cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ዘመድኩን በቀለ

የዘመድኩን በቀለ ጦሟሩን እንደወረደ የሚለቀቅበት ስለሆነ ሁላችሁም ዘመዴን አድናቂዎች ተቀላቀሉት ጆይን አድርጉት ሸሩን ትታችሁ ሼር አድርጉት

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
4 040
المشتركون
-524 ساعات
-137 أيام
-10830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
የመብራት ታሪፍ ነገር "…በዓለም ላይ ዝቅተኛው የመብራት ታሪፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሆነ ከዓለም ጋር እኩል ለመሰለፍ  የታሪፍ ጭማሪ እናደርጋለን" «መብራት ኃይል» እነሱ:- የነዳጅ ዋጋ ኬንያ ላይ፣ የወኃ ዋጋ ጅቡቲ ላይ፣ የኢንተርኔት ዋጋ ኤርትራ ላይ፣ የመብራት ታሪፍ በዓለም ላይ ውድ ነው። ከዓለም እኩል ለመሆን የዋጋና የታሪፍ ጭማሪ እናደርጋለን። አዳዲስ የግብር ዓይነቶች ማለትም እንደ ፕሮፐርቲና የተሽከርካሪ ታክስ ያሉትን ሁሉም ሀገራት ስለሚያስገብሩ እናንተም ትገብራላችሁ እኛ:- ኬንያ ውስጥ አማካይ ዝቅተኛ ግብር የማይከፈልበት የደሞዝ መጠን 111.5 ዶላር ወይም 6438 ብር ነው። የገቢ ግብር ደግሞ አራት እርከን ብቻ ያለው ሲሆን ዝቅተኛው የደሞዝ ግብር የሚጀምረው ከ10% ነው። ከፍተኛው የደሞዝ ግብር ደግሞ 32.5 % ሲሆን በዶላር 2326 ወይም በብር 132,558 በላይ የሚያገኝ ሠራተኛ ላይ ይጣላል።  "…ኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛው ግብር የማይከፈልበት ደሞዝ 600 ብር ወይም 10.5 ዶላር በታች ሲሆን 10% ይከፈልበታል። ከፍተኛው የደሞዝ ገቢ ግብር 35 % ሲሆን ደሞዝህ ከ10,000 በላይ ወይም 175.4 ዶላር ከሆነ ደግሞ 35% ትገብራለህ። ቫት፣ ቲኦቲና ወዘተን ሳይጨምር ማለት ነው። "…ከኬንያና ከዓለም ልምድ በመቅሰም የመብራት፣ የውኃ፣ የፕሮፐርቲ ታክስና የተሽከርካሪ ግብር በመጨመር ከዓለም ጋር እኩል እንዳደረጋችሁን ሁላ የደሞዝ እድገት፣ የገቢ ግብርና ዝቅተኛ የደሞዝ መጠንንም በልምድ ልውውጡ አካታችሁ ከዓለም ሕዝብ ጋር እኩል አድርጉን ያሉት አቶ ሙሼ ሰሙ ናቸው። እኔም ለጊዜው ስለዚህ ጉዳይ ባወራ ይሻለኛል። • እናንተስ…?
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
"…እኔ ዘመዴ ሰፍሬ፣ ቆጥሬ፣ ለክቼ በዓይነት በዓይነቱ አጀንዳ እሰጣለሁ እንጂ ምን አጣሁ ብዬ ነው ከአንተ ዘንድ አጀንዳ የምቀበለው? ሃኣ…! "…የሚወራ የማይወራ አለ። የተገኘው ሁሉ አይወራም። አይነገርም። የአንተን የወሬ ሱስ ለማርካት ብዬ ከየትም ለቃቅመህ እየቃረምክ የምታመጣውን ወሬ ሁሉ በዚህ ሚልዮን ሰው አፍጦ በሚጠብቀው በተከበረ ፔጄ ላይ አምጥቼ እንድለጥፍልህ አትፈልግ። ሰገጤ ሁላ… "…እኔ የትግሬዎቹንም ሆነ የኦሮሞዎቹን ፔጅ በንቃት ነው የምከታተለው። የምንቀው ፔጅ የለም። የዙም ስብሰባ ሲደረግ በሌላ ሀገር መስመር በአሜሪካም ስልኬ ገብቼ እሳተፋለሁ። በትግርኛም ሲያወሩ፣ ሲመክሩ፣ በኦሮሚኛም ሲመካከሩ ተገኝቼ እሰማለሁ። ለዐማራ ይሄን አጀንዳ ጋግረን እንስጥ ብለው ሲመክሩ እሰማቸዋለሁ። እናም አቡኩተው የጋገሩትን ወሬ ለአዳሜ አሻምተው ሲያደነዝዙት እኔ ጋር ወፍ የለም። "…በነገራችን ላይ ከአንዳንድ ዥልጥ ፀረ ዐማራ የዐማራ አክቲቪስት ነኝ ባይ ገተቶች ለየት የሚያደርገኝ እኔ ዘመዴ ትግርኛ ባልናገር መስማቴ፣ ኦሮሚኛ መስማቴም መናገሬ ነው። የትግሬና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ለዐማራ አጀንዳ የሚሆን ነገር በአማርኛ ነው የሚበትኑት። ለውሻ አጥንት እንደመወርወር በሉት። ከዚያ ይሄ ገብሴ ግራ ቀኝ ሳያይ የተወረወረለትን አጥንት ተሸክሞ መጥቶ አንተኑ መልሶ ያዝግህሃል። ፔጅህንም ያግማማል፣ ያጠነባል። "…አሁን አሁን ግን በቲክቶክ፣ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብም ሆነ በቴሌግራም እየመጡ ያሉ እሳት የላሱ ዐማሮችን እያየሁ እየተደመምኩባቸው እገኛለሁ። ሴቶቹንም፣ ወንዶቹንም ቆሜ እያጨበጨብኩላቸው ነው። አይሳደቡ፣ አይጮሁ፣ አይናደዱ፣ አይፈሩ፣ አያፍሩ ንቅንቅ ሳይሉ ከዕውቀትና እውነት ጋር ድባቅ ሲመቱ እያየሁ ፈጣሪዬን እያመሰገንኩ ነው። በርቱ ግፉበት። •እናም ዘመዴ ስለዚህ ነገር ጻፍ አትበለኝ። ሰምተሃል።
إظهار الكل...
🙏 6
00:54
Video unavailableShow in Telegram
"…ሰላም ሰላም ጎደኞቼ…🖐 "…የኬንያ ባርላማ ተመራጭ ሴትዮ የመወገር ጉዳይ በርዕሰ አንቀጽ መልክ ጥፌላችሁ በዚያው ጠፋሁ አይደል? "…ጀነራል ጻድቃንን በተመለከተ የሰማሁት ዜና እውነት ይሁን ውሸት ለማረጋገጥ ብዬ አዎ ወደ ትግራይ ክልል እና የዐማራ ክልል የሰላም ካውንስል ቢሮ ሰዎችን የጓዳ የኋላ የጀርባ ታሪክ ለማጥናት ወደ ዐማራ ክልል ሄጄ ነው የጠፋሁት። ይሄ ይታወቅልኝ። አደራ መዝግቡልኝ። "…የጀነራሉም ጉዳይ አድካሚ ነው የሆነብኝ። ስለ ጀነራል ጻድቃን የመከላከያ ሚንስትሯ ኢንጅነር አይሻ ናቸው የሚያውቁት ተብዬ ነበር። ሚንስትሯን እንደ ዶር ኦላና በቀላሉ ማግኘት አልተቻለም። የጻድቃንም የኢንጅነርም ስልክ ደግሞ የለኝም። "…የሆነው ሆኖ እላላጣለሁ፣ ማገዶ እጨርሳለሁ እንጂ የሰማሁትን ለማጣራት የጀመርኩትን መንገድ እስኪያልበኝ ድረስ እሄድበታለሁ። ወፎቼም ይሠማራሉ። የሰላም ካውንስሉን እንኳ አጥቤ የማሰጣበት መረጃ ነው ያገኘሁት። በተለይ ወልቃይቶች ተጠንቀቁ። አትዘናጉ። "…እኔምለው በርዕሰ ርዕሰ አንቀጼ ላይ የነገርኳችህ የኬንያ ባርላማ ተመራጭ ሴትዮ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታዋ ምን ሆነ ይሆን? • ማስጠንቀቂያ፦ እንዲህ ዓይነት ግምኛ ነገር ከጎረቤት ሀገር እንዳትኮርጁ አደራ። አደራ በሰማይ አደራ በምድር። • ቆይቼ እመለሳለሁ።
إظهار الكل...
2.82 MB
00:54
Video unavailableShow in Telegram
"ርዕሰ አንቀጽ" "…በምሥሉ ላይ የምታዩአቸው ሴት የኬንያ የፓርላማ አባል ናቸው አሉኝ። ባለፈው ሳምንት የኬንያ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ የተቃወመውን የታክስ ጭመራ ሕግ ደግፈው የነበሩ የፓርላማ አባል ናቸውም አሉኝ። "ሕጉ ከጸደቀ የዳቦ ዋጋም አሁን ካለው በእጥፍ ይጨምርብናልና አደራ ሕጉን ከሚቃወሙት ወገን ሁኚልን ብለው የመረጧት ዜጎች ደውለው ወትውተዋት ነበር አሉ። "…ሴትዮይቱም እሺ ብላ፣ ሰምታቸው ነበርም አሉ። ኋላ ምን እንደነካት አይታወቅም በፓርላማ "ሕጉ ይጽደቅ" ከሚሉት ወገን ቆማ እንደ ኢትዮጵያ የፓርላማ ተመራጮች እጇን ወደላይ ቀስራ አውጥታ ሕጉ ይጽደቅ ዘንድ ደግፋ ድምፅ ሰጠች አሉ። "…መቼም የመረጠኝ ሕዝብ ገጠሬ ነው ደግሞስ ምንአባቱ ያመጣል? ለዚህ አንድ ሚሊሻ ለሚበቃው አፈር ሕዝብ ብላ እንደ ኢትዮጵያ የፓርላማ አባላት ሳትታበይ አልቀረችም። እናም ኬኒያ ናይሮቢ ግርግር ስለበዛ፣ ከግርግሩ ዞር ብዬ ገጠር ዘመዶቼ ጋር ሄጄ ልሰንብት ብላ የፓርላማ ደሞዟን እንደያዘች ወደ ትውልድ መንደሯ ቪ8 መሂናዋን እያሽከረከረች፣ መነጥሯን ሰክታ ነው ጆሌ መስላ ሄደች አሉ። "…ድሮ ድሮ የባርላማ አባል መጣ ሲበል ዴየስስ የሚለው የአካባቢው ነዋሪም የሴትዮይቱ ጣቷን ቀስራ ሕጉን መደገፍ ቀድሞ ሰምቶ ኖሯል ሴትየዋ ስትመጣ ቤተሰቦቿ፣ አብሮአደግ ጓደኞቿ፣ ዘመድ አዝማድ አላፊ አግዳሚው ሁሉ ተሰብስቦ ጠበቃት። ጠበቃትና በምታዩት መልኩ በድንጋይ ቀጥቅጦ "ምንአባሽ ቀረኝ ብለሽ ነው የመጣሽ?" ብለው ውሻ አድርገው መለሷት ነው ያሉኝ። "…እናንተ አካባቢ ተመርጦ ባርላማ የገባው ማነው? የአባይ አራጅ መከላከያ ወደ ክልላችሁ ገብቶ ቤተሰቦቻችሁን እንዲያርድ እጁን አውጦ ፈቃድ የሰጠውን ሰው ታውቁታላችሁ? ደግሞ እንደ ኬንያውያን ክፉ ነገር አታስቡ። • ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
إظهار الكل...
2.82 MB
😁 1🏆 1
Photo unavailableShow in Telegram
“…ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።” 1ኛ ዮሐ 4፥18 "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ? "…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
إظهار الكل...
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር "…ዘወትር እሁድ ምሽት በመረጃ ተለብዥን በቀጥታ ስርጭት የሚቀርበው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው መርሀ ግብራች አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ልክ ከምሽቱ 2:10 ሲሆን ወደ እናንተ ይቀርባል። • ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia •በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live • ዩቲዩብ 👉 https://www.youtube.com/watch?v=0ESdYUvKz0A "…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ። 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል። "…ሻሎም !  ሰላም !
إظهار الكل...
2.21 MB
👍 2
ነጭ ነጯን ጀምረናል… • አላችሁ አይደል…?
إظهار الكل...
2.21 MB
1.04 MB
መልካም… "…የዛሬውንም ርዕሰ አንቀጽ ወደ 13 ሺ ያህል ሰዎች እንዳነበቡት እያየሁ ነው። ቀጣዩ መርሀ ግብር ደግሞ የእናንተ አስተያየት የሚኮመኮምበት ሰዓት ነው። እስቲ እናንተ ደግሞ በጎደለ ሞልታችሁ አስደምሙን። • 1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍
إظهار الكل...
32.16 MB
10.64 MB
👍 7
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍  "…አሁን ይህቺ አዲስ አበባን በመብራት ኒውዮርክና ዱባይን አስንቃለች የሚለው የብልፅግና ሰበካ ብዙም ሳይቆይ ሌላም ጣጣ ያመጣበታል። በሌሎች ክልሎች ምንም ሳይሠራ በፒያሳና በ4ኪሎ ብቻ በተሰቀለ መብራት ብቻ እንደ ሀገር አድገናል በማለት ይሄን ነገር ደጋግሞ በሬድዮና በቴሌቭዥን ፕሮፓጋንዳ መሥራቱ ሥራ አጡን ኢትዮጵያዊ በሙሉ ለምን በሊቢያ በባህር ሄጄ የአሸባሪ ሰይፍ ይበላኛል? ለምን ወደ ሳውዲ ልሂድ ብዬ ቀይ ባህር፣ አውሮጳ ልሂድ ብዬ የሜዲትራንያን ባህር ይበላኛል? ለምን በሞያሌ በኩል ኬንያ ደብቡ አፍሪቃ ድረስ በእግሬ ልሂድ ብዬ ጉዞ እጀምራለሁ? ለምን እንደ ዱባይ፣ እንደ ኒውዮርክ ወደሆነችዋ አዲስ አበባ አልሄድም በማለት ከአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ ይጎርፋል። ያንጊዜ አዲስ አበባ ሲመጣ የጠበቃትን ኒውዮርክ እና ዱባይ ያገኛል ወይ? መልሱልኝ። የትግሬ ለማኝ የኔቢጤ የበዛው፣ የዐማራ ተፈናቃይ የተከማቸው፣ የሀረርጌ የተራበ ኦሮሞ የተከማቸው፣ የደቡብ ልጆች የታጨቁት አዲስ አበባ በጌታ ሰው በአቢይ አሕመድ ኒውዮርክና ዱባይን አስንቃለች ተብሎ ስለተሰበከ ነው። ባለአደራው የሚባለው ልጅን ፔጅ ስትከታተሉ የችግሩን መጠን ትረዳላችሁ። "…በኬንያም ልክ አቢይ አሕመድ ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ ያስገነባው እንደ አንድነት እና እንጦጦ ፓርክ ያለ መናፈሻ ተሠርቶ ነበር። የራበው ኬንያዊ በመናፈሻው ገብቶ አየር እንዲበላም ተሰብኮ ነበር። ቤት የሌላቸው ኬንያውያንም በመናፈሻው ገባ ብለው እንቅልፋቸውን ለጥጠው ይወጡ ዘንድ ተሰብከው ነበር። ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ብቻ የሚደፍሩት ሬስቶራንቶችም በዚያ መናፈሻ ውስጥ ነበሩ። በቀደም ዕለት ለተቃውሞ የወጣው የራበው፣ የጠማው የናይሮቢ ሕዝብ ግን ያው በቪድዮው ላይ እንደምታዩት እሳት ለቆበት መናፈሻ ፓርኩን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ዐመድነት ቀይሮታል። ቅድሚያ ለጤና፣ ቅድሚያ ለትምህርት፣ ቅድሚያ ለዳቦ ያለው ሕዝብ ፓርክና መናፈሻ ዳቦ አይሆኑንም በማለት በደቂቃዎች ውስጥ አውድሞታል። እናም ራበኝ፣ ሥራ አጣሁ፣ ቤቴ ፈረሰ፣ መጠጊያ፣ መሸሸጊያ አጣሁ፣ የት ልድረስ? ኧረ የውኃ፣ የመብራት ያለህ! ተቸገርኩ ኧረ ኡኡኡ ብሎ ለሚጮህ ሕዝብ መናፈሻ ሠርቼልሃለሁ። ናና ተዝናና፣ ባይበላስ፣ ባይጠጣስ ቢቀርብህ ብለህ ስታሾፍበት የሆነ ቀን፣ የሆነ ሰዓት ላይ እንዲህ ጉድ ይሠራሃል። • ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
إظهار الكل...
"ርዕሰ አንቀጽ" "…እነ ጫላ የከተማውን ሙሉ ህንጻ ግራጫ በግራጫ ጫ በ ጫ ቀለም በመቀባት፣ በየህንፃዎችም ላይ የቡና ቤት መብራት በመሰቀል፣ በማንጠልጠልም፣ ራሳቸው ካሜራ ፊት በቀረቡ ቁጥርም እንደ ከተማዋ ግራጫ በግራጫ ቀለም ተቀብተው አድገናል፣ ተለውጠናል እንደሚሉት ያለ አይደለም እድገት ማለት። እንደዚያ አይደለም። አንድን ሰፈር፣ ወይም አንድን አውራ ጎዳና በቀለም በማዥጎርጎር እና የቡና ቤት መብራት በመሰቃቀል እንዴት እንደ ሀገር አድገናል፣ ተለውጠናል ተብሎ በድፍረት ዜና ይሠራል? "…እኔ በስደት በጊዜአዊነት በተጠለልኩበ አጎት ሀገር በጀርመንም ሆነ በመላው አውሮጳ፣ በአማሪካም የዲም ላይት ሲበራ የማየው በዓመት አንድ ጊዜ የገና በዓል ሲቃረብ ብቻ ነው። ያኔ ክረምቱም ከበድ ስለሚል፣ ጨለማውም ስለሚያስፈራ፣ ድብርት፣ ጭንቀትም ብዙ ሰው ስለሚያጠቃ፣ በተለይ ከፈረንጆቹ የገና በዓል አንደወር ቀደም ብሎ እና ከገና በዓል በኋላ ለአንድ ወይም ለሁለት ሳምንታት በሁሉም የገጠር ከተማዎች ሳይቀር በህንጻዎች፣ በቪላ ቤቶች፣ በመንገዶች ላይ ሁሉ መብራት ይሰቀላል፣ ይበራልም። መብራት ማብራት ብቻ አይደለም ሰዉ ሁሉ ሲበላ፣ የፈላ ወይን ሲጠጣ ያመሽና የክረምቱ ጨለማ የሚፈጥርበትን ድብርቱን አራግፎ ወደ መኝታው ይሄዳል። ከዚያ ውጪ አንዳንድ ቦታ እንዲያውም የኤሌክትሪክ ኃይል ለመቆጠብ ሲባል የድልድይ ላይ መብራት ራሱ ሲያጠፉ ነው የማየው። "…ያብለጨለጨ ከተማ ውስጥ ያለ ሥራ መቀመጥ እንዴት የእድገት መለኪያ ይሆናል? ፋብሪካዎች በኃይል እጦት ሥራ ባቆሙበት ሀገር ፒያሳና አራት ኪሎ አካባቢ፣ ሜክሲኮና ሳርቤት አደባባይ ላይ መብራት ቦግ አድርጎ አብርቶ እንዴት አደግን፣ ተለወጥን ይባላል? ዩኒቨርስቲዎች ለተማሪዎች የሚያቀርቡት ምግብ በማጣታቸው ምክንያት በሚቀጥለው ዓመት ተማሪ ለመቀበል እንቸገራለን ብለው በይፋ በሚያውጁበት ሀገር እንዴት ነው የፒያሳ መብራት የሀገር እድገት መለኪያ የሚሆነው? እነ ካኑን እና ዳንኤል አሞካቺን አምጥቶ በፓርክ መብራት ላይ አስደንሰህ ስታበቃ ኢትዮጵያ አድጋለች ብለህ ስለ ተናገርክ፣ ፕሮፓጋንዳም ስለ ሠራህ አይኤምኤፍ ገንዘብ አይለቅልህም እኮ። እነ ካኑ በሀገራቸው ቅንጢ ፓርክ የነበሩ ስፍራዎች አሁን የሸረሪት ድር አድርተው እያየን እኛ ባለ ሾርት ሚሞሪያም ናችሁ ስለተባልን ብቻ በእነሱ ሰበካ በቃ አድገናል ልንል ይመስላቸዋልን? "…በአንድ ሀብታም ቤት የተቀጠረ ዘበኛ እንኳ ከደሞዙ ባሻገር ለሆዱ ፍርፋሪ አያጣም። ማደሪያም አይቸግረውም። የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁናቴ እኮ ከሀብታም ቤት ዘበኛ ኑሮ ጋር እንኳ የማይነፃፀር የሰቆቃ ሕይወት የሚገፋው ሕዝብ እኮ ነው። አዳነች አበቤ በቀለምና በመብራት ባሸበረቀችው ከተማ ውስጥ ማደሪያ አጥቶ ባዶ ሆዱን የሚዞር ሕዝብ፣ ማደሪያ ቢኖረው እንኳ በቤት ኪራይ ናላው ዞሮ ጨርቁን ሊጥል የደረሰ ሕዝብ እንዴት ነው በፒያሳ መብራት አድገናል ብሎ ጮቤ የሚረግጠው? የአንድ ነት ፓርክ ምግብ ይሆናል ወይ? እንጦጦ ፓርክ ዳቦ ይሆናል ወይ? "…ራስህን፣ ቤትህን፣ ግቢህን፣ ሰፈርህን፣ አካባቢህን፣ ቀበሌህን፣ ወረዳህን፣ ክፍለ ከተማህን፣ ከተማህን የሚቀይረው እኮ ገቢህ ነው። አንድ ሰው ሥራ እና ገቢ ሲኖረው መጀመሪያ ራሱን ይቀይራል። መጀመሪያ ጭቅቅቱን ያራግፋል፣ በማጣት ጊዜ በሥራ አጥነቱ ወራት ተቀይሮ የማያውቀውን ከመሄድ፣ ከመጓዝ ብዛት ጥንባት፣ ክርፋት፣ ሽታ ያመጣበትን፣ ከማኅበረሰቡም ጋር ያቃቃረውን በመጥፎ ጠረኑ ያስወቀሱትን እነ ጫማ፣ እነ ካልሲ፣ እነ የውስጥ ግልገል ሱሪን፣ እነ ሸሚዝ፣ ኮትን ሁሉ ይቀይራል። ለብብቱ ዶደራንት፣ ለፀጉሩ ቅባት፣ ለልብሱ ሽቶ ይገዛል። በራሱ ላይ ኢንቨስት ያደርጋል። ይሄ የሚሆነው ታዲያ ከተማረ፣ ሥራ ከሠራ ብቻ ነው። ባይማርም ግን ገበሬም ቢሆን ካላረሰ፣ ምርጥ ዘር ማዳበሪያም ሳታቀርብለት ፉሉስ ሊኖረው አይችልም። በባዶ ሜዳ ሥራ አጥ እንደ አሸን በፈላበት ምድር ላይ በፒያሳ መብራት ብቻ አደግን ብለን መበጥረቁ ማንን ያሳምናል? ውኃ ከመጣች አንድ ወር ሆናት ብሎ እንደፈነዳ ሽንት ቤት የሚሸት፣ የሚጠነባ ሰው አዳነች አቤቤ ፋውንቴን አጠገብ ቆሞ አድገናል ሲል ከዚህ በላይ ማፈሪያነት ከየት ይመጣል? "…አንድ ሰው አነሰም በዛም ገቢ ሲኖረው ከራሱ አልፎ ቤቱንም ይቀይራል። እንደ አቅሙ ማለት ነው። ቆርቆሮ፣ ኮርኒስ፣ ወንበር አልጋ ሁሉ ይቀይራል። አንድ ሰው ሥራ ካለው ነው ቅድመ አያቱ የተወለዱበት፣ ከዚያ አያቱ የተወለዱበትን፣ ከዚያም አባቱ ተወልዶ አድጎ እሱ የተወለዶ ያረጀበትን እና የሀገር ቅርስ ለመሆን መስፈርት እያሟላ ያለውን የዘመናት ትውልድ አሳዳጊ የሆነ አልጋ፣ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ እንኳ ሊቀይር የሚችለለው ገቢ ሲኖረው ነው። አሁን በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ እንደ ኢትዮጵያ ይሄን የሚያስደርግ ገቢ ያለው አለ ወይ ነው ጥያቄው። ቤቱን የቀየረ ሰው ግቢውን ይቀይራል፣ የሰፈሩ ሁሉ ሰው ገቢ ያለው፣ ሥራ ያላቸውም ከሆነ ሰብሰብ ብለው ሰፈራቸውን ስለማሰማመር ይነጋገራሉ። ተነጋግረውም ሰፈራቸውን ፏ ሽር ብትን ያደርጉታል። በአንዳንድ ኮንዲሚንየሞች አካባቢ የሚታይ ነው። ሰፈሩ ሲቀየር ደግሞ የቀበሌው ነዋሪ ገቢው ከጨመረ ቀበሌው፣ ከሕዝቡ የሚገኘው ገቢ እየጨመረ ሲመጣ ሌባ የመንግሥት ሓላፊዎች ከሌሉ ከተማው፣ ከዚያም ሀገሩ ሁሉ ውብ ይሆናል። እንዲያ ሲሆን ሕዝቡም ልማቱን በላቡ፣ በጥረቱ ያመጣው ነውና ይንከባከበዋል። ይሄ ነገር በአንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን በመላው ሀገር ተደራሽ ከሆነ ደግሞ እንደ ሀገር ጠቀሜታው ከፍ ይላል። አለበለዚያ እድገቱም፣ ለእይታ የሚሠራው ሥራ ሁሉ በአንድ ከተማ ላይ ብቻ ከሆነ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። "…ለምሳሌ እንውሰድ። አሁን እነ አቢይ አሕመድ የጨበሬ ተስካር ምርጫ ተብዬዋ እየደረሰች ስለሆነ ይሄን ሾርት ሚሞሪያም ያሉትን ሕዝብ በቀለም፣ በዲም ላይት መብራት ሊያጭበረብሩት ይፈልጋሉ። በሀገሪቱ ውስጥ የቀለጠው ጦርነት፣ የኑሮ ውድነት አናቱ ላይ የወጣው ሕዝብ እንዳይበላቸው ከተማን በመብራትና በቀለም በማብለጭለጭ በቶፕ ቪው ቀረጻ ሊሸውዱት ይሞክራሉ። ይሄ ማለት እሳት የላሱ የቡና ቤት ባለቤቶች ሥራ ነው። የቡና ቤት ባለቤቶች ዋነኛ ሥራቸው ደንበኛው በደንብ እንዲጠጣ ሜካፓም ሴቶችን፣ አጭር ቀሚስ  አስለብሰው በፊትህ ላይ ያሯሩጡብሃል። እንድትሰክር ደግሞ ዲጄው ሞንታርቦውን እስከ መጨረሻው ይከፍተውና በመጠጡ ብቻ ሳይሆን በሙዚቃው ናላህ፣ አንጎልህ፣ ማሰቢያህ እንዲበጠበጥ ያስደርጋሉ። መብራቱ ብልጭ ድርግም ሲል ደግሞ ቅዥብርብር ይልብህና ራስህን ትጥላለህ። ገነት የገባህ ሁላ ይመስልሃል። ሲኦል እንደነበርክ የምታውቀው እንኳ የስካሩ አንጎበር ሲለቅህ እና ጨለማው በብርሃን ሲተካ ነው። "…አዲስ አበቤም እንደዚያው ነው እየሆነ ያለው። ጭራሽ አዳነች አቤቤ የኮሪደር ልማቱ ባለበት አካባቢ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ መዝጋት የለባቸውም የሚል ሕግ ሁላ አውጥታለች ነው የሚባለው። መብራቱም ፖሊሱም ያለው አራት ኪሎና ፒያሳ የኮሪደር መብራቱ ጋር ነው። የኮሪደር መብራቱ ጋር ደግሞ ፎቶ እየተነሡ የሚያመሹት በኩራዝ እና ፋኖስ አድገው አሁን በዲሞግራፊ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የተጠሩና የሰፈሩ ባለ ጊዜዎች ናቸው። የንግድ ድርጅቶቹ ሌሊቱን አምሽታችሁ ሥሩ ተብለው ተገደው ወደ ቤታቸው አምሽተው ሲገቡ መብራት በሰፈራቸው የለም እና ለዘረፋ ይጋለጣሉ። እድገት በግድ፣ በዐዋጅ እኮ አይመጣም። 👇 ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍
إظهار الكل...
👍 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.