cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 950
المشتركون
+224 ساعات
+37 أيام
-230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
+"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው #አብርሃም: #አባ_ሲኖዳ እና #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+ +"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"+ =>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና:: +ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ:: +ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን #ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል:: +አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: #ቅድስት_ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው:: +ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና:: +"+ #ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+ =>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:- ¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ ¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ ¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት ¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት ¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ ¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ ¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ ¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው:: +ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን (መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ ¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ ¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ ¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ ¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ ¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና ¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው:: +በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ #አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: ) +ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር:: +በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው #አቡነ_ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: #ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው:: +"+ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ( #GIYORGIS_OF_SEGLA ) +"+ =>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ "ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ #አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ:: +ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው ተሠወረችው:: +ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው: መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ) +ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/ ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:- 1. #ሊቀ_ሊቃውንት 2. #በላዔ_መጻሕፍት 3. #ዓምደ_ሃይማኖት 4. #ዳግማዊ_ቄርሎስ 5. #ጠቢብ_ወማዕምር +ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ 7 ቀን ነው:: =>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን:: =>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ) 2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ 3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ) 4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ የሃይማኖት ምሰሶ) 5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ) 6.አባ መቃቢስ 7.አባ አግራጥስ =>ወርሐዊ በዓላት 1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 2.አባ ባውላ ገዳማዊ 3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ =>+"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +"+ (ዕብ. 6:13) =>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+ (ቆሮ. 13:14) +++ ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር +++ ©ዝክረ ቅዱሳን •|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮     የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን                ➡️      መሰረተ ሚዲያ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇      ቻነሉን share በማድረግ መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ 👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═https://t.me/Meseretemedia
إظهار الكل...
ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

ይህ የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሠረተ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ት ቤት አባላት መማሪያና መልእክት መጋሪያ ብቻ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ አውታር ነው።

አባታዊ ምክር ✥እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ። ✥የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። ✥የተወደዳችሁ ልጆቼ ፡ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።፡ ✥የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ። ✥ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ። ✥ልጆቼ  እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡ ✥ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✥
إظهار الكل...
👍 2
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው.... ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡ "ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡ አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ ለመዳን፣ ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ  መስራቱን አቁም፡፡ #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ https://t.me/dnhayilemikael
إظهار الكل...
ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

👍 3
ሰኔ ፴ ልደቱ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ 👉በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር፤ ሚስቱም ኤልሣቤጥ መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ እርሷም የመውለጇ ዘመን አልፎ ነበር፡፡ ሆኖም ሁለቱም በእግዚአብሔር የታመኑ ጻድቃን ነበሩ፡፡  👉ከዕለታት በአንድ ቀንም ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ለአገልግሎት በገባበት ሰዓት በዕጣን መሠውያው በቀኝ በኩል የእግዚአብሔር መልአክ ቆሞ ታየው፤  እንዲህም አለው ‹‹ዘካርያስ ሆይ፥ አትፍራ፤ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ተሰምቷልና፤ ሚስትህ ኤልሣቤጥም ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡ ደስታና ሐሤትም ይሆንልሃል፤ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጅምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ይመልሳቸዋል፡፡ እርሱም የአባቶቻችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓዲያንንም ዐሳብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስ ቅዱስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል፡፡›› ዘካርያስም መልአኩን እንዲህ አለው፤ ‹‹ይህ እንደሚሆን በምን አውቃለሁ? እነሆ፥ እኔ አርጅቻአለሁ፤ የሚስቴም ዘመንዋ አልፏል፡፡›› መልአኩም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንም እነግርህና አበሥርህ ዘንድ ወደ አንተ ተልኬአለሁ፡፡ አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጸመውን ነገሬን አላመንኽኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም ይሳንሃል፡፡›› (ሉቃ.፩፥፲፫-፳) 👉ከዚህም በኋላ ሚስቱ ኤልሣቤጥ ፀነሰች፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ እናቱ ኤልሣቤጥን ለመጠየቅ በሄደችበት ወቅት በማሕፀኗ ውስጥ ሳለ ሕፃኑ ለእግዚአብሔር ልጅ ሰገደ፡፡ (ሉቃ.፩፥፴፱-፵፩) 👉ኤልሣቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ በደረሰ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች፡፡ መውለዷን የሰሙ ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም ደስ ተሰኙ፤ ልጁንም ስምንት ቀን በሞላው ጊዜ ሊገረዙት መጡ፤ ስሙንም በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ወደዱ፤ ነገር ግን እናቱ ዮሐንስ ተብሎ መጠራት እንዳለበት ተናገረች፡፡ ሆኖም ግን ከዘመዶቿ መካከል ስሙ ዮሐንስ የሚባል ባለመኖሩ አባቱ እንዲወስን ካህኑ ዘካርያስን በጠየቁት ጊዜ መናገር የተሣነው ዲዳ ነበርና ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ሲጽፍ ሁሉም ተደነቁ፤ በዚያን ጊዜም የዘካርያስ አንደበት ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡ 👉ካህኑ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ በመላበት ጊዜ እንዲህ ብሎ ትንቢት መናገር ጀመረ፤  ‹‹ይቅር ያለን፥ ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ከባርያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን፤ ከጥንት ጀምሮ በነበሩ በቅዱሳን በነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፡፡ ከጠላቶቻችን እጅ፥ ከሚጠሉንም ሁሉ እጅ ያድነን ዘንድ፤ ቸርነቱን  ከአባቶቻችን ጋር ያደርግ ዘንድ፤ ቅዱስ ኪዳኑንም ያስብ ዘንድ፤ ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ያስብ ዘንድ፤ ከጠላቶቻችን እጅ ያድነን ዘንድ ያለ ፍርሃት፥ በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ በዘመናችን ሁሉ እንድናመልከው ይሰጠን ዘንድ፤ አንተም ሕፃን፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱንም ትጠርግ ዘንድ በፊቱ ትሄዳለህና፡፡ ኃጢአታቸው ይሰረይላቸው ዘንድ መድኃኒታቸውን እንዲያውቁ ለአሕዛብ ትሰጣቸው ዘንድ፤ ከአርያም በጎበኘን በአምላካችን በይቅርታውና በቸርነቱ፤ በጨለማና በሞት ጥላ ለነበሩት ብርሃኑን ያሳያቸው ዘንድ፥ እግሮቻቸውንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ፡፡›› ሉቃ.፩፥፷፰-፸፱ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አማላጅነት እና ተራዳኢነት አይለየን፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!
إظهار الكل...
4👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
" ራስህን ከቤተክርስቲያን ፈፅሞ አትለይ፤ ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፤ ቤተክርስቲያን ደኅንነትህ ናት፤ ቤተክርስቲያን መጠጊያህ ናት።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ " ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና..." ኢሳ. ፶፮፥፯ /56፥7/ ❤ ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት የጸሎት ቤት ነው። በእዚያም እርሱ አለና።
إظهار الكل...
3
                    ቀናችንን በጸሎት እንጀምር     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ማንም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ከመጀመሪያ ጀምሮ መልካም ነገርን መምረጥ መልካም ነው፤ በመልካምነት አለመቀጠል ግን ብዙ ወቀሳን ያመጣል፤ የብዙ ሰዎች ክፉ መኾን በዚሁ የሚመደብ ነው ፤ ብዙዎች ሕይወታቸውን በመልካም ጀምረው በኋላ ግን በክፋት መርዝ ተጠምቀው ሲሰክሩ ተመልክቻለሁ፡፡ ❖ እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ ምንም እንኳን አሁን ወደ ክፋት ጥልቅ ወርዳችሁ ቢኾንም ✍️"ከዚሁ ተመልሰን መውጣት አይቻለንም ፤ መለወጥም አይኾንልንም" በማለት ተስፋ የምትቆርጡ አትኹኑ፤ እናንተ ስትፈቅዱ እግዚአብሔርም ሲረዳችሁ ከክፋት ዐዘቅት መውጣት በእጅጉ ቀላል ነውና፡፡ ❖ ከኹሉም በላይ አመንዝራ ተብላ በከተማው ትታወቅ የነበረችውን ሴት በመልካምነቷ እንዴት እንደምትወደስ አልሰማችሁምን? እየነገርኳችሁ ያለሁት በወንጌለ ዮሐንስ ስለተጠቀሰችው ሴት አይደለም ፤ በእኛ ዘመን ስላለችውና ፍኒሳ ከተባለችው ክፉ ከተማ ስለተገኘችው ሴት እንጂ ይህቺ ሴት አስቀድማ በመካከላችን በአመንዝራነቷ ትታወቅ ነበር፤ በክብር ቦታ ሁሉ የመጀመሪያውን ስፍራ የምትይዝ ሴት ነበረች፤ ስሟ በሀገሩ ሁሉ የገነነ ነበር በእኛ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በሲልስያና በቀጰዶቅያም የታወቀ ነበር፡፡ ❖ ይህቺ ሴት ብዙ ከተሞችን አፍርሳለች ፤ የብዙ ወላጅ አልባ ሕፃናትን ንብረት በልታለች፤ ብዙዎች "መተተኛ ናት" ይሏታል ውበቷን ብቻ ሳይኾን መድኃኒትም ጭምር ትጠቀም ነበርና፡፡ ❖ ከዚሁ የተነሣ በአንዱ ቀን የንግሥቲቱን ልጅ እስከ ማማለል ደርሳለች፤ ጭካኔዋ ክፉ የክፉ ክፉ ነበር፤ ከዕለታት በአንዲቱ ቀን ግን ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ተለውጣ አየኋት፤ ራሷን በእግዚአብሔር የጸጋው ዙፋን ፊት ድፍት ብላ ስታለቅስ አየኋት አሁን የቀድሞ ክፉ ሥራዎቿ ኹሉ ርግፍ አድርጋ ትታለች በእርሷ ላይ ከነበሩት አጋንንት ጭፍራ ተፋትታ የክርስቶስ ሙሽሪት ኾናለች፡፡ ❖ በእውነት ከእርሷ የሚከፋ ሰው በዓይኔ አላየሁም አሁን ግን ራሷን ከእንደዚህ ዓይነቱ ክፉ ሥራ ከልክላለች፤ ከዚህ በፊት ስትለብሳቸው የነበሩት የምንዝር ጌጦች ስፍር ቁጥር የላቸውም አሁን ግን እነዚህን ኹሉ አወላልቃ ጥላ ለእግዚአብሔር በሚገባ የማቅ ልብስ ራሷን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር አድርጋለች፡፡ ❖ ይህቺን ሴት ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ለመመለስ የሀገሪቱ መኳንንት ከዙፋናቸው ወርደው ለምነዋት ነበር ወታደሮች ከነትጥቃቸው መጥተው አስፈራርተው ሊወስዷት ሞክረው ነበር፤ ነገር ግን ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ይመልሷት ዘንድ አልተቻላቸውም፡፡ ❖ ይህቺ ሴት ከዚያ አስነዋሪ ሕይወቷ ተመልሳ ለቅዱስ ቁርባን በቅታለች፤ ለእግዚአብሔር ጸጋ የተገባች ኾና ተገኝታለች ኃጢአቷን ኹሉ በጸጋው አጥባለች ከተጠመቀች በኋላ ራሷን መግዛት ችላለች፤ ይህቺ ሴት የቀድሞ ሕይወቷን ፣ ገላዋን ለብዙ ወዳጆቿ ያሳየችበትን ሕይወት "የእስር ቤት ሕይወት" ብላ ትጠራዋለች፤ በእውነት "ኋለኞች ፊተኞች ይኾናሉ ፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይኾናሉ" የሚለው የከበረ ቃለ ወንጌል በእርሷ ሲፈጸም አየነው፤ መለወጥ ከፈለግን እኛን ማሰናከል የሚቻለው ኃይል እንደሌለ ዐወቅን ፤ ተረዳን፡፡ ❖ እንኪያስ እኛም ተስፋ በመቁረጥ ፥ በኃጢአት ዐዘቅት ሰምጠን የምንቀር አንኹን፤ ከእኛ መካከል በጽድቅ በረኻነት የሚኖር ማንም አይገኝ ፊተኛ ነኝ የሚል ማንም አይገኝ ፤ ብዙ አመንዝሮች እርሱን አልፈውት ሊሔዱ ይችላሉና፤ ማንም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ ፤ ከልቡ ከተጸጸተና ከተመለሰ ፊተኛ መኾን ይቻለዋልና፡፡ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 📌 ምንጭ ✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ ✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" 📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                               ይቆየን  ───────────                     Channel  https://t.me/dnhayilemikael
إظهار الكل...
ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Photo unavailableShow in Telegram
ጊዜ የለኝም መምህራኑ ገዳማውያኑ ያንብቡ !!! ❖ "ሰው ወደሚበዛበትና የዚህን ዓለም ፍርድ ወደሚሰጡ ቦታዎች አለመኼድ ስለማልችል፣ የምመራው ትልቅ የንግድ ድርጅት ስላለኝ፣ ሥራዬ ጥበበ እድ ስለሆነ፣ ጊዜ ስለሌለኝ፣ ትዳር ስላለኝ፣ ልጆችን ስለማሳድግ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ስለሆንኩ፣ እኔ የዓለም ሰው ስለሆንኩ መጻሕፍትን ማንበብ አይጠቅመኝም፤ "መጻሕፍትን ማንበብ በገዳም ለሚኖሩ መነኮሳት ነው" ብለህ አትንገረኝ። ❖ "አንተ ሰው! ምን ማለትህ ነው?" "ብዙ የዚህ ዓለም አሳብ ስላለብኝ መጻሕፍት ማንበብ ለእኔ አይደለም" ትለኛለህን? እንዲያውም ልንገርህ! አንተም ስማኝ! ከእነዚያ መነኮሳት ይልቅ ማንበብ ያለብህ አንተ ነህ፤ መጻሕፍትን በብዛት ማንበብ  የሚገባቸው ብዙ የዓለም አሳብ ያላቸው ሰዎች እንጂ በምግባር በትሩፉት የተጠመዱ መነኮሳት አይደሉምና:: 📌 ምንጭ ✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ) 📚"የክርስቲያን መከራ" ═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮     የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን                ➡️      መሰረተ ሚዲያ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇      ቻነሉን share በማድረግ መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ 👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═https://t.me/Meseretemedia
إظهار الكل...
👍 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.