cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🎖🎖ሰው ሁን ከሰውም ሰው🎖🎖

For Any Comment Inbox Me @umbeya

إظهار المزيد
Ethiopia1 661Amharic1 328الفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
12 744
المشتركون
-1124 ساعات
-957 أيام
-45330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በልጅነታችሁ በቂ ፍቅርና ትኩረት እንዳላገኛችሁ የሚያሳዩ ምልክቶች 1/  ፍቅር እንዳይገባችሁ ወይም ማንም እንደማይወዳችሁ ይሰማችኋል 2/  ሰዎች ደስ እንዲላቸውና እንዲወዷችሁ ከመጠን በላይ ትጥራችሁ( Even  የማትፈልጉትን ነገር እንኳን ቢሆን ታደርጉታላችሁ ለመወደድና ትኩረትን ለማግኘት ስትሉ)😔 3/ ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶች ውስጥ ደጋግማችሁ ትገባላችሁ👬👭👬 4/  ሰዎች ከእናንተ ህይወት እንዳይወጡባችሁ የትኛውንም አይነት ዋጋ ትከፍላላችሁ😒 5/ ለስሜታችሁና ለራሳችሁ ቀይ መስመር አታበጁም ( ሰዎች ደጋግመው እየጎዷችሁ  Advantage እየወሰዱባችሁ እራሱ መልሳችሁ ዝምታ ነው) 6/ የተሰማችሁን በግልፅ መናገር ይከብዳችኋል (መጮህ😡፣ ማልቀስ😭፣ ለብቻ መሆንና ራሳችሁን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ማድረግ ይቀላችኋል) ከዚህ ውስጥ የሚሰማችሁ ስሜት ካለ ቆም ብላችሁ አስቡ። እወዳችኋለው😘😘😘 ✍በኃይሉ (ታዚ)
إظهار الكل...
👍 4🙏 2
በልጅነታችሁ በቂ ፍቅርና ትኩረት እንዳላገኛችሁ የሚያሳዩ ምልክቶች 1/  ፍቅር እንዳይገባችሁ ወይም ማንም እንደማይወዳችሁ ይሰማችኋል 2/  ሰዎች ደስ እንዲላቸውና እንዲወዷችሁ ከመጠን በላይ ትጥራችሁ( Even  የማትፈልጉትን ነገር እንኳን ቢሆን ታደርጉታላችሁ ለመወደድና ትኩረትን ለማግኘት ስትሉ)😔 3/ ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶች ውስጥ ደጋግማችሁ ትገባላችሁ👬👭👬 4/  ሰዎች ከእናንተ ህይወት እንዳይወጡባችሁ የትኛውንም አይነት ዋጋ ትከፍላላችሁ😒 5/ ለስሜታችሁና ለራሳችሁ ቀይ መስመር አታበጁም ( ሰዎች ደጋግመው እየጎዷችሁ  Advantage እየወሰዱባችሁ እራሱ መልሳችሁ ዝምታ ነው) 6/ የተሰማችሁን በግልፅ መናገር ይከብዳችኋል (መጮህ😡፣ ማልቀስ😭፣ ለብቻ መሆንና ራሳችሁን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ማድረግ ይቀላችኋል) ከዚህ ውስጥ የሚሰማችሁ ስሜት ካለ ቆም ብላችሁ አስቡ። እወዳችኋለው😘😘😘 ✍በኃይሉ (ታዚ)
إظهار الكل...
ራስን የማጥፋት ምልክቶች ( warnning signs of sucide) 1/ ከረጅም የድብርት ግዜ በኋላ ደስተኛና ተጫዋች መሆን 2/ በ social media ላይ ስለራስ ማጥፋትና ተስፋ መቁረጥ post ማድረግ 3/ ብቸኝነትና ራስን ከሌሎች መነጠል 4/ ለመሞት እንደሚፈልግ ሰው ማውራትና Act ማድረግ 5/ ባዶነት፣ ተስፋቢስነት፣ የመኖር ፍላጎትና የመኖር ምክንያት ማጣት 6/  ለሰዉ ሸክም እንደሆኑ መስማት፣ ማሰብና መናገር፣ እንዲሁም ደጋግሞ ይቅርታ መጠየቅ…… ንስሀ መግባት 7/ የመሞቻ መንገድ ማፈላለግ Search ማድረግና ( maybe In Social Media) ማቀድ 8/ የራስን እቃ ወይም ንብረት መስጠት፣ መለገስ 9/ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም መጨመር 10/ እንቅልፍ ማጣት ወይም አብዝቶ መተኛት ከእነዚህ ውስጥ የሚሰማችሁ ስሜት ካለ ቆም ብላችሁ ራሳችሁን ፈትሹ። አስቡ ዋጋ ያላችሁ ሰዎች ናችሁ። እወዳችኋለው😘😘😘 ✍በኃይሉ (ታዚ)
إظهار الكل...
👍 4🙏 1
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡ በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡ ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡ ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡ አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን? መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች … • ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት  ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡ • ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡   • አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡ እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ? dr eyob mamo ✍ታዚ
إظهار الكل...
👍 3
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡ በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡ ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡ ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡ አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን? መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች … • ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡ • ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡ • አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡ እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ? https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
إظهار الكل...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”
إظهار الكل...
7ቱ የሴቶች ውሸት / ለፈገግታ 1 "አንተኮ በጣም መልካም ሰዉ ነህ፡፡ አሪፍ ጓደኛህ እሆናለሁ" ትርጉም፡- ከጓደኝነት ዉጪ እኔን ፍቅረኛህ ለማድረግ እንዳትሞክረዉ! 2 "ፔሬድ ላይ ነኝ ራሴን አሞኛል" ትርጉም፡- ፔሬድ ላይ አይደለሁም... ራሴንም አላመመኝም፡፡ ግን ወሲብ መፈፀም ስለማልፈልግ እባክህን ተወኝ! 3 "አንተኮ ከኔ የተሻለ ሰው ይገባሃል!... እኔ ላንተ ምርቃት ነገር ነኝ!" ትርጉም፡-በል አርፈህ ተቀመጥ፡፡ ደባሪ ነህ ! ባይገርምህ አትመጥነኝም! 4 "ከ 5 ደቂቃ በኋላ እወጣለሁ፡፡" ትርጉም፡- በል 30 ደቂቃ ጨምርበት፡፡ ደፋር!   5 "እሺ በቃ ይቅር ብዬሃለሁ የኔ ዉድ!" ትርጉም፡-የእጅህን ካልሰጠዉህ እኔ ሰዉ አይደለሁም! ያደረከዉን የምረሳ አሻንጉሊትህ አይደለሁም! 6 "ደህና ነኝ" ትርጉም፡- ኤጭ ምን ይጨቀጭቀኛል...ገና መከራህን ትበላታለህ!   7 "ክብደቴን ለመቀነስ እራት አልበላም" ትርጉም፡- ለእናንተ ተውኩት.. ... እስኪ የተረሳ ካለ ጨምሩበት ✍ታዚ
إظهار الكل...
😁 7👏 3👍 2🥰 1
# መናገር ወይስ ማሰብ የቱ ይቅደም? በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል፤ ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት...፡፡ 1. አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፣ 2. አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፣ 3. አምስት መቶ ብር መክፈል፡፡ ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ ሽንኩርቱን እበላለሁ» አላቸው...፡፡ ከቀረበለት አንድ ኪሎ ሽንኩርት ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ጊዜ ዓይኑ ማልቀስ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ አልቻለም። ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና «መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡ ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም ፤ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡ «እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡ «አልቻልኩም» አላቸው፡፡ «ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡ «በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡ «ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት ይባላል። # ከመናገር ይልቅ ማሰብ ይቅደም!!! ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እውነት ነው የብዙዎቻችን ችግር ሳናስብ መናገር መልካም ቀን❤ https://t.me/gates5gatesjo https://t.me/gates5gates
إظهار الكل...
👍 7
የአእምሮ ህክምና እርዳታ እንዴት ማግኘት እንችላለን? በአዲስ አበባ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች  የአዕምሮ ህክምና ባለሙያዎች አሉ:: እነዚህ ባለሙያዎች፣ ታካሚዎችን ከመረመሩ በኋላ እንደየአስፈላጊነቱ የተሻለ ህክምና ካስፈለገ ወደ ሆስፒታሎች ሊልኳቸው ይችላሉ:: የአዕምሮ ህክምና ከአማኑኤል ሆስፒታል በተጨማሪ በኤካ ኮተቤ፣ በጥቁር አንበሳ፣ ቅ/ጳውሎስ፣ ዘውዲቱ፣ በራስ ደስታ እና በአለርት ይገኛሉ።  እንዲሁም በክልሎች በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች ይሰጣል። የአእምሮ ህክምና በግል ተቋማትም ይሰጣል። ""ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!!"  ከEthio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ) ✍ታዚ
إظهار الكل...
👍 4
#ማማዬ ሁሉንም ነገር ትክክል ለማድረግ አትጨነቂ። ሱፐር እናት ሱፐር ሚስት ሱፐር የቢሮሰራተኛ ሱፐር ሱፐር ሱፐር ለመሆን አትሞክሪ ምክንያቱም ሰውነትሽና አይምሮሽ ሲደክም ሁሉንም ነገር ፐርፌክት ማድረግ እንደማትችይ ይገባሻል እናም ቤቱን ለትንሽ ጊዜ ተይው እስቲ። ወጣ በይ ዎክ አድርጊ፣ ከጓደኞችሽ ጋር ሻይቡና በይ፣ ወደሀይማኖት ቦታ ሂጂ፣ እስፖርትሽን ስሪ፣ ፀጉር ቤት ሂጂ፣ ባጭሩ ለራስሽ ጊዜ ስጪ የሚያስደስትሽን ነገር አድርጊ ልጆችም ያድጋሉ አንዳንዴም ባልሽም ጥሎሽ ሊሄድ ይችላል ስራቦታሽም በሌላ ሰራተኛ ሊተካሽ ይችላል ቤቱም ተመልሶ ሊቆሽሽ ይችላል ነገር ግን አንቺ ዳግም ለመኖር ሁለተኛ እድል የለሽም አራት ነጥብ❗️ሩጫና ጭንቀትሽን ቀንሺና ለራስሽ ጊዜ ስጪ ራስሽን አክብሪ ራስሽን ውደጂ ©️kiya Bekele #እናትነት #እረፍት #mindthemind
إظهار الكل...
🙏 7 1