cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

The Christian News

ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት። @TCNEW

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
5 067
المشتركون
+224 ساعات
+367 أيام
+13130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
በኦክላሆማ ግዛት በህዝብ ትምህርት ቤቶች መጽሐፍ ቅዱስ በትምህርት ስርዓት ውስጥ እንዲካተት ታዘዘ የአሜሪካዋ የኦክላሆማ ግዛት ከፍተኛ የትምህርት ቢሮ የስራ ሃላፊዎች ሁሉም የህዝብ ትምህርት ቤቶች መጽሐፍ ቅዱስን በትምህርት ስርዓታቸው ውስጥ በአስቸኳይ እንዲያካትቱ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ለትምህርት ቤቶች የተላለፈው መመሪያ አስገዳጅነት ያለውና “አፋጣኝ እና ጥብቅ ተፈጻሚነትን” የሚጠይቅ ደንብ ያካተተ ነው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል። በመመሪያው መሰረት በሁሉም የግዛቷ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ እና ዕድሜያቸው ከ11 እስከ 18 ለሆኑ ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት እኩል መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይሰጣል ነው የተባለው። ይሁን እንጅ ይህ አዲሱ መመሪያ ከሲቪል መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም ሃይማኖት እና መንግሥት መለያየት አለባቸው ከሚሉ ቡድኖች ትችት ቀርቦበታል። ተጨማሪ ዝርዝር ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ!!! https://www.facebook.com/share/p/rMUnwx8fPrDDKfYy/
إظهار الكل...
👍 14 10👏 6🔥 3🙏 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 12 4👏 1👌 1
#ብዙ ዋጋ የተከፈለበት #በኢትዮጵያ ትልቁ የመፅሐፍ #ቅዱስ ማብራሪያ ተመረቀ። በዘላለም #መንግስቱ ተጽፎ ከ1,300 ገጾች በላይ ተዋቅሮ ከ4,800 በላይ ቃላት ያካተተው ይህ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የጸሀፊው ወዳጆች በተገኙበት በCETC) ኢትዮጵያን ቴዎሌጂካል ኮሌጅ በድምቀት ተመርቆ ለአንባብያን ተሰራጭቷል። በመድረኩ መጽሀፉን #ሙሉ በሙሉ ጽፎ ለማጠናቀቅ 23 ዓመታት እደፈጀ እና በዚህ ስራ #ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል። ዘላለም መንግስቱ በንግግሩ ይህ መፅሐፍ ማለት እንደ "ማንኪያ" ነው። ዋናው ምግቡ ግን "መፅሐፍ ቅዱስ" ነው። ያለ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስን የበለጠ ለመረዳት የሚያግዝ መጽሐፍ እንደሆነ ተናግሯል። አክሎም ምንም እንኳን እጨርሰዋለሁ ብዬ ባልጀምረውም ለብዙዎች የሚያግዝ በመሆኑ በእግዚአብሄር እርዳታ ተጠናቋል። ይህ መጽሐፍ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ የተጻፈ እንደመሆኑ መጠን ይህ መጽሀፍ መጽሀፍ ብቻ ሳይሆን አደራም ጭምር ነው ሲል ተናግሯል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉ መሪዎች እረጅም አመታትን በትዕግት በመጻፍ ይህንን መጽሀፍ በዚህ ወቅት ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በማበርከቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዚህ ዘመን ያለን አገልጋዮች ይህንን መጽሀፍ ባንጠቀምበት ፤ እና ባንሰራበት ለእኛ እዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ዘላለም መንግስቱ ከዚህ ቀደም መንፈስ ቅዱስ እና ካሪዝማዊ ቀውሶች ፤ እንዘምር ወይስ እንዝፈን ፤ ክርስቲያናዊ ኢትዮጵኝነት ፤ የሐሰተኞች እሳተ ጎመራ ፤ ትንቢተ ዕምባቆም ፤ የይሁዳ መልዕክትን ጨምሮ ወደ 20 የሚደርሱ መጽሀፍትን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አበርክቷል። #የኢትዮጵያ ቃለ #ሕይወት #ቤተክርስቲያን #ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት #እና የአብያተክርስቲያናት መሪዎች በጽሎት መጽሀፉን መርቀው ለንባብ እንዲበቃ በይፋ መርቀውታል። The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ሙሉ ዘገባውን አሰናዳንላችሁ። በቻናላችን ስም ለወንድም Zelalem Mengistu የተሰማንን እጅግ ትልቅ ደስታ እየገለጽን ሁላችሁም ትጠቀሙበት ዘንድ እናበረታታለን።
إظهار الكل...
The Christian News

ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት። @TCNEW

👍 8 2👏 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ዜና #ማብቃት_ለክርስቶስ_አገልግሎት_ተማሪዎች_ምረቃ ማብቃት ለክርስቶስ አገልግሎት የመጽሃፍ ቅዱስ ት/ቤት በማስተርስና ዲፕሎማ ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ። ት/ቤቱ ያለፉትን 3 ዓመታት ከሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ተማሪዎቹን ቦሌ በሚገኘው ዩ ጎ ሲቲ ቸርች ነው ያስመረቀው። ማብቃት ለክርስቶስ ትምህርቶቹን የሚሰጠው አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው ካይሮስ ዩኒቨርሲቲ (Sioux Falls Seminary) ጋር በመተባበር ነው። የAdams Thermal Foundation እና ማብቃት ለክርስቶስ አገልግሎት አፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል ጌታቸው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት አጋርተዋል። ማብቃት ለክርስቶስ የመጽሃፍ ቅዱስ ት/ቤት፣ ተማሪዎችን በመጽሃፍ ቅዱስ እውቀት በማስታጠቅ ለወንጌል አገልግሎት ለማብቃት ይሰራል። አገልግሎቱ በተጨማሪም “10/40 መስኮት” በሚባለው የአለማችን ክፍል የወንጌል ተልዕኮ ሰራተኞችን በማስታጠቅ ይሰራል።
إظهار الكل...
👍 6 4👏 1
#ዜና #ማብቃት_ለክርስቶስ_አገልግሎት_ተማሪዎች_ምረቃ ማብቃት ለክርስቶስ አገልግሎት የመጽሃፍ ቅዱስ ት/ቤት በማስተርስና ዲፕሎማ ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ። ት/ቤቱ ያለፉትን 3 ዓመታት ከሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ተማሪዎቹን ቦሌ በሚገኘው ዩ ጎ ሲቲ ቸርች ነው ያስመረቀው። ማብቃት ለክርስቶስ ትምህርቶቹን የሚሰጠው አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው ካይሮስ ዩኒቨርሲቲ (Sioux Falls Seminary) ጋር በመተባበር ነው። የምረቃ መርሃ ግብሩን የማብቃት ለክርስቶስ አገልግሎት ካንተሪ ዳሬተር መጋቢ ባህሩ በጸሎት ሲከፍቱ፣ ዘማሪት ሃና ተክሌ በዝማሬ አገልግላለች። የAdams Thermal Foundation መስራችና መሪ ማይክ አዳምስ የማብቃ ለክርስቶስ አገልግሎትን የ6 አመታት ጉዞ አቅርበዋል። የAdams Thermal Foundation እና ማብቃት ለክርስቶስ አገልግሎት አፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል ጌታቸው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት አጋርተዋል። ማብቃት ለክርስቶስ የመጽሃፍ ቅዱስ ት/ቤት፣ ተማሪዎችን በመጽሃፍ ቅዱስ እውቀት በማስታጠቅ ለወንጌል አገልግሎት ለማብቃት ይሰራል። አገልግሎቱ በተጨማሪም “10/40 መስኮት” በሚባለው የአለማችን ክፍል የወንጌል ተልዕኮ ሰራተኞችን በማስታጠቅ ይሰራል።
إظهار الكل...
Screenshot 2024-06-23 154219.jpg1.44 KB
Photo unavailableShow in Telegram
#ድንቅ #መፅሐፍ ... #ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። #ጌታ ይመሰገን ዘንድ ነው። የምስጋና ጊዜው የሚደረገው በETC (The Evangelical Theological College) ቅዳሜ June 22, 2024 (በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ ፲፭ ቀን ፳፻፲፮) ከጠዋቱ 4 እስከ 6 ሰዓት ነው። ከአክብሮት ጋር። ዘላለም መንግሥቱ
إظهار الكل...
👍 7 7👏 3👌 2🔥 1
#እኔ በወጣውበት ልቀር ስለምችል ለልጆቼ ሚስቴ ትቆይልኝ እላለው #እግዚኣብሄር ግን አሻገረኝ #ብዙዎች ተጽናኑበት እኔ ግን አልቻልኩም https://youtu.be/xgsmxwNgVBY
إظهار الكل...
#እኔ በወጣውበት ልቀር ስለምችል ለልጆቼ ሚስቴ ትቆይልኝ እላለው #እግዚኣብሄር ግን አሻገረኝ #ብዙዎች ተጽናኑበት እኔ ግን አልቻልኩም

#እኔ በወጣውበት ልቀር ስለምችል ለልጆቼ ሚስቴ ትቆይልኝ እላለው #እግዚኣብሄር ግን አሻገረኝ #ብዙዎች ተጽናኑበት እኔ ግን አልቻልኩም ተወዳጁ ዘማሪ አስፋው መለሰ ከማይጠገብ ጨዋታዎቹ እና በኣንባ የታጀቡ ቁም ነገር አዘል የሆኑት ምክሮቹ እና የትም ያልተሰሙ የቤተሰቡ ድንቅ ምስክርነት የቤታችን እንግዳ ሆኗል። በብዙ ጉጉት ሲጠበቀ የነበረው #የተወዳጁ #ዘማሪ አስፋው መለሰ #ድንቅ ቃለ መጠይቅ እንድትመለከቱ ግብዣችን ነው። #gospel #thechristiannews #singer #jesus #jesuschrist #መልካም በዓል #marsiltvworldwide #yonatanaklilu #abiye #ebc #fana_tv #ebs #reels #saturdayafternoonshow_ebstv #ethiopia #ethiopiantvshow #saturdayafternoonshow_ebstv #ethiopianews #ethiopiantvshow #ebstv #ebstvworldwide #ethiopianbroadcastingservice #1choice #ebc #news #newsong #newvideo #newsupdate #entertainment #enjoy #habesha #video #song #songs #blessed #christian #christianity #christ #christiansongs #christianmusic #happy #happynewyear #sifu ወዳችሁ እና ፈቅዳችሁ ስለምትመለከቱን ከልብ እናመሰግናለን!!! Like, Share ማድረጎን አይርሱ!! #በ0930699543_ማንኛውንም_አይነት_የክርስቲያን_መረጃዎችን_በቴሌግራም_ለክርስቲያን_ዜና_ሚዲያ_መጠቆም_ይችላሉ #The_Christian_News Welcome to Our channel This is The Christian News from Ethiopia if you subscribe Our channel you get more benefits. news, blogging , information, vine ... all Entertainment are available in Our channel subscribe now Thanks For Watching. LIKE, SHARE & SUBSCRIBE For More Videos! Subscribe Now ⏩

https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

FACEBOOK ⏩⏩

https://www.facebook.com/The-Christian-News-%E1%8B%A8%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%88%B5%E1%89%B2%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8B%9C%E1%8A%93-2009919145963732/?modal=admin_todo_tour

Note: unauthorized use, distribution and re upload of this content is strictly prohibited Copyright ©2024: #thechristiannews

👍 7🥰 4 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#አዲስ መጽሐፍ #በቅርብ #ቀን... ከ1,300 ገጾች በላይ ተዋቅሮ ከ4,800 በላይ ቃላት ያካተተ #ድንቅ የአማርኛ መጽሐፍ #ቅዱስ መዝገበ ቃላት በዘላለም መንግስቱ ተዘጋጅቶ በቅርብ ቀን ወደ አንባቢያን ይደርሳል። 23 ዓመታት የፈጀው #ይህ #ድንቅ መጽሀፍ በቅርብ ቀን በአዲስ አበባ ሰኔ 15 2016 በኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ (ETC) የምስጋና ጊዜ ከጠዋቱ 4 እስከ 6 ሰዓት በድምቀት ይመረቃል።
إظهار الكل...
👍 31 8🔥 2🥰 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#የዛሬ -ሃምሳ #ዓመት #እኔ #በጌታ ምሪት #ወደ ባሌ ጎባ ገብቼ ቤተክርስቲያን ለመትከል ቤት የተከራየውበት ቀን #በሮቤና በአጋርፋ ይሠሩና ይኖሩ ከነበሩት ሁለት ወንድሞች #አያና መኳንንና #ከአባተ ወላኒዎሰ ጋር ከሮቤ አንድ ታጣፊ አልጋ ከነፍራሹ በ28 ብር ገዝተን ቤቱን ደግሞ በ10 ብር ተከራይተን የኪራይ ውል ፈጸምን። ኪራዩን ከሁለቱ ወንድሞች ማን እንደከፈለ ትዝ አይለኝም ። ቤቱ ወንዝ ደር ከመሆኑም በላይ ንፋስ ያስገባል እና በጣም ይበርዳል። በተለይም በማያውቁት አገር ሌሊቱን ለብቻ ማደር እንዴት ያስፈራል። ሃምሳ ዓመት ወደ ኋሊት አሰብኩ ። የአምላኬ ምህረትና ማደን ቸርነቱም ገረመኝ ደነቀኝም። ስሙ ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን ። 🙏🙏🙏 ከመጋቢ ጻድቁ አብዶ (የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ኅብረት ፕረዚዳንት) ገጽ የተወሰደ
إظهار الكل...
👍 23 12🔥 3🙏 3🥰 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
በመቱ የሙሉ #ወንጌል አማኞች #ላይ ደረሰ የተባለው ድብደባ እንዲጣራ የአብያተ ክርስቲያናት ኅብረቱ ጠየቀ። #እሁድ ግንቦት 25 በመቱ ከተማ ለወንጌል ስርጭት በወጡ ክርስቲያኖች ላይ በፖሊስ እና ሚሊሻዎች ድብደባ ተፈጽሟል። ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ወገኖች መካከል አስተያቷን ለአሜሪካ ድምጽ ራድዮ የሰጠችው ኤደን ግርማ እንዲህ ብላለች። ኤደን ግርማ፣ ጥቃት የደረሰባት “የእሁድ አምልኮ ጨርሰን ለወንጌል ስርጭት ሶሪ ዳቦ የሚባልበት አካባቢ ስንደርስ ፖሊሶችና ሚልሻዎች በመኪና መጡ። መሬት ላይ ተቀመጡ ካሉ በኋላ፣ የተወሰኑ ወጣቶች ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱን። አመሻሽ ላይ ከአንዱ አመራር ጋር ፖሊስ ጣብያው አካባቢ መሬት ተቀመጡ ብሎ እያወራን፣ ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ድብደባ ጀመሩ። እኔ ጭንቅላቴን ተመቼ ስደማ፣ ሌሎችም በጣም ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ለህክምና ተወስደናል።” ስትል ተናግራለች። #ቄስ ደበላ ያደታ፣ የኢሉባቦር ዞን ወንጌላዊያን አብያተ ክርስትያናት ህብረት ሰብሳቢ በበኩላቸው “እኛ ህገ መንግስቱ በሚሰጠን መብት መሰረት እምነታችንን የማካሄድ መብት አለን። ከመንግስት ጋርም በሚያስፈልጉ ነገሮች ዙርያ በትብብር ስንሰራ ቆይተናል። መንግስት እንደዚህ ያደርጋል የሚል እምነት ባይኖረንም፣ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን ይሄንን እንዳደረሱ በትክክል እናውቃለን። ስለዚህ ሁኔታው በትክክል እንዲታራ እንጠይቃለን።” ብለዋል። አቶ ተሻለ ኤጄርሶ፣ የመቱ ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው “ከሳምንት በፊት ለነበረው ስብከተ ወንጌል ፍቃድ የተሰጠ ቢሆንም፣ እሁድ ግንቦት 18 ሲደረግ ለነበረው የወንጌል ስርጭት የተሰጠ ፍቃድ የለም። አላስፈላጊ ድብደባና ግጭት ከፖሊስ ዘንድ መድረሱን ተመልክተናል። ከጸጥታ አካላት ጋርም ይሄንኑ ጉዳይ በተመለከተ ምርመራ እየተካሄደ ነው።” VOA Amharic
إظهار الكل...
👍 22 3🔥 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.