cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🙏አሜን💞 ማስታወሻዬ📝📨💌

የራሴን ውብ የነፍስ ከተማ በመስራት ላይ እተጋለው..... • • • ✍ @Madi23 ✏️ ለማንኛውም አስተያየት 👇👇👇 @ItsMeMadi

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
270
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
-530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼            ~~~ እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ: ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ። እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ á‹ŽáˆáŠ•áˆľ አሸጋገራችሁ አሸጋገረን::                                                    መልካም አዲስ ዓመት!        🌼እንቁጣጣሽ                                                                🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
إظهار الكل...
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼            ~~~ እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ: ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ። እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ á‹ŽáˆáŠ•áˆľ አሸጋገራችሁ አሸጋገረን::                                                    መልካም አዲስ ዓመት!        🌼እንቁጣጣሽ                                                                🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በሰላም ብርሀን ያማረ፥ ጤናን ከደስታ ያጣመረ፥ በስኬት በድል የታጀበ...ዓዲስ ዓመት ይሁንልን🙏        ✍ #ዮቶራዊት     @Mahder_Kasahun
إظهار الكل...
🌿#አንጀት_አርስ_እውነታ! ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳንችም በህይወት አንገኝም፡፡ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡ እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው? ማንም፡፡ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡ አስታውሳለሁ ፥ የሀይስኩል ተማሪ እያለሁ የትምህርት ቤቱ ፌመስ ለመሆን ብዙ ነገር አደርግ ነበር፡፡ዛሬ ከጥቂት አመታት በኋላ እንኳን ያኔ የነበረኝ ዝና ፥ በትምህርት ቤቱ መማሬንም የሚያስታውስ ሰው የለም፡፡አስቡት የዛሬ 150 አመት ደግሞ … ጭራሽ ትምህርት ቤቱም ላይኖር ይችላል፡፡ አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን እስኪ በዚህ ዘመን እንኳ ዝነኛ የሆኑትን እናስታውስ፡፡ማይክል ጃክሰን በጊዜው ዝነኛ ነበር፡፡ነገር ግን ከሞተ ገና ሁለት አስርት አመታት እንኳ ሳይሞላው እየተረሳ ነው፡፡ዛሬ ላይ ካለው ትውልድ ማይክልን የሚያስታውሰው በጣም ጥቂቱ ነው፡፡እሱንም ገና ካወቁት ነው፡፡ ከ150 አመታት በኋላ ደግሞ ማይክል ጃክሰን የሚለው ስም ጨርሶ ለማንም የማይታወቅ ይሆናል፡፡ ማጠቃለያው፥ ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡ እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡ @Human_intelligence
إظهار الكل...
ክፍል ፭         á‰  #ሄኖክ_በቀለ ✍      ማንም ሰው እጁን አላወጣም። ዕድሉ ይባስ ከፋው። ከዚህ ሁሉ በደሉ ጀርባ ዓለም ያሴረ መሰለው።      “ተው አንተ ሸንጎ አንተም እንደምሳር በወደቀ ላይ አትዝመት፣ ተው ንጉሥም ሲያጠፋ አጥፍተሃል ይባል፣ ተው መፈራራት ይቅር፤ ተው ለበዳዮችህ አታቀርቅር፣ ተው ፍርዴን አታጣምም፤ ተው ተፈጥሮን አታሳምም። ተው እውነት እየመረረችህም ጠጣት። ተው የምታሽርህን ጋታት!”      “ፈጣሪና መጥረቢያን ነጻ ናቸው የምትል። ፈጣሪ አይከሰስም! የምትል እጅህን አውጣ ተብለሃል” ሁሉም እጁን አወጣ። ማውጣት ብቻ ሳይሆን ፈጣሪ በደንብ እንዲያየው ወደ ሰማይ እየተንጠራራ። ሽማግሌው ወደ ዋናው ዳኛ ዞረው “እንግዲህ ፍርዱን ለእርስዎ ሰጥተናል!” አሉ።      “እንግዲህ ፍረድ ካላችሁኝ ይኸው ፍርዴ። በእውነት ይሄ ሰው ቀላል ፍዳ አላሳለፈም። ፈጣሪም መጥረቢያም በድለውታል። ኧረ እንደውም እስከ ዛሬ እንደዚህ የተበደለ ሰው ገጥሞኝም : አያውቅም። ስለዚህ መጥረቢያው በእጃችን ነው። እንጨቱ ተፈልጦ ማገዶ ይሁን። ብረቱ ሲቃጠል ይኖር ዘንድ፤ ያበላሸውን ይክስ ዘንድ ተቀጥቅጦና ቀልጦ የተበሳ ሰታቴ ወይ ላመፈጅ ይጠገንበት። ፈጣሪም ካለበት ተይዞ “ዕድሜ ይፍታሕ” እንዲታሰር ፈርጃለሁ። ይዞ ላመጣውም ያሻውን ያህል የምትታለብ ጥገት፤ ሮጦ የደረሰበትን ያህል ጋሻ መሬት፤ ልቡ የፈቀደውን ያህል ሚስትና እቁባት ይሸለም ዘንድ ፈርጄያለሁ። ይግባኝ አለኝ! የሚል ተከሳሽ ከተያዘ በኋላ ማሰማት ይችላል። ጨርሼያለሁ!”      ዕድሉ ቀና በአዛውንቱ ቅንነት እየተደነቀ አመስግኖ ወረደ። ሕዝቡም ገጸበረከቱ እያጓጓው፤ ፈጣሪን በየመቅደሱ በርብሮ ሊያገኝ ተመመ። “ፈጣሪ” ያልነው ማንን ነው? ዳኛውም ማንንም ሳያስከፋ ሸንጎውን መበተኑን ለሚቀጥሉት ብዙ ዓመታት በኩራት ሊያወራ ከግንባሩ ግራ እስከ አገጩ ከተዘረጋው፤ በከንፈሩና በዓይኑ ከሚቋረጥ ጠባሳው ጋር አንከስ አንከስ እያለ ወደ ቤቱ አዘገመ። ተከሳሽ በሌለበት ከሳሽ ሙግቱን ቢረታ ማነው ያሸነፈው?            ድሕረ ሸንጎ      የዕድሉ መጥረቢያ እጀታ ተፈልጦ በጋመ እሳት ውስጥ ገባ። እንደ ትዝታ በትናንሽ ዓይኑ የሚያፈጥ እንጀራ ለመጋገር ከሌሎች እንጨቶች ጋር አበረ። ሚስቱ ሰው ጠርቷት በወጣችበት ኩሽናው በእሳት ተያያዘ። በቀላል ሊያጠፉት አልቻሉም። እሳቱ እንደሰደድ ተዛምቶ የአዝማሪው ሐዋዝንና ሌሎች ሦስት ቤቶችን አወደመ። ሚስቱ ስትጠየቅ “እንዲህ በፍጥነት የሚዛመት እሳት አይቼ አላውቅም! ይኸማ የፈጣሪ ቁጣ ነው!” ትላለች። በደዌ ዳኛ፣ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የተኙት እትዬ ተዋቡ በእሳቱ ተቃጥለው ሕይወታቸው አለፈ። ዕድሉ ሞታም ሰው መፍጀት ያልተወችውን መጥረቢያው ውስጥ ዕጣ ፈንታው እያወካ የሚስቅበት መሰለው። ከሰማይ፣ ከምድሩም እንደተጣላ ጠረጠረ። “እንጀራ እበላበታለሁ” ባለበት አንድ መጥረቢያ ጦስ ሕይወቱ ምስቅልቅል ሲል መታገስ አልቻለም። ሞቱን አልፈራም። እየተበደሉ ይቅር አለማለት ዞሮ ራሱን ተገተገው። “ተበድለህም ይቅርታ መጠየቅ ምን ማለት ነው?” ...ልጆቹን ሳያሳድግ መሞቱ እያንገበገበው አጣጣረ። ከሰውም፣ ከአማልክትም መታረቅ የማይችል ቂም ቋጥሮ ሳይበረክት በተወለደበት አልጋ ላይ ሞት ተገናኘው።     ልክ ነፍሱ ስትወጣ አንዳንዶች “መጣሁልህ! ምን ልታደርገኝ እንደሆን አይሃለሁ?!” ብሏል ይላሉ። አንዳንዶች “ይቅር በለኝ?! እኔም ይቅር ብዬሃለሁ!” ብሏል ይላሉ። ሚስቱ ግን ዛሬም ድረስ ዕድሉን ሲያነሡባት ልጆቿን ታቅፋ አምርራ ታለቅሳለች። “እንግዲህ አይዞሽ! ፈጣሪ የወደደውን ነው የሚጠራው!” አሉ ሰባኪው ሾላ።     ጤናው እብዱ ከነግሣንግሡ እያለፈ ሳቀ። ረዥም ሳቅ ሳቅ ...ሁሌ እንደሚስቀው የልግጫ ሳቅ ሳቀ። “ታዲያ ፈጣሪ ሲጠራ፤ እንዳንከራተተ ነው እንዴ? ሳይክስ? ሳይዳስስ?”                አ በ ቃ።      @Mahder_Kasahun🦋
إظهار الكل...
ክፍል ፬         á‰  #ሄኖክ_በቀለ ✍     ታላቁ ልጄ እንደምታውቁት የቀኝ እጁ አራት ጣቶች ቆራጣ ናቸው። የእርሱ ታናሽ ደግሞ እጁም እግሩም ላይ ስድስት ስድስት ጣት አለው። ይህ እንዴት ሆነ? ሲቀለድብኝ መሆኑ ነዋ! .....አንድ ቀን ጠዋት የጀመርሁ ሼል ፍለጋ ስንከራተት ውዬ ሰውነቴ ዝሎ አመሻሽ ላይ ቤት ደረስኩ። ምንም ምንም ሳልል፤ እህልም ሳልቀምስ፤ ልብሴንም ሳላወልቅ መጥረቢያዬን ቆጥ ላይ ሳልሰቅል ተኛሁ። ብዙም አልቆየ ታላቅ ልጄና ነፍሰጡር ሚስቴ በጩኸት ቤቱን ሲያናጉት ብትት ብዬ ተነሣሁ። ሳይ ከልጄ መዳፍ ላይ ደም እንደወራጅ ውኃ ይንዠቀዠቃል። ዘልዬ አፈፍ ሳደርገው አራት ጣቶቹ ተራ በተራ ጠብ፣ ጠብ ብለው እንደጉድፍ መሬት ላይ ወደቁ። ያ መጥረቢያ ከንፈሩ ደም ጠግቦ ተጋድሟል። የሆነው ወዲያው ገባኝ። ታዲያ ምን ዋጋ አለው? ከረፈደ ዕውቀት የቀደመ ጠርጣራነት እንደሚበልጥ ማን አስተምሮኝ  ያኔ? ደንቆሮ፣ የደንቆሮ ዘር አይደለሁ። አንድ ቀን መጥረቢያዬን ማራቅ ብረሳ... ። ዛሬም ድረስ አውራ ጣቱ በመዳፉ ላይ ብቻዋን ፍርፍር ስትል ሳያት እንባዬ ይመጣል። ጠማማ ዕድሌን መግራት ተስኖኝ እንዳጎደልሁት ይሰማኛል!”     "ይበቃል ተብለሀል።"      “አይበቃኝም ገና መች ጀመርኩትና?! ኋላ ስንቀዠቀዠ ቤቱ ሄድኳ። ምነው ፈጣሪ ምነው ሳምንህ ጉድ ሠራኸኝ? ስል አለቀስሁ። ስለትህን አጉድዬ አውቃለሁ? የምበላው ባጣ እንኳ አሥራትና መባህን ነክቼ አውቃለሁ? ውለታ አታውቅም? አምላክ አይደለህም ተንደርድረህ ከሰው ልታንስ ነው? ምነው እኔን እንዳሻህ ብታደርገኝ? ምነው ልጆቼን ብትተውልኝ?” አልኩት። ሞኝ፣ የሞኝ ዘር አይደለሁ? ...የሰማኝ መሰለኝ። “አይዞህ ያለኝ መሰለኝ። “ይቅርታህን! የዛሬን ብቻ እለፈኝ ትቼሃለሁ” ያለኝ መሰለኝ። “ታርቀናል” ብዬ እንባዬን ጠርጌ ተነሣሁ። ቤት ስደርስ ያቺ ወረግቡ ሚስቴ ስታምጥ ደረስኩ። ቀበቶዬን አላልቼ የምትሰጥም አንተ፤ የምትነሣም አንተ ተመስገን!” አልሁት። ክፋቱን ረሳሁለት። ሚስቴ ምጥዋ ሳይጠና ተገላገለች። ቆንጅዬ ወንድ ልጅ በጨርቅ ጠቅልለው አሳቀፉኝ። ሳይደግስ አይጣላም!” ይሉ የለ የእኛ ሀገር ሰዎች? ...ደጋጎቹ። “መከራዬን አይተሃልና ኀዘኔን በሳቅ፣ ለቅሶዬን በደስታ ቀይረሃልና” ስል ስሙን ካሣ አልኩት። የካሠኝ መስሎኝ! አይ ደንቆሮ፣ የደንቆሮ ዘር ...ቶሎ አይነቃም እኮ።      ያዋለደችው ሴት በደስታ የምሆነውን ሲያሳጣኝ ፊቷን ጨምታ ስታየኝ ጠረጠርኩና ጨርቁን ገለጥሁት። በእጆቹ በእግሮቹም ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች አሉ። ስድስተኛ ሆነው የበቀሉት እንደሌሎቹ ጠንካራ ስላልሆኑ ወዲያና ወዲህ ተንከርፍፈዋል። ደነገጥሁ። ከማዘን ማበድ ቀረበኝ። ጣቱ ስድስት መሆኑ አይደለም፤ ነገረ-ሥራው ገርሞኝ እንጂ። የታላቁን አራት ጣት ነሳኸኝ ብዬ “ምነው?” ስላልኩት ካሣ ላይ መመለሹ ነው? ይሄ ቀልድ እንጂ ሌላ ምን ይሆናል? ድርቅ በጎርፍ ይካሣል? ሥርጉዳት በእባጭ ይሣሳል? ኧረ እንዲህም አድርጎ ቀልድ የትም የለ!      ሽማግሌው የግራ ጆሯቸውን፤ ከፊቶች አንዱን እያከኩ ተነሡ።      “እንግዲህ ሰማንህ 'ዕድሉ'። ለሰሚ የቸገረ ነገር ነውና የሸንጎውን ሐሳብ አድምጠን ፍርዱን ለዋናው ዳኛ እንሰጣለን።  ወደ ሸንጎው ዞረው  ፈጣሪና መጥረቢያ አጥፍተዋል። ፍርድ ይገባቸዋል? የምትል እጅህን አውጣ ተብለሃል!”            ይቀጥላል.........     @Mahder_Kasahun🦋
إظهار الكل...
ክፍል ፫         á‰  #ሄኖክ_በቀለ ✍      “መቼም አልሰማ á‰Ľáˆˆáˆ… ክሴን እቀጥላለሁ” ካልክ የሆንከውን አብራርተህ ተናገር! አታደናግር!” ሽማግሌው ጮኸ።      “ነገሩ እንዲህ ነው። የሆነ ቀን አለልማዴ ዓለሜን አስከትዬ ዛፍ ቆረጣ ሄድሁ። በእኔ ቤት ዛፍ ቆርጬ ገንዘብ ላገኝ ነው እንግዲህ። አዬ! ...ምነው በቀረብኝ። ዓለሜን አርቄ አስቀምጬ መጥረቢያዬን ይዤ ዛፉ ላይ ወጣሁና መተግተግ ጀመርሁ። ምን የተረገመው ቀን እንደሆነ እንጃ ከዛፉ ላይ አንዲት ሰላላ ቅርንጫፍ ብላት ብሠራት አልቆረጥ አለችኝ። ዛሬ ደግሞ የምን ተአምር ነው የገጠመኝ? እያልሁ ደጋግሜ ብመታት ጭራሽ እንደድንጋይ መጥረቢያዬን አንጥራ ትመልሳለች እንጂ ፍንክችም አትልም። ሠላሳ ዓመት ዛፍ ስቆርጥ እንዲህ ዓይነት ነገር ገጥሞኝም አያውቅም። የዚህ ሀገር እንጨት እንደምታውቁት ገራም ነው፤ እንኳን ቅርንጫፍ ግንዱም አስሬ ደኅና ካገኙት ይበቃዋል። ተንጋልሎ ያርፋል። የትንግርቴን ተፋጥጬ ሳነሣ ስለው፣ ሳነሣ –ስለው ...እልህ ይዞኝ እንጂ እጄ ዝሎ ኖሮ መጥረቢያው አምልጦኝ ቁልቁል ተምዘገዘገ። በዓይኔ ስከተለው...    ዕድሉ ቀና ሳግ አንቆ አላናግር ስላለው አቀርቅሮ ጊዜ ወሰደ።    “ለቅሶህን ተውና ቀጥል ተብለሃል!”    “በዓይኔ ስከተለው እንደ ኪሩብዔል ሰይፍ ሲገለባበጥ ወርዶ ከየት መጣች ያላልኳት የልጄ አናት ላይ ሰመጠ። ይታያችሁ! ለእንጨት የሰነፈ መጥረቢያ ለልጄ ሲሆን በረታ። ለካ ዓለሜን አርቄ ባስቀምጣትም አሳዝኛት ሼሏ መጥታ ሽቅብ ስታየኝ ነበር። እኔ አፈር ልብላላት ...ሞት ሲጠራት እኮ ነው! ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል ሠላሳ ዓመት ሙሉ ገጥሞኝ የማያውቀውን የእዚያ ቀን መጥረቢያ ያመለጠኝ? ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል አድርጌ የማላውቀውን መጥረቢያ የሚያመልጠኝ ቀን ልጄን ይዤ የመጣሁት? ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል ከዓመት እስከ ዓመት የሚያሰቃያት ንዳድ ያንን ቀን ጋብ ያለላት? ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል ለእጅ የምትሰንፍ ቅርንጫፍ በስል መጥረቢያ የለገመቸው? ለምን “እንቢ! ስትለኝ አልተውኋትም? ምነው መጥረቢያውስ ካልጠፋ አውላላ መዳፍ የማታህል የልጄን አናት የመረጠው? ፈጣሪ ቢለው አይደል?”     አዝማሪው ሐዋዝ ተነሣ “መቼም እንደሰው ልጅ ጉድ የትም የለም። ጠማማ ዕድሉንም፣ ስንፍናውንም በፈጣሪ ማሳበብ ይወዳል። አንተ የአርባ ዓመት ጎልማሳ ስትሆን ምነው ልጅህን መጠበቅ አላወቅህበት? እጅህ እስኪዝል አንድ ቅርንጫፍ ቀጥቅጥ ያለህ ፈጣሪ ነው? ከእጅህ አሽቀንጥረህ ስትጥለውም ወደወረወርክበት ይሄዳል እንጂ መጥረቢያ እግር የለው፤ ዓይን የለው፤ ምን አድርግ ነው የምትለው? ይህን ድፍረት ለተናገርህበት ልሹ ቅጣት ይገባሃል። ኧረ ምነው! ስንት ነገር ጥለን ነው የመጣነው፤ ጊዜያችንን ባንፈጅ...?”      ዕድሉ ቀና ክሱን ሰምቶ የሚደግፈው አለማግኘቱ አንገበገበው። ኀዘኑ እጥፍ ድርብ ሆነ። መናገሩ እንደማይጠቅም ሲሰማው ልቡ አመነታ። ቢሆንም የተበደለው አላለቀም። ቢያንስ “ተናግሬ ይውጣልኝ!” ብሎ ተቀበለ።      “አይ ሐዋዝ! አንተ ጎረቤቴ ሆነህ የደረሰብኝን ሁሉ ስታውቅ እንዲህ ማለትህ አሳዝኖኛል። ጊዜ የተፈጀብህ ለምኑ ነው? አናውቅም የት ውለህ የት እንደምታነጋ? ሌላ ምንም አልልህም አንተም ሴት ልጅ አለችህ። በልጅ የመጣ እንዴት እንደሚያንሰፈስፍ ደርሶብህ እየው።” ንግግሬ እንዳልጠቀመ አይቼያለሁ። ቢሆንም ልናገረውና የመጣው ይምጣ...”    ዋናው ዳኛ አንካሳ እግራቸውን በእጆቻቸው እያመቻቹ የሚሆነውን በዝምታ ይሰማሉ። “ይቅር ብዬ አልፌው እንጂ የተበደልሁትስ ይህ ብቻ አልነበረም። ከሆነ አይቀር ግን ይኸው ስሙት።              ይቀጥላል.........       @Mahder_Kasahun🦋
إظهار الكل...
ክፍል ፪         á‰  #ሄኖክ_በቀለ ✍      ዙሪያውን ከቦ የተዘለለው የሀገር ሰው ቦታውን በቱማታ አተረማመሰው። እዚያም እዚህም የተቆጡ ሰዎች በዕድሉ ድፍረት ተለኩሰው መንቦግቦግ ጀመሩ። አንዳንዱ ፈጣሪ ለእዚህ የንቀት ንግግር እዚያው በመብረቅ እንዳያደባያቸው ይለምናል። እስከነተረቱስ “ለኃጥአን የመጣ ለጻድቃን ይተርፋል!” ይሉ የለ? አንዳንዱ “ዕድሉ መወገሩ አይቀርም!” በሚል ተስፋ ሹል ባልጩት ፍለጋ በዓይኑ ይማትራል። አንዳንዱ ዓይናቸው ሼር ላበደው ዛፍ ቆራጭ ከንፈር ይመጥጣል። ከዋርካው ጀርባ ያደፈጡ አመዳም ሕፃናት ምን እንደተከሰተ ለመቅለብ ጆሮዎቻቸውን ዘርግተው ይቀላጠፋሉ።      ዕድሉ ድምፁ በጩኸት ማዕበል ተውጦ ምን እንደሚል አልተሰማም እንጂ፤ የሀገር ሰው ቁጣ ምንም ሳይመስለው ኃይለቃል እያወራ ይውረገረጋል።      ሽማግሌው ሕዝቡን እንደምንም ዝም አሰኝተው ወደ ዋናው ዳኛ ዞሩ። ፊታቸው ላይ ወፍራም ቁጣና ቀጭን ደስታ እኩል ተሸርቧል። በሰው ፊት ያዋረዳቸው ይህ ሰው አፍታ ሳይቆይ የሞቱን መግነዝ በራሱ እጅ ስለፈተለ ከንፈራቸው ላይ የታፈነ ፈገግታ ያጣጥራል።    “ምን ይላሉ እርስዎ?”      ዋናው ዳኛ ፊታቸው ላይ የተጋደመውን ጠባሳ ቆርጣ የምትስለመለም ዓይናቸውን አጨንቁረው “እስቲ እንስማው?! መቼም አይገድለን...” አሉ። ቁጣ ያደበላለቀው ሸንጎ ከዕድሉ ድፍረት በላይ በዳኛው ውሳኔ ተደናገጠ። ፊቶች ወዛቸው ተመጦ ተቁለጨለጩ። እንኳን ፈጣሪን ያህል ነገር ተከሶ ወትሮም ግራና ቀኝ ማገናዘብ አልተለመደም። ዋናው ዳኛ ከእዚህ በፊት ሸንጎ ረግጠው የማያውቁ ለሄላ-ገነት በቀረበው ሀገር በኩል የሚኖሩ ሽማግሌ ናቸው። በሰው በሰው ጠቢብነታቸው የሀገር ሸንጎ ጠሪዎች ጋር ደርሶ ተፈልገው የተገኙ ስለነበሩ ሕዝቡ እያጉረመረመም ቢሆን ትዕዛዛቸውን ተቀበለ።      ሽማግሌው እየቀፈፋቸው ወደ ዕድሉ ዞረው “ቀጥል ተብለሃል!” አሉ። የጎበጠ ጀርባቸው ተቃና። ያበጠች ልባቸው ፈርጣ ይሆን? ዕድሉ ጉሮሮውን ጠራርጎ፤ ለፍልሚያ እንደሚዘጋጅ ሰው ሰውነቱን አፍታቶ ቀጠለ።      “እንግዲህ ክሴን ስሙት። ይህቺ መጥረቢያና ፈጣሪ በደካማ ጉልበቴ ገብተው በድለውኛል። በማይመጣ መጥተውብኛል። ካደፈጠ አውሬ፤ ከተሰበቀ ጦር፣ በክፉ ከሚያይ ጎረቤት ሸሽጌ ለወግ ትብቃ ያልኳት ልጄን ገድለውብኛል። እውነት እዚህ ሀገር ፍትሕ ካለ በእዚህ እንዲጠየቁልኝ ነው የምሻው።” አንዱ ቁጣው ያልበረደ ወጣት ብድግ ብሎ...      “ምነው? ምነው ዕድሉ ምነው? ሰብሉ ሰምሮ፤ አዝመራው አሽቶ፤ ጠላት ደሞ በደጅ ቆሞ እያጓራ እያየህ ሲሆን ሲሆን ማመስገን ሳይሆን በንስሓና በጸሎት መትጋት ሲገባህ፤ ደረትህን ገልብጠህ ከአምላክ ጋር እኩል ቤት ትገጥማለህ? ምናል መቅሰፍት ባትጠራብን?!!”    ዕድሉ ቀና የወጣቱ መልስ እንደ አንዳች እያደረገው ከአፉ ላይ ነጥቆ ቀጠለ።      "ዝ ም በ ል!" “ያልተነካ ግልግል ያውቃል! ማለት እንደአንተ ዓይነቱን ነው። የራስህ ጉዳይ! የልጄን ደም ጠጥቶ የበቀለ አዝዕርት ምን ይረባኛል? ለምን ያሸተውን ጠራርጎ ነቀዝ አያነቅዘውም። ለምን አንበጣና ተምች አያደብነውም?! ሆድ ቢሞላ የልጄን ክብልል ዓይን ይሆነኛል? ጠግቤ ባገሳ የአንገቷን ሽታ የአንገቷን ሽታ ይለኛል? ምነው ደኅና ሰው ነህ ስልህ እንዲህ ቀለልህ?!”           ይቀጥላል.........   @Mahder_Kasahun🦋
إظهار الكل...
ክፍል ፊ         á‰  #ሄኖክ_በቀለ ✍      እዚህ ሀገር ውስጥ መቃብራቸው ሊማስ አንድ ሐሙስ የቀራቸው፤ ሕይወትን በዓይናቸው ቂጥ ገላምጠው የጨረሱ፤ “ፍርድና ርትዕ ዘልቋቸዋል” የተባሉ አዛውንት የሚፈርዱበት በሰንበት አንዴ የሚቆም ሸንጎ አለ። በዳይና ተበዳይ ተጠፍረው ይቀርቡና ይካሰሳሉ። በዳይም፣ ተበዳይም የመጡበትን ተናግረው የተሰጠውን ፍርድ ተቀብለው አመስግነው ይሄዳሉ።      ዕድሉ ቀና “ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ!” በሚል ማኅበረሰብ መሃል እየኖረ —ሰማይ ሊያርስ ንጉሥ ሊከስ እንባውን እያዘራ ደረሰ። ነታባ ጋቢ የለበሱ ዳኞች በሸንጎው መሃል ተሰይመዋል። ተከሳሽና ከሳሽ፤ ወሬ ሊያጦለጡል የመጣ የሀገር ሰው፤ ከወደቀው ዋርካ ጀርባ ተንቋጠው አሰፍስፈው ገቢር የሚቀላውጡ ሕፃናት ቦታውን ሞልተውታል።      ሸንጎውን የሚመሩት ሽማግሌ ከተቀመጡበት ብድግ ብለው ሁሉም ዝም እንዲል እጃቸውን እያወዛወዙ ምልክት ሰጡ። ሽማግሌው ፊታቸው በሽብሽባት የተፈሰፈሰ አሮጌ ቦርሳ የመሰለ፤ ድክም ፍዝዝ ብለው ዓይኖቻቸው ብቻ የነቁ፤ ጭብጥ የምታህል አናታቸው ላይ ግራና ቀኝ ትላልቅ ጆሮዎቻቸው ተሰፍተው ሦስት ፊት እንዳላቸው ነገር የሚያስቱ፤ ከወገባቸው ጎበጥ ያሉ ሰው ናቸው።      “ክስ ያለህ ቅረብ ተብለሃል!” አሉ ባለች በሌለች አቅማቸው ጅንን ብለው። ከልባቸው አበጥ ስላሉ ይሆን ከወገባቸው ጎበጥ ያሉት?      ዕድሉ ተንደርድሮ ከሳሽ የሚቆምበት ጉብታ ላይ ተሰየመ። “ይህ ሁሉ ነሆለል የተሰበሰበው “ሚስቴን ወሸሙብኝ”፤ “በሬዬን ነዱብኝ”፤ “አጥሬን ደፈሩብኝ” ሊል አይደል? እንደእኔ የተበደለ በድፍን ሀገሩ ቢታሰስ አንድ ይገኛል? ...ኧረ እንዲያውም!”      ዕድሉ ቀና ለወትሮው ክስና ክርክር ባለበት የማይደርስ፤ ከምድርም ከሰማይም የተስማማ፤ ቢበድሉት ውጦ ቢወጉት ደምቶ ዝም የሚል ጭምት ነበር። ዛሬ የከሳሽ ጉብታ ላይ ቆሞ ሲታይ የሸንጎው ታዳሚ ጸጥ እረጭ ብሎ አፈጠጠ። ሸንጎውን የሚመሩት ሽማግሌ ብቻ ደስ አላላቸውም ። ዕድሉ በዕድሜ የሚበልጡትን ከሰሾች ገፈታትሮ መቅደሙ አበሳጭቷቸው ይሁን፤ ወይ የስልጣናቸውን  አቅም የሚያሳዩበት ምቹ ጊዜ ጠብቀው ስላገኙ ይሁን.. “ተከሳሾችህን ወደ ፊት ጥራ ተብለሃል!”      ዕድሉ ቀና ከከሳሽ መደቡ ላይ ፈንጠር ብሎ ወረደ። ለተከሳሽ የተዘጋጀው ክብታ ላይ ደርሶ በእጁ የያዛትን መጥረቢያ አስቀመጣት። የተሰበሰበው የሀገር ሕዝብ ሁኔታውን በግራ መጋባት ይከታተላል።    “ተከሳሾቼ ሁለት ናቸው። አንዱ ይኸው! ይሄ መጥረቢያ ነው። ሁለተኛውን እንኳ የት እንዳለ አላውቅም። ብጠራው አይመጣም። ብቆጣው አይፈራም። በሰው ሕግ አይመራም። “ተወኝ! ስለው ይስቅብኛል። ምን እንደበደልሁት እንጃ ብቻ ሰባት ሰማያዊ ጋቢ ለብሶ እያደፈጠ ያጠቃኛል። ባለክንፍ አሽከሮች፣ የገዘፉ አዝማቾች፣ እልፍ ነጫጭ ሎሌዎች አሉት...”    “ማሸሞሩን ትተህ ምናል ብትናገር?” ሽማግሌው ትዕግስት አጥተው ይቅበዘበዛሉ። “እንደውም ሁለተኛው ተከሳሽ ፈጣሪ ነው።”            ይቀጥላል........    @Mahder_Kasahun🦋
إظهار الكل...