Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
2 386
المشتركون
+624 ساعات
+787 أيام
+36130 أيام
أرشيف المشاركات
ነገን ዛሬ እንተክላለን!
በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ 800 ሺህ ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
በዛሬው ቀን ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም የኮሌጁ አመራሮችና ሰራተኞች ችግኝ በመትከል መርሃ-ግብሩ ላይ ከማለዳ ጀምሮ ለዚሁ መርሃ-ግብር በተዘጋጀው የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ በመገኘ ችግኞችን ተክለዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1444ኛ ዓመተ ሂጂራ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ ይላል።
ኢድ ሙባረክ!!
Calling all innovative minds in Ethiopia! Solve IT 2023 registrations are now OPEN! Don't miss your opportunity to be part of the most exciting innovation competition in Ethiopia.
Register at solveit-et.com
Telegram bot @solveit_et_bot
.
.
.
የሶልቭ ኢት 2023 ምዝገባ ተጀምርዋል! በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አጓጊ የሆነውን የፈጠራ ውድድር አካል ለመሆን ዕድሉ እንዳያመልጥዎት።
#SolveIT2023 #SolveITEthiopia #SolveITet #SolveITWithTech #InnovationCompetition #Startups #icogacc #USEmbassy #DashenBank
.
.
.
ለበለጠ መረጃ ፔጃችንን ይከታተሉ!
facebook.com/SolveIT.et
Instagram.com/SolveIT.et
Telegram: @solveit2023
TikTok.com/Solveit2023
Email: contact@solveit-et.com
Phone no: +251 991 440049
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 ትግበራን በኮሌጅ ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ ለሚሰሩ ስራዎችከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንቲትዩት በተመደቡ አሰልጣኞች ከኮሌጁ የስራ ሂደቶችና ክፍሎች ለተወጣጡ ሰራተኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ኮሌጁ የ ISO 9001:2015 QMS ትግበራ ላይ እየሰራ የሚገኝ በመሆኑና ይህንን ትግበራ በተጠናከረ መልኩ በመስራት ኮሌጁ የ ISO 9001:2015 QMS CERTIFICATE ተሸላሚ/ certify እንዲሆን በትጋት እየሰራም ይገኛል።
ይህን የተጀመረውን ተግባር ስኬታማነቱን ለማረጋገጥ ከ INSTITUTE OF ETHIOPIAN STANDARD ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት ከኢንስቲትዩቱ ከተመደቡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የISO 9001:2015 ትግበራ ስራ ነባራዊ ሁኔታውን በመገምገምና ተጨማሪ ስራዎችን በመስራት እንዲሁም የISO 9001:2015 QMS ትግበራን በኮሌጅ ደረጃ ኦዲት / INTERNAL AUDIT IES ለማከናወንና የሚያስችል ስልጠና AUDITING MANAGEMENT SYSTEM BASED ON ES ISO 19011:2018 ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንቲትዩት በተመደቡ ባለሙያዎች/EXPERTS ስልጠናው በመሰጠት ላይ ይገኛል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ግንቦት 24/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
#እንኳን_ደስ_አለን🥇🥈🥉
በሀገር አቀፍ ደረጃ በመዲናችን አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው 3ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደርን ወክለው በክህሎት፣ በቴክኖሎጂ እና በስራ ፈጠራ የተሳተፉ የኮሌጃች አሰልጣኝ መምህራንና ሰልጣኝ ተማሪዎቻች በውድድሩ 2 የወርቅ፣1 የብር እና 2 የነሀስ በድምሩ 5 ሜዳልያዎ በማሸነፍ ድሬዳዋን እንዲሁም ኮሌጃችንን ከፍ ባለ ደረጃ ስላስጠሩ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ።
"ክህሎት ለተወዳዳሪነት " በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ የሚገኘውን 3ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ ኮሌጃችንን እና የድሬዳዋ አስተዳደርን ወክለው እየተሳተፉ የሚገኙ ተወዳዳሪዎች በምስል📸
🏓🏓🏆🏆🏆
በድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ኮሚሽን አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የሰራተኞች ስፓርት ቭፌስቲቫል በዛሬው እለትም ቀጥሎ ሲካሄድ ኮሌጃችንን ወክለው በሴቶች ጠረቤዛ ቴኒስ የፍፃሜ ውድድር ያደረጉት ተወዳዳሪዎቻችን 1ኛ እና 2ኛ በመውጣት የወርቅና የብር ሜዳልያን ጨምሮ ለውድድሩ የዘጋጀውን ዋንጫ ወስደዋል።
በዚህም:-
🥇 አሰልጣኝ መምህር ሉሲ አብደላ 1ኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳልያና የዋንጫ ተሸላሚ…🥇🏆👏👏
🥈 ወ/ት እየሩስ ከበደ 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል።👏👏
በተመዘገበው ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን።👏👏👏👏
በድሬዳዋ አስተዳደር የሚካሄደው የሰራተኞች የስፓርት ፌስቲቫል በዛሬው እለት ጅማሬውን በማድረግ የመክፈቻ ውድድሮችን ያካሄደ ሲሆን
ኮሌጃችንን ወክለው በሴቶች ጠረቤዛ ቴኒስ የተወዳደሩት እንስቶቻችን ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ነገ ለሚደረገው የፍፃሜ ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።👏👏👏👏👏
ኮሌጁ በቀጣይ ቀናት በተለያዩ የስፓርት ውድድሮች የሚወከልም ይሆናል።
