Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
2 318
المشتركون
+2124 ساعات
+817 أيام
+36330 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
#ዜና |የቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና በገበያ ተፈላጊ በሆነ ሞያና ክህሎት የበቁ ዜጎችን በማፍራት ብዙዎች ተጠቃሚ እነሆኑ ነው ።
#DireTvአማርኛ | መስከረም 27፥2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
የሞያና ክህሎት ስልጠና ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ በኩልም የህብረተሰቡ ንቃት መዳበሩ ይነገራል።
በዚህ ዙሪያ የድሬዳዋ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ከቴክኒክና ሞያ ሰልጥነው ስራ ላይ ከተሰማሩ ነዋሪዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።
ነጃት ተገኔ እንደሚከተለው አዘጋጅታዋለች
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
ለፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን የተዘጋጀ በተግባር የተደገፈ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ፡፡
ይህ የአቅም ግንባታ መድረክ የኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ሙያዊ ብቃታቸውን ከማሳደግ ባሻገር በየሙያ መስኩ በየኢንዱስትሪው ተግባራዊ ዕውቀትና ክህሎት የሚያገኙበት ሆኖ መሰናዳቱና የተሻለ ልምድና ተሞክሮዎችን ከአቻዎቻቸው የሚቀስሙበትን ዕድል የሚፈጥር መድረክ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት እንዲሳተፉ እና ስልጠናውን አጠናቀው ሲጨርሱ በማሰልጠን የስልጠና ጥራትን ለማሻሻልና የሥራ ገበያውን ፍላጎት ለመመለስ በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ርብርብ ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ለማበርከት ከወዲሁ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡
በዚህ የአቅም ግንባታ ስልጠና የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ተሳታፊ ሲሆኑ ገበያው የሚፈልገውን ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ ለማፍራት የአሰልጣኞችን ብቃት ተከታታይነት ባለው መልኩ ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይም ትኩረት እንደሚሰጠውም በቢሮው የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 27/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች በዛሬው እለት “ከጂኦስትራቴጂ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና እና ወደ ተሻለ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ የመንግስት ያለፉት ዓመታት ጉዞና የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ አካሄደዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት ሰራተኞች በሀገራዊ ቀጣይ የእድገት ጉዞ ላይ የጠራ ግንዛቤን እንዲጨብጡና ለሀገራዊ ለውጡ በሁሉም መስክ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አቅም የሚፈጥርላቸው ይሆናል።
መድረኩም የድሬዳዋን እድገትና ተምሳሌትነት እንዲሁም የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በቀጣይም የመንግስትን አሻጋሪ ዕሳቤዎች በቁርጠኝነት ለመፈፀምና ለማስፈፀም ተግባቦት የፈጠረ መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 27/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
🛑 ድንበርና ወሰን የማይገድበው ሰው መሆን ይቻላል! ✨
🤔 እንዴት? የዓለም ቋንቋ የሆነውን ክህሎት ባለቤት ሲሆኑ፤
📚 ወቅቱ የሚፈልገውን እውቀትና ክህሎት ሲታጠቁ ድንበርም ወሰንም እርስዎን አያገድብም፡፡ ይልቁንም ዓለም እርስዎን ይፈልጋል!
የክህሎት ባለቤት በመሆን፦
✅ አለም አቀፋዊ ተፈላጊነት ይፍጠሩ!
✅ ድንበር የለሽ የስራ እድሎችን ያግኙ!
🏫 አቅራቢያዎ በሚገኝ የቴክኒክና ሙያ ተቋም ዛሬውኑ የክህሎት ስልጠና ይጀምሩ!
🚀 ክህሎት - የዓለም ቋንቋ! 🌐
መስከረም 21/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ በሚል መርሃግብር የክረምት የሙያ ክህሎት ስልጠናን ሲከታተሉ የነበሩ ከ250 በላይ ወጣቶች ተመረቁ
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ዜጎች ቢያንሰ የአንድ ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ "አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የክረምት ስልጠናን ሲከታተሉ የነበሩ 270 ወጣቶችን አስመርቋል።
በኹነቱ ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ያለፉትን 3 ወራት በ14 ዘርፎች የተሰጠውን ክህሎት መር ስልጠና የእረፍት ጊዜያቸውን በመሰዋት ወስደው የተመረቁት ወጣቶች ህብረተሰቡ ለዘርፉ ያለውን የተዛባ አመለካከት በመቀየር በኩል የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የአንድን ሀገር እድገትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ቢያነስ የአንድ ሙያ ባለቤት የሆነ የሰለጠነ ዜጋ ማፍራት አስፈለጊ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በክረምት አጫጭር ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ስራን በራሳቸው በመፍጠር በኩል አይነተኛ ክህሎት መቅሰማቸውን ገልፀዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው ተቋሙ ባለፉት ሁለት አመታት በዘርፉ በረካታ ወጣቶችን የሙያ እና የክህሎት ባለቤት ማድረጉን ጠቅሰው ስልጠናው ወጣቶች ያላቸውን ዝንባሌ በጊዜ አውቀው ክህሎታቸውን እንዲያሳደጉ ያገዘ እንደሆነ አሰታውቀዋል።
ሰልጣኞች በበኩላቸው የወሰዱት የክህሎት ስልጠና የወደፊት ህይወታቸውን የተቃና በማድረግ በተለይም የራሳቸውን ሞያ ተጠቅመው ሥራ እንዲፈጥሩ አይነተኛ ድጋፍ እንደሚደርግላቸው ገልፀዋል።
©️ DGC
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
🔑 ቴክኒክና ሙያ: የስኬት ቁልፍ
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የመጨረሻው ግብ በክብር የሚያስቀምጡት የምስክር ወረቀት አይደለም። ይልቁንም ነገዎን ከዕድልና እጣ ፈንታ እንዲሁም ከጥገኝነት ነፃ አውጥተው በራስዎ መሻት እንዲቀርጹ የሚያስችልዎትን አቅም በእጅዎ ማድረጉ ነው።
ሙያ የሚያጎናፅፍዎ ሦስቱ ነፃነቶች፦
💸 የገንዘብ ነጻነት: ሰርቶ ለማትረፍ፣ አትርፎ ለመቆጠብ እና ቆጥቦ ኢንቨስት በማድረግ ለቤተሰብ/ለህብረተሰብ/ለሀገር የተሻለ ነገር ለመፍጠር የሚያስችል ⚡ ኃይል፣
🛠️ የሙያ ነጻነት: በራስ መንገድ መሄድ፣ የሚወዱትን የሙያ መስክ የመምረጥ እና የራስዎ አለቃ የመሆን በራስ የመተማመን አቅም፣
🚀 የሕይወት ነጻነት: በዕድልና እጣ ፈንታ አለፍ ሲልም በሰዎች በጎ ፍቃድ ሳይሆን በራስዎ ፍላጎት የሚመራ ሕይወት የመኖር ብቃት
👉 ታዲያ ምን ይጠብቃሉ! አሁኑኑ አቅራቢያ ወደሚገኝ የቴክኒክና ሙያ በመሄድ እውነተኛ ነፃነትዎን የሚያጎናፅፍዎትን ቁልፍ መቅረፅ ይጀምሩ።
መስከረም 17/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
✨ እንደ እንቁ የሚፈለጉ የሙያተኛ እጆች ✨
🔍 ዙሪያችንን በትኩረት እናስተውል
🏛 በግርማ ሞገሳቸው የሚያስደምሙን ህንፃዎች
🛋 አስደማሚ የቤት ቁሳቁሶች
⚙️ ህይወታችንን የሚያቀሉ ማምረቻ ማሽኖች
👗👞 በውበታቸው የሚያማልሉ አልባሳትና መጫሚያዎች
💍 የመዋቢያ ጌጣጌጦች………..
✋🎨 እነዚህ በጥበበኛ እጅ የሚሠሩ፣ የሚቀረፁ፣ የሚዋቡና የሚዘጋጁ ቁሶች ሁሉ የሙያተኛ እጆች በእጅጉ ይፈልጋሉ
💡 የዕለት ፍላጎታቸውን ለመሙላት፣ ሕይወታቸውን የተሻለ ለማድረግ፣ ጥበብና ውበት የሚለግሰውን ደስታ ለማጣጣም የሚሹ መላ የሰው ዘሮች ፍላጎት ምላሽ የሚያገኘው በጥበበኛ✋ባለእጆች ነው።
• 📚 ሙያ ይሰልጥኑ፣
• 🎭 ጥበብን ይቅሰሙ፣
•🚀 ድንበርና ወሰን ሳያግድዎት እንደ እንቁ ተፈላጊ ይሁኑ!
መስከረም 14/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
"የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድሉ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለተቀሩት የአፍሪካ ወንድሞቻችን የኢኮኖሚ ነጻነት ማረጋገጥ እንደሚቻል ብርሀን ያሳየ ነው"። ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የኮሌጃችን አመራሮችና ስራተኞች የተሳተፉበትና በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል እስታድየም የተካሄደው ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በፎቶ📸
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
"የሚደገም ድል፣ የሚጨበጥ ብስራት፣ ህዳሴ ግድብ!"
"ግድባችን ተጠናቅቋል፣ የጠላቶቻችን ሴራ በኢትዮጵያዊ አርበኝነት እሳት ተቃጥሎ ከስሟል!"
ዛሬ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አጠቃላይ ሰራተኞች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የድጋፍና ደስታቸውን የገለጡበትን ሰልፍ አካሄዱ።
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
🎉 #የሙያ_ባለቤት_ሆነው_ነገገዎን_ብሩህ_ለማድረግ_አቅደዋል? ✨
በአዲሱ የስልጠና ዘመን በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ነባርና አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። 🚀
ይህም ለወጣቶች፣ ለሙያ ስልጠና ፈላጊዎች እና ወቅቱ በሚፈልጋቸው ሙያዎች ተክነው ነጋቸውን ብሩህ ለማድረግ ላቀዱ ባለራዕዮች ወርቃማ ዕድል ነው።🌟
🌟 #የሙያ_ስልጠና_ለምን?
📚 ለሥራው ዓለም የሚያዘጋጁዎትን የንድፈ ሀሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ ስልጠና ሙሉና ተፈላጊ ሆነው መውጣት ስለሚያስችልዎ፣
📚 የሥራ ገበያውና ወቅቱ ከሚፈልገው ሙያ ጋር የተጣጣመ እና በከፍተኛ ደረጃ ተፈላጊ የሚያደርግዎትን ስልጠና ስለሚያገኙ፣
📚 ተቀጣሪ ሳሆን ቀጣሪ የመሆን ዕድል ስለሚያጎናጽፍዎ፤
📌 #ማን_ሊሰልጥን_ይችላል?
🎓 ሙያ ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንም ሆነ ሀገራቸውን መቀየሪያ ዋነኛው መሳሪያ እንደሆነ የገባቸው እና ሙያን ምርጫቸው ያደረጉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አጠናቃቂዎች፣
🎓 ሙያ ሰልጥነው የራሳቸውን ሥራ ለመጀመር የወሰኑ ሥራ ፈጣሪዎችና የመጪው ዘመን ባለሀብቶች እንዲሁም
🎓 ተጨማሪ ሙያና ክህሎት አግኝተው ሥራቸውን ለማሳደግ፣ ገቢያቸውን ለማስፋት እና መጪውን ዘመን እየዋጁ ራሳቸውን መቀየር ያቀዱ ዜጎች በተለያዩ መርሃ ግብሮች መሰልጠን ይችላሉ፡፡
👉 #ዕድሉ_እንዳያመልጥዎ!
🌠በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ጎራ ይበሉ!በአዲሱ የስለጠና ዘመን መጪውን ዘመን በሙያ ለመዋጀት ቀድመው ይመዝገቡ!
መስከረም 11/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
