስ ትወስዳላችሁ ወይ የሚለው ነው። እኔ ምመክራችሁ ግን ባለ ብዙ subject ደብተር ግዙ። ይሄ በአንድ ላይ አራት እና አምስት subject የሚይዘውን ከገዛችሁ ምርጥ ነው። አስፈላጊ ሲሆን ሌላ ትጨምራላችሁ። ፁሁፍ እንደየአስተማሪው ነው። አንዳንዱ ሞጁሉን ይገለብጣል 😏 ... አንዳንዱ ደግሞ ብትለምኑትም ምንም አይፅፍም። ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ሁሉ ማይፅፍ አለ። በቃ ዝም ብሎ ይገባል ያወራል ከዛ ይወጣል ... እሱ ሲወጣ ሁልጊዜ ሰሌዳው ፅድት እንዳለ ነው 😅... እና እንደየራሳችሁ የንባብ ዘዴ ነው ማስታወሻ ሚያስፈልጋችሁ። በተለይ ደግሞ ወረቀት አስጠርዞ መጠቀም እዚህ ግቢ common ነው። ስለዚህ እንደሚመቻችሁ ማድረግ ትችላላችሁ። Pls አትጨናነቁ ... feel free!🤗

#ASTU #Grading_system (የ Grade ፊደላት ዋጋ) #Mark    #Letter_Grade   #Grade_Pt 1. (90 - 100)       A+                        4.00 2. (85 - 89)         A                           4.00 3. (80 - 84)         A-                          3.75 4. (75 - 79)         B+                         3.50 5. (70 - 74)         B                           3.00 6. (65 - 69)         B-                          2.75 7. (60 - 64)         C+                         2.50 8. (50 - 59)         C                           2.00 9. (45 - 49)         C-                          1.75 10. (40 - 44)       D                           1.00 11. (0 - 39)         F                            0.00 12.    I            Incomplete                   _ 13.  NG           Non Grade                   _

መምህራን 👨‍🏫 በምንም አይነት ሁኔታ ከአስተማሪ ጋር የማይሆን ነገር ውስጥ አትግቡ ፤ አትነካኩ። አስተማሪ አንዴ ከጠመዳችሁ አይፋታችሁም። Pls pls pls pls ከአስተማሪ ጋር ያላችሁን ግንኙነት በተቻለ መጠን መልካም ብቻ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት አድርጉ። አንዴ አይን ውስጥ ከገባችሁ ትቸገራላችሁ። አንዳንድ አስተማሪ ደግሞ መከራ በልታችሁ የምታመጡትን ግሬድ ሁሉ ገደል ሊከትባችሁ ይችላል። ስለዚህ ተጠንቀቁ። አስተማሪው በድሏችሁ እናንተ ይቅርታ ጠይቁ። "መብት አለኝ ፣ ሰርቼ ያገኘሁት ውጤቴ ነው ፣ ምን ያመጣል..." ምናምን የሚሉ ድንፋታዎች ገደል ከመክተት በስተቀር ምንም አይፈይዱም። በእርግጥ ብዙ ጊዜ የሚያናድድ ሁኔታ ሊገጥማችሁ ይችላል። ነገርግን እራሳችሁን በደንብ ተቆጣጠሩ። በሚገባ መምህራኖችን አክብሩ። ትልቅ ክብር ስጡአቸው። ትልቅ ሰው እየሆንኩ ነው 🫨 ፣ እራሴን መራለሁ እንጂ በማንም አልመራም 🫢፣ የራሴ ህግ ያለኝ 🤓 በራሴ ህግ የምመራ ሲግማ ነኝ 💀🤣... " ምናምን የሚሉ ቅዠቶች ውጤታቸው የማትፈልጉትን ነገር መማር ወይም ሻንጣ ተሸክሞ ወደ ቤት መሄድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ጠንቀቅ በሉ ፣ መምህራንን (ምንም አይነት ቢሆኑ) አክብሩአቸው ለማለት ያክል ነው።

#ASTU 🚪 የበር ቁልፍ 🔑 የዶርማችሁ በር ቁልፍ የሲሊንደሩ ቁልፍ ሲሆን ሎከር የምትቆልፉበት ደግሞ እንዲህ 🔐 አይነቱ ቁልፍ ነው። እናም ጠንከር ያለ የሎከር ቁልፍ ቢኖራችሁ ጥሩ ነው። የመጋዘን ቁልፍ ገዝታችሁ ደግሞ አልገባም እንዳይል 😁 ... ስለዚህ መጠነኛ ቁልፍ ግዙ።

#ASTU ፍሬሽማን ላይ ቻሌንጅ ሚያደርገው ብዙ ተማሪ ነው ወይስ ጥቂት ተማሪ ነው ❓ እውነት ለመናገር ሁሉም ተማሪ ማለት በሚቻል ደረጃ ጥሩ ውጤት ለማግኘት የማይፈነቅለው ድንጋይ ፣ የማይወጣው ተራራ ፣ የማይወርደው ሸለቆ የለም። ተኝቶ የሚያድር ተማሪ የለም። አስባችሁታል ስምንት / ዘጠኝ ሰዓት ላይ ከላይብረሪ እየወጣችሁ በዛን ሰዓት ለማንበብ የሚገባ ተማሪ ስታገኙ ... 🫢🤭 ስለዚህ ቻሌንጅ አለ እናም ጠንከር ብላችሁ መዋጋት ነው። 🫡 በእርግጠኝነት ታሸንፋላችሁ 🔥

#ASTU ክሊኒክ 🏥 ክሊኒክ የምትታከሙት በነፃ ነው። ምናልባት የግቢው ካፌ ምግብ ካሳመማችሁ እና ጨጓራችሁ ላይ ጉዳት የማስከተል እድል ካለው ግቢው ለጤንነታችሁ ቅድሚያ ስለሚሰጥ ስፔሻል ተመጋቢ እንድትሆኑ ያደርጋል። ስፔሻል ተመጋቢ ማለት ተማሪዎች ከሚመገቡት መደበኛ ምግብ በጥራቱ እጅግ ከፍ ያለ ምግብ የሚመገብ ማለት ነው። የቤት ምግብ በሉት። እንደውም ከቤትም ይበልጣል ይላሉ 😁። ስፔሻል ተመጋቢ ትንሽ ስለሆነ እጥር ምጥን አድርገው መስራቱን አዘጋጆቹ ተክነውበታል 👌። ከመደበኛው ምግብ በጣም ይለያል ፤ ጣዕሙም እንዲሁም ሁሉ ነገሩ ይለያል።

#ASTU ማታ ማታ እስከፈለጋችሁበት ሰዓት ድረስ ላይብረሪ መቆየት ትችላላችሁ። በእርግጥ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ይዘጋል እናም ጠዋት 2 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ማታ ላይ አንብባችሁ ስትመለሱ like 6 ፣ 7 ወይ 8 ሰዓት ላይ ብቻችሁን ባትሆኑ ይመረጣል። ሌባ አግኝቷችሁ ልትዘረፉ ትችላላችሁ (ይሄ ብዙም risk የለውም)። ምናልባት ጅቦቹ በብዛት አሉ በዛ ሰዓት። አይነኳችሁም። ግን ብቻችሁን ከሆናችሁ መፍራታችሁ እና መሸበራችሁ ስለማይቀር ከጓደኞቻችሁ ጋር ሆናችሁ አምሹ እንጂ ብቻችሁን አትሁኑ።