cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ብዕር ሲደማ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
196
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

አስደሳች ዜና ለኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ ኪናዊ ለዛን የተላበሱ ስራዎችን ለህዝቡ በማቅረብ የሚታወቀው አቢላማ የቴአትር እና የፊልም ማሰልጠኛ ፕሮዳክሽን በፊልም፣ በቴአትር እና በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን ተማሪዎች #በቅርቡ ያስመርቃል በመሆኑም በቀጣዩ ጊዜ በቴአትር እና በፊልም ችሎታው እና ፍላጎቱ ያላቸውን ተማሪዎች አስተምሮ ብቁ ለማድረግም ዝግጅቱን ጨርሷል ። እርሶም ፍላጎቱ አለኝ ብቁ መሆንን እሻለሁ የኪነጥበብ አለምን መቀላቀል እፈልጋለሁ ካሉ ምርጫ የሌለው ምርጫዎ አቢላማ ነው ይምጡ ይመዝገቡ የጥበብ ጥሞን ያርኩ ብቁ የጥበብ ሠው ይሁኑ። አቢላማ የቴአትር እና የፊልም ኘሮዳክሽን YouTube ቻናላችንን https://www.youtube.com/channel/UCJxENxv5Mfg1Bj7uimjyWmQ subscribe በማድረግ የቤቱን አስደናቂ ማለፊያ ስራዎች ይመልከቱ ። ለበለጠ መረጃ @sew19 ላይ ያናግሩን @abilam @abilam
إظهار الكل...
ክርስቶስ ወ ገብረክርስቶስ (በቴዎድሮስ ካሣሁን) እዩት ይሔን ጠቢብ ሸራው እስኪደማ፡ በቀይ እየወጋ በደም እየሣለው፡ እንጨት አመሳቅሎ፡ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ላይ ሰቀለው፡፡ ቀራንዮ ሆነ የወጠረው ሸራ፡ ጎለጎታ ሆነ የወጠረው ሸራ፡ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ፡፡ ደም ከደም አረገው አበዛበት ጣር ብሩሹን አሹሎት እንደ ጎኑ ጦር፡፡ እየወጋ ሣለው፡ በጣም ጨከነበት፡ ገብረክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ፡ የቆዳው ዓይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ እየወጋ ሣለው፡ እየሣለ ወጋው፡ ዘሩ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ ደሙ እስከሚናገር፡ የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው አገር፡ እንዳንለው ፈረንጅ እንዳንለው ጥቁር፡ እንዳንለው ቀይ፡ በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ስቃይ በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው፡፡ ከቀናት ባንዱ ዕለት፡ ሰዎች ሲሟገቱ በቀለሙ ጉዳይ፡ ሲከራከሩበት በተመፃዳቂ የምሑር አንደበት፡ ባንዱ አፍ ሲጠቁር፡ ባንዱ አፍ ሲነጣ፡ መታገስ አቃተው ሠዓሊው ተቆጣ! ሥሜቱ ገንፍሎ በብሩሽ ጫፍ ወጣ፡፡ ሐሣቡን የሚገልፅ ቀለም እስከሚያጣ፡ ሸራ ላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ፡ አልወጣልህ አለው ፍቅርን ሥሎ ሥሎ፡፡ ሥሎ---ሥሎ----ሥሎ፡ ፍቅርን ሥሎ ሥሎ፡ በሣለው እየወጋ፡ በደማው እየቀባ፡ 'ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀለም እንጨቱ ላይ ያለው ዕውነት ይሔ አይደለም፡፡' እያለ እስኪናገር የሥዕሉ አንደበት ገብረክርስቶስም ለክርስቶስ 'ሚሆን ቀለም እስኪያልቅበት፡ በነጩ ሸራ ላይ እስካሁን የሚወርድ ደም አፈሰሰበት፡፡ ቀለም፡ ቀይ ቀለም የደም ቀለም፡ የጥላ ቀለም የሁሉም ነው'ንጂ የማንም አይደለም፡ ፍቅር ዘር አይደለም፡፡ ለሠዓሊና ገጣሚ ገ/ክርስቶስ ደስታ የተፃፈ
إظهار الكل...
<<ዝናብ -ገበሬ-ሊስትሮ>> (በላይ በቀለ ወያ) ገጠር ዝናብ ነጥፎ..... ከተማ ምድር ላይ ፣መዝነቡ እንደታየ የከተማው ኗሪ እንዲህ ፀለየ <<ከተማ ምድር ላይ፣ዶፍ ዝናብን ጥለህ ሒያጅ ከምታቆሽሽ... በየጎዳናው ላይ ፣ጭቃ፤ጎርፍ አብቅለህ እዚህ ሚዘንበውን..... ገጠር ላለው ኗሪ ፣ውሰደው ጠቅልለህ። አብቅ ነው ሚዘራው.... እኛ እየሸመትን የምንመገበው ዝናብህን ሁሉ ፣ገጠር ላይ አዝንበው።>> እያለ ሲማፀን፣የከተማው ኗሪ <<መንገዱን ጭቃ አርገህ.... ጫማ ምታቆሽሽ፣ተመስገን እያለ።>> ብሎ ሚያመሰግን ፣የቆሸሸ ጫማን እየወለወለ ለካስ ከተማም ላይ... ከገበሬው እኩል ዝናብ ሚያስፈልገው ፣ጫማ ጠራጊ አለ። (ከበላይ በቀለ ወያ)
إظهار الكل...
Repost from ብዕር ሲደማ
ብዕር ሲደማ https://t.me/bear7sidema7with7elask7crezy ቻናላችንን ይቀላቀሉ ....
إظهار الكل...
ድሮና ዘንድሮ😕 ድሮ አያቶቻችን ህክምና ሳይማሩ ሃኪሞች...ቀይ ጋዎን ተከናንበው በህግ ሳይመረቁ ድንቅ ዳኞች... በኢንጅነሪግ ሳይመረቁ ቀያሽሾች. የቋንቋ ዲግሪ ሳይጭኑ የበዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች..ያለጥቅማጥቅም ፍቅር አዋቂዎች..ያለጦር ትምህርት ተዋጊዎች..ያለሰባኪ ሃይማኖተኞች ..ነበሩ አባቶቻችን ትንሽ ቀለም ቆጠሩና እውቀት ሞልቶ ቢፈሳቸው..ሙህርነት አቁነጥንጧቸው የፖለቲካ ርዮት. ዓለም አብዝተው እርስ በርስ ተጋደሉ..ተጨራረሱ..ዛሬ እኛ በየአመቱ በየዩኒቨርስቲው በሺ የሚቆጠሩ ቆብ ደፍቶ ተመርቆ ሲወጣ ጭራሽ አእምሮው ጠቦ..በሱስ ሲደነዝዝ ውሎ ያድራል..ከድሮ ካያቶቻችን ያረጀችና የተዛመመች የእንጨት ቤት ጎን ፎቅ ይገትራሉ ታዲያ የተዛመመችው አንድም ምርጊቷ ሳይረግፍ በዘመኒዮች መሀንዲስ የተሰራ ፎቅ ፍርክስክሱ ወጥቶ የፍርስራሹ ፍንጣሪ የተዛመመችውን ይደረምሳል..ግም ያገማል አይደል..ታሞ ሊታከም ሆስፒታል የሚገባው ህሙማን በሽታው ከሚገለው ይልቅ ሀኪሙ የሚገለው ይበዛል..በትክክል ፍርድ ውሎ በስህተት ቅጣት የሚበየንበት ንጹሀን ይበዛል..ገበሬው በራሱ ልምድ አር ሶ ያመርት ከነበረው የተማረው የመከረው ወዲህ የምርት ውጤት ያሽቆለቆለ ነዉ..እውህነት ጠፍታ ውሸት ነግሳለች..ድሮ ወንድ ልጅ አለባበሱ ግርማ ሞገስ ነበረው..ዛሬ እንደሴት አይነት ልብስ የተጣበቀ ቃሪያ ሱሪ ዋትፎ ያለማፈር አስፖልት ሞልቶ ሲንጎራደድ ይውላላል ድሮ የሰው ገንዘብ መመኘት .በሰው መጋበዝ ውርደትና ..የበታችነት ነበር። ዛሬ ሁሉም ባገኘው አጋጣሚ ያገኘውን መዝረፍ ይፈልጋል..መጭውስ እንዴት ይሆን በ ዓሲ ዓለሙ ሀሰን
إظهار الكل...
😍ይስጥሽ😍 (በዕውቀቱ ስዩም) እቴ… ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤ ይስጥሽ ከጸጉሬ ከአናቴ ላይ ዘግኖ ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤ እቴ… ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ። እቴ… እጄን ብትፈልጊ እግሬን ብትፈልጊ አንገቴን ደረቴን ተሰጥኦ ሀሳቤን ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ ያስቀርልኝ አይኔን አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን።
إظهار الكل...
"#ሰው_በቃኝ_አልልም" ሰው በቃኝ አልልም ብዙ ሰው አለና ለሰማይ ለምድር የሚሆን ጓደኛ ለሰው ጥሩ አሳቢ አእምሮው የጠና አስታዋሽ ሰው ወዳጅ በንፁህ ልቦና ለሰዎች የሚኖሩ አሉ ብዙ ጀግና በጭራሽ የማይኖሩ ለብር ለዝና ሰው በቃኝ አልልም ሌላ ሰው ባስከፋኝ አሉ ብዙ ሰዎች እውነትን ያስተማሩኝ አብሽር ከጎንሽ ነኝ በጭንቀት ቀን ያሉኝ እውነትና ፍቅር ፅናት ያስተማሩኝ በብር በዝና ገድለው ያልቀበሩኝ በቃላት ቫይረስ ያላደናገሩኝ ለሰው የሚኖሩ ሁሌ የማረኩኝ ሁሌም ደግ ሰሪ ምንጊዜም ታማኝ በእህት በወንድምነት ገመድ ያሰሩኝ የመኖር ጥበብ ቅኔ ያስተማሩኝ #ሰው_በቃኝ_አልልም ይቺ አለም ብዙ ናት ብዙ ሰው ያቀፈች ጥሩና መጥፎውን አንድ ላይ የያዘች
إظهار الكل...
መልካምነት ለራስ ነው (ዲ/ን ዳንኤል ክብረት) አንድ ሰው ሶሰት ጓደኞች ነበሩት በጣም ነው የሚወዳቸው ብዙ ነገር ያደርግላቸዋል ያደርጉለታልም፡፡ አንድ ቀን አባቱ "ልጄ ጓደኞች አሉህ" አሉት "አዎ ሶስት ጓደኞች አሉኝ በጣም የሚወዱኝ የምወዳቸው" አላቸው፡፡ እርሳቸውም "ከእነዚህ ውሰጥ የልብ ጓደኛህ ማነው?" አሉት "ሁሉም" አለ "እርግጠኛ ነህ ልጄ" ሲሉት "አዎ" አለ፡፡ "እንደዚያ ከሆነ የሆነ ነገር እንፍጠርና እውነተኛ መሆናቸውን እናረጋግጥ" ይሉታና ጓደኞቹን እንዲፈትን ያደርጉታ፡፡ ልጁም አባቱ ባለው መሰረት ለአንዱ ጓደኛው ይደውልና "ያለጥፋቴ ሰው ገድለሃል ተብዪ ፍርድ ቤት ነኝ ድርሰልኝ" ይለዋል ጓደኛውም "አዝናለሁ አልችልም" ይለዋል፡፡ አሁንም ለሁለተኛው ይደውላል ሁለተኛ ጓደኛውም "ችግር የለውም እመጣለው እርዳታየም ካሰፈለገህ የምችለውን ሁሉ አደርግልሀለው ፍርድ ቤት ግን አብሬህ አልገባም አዝናለው" ይለዋል አሁንም ለሶሰተኛው ይደውላል ሶሰተኛውም "እንዴ ኧረ ችግር የለውም ደሞ ለአንተ አይደለም ፍርድ ቤት ሌላም ቦታ እመጣልሃለሁ" አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ልጅ በአባቱ ምክር እውነተኛ የህይወት ጓደኛው ማን እንደሆነ አረጋገጠ ። ፍርድ ቤት የተባለው የሰው ልጅ ይችን ዓለም ተሰናብቶ የሚኖርባት የዘላለም ቤቱ ሲሆን 1-የመጀመሪያው አልችልም ያለው ገንዘብ ነው መቸም የሰው ልጅ በዚች ምድር ሲኖር ምን ያህል ሀብት ቢኖረው ከሞት አያሰጥለውም በሞት ጊዜ ተከትሎን አይመጣም ። 2-ሁለተኛው ፍርድ ቤቱ አመጣለው እረዳሃለሁ እንጅ አልገባም ያለው ዘመድ ወይም ጓደኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሰው ምን ያህል ቢወድህ ያለቅሳል ያዝናል ወደ ቀብር ቦታህ አብሮህ ይመጣል እንጅ መቸም አንተ ሞተሀልና ልሙት አይልም። 3- ሶሰተኛው እሰከ መጨረሻው አንተ ጋ ነኝ ያለው በዚች አለም ሰትኖር የሰራናቸው ጥሩና መልካም ሰራዎች ናቸው፡፡ በዚህ ምድር ላይ የምንሰራቸው ጥሩ ሰራወች የዘላለም ሰንቃችን ናቸው እስከ መጨረሻው ከአኛ ጋር ይከተሉናል፡፡ ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና መልካም ጎደኛ ይስጠን።
إظهار الكل...
መስቀል ና እኔ ሀገር ምድር ጋራ ሸንተረር በእረጓዴዉ ሳር ከውበት ቀንዲል በፍካት ሲነከር። ዱፌ አያኒ መስቀላ ቺቺሳ እንጨፍር በቀዬው ሰቀላ ። ዮ መስቀላ ያሆዴ መስቀላ አፍቃሪ ከፍቅሩ ወዳጅ ከዘሩ ሲቀላቀል ክትፎውን ሲጡ ጥሬውን ሲቆርጡ እኔ ! እኔ ! እኔ! አንቺን እደተራብኩ እንቡጥ ፍቅሬን በትዝታ እየኮመኮምኩ ብቻዬን ወና ሰውነት ታቆፌ ልቤን ባንቺ አስለክፌ ይኸው አለው አለው! አለው ! አለው ! የመስቀልን ወፍ ካመት አመት ደመራ ሲወድቅ ሲተነበይበት እኔ አለው ልቤ ከተመለሰ ብዬ ወይ ባዶውን ወይ አንቺን ይዞ ጠሎቴ ሰምሮ ከመጣሽ ብዬ አንቺን መጠበቄን ሰው እዳያቅ አምላክ ፍቅር ሊሰጥ በተሰቀለበት እኔም ልቤን እድታይው ከፍ አድርጌ ከአደባባይ ሰቅዬ ከአናቱ የአንቺ አፍቃሪ ብዬ እኔ ከስር አለው አፍቃሪ የሚለውን በገመድ አጥብቄ አንጠልጥዬ ። ELA SK )( CRAZY)( 16/01/14 4:10 - 4:50 Pm
إظهار الكل...
ብዕር ሲደማ https://t.me/bear7sidema7with7elask7crezy ቻናላችንን ይቀላቀሉ ....
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.