ጦር ሜዳ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ምክንያቱም ተጋድሎአችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን -ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ -ከሥልጣናትና ከኀይላት -እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው። ኤፌ 6:12 *ጦር ሜዳ ውስጥ መሆኑን ያላወቀ ሰው ለውግያ የተዘጋጀ አይደለም፡፡ ሁሌ የተማረከ እና የተሸነፈ ነው፡፡ ሰለዚህ "የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ ኤፈ 6:13.... ... አስተያየት ካላችሁ @endyab
إظهار المزيد1 199
المشتركون
-124 ساعات
-27 أيام
-830 أيام
أرشيف المشاركات
1 199
ዓይኖቼ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ይዩ (፬x)
ጆሮቼ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ይሥሙ (፬x)
እግሮቼ ፡ ለአንተ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ይቅኑ (፬x)
ሙሉ ፡ አካላቶቼን ፡ ለአንተ ፡ ላስገዛልህ ፡ ያክብሩህ
መላው ፡ እኔነቴ ፡ ለአንተ ፡ መቅደስ ፡ ሆኖ ፡ ይኑሩልህ (፪x)
ቸር ፡ ጌታ ፡ ፍፁም ፡ ሆኜ ፡ ላመልክህ ፡ ዘንድ ፡ ወደድኩኝ
ዓይኖቼ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ይዩ
ጆሮቼ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ይሥሙ
እግሮቼ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ይቅኑ
መላ ፡ እኔነቴ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ያክብርህ (፪x)
1 199
ዓይኖቼ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ይዩ (፬x)
ጆሮቼ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ይሥሙ (፬x)
እግሮቼ ፡ ለአንተ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ይቅኑ (፬x)
ሙሉ ፡ አካላቶቼን ፡ ለአንተ ፡ ላስገዛልህ ፡ ያክብሩህ
መላው ፡ እኔነቴ ፡ ለአንተ ፡ መቅደስ ፡ ሆኖ ፡ ይኑሩልህ (፪x)
ቸር ፡ ጌታ ፡ ፍፁም ፡ ሆኜ ፡ ላመልክህ ፡ ዘንድ ፡ ወደድኩኝ
ዓይኖቼ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ይዩ
ጆሮቼ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ይሥሙ
እግሮቼ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ይቅኑ
መላ ፡ እኔነቴ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ያክብርህ (፪x)
1 199
📖 ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች፦
ዘኁልቁ 30፥1-16 | ኤፌሶን 5፥22-24 | ቆላስይስ 3፥18 | 1ኛ ጴጥሮስ 3፥1-2 | 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3
1 199
📖 በክርስቲያናዊ ቤተሰብ ውስጥ ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓትና አገዛዝ ሴቶችን በተመለከተ
ሴት ልጅ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የቤተሰብ ሥርዓት ውስጥ ያላት ቦታ
መጽሐፍ ቅዱስ ሴት ልጅ ከጋብቻ በፊትም ሆነ ከጋብቻ በኋላ በቤተሰብ ሥልጣንና ኃላፊነት ሥር እንደምትኖር ያሳያል። በራሷ ላይ ሥልጣን ኖሯት የፈለገችውን እንድትወስን፣ በራሷ ውሳኔና ፈቃድ እንደፈለገች በነጻነት እንድትመላለስ አይደግፍም።
ሴቶች ካገቡ በኋላ ለባሎቻቸው መገዛት እንዳለባቸው ሁሉ፣ ከመግባታቸው በፍት በአባታቸው ቤትም የፈለጉትን ለማድረግና ለመወሰን ሙሉ ነጻነት እንዳላቸው ማሰብ አይገባም።
ይህንን የሚያሳይ አንድ ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አለ።
📖 ዘኁልቁ 30፥1-16
ከጋብቻ በፊት፦ ያላገባች ሴት በአባቷ ሥልጣንና ኃላፊነት ሥር ናት
በአባቷ ቤት የምትኖር ሴት ልጅ ለእግዚአብሔር (ለያህዌ) ስእለት ብትሳል፣ ወይም አንድ ነገር ለማድረግ በመሐላ ራሷን ግዴታ ውስጥ ብታስገባ፣ አባቷም ይህንን ሰምቶ ምንም ነገር ሳይላት ቢቀር፣ ስእለቶቿ በሙሉና ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች ሁሉ መፈጸም ይኖርባቸዋል። አባቷ ይህንኑ ሰምቶ ከከለከላት ግን የትኛውም ስእለቷ ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበት መሐላ አይጸናባትም። አባቷ ስለከለከላት እግዚአብሔር (ያህዌ) ነጻ ያደርጋታል።
📖 ዘኁልቁ 30፥3-5
አያችሁ?! ይህ የእግዚአብሔር ሥርዓት ነው!
ያላገባችና በአባቷ ቤት የምትኖር ሴት ልጅ እንደፈለገች መወሰንና መመላለስ አትችልም። አባቷ መወሰንና መፍቀድ አለበት። እግዚአብሔርም ይህንን ሥርዓት አጽድቋል። ሴት ልጅ በአባቷ ሥልጣንና ኃላፊነት ሥር ናት።
ይህ የአባት ሀላፊነት በጋብቻ ሥርዓት ውስጥም ይታያል
ለዚህ ነው በጋብቻ ሥርዓት ውስጥ ሊያገባት የፈለገ ወንድ ሽማግሌዎችን ወደ ሴቷ ቤተሰብ በመላክ፣ "ልጃችሁን ለልጃችን" በማለት የጋብቻ ጥያቄ የሚያቀርበው። ይህም የአባቷን ፈቃድና የቤተሰቡን ስምምነት ለመጠየቅ ነው።
የአባትና የቤተሰብ ስምምነት ከፍተኛ ቦታ አለው። አባቷ ፈቃደኛ ከሆነ ብቻ ነው ልያገባት የምችለው።
አባቷ ፈቃደኛ ካልሆነና ሽማግሌዎችን ካልተቀበለ፣ እርሷ ትዳሩን ብትፈልግም በእርሷ ፈቃድ ብቻ ትዳሩ ሊመሠረት አይችልም። አባቷ "ልጄን አልሰጥም" ማለት ይችላል።
ምክንያቱም እርሷ በአባቷ ሥልጣንና ኃላፊነት ሥር ናት።
ለዚህ ነው ሴት ልጅ በአባቷ ቤት ውስጥ እስካለች ድረስ ያለአባቷ ፈቃድ የፈለገችውን ማድረግ የማትችለው።
ይህ የእግዚአብሔር ሥርዓት ነውና።
📖 ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች፦
- ዘፀአት 22፥16-17
- ዘፍጥረት 24፥51
- ዘዳግም 22፥28-29
- ዘዳግም 22፥16
- 1ኛ ቆሮንቶስ 7፥36-38
- ዘሌዋውያን 21፥9
- ዘፍጥረት 29፥18-19
⚠️ ማስጠንቀቂያ፦ ይህ መርህ በክርስቲያናዊና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ቤተሰብ ውስጥ ስላለው ሥርዓት እንደሆነ እየገለጽኩ ነው።
---
ከጋብቻ በኋላ፦ ያገባች ሴት በባሏ ሥልጣንና ኃላፊነት ሥር ትሆናለች
ሴት ልጅ ካገባች በኋላ በባሏ ሥልጣንና ኃላፊነት ሥር ትሆናለች።
ስእለትን በተመለከተ ይህንን መርህ የሚያሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዲህ ይላል፦
አንዲት ሴት ስእለት ከተሳለች ወይም አምልጧት ተናግራ ራሷን ግዴታ ውስጥ ካስገባች በኋላ ባል ብታገባ፣ ባሏም ሰምቶ ምንም ነገር ሳይላት ቢቀር፣ ስእለቶቿ ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች መፈጸም ይኖርባቸዋል። ሆኖም ባሏ ይህንኑ ሰምቶ ከከለከላት፣ ለመፈጸም የተሳለችውንም ሆነ አምልጧት ተናግራ ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ነገር ስለሚያስቀር፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ከዚህ ነጻ ያደርጋታል። 📖 ዘኁልቁ 30፥6-8
ይህ ቃል ስእለትን በተመለከተ የተሰጠ ቢሆንም፣ በሌሎችም የሕይወት አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንደ መርህ ያስቀመጠውን የቤተሰብ ሥርዓት ያሳያል።
📖 ይህንኑ መርህ የሚያጸኑ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች፦
- ኤፌሶን 5፥22-24
- ቆላስይስ 3፥18
- 1ኛ ጴጥሮስ 3፥1-2
- ቲቶ 2፥4-5
- 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3
- ዘፍጥረት 3፥16
በሚስት ጥፋት ባል በኃላፊነት ይጠየቃል
ይህ ብቻ አይደለም፤ ያገባች ሴት ለምታደርገው ነገር በኃላፊነት የሚጠየቀው ባሏ እንደሆነም ያሳያል።
📖 ዘኁልቁ 30፥10-15
"ከባሏ ጋር የምትኖር ሴት ብትሳል ወይም አንድ ነገር ለማድረግ በመሐላ ራሷን ግዴታ ውስጥ ብታስገባና ባሏም ይህንኑ ሰምቶ ምንም ነገር ባይላትና ባይከለክላት ግን ስእለቶቿም ሆኑ ለማድረግ ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች ሁሉ የጸኑ ይሆናሉ። ባሏ ሰምቶ እንዲቀሩ ካደረገ ግን ስእለቶቿንም ሆነ ለማድረግ ቃል የገባቻቸውን ነገሮች የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ባሏ እንዲቀሩ ስላደረጋቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) ነጻ ያደርጋታል። የትኛውንም ስእለቷን ወይም ራሷን ለመከላከል በመሐላ የታሰረችበትን ሁሉ ባሏ ሊያጸናው ወይም ሊያፈርሰው ይችላል።
ይሁን እንጂ ባሏ ስለ ጉዳዩ ከዕለት ወደ ዕለት ምንም ነገር ሳይላት ቢቀር፣ ስእለቶቿን ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸውን ነገሮች ሁሉ እያጸናላት ነው ማለት ነው፤ ስለ ነገሮቹ ሰምቶ ምንም ነገር ሳይላት በመቅረቱ አጽንቶላታል።
ስለ ነገሮቹ ከሰማ በኋላ እንዲቀሩ ካደረገ ግን፣ #ለፈጸመችው_በደል_በኃላፊነት_የሚጠየቀው_ራሱ_ነው።" ዘኁልቁ 30፥10-15
በሚስት ጥፋት ባል በኃላፊነት ሰለመጠየቅ የሚያሳዩ ሌሎች ምሳሌዎች
📖 ዘፍጥረት 3፥9፣17 እና ሮሜ 5፥12
ሐዋርያው ጳውሎስ ኃጢአት ወደ ዓለም ስለመግባቱ ሲያስተምር ሔዋንን ሳይሆን አዳምን ዋና ተጠያቂ ያደርገዋል። ምክንያቱም አዳም የቃል ኪዳኑ የበላይ ጠባቂ (Head) ስለነበረ ነው።
ሮሜ 5፥12፦ "ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው (በአዳም) ወደ ዓለም ገባ..."
📖 1ኛ ሳሙኤል 3፥13፣ 4፥18
ልጆቹ ባጠፉት ጥፋት ምክንያት አባትየው ዔሊ ጭምር በአንድ ቀን ሞተ፤ የክህነት ክብሩም ከቤተሰቡ ተወሰደ።
📖 1ኛ ነገሥት 21፥19
ጥፋቱን የጠነሰሰችውና ያስፈጸመችው ኤልዛቤል ብትሆንም፣ እግዚአብሔር ግን ነቢዩ ኤልያስን ልኮ የሞት ፍርድ ያወጀው በባልየው በአክዓብ ላይ ነበር።
📖 የሐዋርያት ሥራ 5፥3
በአዲስ ኪዳን አናንያና ሰጲራ የተባሉ ባልና ሚስት መሬታቸውን ሸጠው ብሩን ደበቁ። ሁለቱም ተስማምተው ያደረጉት ቢሆንም፣ የቤተሰቡ ራስ አናንያ በመሆኑ ሐዋርያው ጴጥሮስ መጀመሪያ የጠየቀውና የቀጣው አናንያን ነበር።
---
መበለትና የተፋታች ሴት በራሷ ላይ ሥልጣንና ኃላፊነት አላት
ይህ መርህ ባል በሞተባት (መበለት) እና በተፋታች ሴት ላይ እንደማይሠራ ስለ ስእለት በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያስረዳል።
እነዚህ ሴቶች ስእለታቸውን በራሳቸው የመወሰንና የመፈጸም ሥልጣንና ኃላፊነት እንዳላቸው ይገልጻል።
ዘኁልቁ 30፥9፦
"ባሏ የሞተባት ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት የትኛውም ስእለቷ ወይም የገባችበት ግዴታ ሁሉ የጸና ይሆናል።"
📖 ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች፦
- 1ኛ ቆሮንቶስ 7፥39
- ሮሜ 7፥2-3
---
📌 መደምደሚያ
በአጠቃላይ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በቤተሰብ ውስጥ የሥልጣንና የኃላፊነት ሥርዓት እንዳለ ያስተምራል።
- ከጋብቻ በፊት፦ ሴት ልጅ በአባቷ ሥልጣንና ኃላፊነት ሥር ትሆናለች።
- ከጋብቻ በኋላ፦ በባሏ ሥልጣንና ኃላፊነት ሥር ትሆናለች።
- ባል የሞተባት ወይም የተፋታች ሴት፦ በራሷ ላይ የውሳኔና የኃላፊነት ሥልጣን አላት።
ይህ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ቤተሰብ ውስጥ ያለው የሥልጣን፣ የአመራርና የኃላፊነት ሥርዓት ነው።
1 199
15, #ትዕቢተኞች(proud) የራስን ማንነት ራስን የራስን ነገር ከሌሎች እንደሚበልጥ እና የሌላው ሁሉ ከሱ በታች እንደሆነ የማሰብ ዝንባሌ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በትምህርት ብዙ ስለሄደ ብቻ በተሳሳተበት ጉዳይ ከሌሎች እርምትን መቀበል አለመፈለግ ምክንያቱም 'እኔ አልሳሳትም' ብሎ ስለሚያስብ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
16, #ትምክህተኞች(Boasters)፦ስላላቸው ነገር ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የማውራት ዝንባሌን ያሳያል። ስለራሳቸውም የተጋነነ እሳቤ መያዝ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ስላገኛቸው ድሎች መንፈሳዊ ስጦታዎች አጋኖ ተፅዕኖ እንዲፈጥር በመፈለግ ማውራት። (#ጉራ ማለት ነው) እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
17, #ክፋትን የሚሰሩበትን መንገድ ማውጠንጠን(Inventors of evil things) ይሄ በዚ ዘመን ፈጠራ ወይም አዲስ ነገር የመስራት ችሎታ እንደሚባል፤ ክፋትን ሌሎችን የመጉዳት አዲስ መንገድ መፈለግይ ያሳያል። እንዴት ልጉዳው፣እንዴት ላጥፋው፣እንዴት ቤቱን ልበጥብጥ፣እንዴት ስሙን ላጥፋ፣እንዴት ልጣለው እያሉ ጋዢዜ ሰጥቶ ማሰብ መንገድ መፈለግ ነው።
ለምሳሌ፦አንድ ሰው ሌሎችን ጎድቶ ወይም ሰሮቆ እንዴት ገንዘብ እንደሚያገኝ ማሰብ፤ በsocial media ሌሎችን ለማንቋሸሽ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ለማደረግ በአደባባይ እነሱን የሚያዋርዱበትን መንገድ መፈለግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
18, #ለወላጅ የማይታዘዙ(Disobedient to family)፦ ልጆች ለወላጆቻቸው ሊታዘዙ እንደሚገባ ይህም በረከትን እንደሚያስገኝላቸው መፅሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ወላጆች የተማሩም ሆኑ ያልተማሩ ሃብታም ሆኑ ድሃ ልንታዘዛቸው ዘንድ እግዚአብሔር ያለምንም ቅድመሁኔታ አዟል።ወላጆችህን የመረጠለህ እግዚአብሔር እንጂ አንተ ወይም ወላጆችህ አይደሉም ስለዚህ ያለምንም ጥያቄ ለወላጅ መታዘዝ ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ነው
ወላጅን አለመታዘዝ ደግሞ ለእግዚአብሔር ቃል አለመታዘዝን ያሳያል።
19, #የማያስተውሉ፣የማያመዛዝኑ፣የድርጊታቸውን መዘዝ ቆም ብለው የማያስተውሉ።(የማያስተውል ልቦናቸው ጨለመ የሚለው ትርጉም ከዚህ ጋር ይመሳሰላል።)፣መለየት የሌላቸው(Without Understanding)፦በደመ ነፍስ መመራትን ያሳያል ይህም ልናዳረግ ስላለው ነገር መጥፎና መልካም ጎን አለማየትን ይገልፃል።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው የድርጊቱን መጥፎ መዘዝ እያወቀ ከማድረግ መመለስ አለመፈለግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
20, #ውል የሚያፈርሱ(covenant breakers)፦ ታማኝነትን ማጉደል፣ ቃልን ማጠፍ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በአሆነ ጉዳይ ቃል ገብቶ ወይም ውል አድርጎ ግን ውሉን ለማፍረስ አስቦ ኋላም ሲያፈርስ
እና የመሳሰሉትን ያካትታል። ከአንደበታችን ለሚወጣ ቃል መጠንቀቅ እና ከተናገርን ግን ቃላችንን ልንፈፅም ይገባናል።
21, #ርህራሄ_የሌላቸው(Without natural affection)፦ በተፈጥሮ ለሰዎች ወይም ለቅርብ ሰዎች፣ለቤተሰብ፣ለልጆች፣ለወላጅ፣ለትዳር አጋር ሊኖር የሚገባን ፍቅርና ርህራሄ ማጣት።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ለራሱ ለመጠቅም ሲል የገዛ ወንድሙን ሲገፋ፣ ሲጠላ፤እናት ባለውና በሌለው ልጆቿ መሃል አድሎ ስታደርግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
22, #እርቅን የማይወዱ(Implacable)፦ ሰላምን መፍጠር የማይወዱ ወይም የማይታረቁ ይቅርታ የማያደርጉ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ከተጋጨው ሰው ጋር ሰው ለማስታረቅ ሲሞክር ወይም የተጣለው ሰው ራሱ ሆዶ ይቅርታ ሲጠይቅ አለመቀበልና ሆን ብሎ በጥል መቆየት ቂመኛ መሆን እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
23, #ምህረት የሌላቸው፣ጨካኞች(Unmerciful)፦
ርህራሄ ማጣት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አለማድረግ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው የተጎዳን ሰው መርዳት እየቻለ ከጭካኔ የተነሳ ለመርዳት አለመፈለግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
NB እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ድርጊቶች እንደሁኔታው እግዚአብሔር በሚሰጠን ጥበብና ማስተዋል የምንይዛቸው እንጂ ወጥ የሆነ ተፈፃሚነት አላቸው ማለት አንችልም ለምሳሌ አንድ ሰው መንገድ ላይ ታሞ የወደቀ መስሎ ሊረዳው የሚመጣውን ሰው ለመዝረፍ የሚሰራ አለ ይህን ሰው ትቶ መሄድ ጭካኔ አይባልም። ነገር ግን በእውነት ሰውየው የተጎዳ ሆኖ፣ እኛ መርዳት እየቻልን፣መንፈስ ቅዱስ እያሳሰበን ችላ ብሎ መሄዱ ነው በደል!!
🙏ራሳችንን እንገምግም!!
1 199
ሮሜ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤
²⁹ ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥
³⁰ ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚያንገላቱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥
³¹ የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው፤
³² እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም።
Romans 1 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹ Being filled with all unrighteousness, fornication, wickedness, covetousness, maliciousness; full of envy, murder, debate, deceit, malignity; whisperers,
³⁰ Backbiters, haters of God, despiteful, proud, boasters, inventors of evil things, disobedient to parents,
³¹ Without understanding, covenantbreakers, without natural affection, implacable, unmerciful:
³² Who knowing the judgment of God, that they which commit such things are worthy of death, not only do the same, but have pleasure in them that do them.
፦በዚህ ክፍል ላይ የተጠቀሱትን የሐጢያት አይነቶች በዝርዝር እንመልከት፤ ሌሎችን ለመገምገም እና ለመፍረድ ሳይሆን እራሳችንን እንመርምር፤
1#አመፃ(Unrighteousness,Injustice, wrongdoing) አመፃ ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክለኛ ከተባለው ነገር ተቃራኒን መስራት ነው።
ለምሳሌ፦ፍትህን ማጓደል፣ የሰራተኛን ደሞዝ ማወናበድ፣ ማጭበርበር፣ ችግረኛውን ድምፅ የሌለውን መጨቆን፣ አድሎ ማድረግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል ።
2,#ዝሙት፣መመኘት(fornication,sexual immortality,adultery)፦
#ዝሙት የሚለው ቃል የትኛውንም አይነት ወሲባዊ ርኩሰትን ያካትታል።
ለምሳሌ፦ #መዳራት፣ ከጋብቻ በፊትና ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ግንኙት፣ ግለ ወሲብ፣ የወሲብ ምስሎችን ሆን ብሎ ለወሲብ አላማ መመልከት፣ሴተኛ አዳሪነት፣ተመሳሳይ ፆታ ወሲብ እና የመሳሰሉትን የሚያካትት ነው።
3, #ክፋት(wickedness)፦ ክፉ ጠባይ፣ ከመጥፎው ጋር የመወዳጀት ዝንባሌ፣የክፋት ስራ።
ለምሳሌ፦አንድ ሰው ሆን ብሎ ሌላውን ሰው ለራሱ ጥቅም ሲል መጉዳት፣ ህፃናትን መጉዳት ማሰቃየት እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
4, #ስግብግብነት፣መጎምጀት ፣የማይረካ፡በቃኝ የማይል ምኞትና አምሮት(Covetousness,greed,insatiable desire to have more) በቆላስይስ 3:5 ላይ ስግብግነት አምልኮተ ጣዖት ተብሎ ተጠቅሷል?? ምን ለማለት ፈልጎ ነው ለሚለው እናንተ የራሳችሁን ጥናት አድርጉ.....
ለምሳሌ፦ አንድ ነጋዴ የሚበቃው ነገር እያለው የበለጠ ትርፍ ለማግኘት ሲል ያለአግባብ ዋጋ ሲጨምር ወይም ሲያጭበረብር፣ሚዛን ሲሰርቅ፣ 😁የዘመኑ ሴቶችና አንዳንድ ወንዶች በተፈጥሮ ባላቸው ውበት ባለመርካት ያለማቋረጥ እራሳቸውን መልካቸውን ለማሻሻል ጥረት ሲያደርጉ እና እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎችም ብዙ አሉ።
እናንተ ከዚ ማብራሪያ አንፃር የተረዳችሁትን በcomment ማጋራት ትችላላችሁ።
5, #ምቀኝነት ፣ምግባረ ብልሹነት፣ ሆደመጋዝነት(Maliciousness,morally bad disposition)
ለምሳሌ ፦አጠገባችን ያሉ ሰዎች ሲጎዱ ውስጣችን ሲደሰት፣ የምንረዳ እያስመሰልን በጉዳታቸው ላይ ጉዳት ለመጨመር መፈለግ፣በንግግር መውጋት፣ ህመማቸውን የሚያባብስ ነገር ሆን ብሎ ማንሳት እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
6, #ቅናት(Envy,)፦ በሌሎች መልካም እድል ወይም መጠቀም ቅር መሰኘት ማዘን፣እንዳይሳካላቸው መመኘት ወይም መፈለግ፦
ለምሳሌ፦ ጓደኛችን ነፃ የትምህርት እድል ቢያገኝ ለሱ ደስ ሊለን ሲገባ እንዳይሳካለት እንዲወድቅ መመኘት ምክንያቱም የሱ ስኬት እኛን ዝቅ እንደሚያደርግን ስለምናስብ።
7, #ነፍሰ ገዳይነት(murder)፦
ለምሳሌ፦ ሆን ብሎ የሰውን ነፍስ ማጥፋት ይኸውም ለራስ ጥቅም ሲባል የሚደረግ ነው(ፅንስን አንዳች የጤና እክል ከሌለ በስተቀር ወዶና ፈቅዶ ማስወርድ እዚህ ስር ይካተታል።
8, #ክርክር፣ጥልን(debate/strife,quarrelling, contention, rivalry)፦
ለምሳሌ፦ ሁለት ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ እውነትን ከመፈለግ ይልቅ እርስ በርሳቸው ለመሸናነፍና የሰውን ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ሲከራከሩ ይሄ ብቻ አይደለም በሁሉም ግንኙነቶች መሃል ሰላምን የማያመጣ ችግርን የማይፈታ ወደ ስምምነት የማያደርስ በአልሸነፍ ባይነት መንፈስ እውነትን ከመፈለግ ይልቅ የራስን ማንነት ላለማስነካት የሚደረግ ጥረት ሁሉ እዚህ ስር ይካተታል።
9, #ተንኮል፣ማታለል(Deceit):- ለራስ ጥቅም ሲባል ሌሎችን የሚጎዳ ዘዴ መጠቀም።
ለምሳሌ፦ ለድሆች ድጋፍ እናድርግ ወይም የቤተክርስቲያንን ስራ እንስራ በማለት ገንዘብ ሰብስቦ ለራስ መጠቀም፤ ገንዘብ አንድ ላይ እናስቀምጥ በማለት ወይም እኔ ጋር ይሁን በማለት ኋላ መካድ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
10,ክፉ ጠባይ(Malignity):-
ለምሳሌ፦የሌሎችን ደካማ ጎን መፈለግ፣ የሌሎችን ድርጊት በቀና መረዳት አለመቻል እና ስለሌሎች መጥፎውን ማሰብ የሚወድቁበትን መንገድ ማውጠንጠን በሌሎች መከራ መደሰት እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
11, #ሐሜተኞች፣ የሚያንሾካሽኩ(Whisperer)፦ በቡድን ወይም ህብረት መካከል አፍራሽ መረጃን የሚያሰራጩ የህብረት ጠንቆች።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በህብረት መካከል ስለ አንድ ወንድም ወይም እህት ያልተረጋገጠ ክስን በድብቅ ማሰራጨትና ህበረቱ በዚያ ሰው ላይ እንዲነሳበት ማድረግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
12, #ስም
አጥፊዎች(backbiters) ፦ ሆን ብሎ የአንድን ሰው ስም ወይም ክብር ወይም ተቀባይነት ለማጉደፍ የሚደረግ ነው።
ለምሳሌ፦ ስለ አንድ ወንድም/አገልጋይ ታማኝ አለመሆን ሆን ብሎ ማውራት ይህም ሰውየው ታማኝ ስላልሆነ ሳይሆን ሰዎች እሱን እምነት እንዳይጥሉበት፤ በሌሎች ዘንድ ያለውን ምስል ማጥፋት እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
13, #አምላክን የሚጠሉ(haters of God)፦ የእግዚአብሔርን ፅድቅ ማንነት አምላክነት ከሐጢያቲዊ ድርጊታቸው ጋር ስለማይሄድ መጥላትን ያመለክታል።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው እግዚአብሔር ውሸት ሐጢያት ነው እንዳለ እያወቀ ነገር ግን ውሸት ጥቅምን ስለሚያስገኝለት ሲል የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ወደጎን ትቶ ወይም ችላ ብሎ ውሸትን መናገርእና የመሳሰሉትን ያካትታል።
14, #ተሳዳቢዎች፣ የሚያንገላቱ(Despiteful)፦ሌሎችን በንቀትና በወረደ አመለካከት መመልከት፣ በንግግር መሃል ክብራቸውን ማዋረድ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ጓደኛውን ስለሌለው ነገር በማንሳት በሰዎች ፊት እንዲሸማቀቅ ማድረግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
1 199
ሙሉ ወንጌል ሀ መዘምራን-አምላክ እረኛዬ ነው
*****
ክንድህ ይበርታ በጠላትህ በር
ሥራቸው ይፍረስ ይድቀቅ ይሰበር ሃሌሉያ
ስምህ ይለምልም ዙፋንህ ይጽና
ለባሪያህ በጐ ውለሃልና ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ውዳሴን ከአፌ አንተን ከልቤ
ከቶም አይጠፋ ብኖር ተርቤ ሃሌሉያ
የቅርብ ወዳጄ የጦር አዝማቼ
ብቻ አትለየኝ ብቆይ ታክቼ ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ብቆም ብቀመጥ ብሄድ ብተኛ
አምላኬ አንተ ነህ የእኔ ጓደኛ ሃሌሉያ
ጽልመት ሲመጣ የመከራ ጉም
አንተን ጠርቼ እኔ አላፈርኩም ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ሕመም ሞትህን ሥጋዬ ለብሶ
ይዋረድ ይለፍ ጽዋህን ቀምሶ ሃሌሉያ
የጻድቁን ሞት ነፍሴ ተጠምታ
ትጥገብ አትፈር ስምህን ጠርታ ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
1 199
ሙሉ ወንጌል ሀ መዘምራን-አምላክ እረኛዬ ነው
*****
ክንድህ ይበርታ በጠላትህ በር
ሥራቸው ይፍረስ ይድቀቅ ይሰበር ሃሌሉያ
ስምህ ይለምልም ዙፋንህ ይጽና
ለባሪያህ በጐ ውለሃልና ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ውዳሴን ከአፌ አንተን ከልቤ
ከቶም አይጠፋ ብኖር ተርቤ ሃሌሉያ
የቅርብ ወዳጄ የጦር አዝማቼ
ብቻ አትለየኝ ብቆይ ታክቼ ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ብቆም ብቀመጥ ብሄድ ብተኛ
አምላኬ አንተ ነህ የእኔ ጓደኛ ሃሌሉያ
ጽልመት ሲመጣ የመከራ ጉም
አንተን ጠርቼ እኔ አላፈርኩም ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ሕመም ሞትህን ሥጋዬ ለብሶ
ይዋረድ ይለፍ ጽዋህን ቀምሶ ሃሌሉያ
የጻድቁን ሞት ነፍሴ ተጠምታ
ትጥገብ አትፈር ስምህን ጠርታ ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
1 199
አውጃለሁ- ቃልኪዳን ጥላሁን
******************
አውጃለሁ ዛሬ ታላቅነቱን
አውጃለሁ ዛሬ አምላክነቱን (4x)
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ (2x)
ትልቅ ነዉ ትልቅ ከሚመስለው በላይ
ኃያል ነዉ ኃያል ከሚመስለው በላይ
ብርቱ ነው ብርቱ ከሚመስለው በላይ
ጌታ ነው ጌታ ከሚመስለው በላይ (2x)
ከእግዚአብሔር የሚበልጥ አንድ ነገር አላውቅም
ይህ እንደዚህ ነው አንደዚያ ነው አልልም
ግን እርግጠኛ ነኝ አንድ ነገር አውቃለሁ
የማምልከው አምላክ ከዚህ ሁሉ በላይ ነው (2x)
በላይ በላይ ፣ በላይ በላይ (4x)
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
አውጃለሁ ዛሬ ታላቅነቱን
አውጃለሁ ዛሬ አምላክነቱን (4x)
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነዉ ትልቅ ከሚመስለው በላይ
ኃያል ነዉ ኃያል ከሚመስለው በላይ
ብርቱ ነው ብርቱ ከሚመስለው በላይ
ጌታ ነው ጌታ ከሚመስለው በላይ (2x)
ከእግዚአብሔር የሚበልጥ አንድ ነገር አላውቅም
ይህ እንደዚህ ነው አንደዚያ ነው አልልም
ግን እርግጠኛ ነኝ አንድ ነገር አውቃለሁ
የማምልከው አምላክ ከዚህ ሁሉ በላይ ነው (2x)
በላይ በላይ ፣ በላይ በላይ (4x)
1 199
🌿✨ ከግል ምልከታ ይልቅ ለእውነት ዋጋ ስጡ! ✨🌿
📌 ይህ መርህ ሁሉም የሕይወታችን አቅጣጫ ይመለከታል።
🏫 በትምህርት ቤት፣
👨👩👧👦 በቤተሰብ መካከል፣
🤝 በጓደኝነት ውስጥ፣
💼 በሥራ ቦታ፣
👑 በአመራር ውስጥ፣
📖 በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣
🌍 በባህልና በማኅበረሰብ አመለካከቶች፣
🔄 በዕለት ተዕለት ኑሮና በማንኛውም ውይይት።
የትም ብትሆኑ፣ ከማንም ጋር ብትሆኑ፣ ምንም እያደረጋችሁ ብትሆኑ፦
✅ ከግል ምልከታ ይልቅ ለእውነት ዋጋ ስጡ።
✅ ከግል አመለካከትና አስተያየት ይልቅ እውነትን አስቀድሙ።
✅ ከሰዎች ሀሳብ ይልቅ እውነታውን ምረጡ።
✅ ከግል ጥቅም ይልቅ ለእውነት ቁሙ።
📖 የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት
🌿 «ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ።»
📌 1 ተሰሎንቄ 5:21
🌿 «ይልቁንም እውነትን በፍቅር እየተናገርን፣ ራስ ወደ ሆነው ወደ እርሱ በነገር ሁሉ እናድጋለን፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።»
📌 ኤፌሶን 4:15
✨ እውነትን ፈልጉ። እውነትን ምረጡ። እውነትንም በፍቅር ተናገሩ! 🌿
1 199
በምድር #እንደመፃተኛ እና #እንግዳ የምኖር ነኝ፤ ከአለም ጋር የማልስማማ ነኝ።
የአለምን ያደፈ የቆሸሸ ግብዣ በደም በተጨማለቀ እጅ ከእግዚአብሔር ቁጣ በታች ያለ የእግዚአብሔር ጠበኛ የሚያቀርበውን ነፍሴ እጅጉን ትፀየፋለች።
በአለም የሚያምር ነገር የለም።
ጌታ ኢየሱስ ሆይ ናና፤
አመፀኞችን ተበቀል፣
እምቢተኞችን ዋጋቸውን ክፈላቸው
ናና ከዚች አለም አመፃ አሳርፈን።
ክርስቲያን እንዴት ከአለም ጋር ይተባበራል።
እንዴትስ በአመፀኞች ድል አብሮ ይደግሳል።
ክርስቲያን ድንበሩን ጠብቆ ይኖራል።
ክርስቲያን በአለም ውሸት አይታለልም።
የጠራውን ታምኖ ይኖራል እንጂ ተበልቶ ለሚጠፋ እንጀራ ብዙ ዋጋ በመክፈል የተጠራበትን ትልቁን ሽልማት አይጥልም።
ወገኖች ንቁ ተግታችሁ ጌታችሁን ጠብቁ እሱ እንደተናገረው ይመጣል።
መምጫው ቀርቧል
አሁን ጊዜው ነቅተን ታጥቀን የምንቆምበት እንጂ ከአላፊው አለም ጋር የምንሟሟቅበት ጊዜ አይደለም።
#ኧረ_እንንቃ!
ለኔ ግን ኢየሱስ ይምጣልኝ ተስፋዬ ምፅዓቱ ነው። እንጂ በዚህች አለም እኔስ #እንግዳና_መፃተኛ ነኝ!!
1 199
ሮጦ ሮጦ-ደረጄ ከበደ (ዶ/ር)
━━━━
ሮጦ ሮጦ ሳይደርስ የልቡ
ለሞተ አዝናለሁ ሳይሞላ አሳቡ
አንተስ በሕይወት ሰምተሃል ቃሉን
ፍርድ ባንተ ነው ብትንቅ ማዳኑን
ወንድሜ ስማ ቁምነገር ምክሬን
ላንተ የሚበጅ
ሳትሆን በአንቀልባ አቅም ሳያንስህ እንደ ሕጻን ልጅ
ሞት አጥልቶብህ መቃብር ውጦህ
ትንፋሽህ ሳይቆም
ጌታን ተቀበል ዋስትና አድርገው ሳትጠፋ ከአለም
እድሜ ጤዛ ነው ረጋፊ አበባ
ባለም ስትኖር
የጭንቅ የስቃይ ዘመነ ለቅሶ
ዋይታና ሽብር
የእፎይታህ ናፍቆት የሰላም ፍቅር
ካለ በልብህ
ጌታን ተቀበል እርሱ ታማኝ ነው ሁሉን ሊሰጥህ
ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ
ሮጠህ ሮጠህ
ዛሬም ሮጠህ ሮጠህ
ትላንትም ሮጠህ
ነጌም ትሮጣለህ
ነገር ግን የትስ ትደርሳለህ
ሁሉም አልረባህ
ሁሉን ሞክረህ
ቧጠህ ቆፍረህ
ትንፋሽ አልቀረህ
ዛሬ ግን ተው ይብቃህ
አጋዥ ጌታ እያለህ
ሮጠህ ሮጠህ
ዛሬም ሮጠህ ሮጠህ
ነጌም ሮጠህ
ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ
የትስ ትደርሳለህ
ኦኦ የትስ ትደርሳለህ ሮጠህ ሮጠህ
ሮጦ ሮጦ ሳይደርስ የልቡ
ለሞተ አዝናለሁ ሳይሞላ አሳቡ
አንተስ በሕይወት ሰምተሃል ቃሉን
ፍርድ ባንተ ነው ብትንቅ ማዳኑን
ሌላ ምን አለ የሚያስጨንቅህ ላንተ ያቃተህ ሱስ ነው መዋተት ባሪያው አድርጎ አንተን የገዛህ
ዝሙት ነው ስካር ያስፈራህ ጓዴ ካንተ አይሎ
ጌታን አማክረው እርሱ ችሎታል ሕይወቱን ከፍሎ
ወንድሜ ስማ ቁምነገር ምክሬን ላንተ የሚበጅ
ሳትሆን በአንቀልባ አቅም ሳያንስህ እንደ ሕጻን ልጅ
ሞት አጥልቶብህ መቃብር ውጦህ ትንፋሽህ ሳይቆም
ጌታን ተቀበል ዋስትና አድርገው ሳትጠፋ ከአለም
ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ
....
1 199
🎵 የልጆች መዝሙር 🎵
ግጥም ፦ አንድነት እና አያንቱ
የሙዚቃ ቅንብር እና ድምጽ፦ AI
🎶 አታስተምሩኝ ዘረኝነትን 🎶
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🎤 አዝማች (Chorus)
አታስተምሩኝ፣ አታስተምሩኝ፣
አታስተምሩኝ ዘረኝነትን፤
አድኑኝ፣ ከማይጠቅመኝ ሚዲያ፤
አስመልጡኝ ከሱስ፣ ከጥፋት።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🎵 ቁጥር 1
ዘሬ ክርስቶስ ነው፣ ቤቴም በሰማይ ነው፤
የምድርን ዘር ጎሳ አታስተምሩኝ፤
ከነገድ ከቋንቋ፣ ክርስቶስ የዋጀኝ፤
በፍቅርና ሰላም እንድኖር ነው።
ልቤ በክርስቶስ፣ በቃሉ እንዲጸና፤
የእግዚአብሔርን ቃል፣ ፍቅሩን ንገሩኝ፤
ከዓለም ብዙ ጥፋት፣ ከዓለም ብዙ ውድቀት፤
አድኑኝ በጸሎት፣ አስመልጡኝ።
🎤 አዝማች
አታስተምሩኝ፣ አታስተምሩኝ፣
አታስተምሩኝ ዘረኝነትን፤
አድኑኝ፣ ከማይጠቅመኝ ሚዲያ፤
አስመልጡኝ ከሱስ፣ ከጥፋት።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🎵 ቁጥር 2
ለዓይኔ መሰናክል፣ ለጆሮዬም ጥፋት፤
የሆነውን ሥር፣ ከፍቴ ንቀሉ።
ስልኩ ቴሌቪዥኑ፣ ሲኦል እንዳይወስዱኝ፤
ለወንጌል እንድጠቀም፣ አስጠንቅቁኝ።
ከሱስ ውድቀት ርቄ፣ ጥፋቱን አውቄ፤
እንድቀደስ ሰውነቴን ጠብቄ፤
ትክክለኛውን አቅጣጫ፣ አሳዩኝ፤
ምሩኝ መንገዱን፣ የኢየሱስን።
🎤 አዝማች
አታስተምሩኝ፣ አታስተምሩኝ፣
አታስተምሩኝ ዘረኝነትን፤
አድኑኝ፣ ከማይጠቅመኝ ሚዲያ፤
አስመልጡኝ ከሱስ፣ ከጥፋት።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
❤️ መልዕክቱ፦ ዘረኝነትን እንቃወም፤ ልጆቻችንን በክርስቶስ ፍቅር፣ በእግዚአብሔር ቃልና በቅድስና እናሳድግ።
1 199
ሰላም
Dr. ደረጄ ከበደ
---
በየአመቱ ሲፋረሙ የብራናው የቀለሙ
እንዲያው ሊፋት መካሪ አጡ
ሰላም ውድዋን ከየት ያምጡ
ይህን ቋጥረው ያን ሲፈቱ
ጀንበር ገባች መላ አልመቱ
ምስጥሩማ ቅርብ ነበር
ለእግዚአብሔር ሰው ቢሰበር
ሰላም! ሰላም! ሰላም! ሰላም!
ወዴት አለሽ?
እሩቅ ሀገር፣ እሩቅ ሀገር
ተሸሽገሽ!
ያለሽበት ያንቺ ማረፍያ ከጠፈር በስቲያ
ሰው ተፍጨርጭሮ ሊያገኛት እንቅልፉን አጥቶ
ዛሬም እንደ ትላንት ባዶ እጁን ቀረ መና ለፍቶ
የሰማዩን አምላክ አቤት ማለት ጠልቶ
መና ቀረ ለፍቶ፣
መና ቀረ ለፍቶ!
የሰላሙን ልዑል ናቁት
አልፈው ሄዱ ገላመጡት
አቅማቸውን ያለወቁ
በምድር ገነው የመጠቁ
በስቅል ወርቅ በእልፍ ሽልንግ
በጠፍ መሬት ያም ቢያስፈልግ
ከገበያ ሊሸምቷት
በምጥ ውለው ወይ ሊወልጧት
ሰላም ስሟን ወተወቷት!
ሰላም! ሰላም! ሰላም! ሰላም!
ወዴት አለሽ?
እሩቅ ሀገር፣ እሩቅ ሀገር
ተሸሽገሽ!
ያለሽበት ያንቺ ማረፍያ ከጠፈር በስቲያ
ሰው ተፍጨርጭሮ ሊያገኛት እንቅልፉን አጥቶ
ዛሬም እንደ ትላንት ባዶ እጁን ቀረ መና ለፍቶ
የሰማዩን አምላክ አቤት ማለት ጠልቶ
መና ቀረ ለፍቶ፣
መና ቀረ ለፍቶ!
ሰላም! ሰላም! ሰላም!
ሰላም ለዓለም!
ሀገሯ ሰማይ ነው
ዘሯ በምድር የለም
ምንጯ በዚህ የለም
በሩቅም በቅርቡም
ክቡራን ክቡራት
ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ክቡር ፕሬዚዳንት
ዘውድም የጫናችሁ
ንግስተ ነገስታት
እሩጫችሁ ይብቃ!
ሰላም ከእግዚአብሔር ናት!
ሰላም ከእግዚአብሔር ናት!
ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በትጋት
ግራ የተጋቡ ተላላቅ መንግሥታት
ደመሩ ቀነሱ
አወጡ አወረዱ
የሰላም መኖሪያ
ጠፍቷቸው መንገዱ።
