cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የስብዕና ልህቀት

በዚህ ቻናል ⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች ⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች ⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች ⚡ውብ የጥበብ ስራዎች በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ። #ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
85 841
المشتركون
-2624 ساعات
-3107 أيام
-1 26030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ጉዞው የፍጻሜውን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስታውስ! “ለአንድ ጉዞ ግብና ፍጻሜ የመኖሩ ጉዳይ አስፈላጊ ነው፡፡ በመጨረሻው ላይ ግን የጉዞው ጉዳይ ነው አስፈላጊው ነገር” - Ursula K. LeGuin አንዳንድ ሰዎች ህልማቸውን እውን ለማድረግ የሚሄዱበት ጎዳና ለድካም፣ ለህመምና ለቆሰለ ስሜት አሳልፎ ሲሰጣቸው ይታያሉ። በእንደዚህ አይነት መልኩ ማንነቱን ለጉዳት ያጋለጠ ሰው ህልሙ ጋር ቢደርስ ትርጉሙ ምንድን ነው? ህልሙ ጋር ሲደርስ በስኬቱ ለመደሰት የሚያበቃ ጤንነቱም እንኳን አይኖረውም፡፡ ሰዎች ገንዘብ የማግኘትን ህልም ይዘው ያሰቡትን ገንዘብ ለማግኘት ጤንነታቸውን ሲያጡ ክስረቱ ሁለት ነው። አንዱ ክስረት ያገኙትን ገንዘብ ጤንነታቸውን ለመመለስ እንደገና ማጥፋታቸው ነው፡፡ ሁለተኛው ክስረት ደግሞ ገንዘብ የማግኘት ህልም ጋር የደረሰው ሰው ገንዘቡን እንደፈለገው ለማድረግ የሚያበቃ የስሜትም ሆነ የአካል ጤንነት ማጣቱ ነው፡፡ ለአንዳንድ ሰዎች ሕይወት ማለት አንድ የሚደረስበት ግብ ነው፡፡ ሕይወት ግን የሚደረስበት ግብ አይደለም፤ ሕይወት የየእለት ሂደት ነው፡፡ ምንም እንኳ ይህ ሂደት በመጨረሻው አንድ ደረጃ ላይ ቢያደርሰንም፣ የሕይወት ዋናው ክፍል ያለው ወደዚያ ጥግ ለመድረስ የምናደርገው ጉዞ ነው፡፡ አላማ ላይ በመድረስ ምክንያት ሰዎች ትዳርን፣ ልጆችን፣ ቤተሰብን ሲበትኑ ማየት አሳዛኝ ነው፡፡ አንድን በንግዱ ስኬታማ ለመሆን ብዙ የለፋ፣ የተጨቃጨቀና በብዙ የስሜት ውጣ ውረድ ያለፈን ሰው አስብ፡፡ ንግዱን ለማጧጧፍ ሲሯሯጥ ለትዳሩና ለልጆቹ ያለውን ጊዜ ሰርቆበት ከቤተሰቡ ጋር ብዙም ጤናማ ግንኙነት የለውም፡፡ ከወዳጆቹ ጋር በገንዘብ ምክንያት ተለያይቷል፣ የተለያዩ ከስሜት ቀውስ የተነሳ የሚመጡ በሽታዎች አግኝተውታል፣ ስሜቱ ተጎድቷል ...። በመጨረሻ ግን ንግዱ ተሳካለትና ገንዘብን አካበተ። ሰብሰብ ብሎ ሲያስበው ግን ጤንነቱን አጥቷል፣ ቤተሰቡ ፈራርሷል፣ ወዳጆቹ ተለይተውታል ... የክስረት ሁሉ ክስረት! ይህንን አስታውስ፡- ትርፍና ኪሳራ ሁል ጊዜ ከገንዘብ ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ መፍትሄው ምን መሰለህ፣ ወደህልም የምትሄድበትን ጉዞ ህልሙን የማግኘትህን ያህል አስፈላጊ ነውና ተደሰትበት፡፡ 🙏 መልካም ምሽት!! Join: @Human_Intelligence Join: @Human_Intelligence
إظهار الكل...
🙏 16👍 6👏 2 1
Abush_Zeleke_HAGER_ENA_SEW_ሀገር_እና_ሰው_Official_Lyric_Video128k.m4a4.25 MB
👏 50🙏 10👍 7😢 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ ሰው ሳይኮአናሊስስ ጆርጅ በርናርድ ሾውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ "ከዚህ ሁሉ እድሜ በኋላ ያንተ የህይወት ፍልስፍና ምንድን ነው?" ጆርጅ መለሰ፡- `` በሕይወቴ ውስጥ የእኔ ፍልስፍና በጣም ቀላል ነው። እነሱ ከሚፈቅዱት በላይ ወደ ሰዎች አልቀርብም፤ ሰዎችም ከሚገባቸው በላይ እንዲቀርቡኝ አልፈቅድም..!። ``
إظهار الكل...
👍 73 15
`` ልጆችን ከማሳደግህ በፊት መጀመሪያ እራስህን ማሳደግ አለብህ። ይህ ካልሆነ ግን ከእንስሳዊ ፍላጎት የተነሳ ልጅ መውለድ ትፈልጋለህ፤ ብቸኝነት አልያም በራስህ ውስጥ ጉድለቶችህን ለመሙላት እንደማለት ነው። የአባትነት ተልዕኮህ ልጅ መውለድ ሳይሆን በቅድሚያ እራስህን መውለድ ነው ከፍ ወዳለ ነገር.. ``    -Thus spoke Zarathustra 📖
إظهار الكل...
👏 51👍 33 7🤔 1
Repost from Tesfaab Teshome
"ሳያሰቃዩ ቢገድሉን ጥሩ ነው" * * * እንደ ህዝብ በአንድ እንቅፋት ደጋግመን እንመታለን። አልፈነው የተሻገርነው የመሰለን ገደል አፈፍ ላይ እየደጋገመን እንገኛለን። ትላንት ያደናቀፈን ዛሬም ያደናቅፈናል። የቀደመውን የሚመስል ሰቆቃን እንኖራለን። ለቅሶ እንደጋግማለን። ተቀፀል የደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ ጓደኛ ነው። የአበባነት ዘመኑን የፖለቲካ እሳት የለበለው ወጣት ነው ፥ ተቀፀል። ፍቅረ ማርቅስ ደስታ እና ተቀፀል በዘመነ ደርግ ለእስር ተዳረጉ። ያ ዘመን ወጣት ሁሉ ወደእስር ሲከፋ ደግሞ ወደ ሞት የሚነዳበት ዘመን ነበርና ተቀፀል እና ፍቅረ ማርቆስ ደስታ ታሰሩ። የታሰሩት በባህርዳር ከተማ ነው። የእስራቸው ሰበብ ደግሞ "ኢህአፓን ደግፋችኋል" የሚል ነበር። ፍቅረ ማርቅስ "የሚሳም ተራራ" በሚለው መፅሐፉ 'ባዶ የሲሚኒቶ ወለል ላይ አስተኝተው እንደ ሲጋራ ሰውነታችንን ደፈጠጡት' ብሏል። እነ ፍቅረ ማርቆስ ከገበሬዎች ፥ ከሙህራን ፥ ከተማሪዎች ፥ ከመምህራን ወዘተ ጋር ታጭቀው ለአመት ያህል ታሰሩ። በእስራቸው ዘመን ሞት ወግ ሲያጣ ተመልክተዋል። ገላ በግርፋት ብዛት ሲተለተል አይተዋል። ፍቅረ ማርቆስ 'የሚሳም ተራራ' መፅሐፍ ላይ 'ተቀፀል ጓደኛዬ' በሚል ርዕስ ስለ ወዳጁ ፅፏል። አንድ ቀን "ዛሬ እኛንም ይገድሉናል" አለ ተቀፀል። "ኧረ" አለ ፍቅረማርቆስ ፍርሃት እያራደው። ሁለቱ እስረኞች አጠገብ ለአጠገብ ፍርሃት እያራዳቸው ተቀምጠዋል። የሞታቸው ቀን እንደደረሰ ያመነው ተቀፀል "ሳንሰቃይ ብንሞት ጥሩ ነበር" አለ። ምኞቹ በህይወት መቆየት አልነበረም። መንግስትን ተቃውመሃል ተብሎ ዘብጥያ የወረዳው ወጣቱ የፖለቲካ እስረኛ በህይወት መቆየትን አልተመኘም። ከአሳሪዎቹ ዘንድ ምህረት ማግኘት ቅንጦት መሆኑ ገብቶታል። ምኞቱ ስቃይ አልባ ሞት ነበር። "ሳያሰቃዩ ቢገድሉን ጥሩ ነበር" ዘመነ ደርግን የሚያሳዩ መፅሐፍት የሰዎችን አሟሟት ሲዘግቡ ከስቃይ ጋር ነው። ሰዎች ወፌ ላላ ይገረፋሉ ፥ ሰውነታቸው ተዘቅዝቆ ይሰቃያሉ ፥ መፈጠራቸውን እስኪጠሉ ይደረጋሉ። ከመሞት በፊት ብዙ ሰቆቃ አለ። እንዳለ ጌታ ከበደ "ማዕቀብ" በሚለው መፅሐፉ በጋዜጣ ተጠቅልሎ እሳት ተለቆበት ስለተሞተ ሰው አስፍሯል። ያ ዘመን እንዲህ ነው። ወግ ያለው ሞት ማግኘት ብርቅ ነው። ሮጠው ያልጨረሱ ወጣቶች ተሰቃይቶ ይገደላሉ። የፍቅረ ማርቆስ ጓደኛ በህይወት መትረፍን አልተመኘም። ምኞቱ ሳይሰቃይ መሞት ነበር። እንዲህ ነን። የተሻገረነው የመሰለን ገደል ዳግመኛ ይጠብቀናል። አባቶቻችንን የመታ እንቅፋት እኛን ይደግማል። ታላላቆቻችን የተሸከሙትን መስቀል እኛም እንሸከማለን። ያልታደልን @Tfanos
إظهار الكل...
👍 80 17👏 3🤔 1😢 1
📚ርዕስ: የልማድ አስደናቂ ሀይል 📝ደራሲ: ጄምስ ክሌር 👤ትርጉም: ድረስ ጋሻነህ 📜ዘውግ: self help 📖የገፅ ብዛት:264 📅ዓ.ም: 2013 @Human_Intelligence
إظهار الكل...
የልማድ አስደናቂ ሀይል.pdf75.17 MB
👍 32 6
Atomic_Habits_Tiny_Changes,_Remarkable_Results_James_Clear.pdf5.10 MB
👍 19 5
Photo unavailableShow in Telegram
👍 39 6🔥 4😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
👍 7
📚ርዕስ: የልማድ አስደናቂ ሀይል 📝ደራሲ: ጄምስ ክሌር 👤ትርጉም: ድረስ ጋሻነህ 📜ዘውግ: self help 📖የገፅ ብዛት:264 📅ዓ.ም: 2013 @Human_Intelligence
إظهار الكل...
የልማድ አስደናቂ ሀይል.pdf75.17 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.