ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
2 370
المشتركون
+324 ساعات
+937 أيام
+36430 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+7

photo content
+9

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስራ ሂደት የተዘጋጀና በተማሪዎች ቅበላ መጠነ መቀነስ ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀረበ:: ስራ ሂደቱ በአዲስ መልክ በ2016 ዓ.ም በሰው ሀይል ተደራጅቶ ስራ ከጀመረባቸው ዘርፎች ውስጥ የጥናትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዋነኞቹ ሲሆን በሂደቱ ጥናትና ምርምር ላይ የሚሰሩ አሰልጣኝ መምህራን ከድሬድዋ ዪኒቨርስቲ መምህራን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ጥናታዊ ጽሁፍ የተማሪዎች ቅበላ መጠነ መቀነስ ጋር ተያይዞ መንስኤ ይሆናሉ ተብለው የተለዩ ጉዳዮችን ላለፉት ወራት ጥናት በማድረግ በዛሬው እለት ለኮሌጁ ፑል አመራር እና ባለ ድርሻ አካላት በጥናቱ ያገኙትን ውጤት አቅርበዋል:: በመድረኩ የቀረበውን ጥናታዊ ጽሁፍ መነሻ በማድረግም ከተሳታፊዎች በርከት ያሉ ገንቢ አስተያየቶች የተሰጡበት ሲሆን የጥናቱ ባለቤቶችም በቀጣይ እነዚህ ከመድረኩ የተሰጡ ግብአቶችን በማካተት ከኮሌጅ አልፎ እንደ ሀገር የተሻለ ችግር ፈቺ ጥናታዊ ጽሁፍ ለማዘጋጀት እንደሚያግዛቸው በመጠቆም በቀጣይ የታዩ ውስንነቶችን በመሙላት ጥናታዊ ፅሁፉ ተጠቃሎ እንደሚቀርብ ለመድረኩ ገልፀዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሚያዝያ 21/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ላይ ባተኮረ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ላይ ተሳትፈው የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል:: የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀውና ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን በቀረቡበት ውድድር ላይ የኮሌጃችን አሰልጣኝ መምህር ነዋይ ይልማ እና አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ የተሳተፉ ሲሆን ያቀረቡት ጥናትና ምርምርም የተሻለ ሆኖ በመገኘቱ የውድድሩን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችለዋል:: በዚህም ውድድር ላይ በዘርፉ በተለይም በኮሌጆች የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና አሰጣጥ ስርዓት፣ የሰልጣኝ ተማሪዎች ቅበላና መጠነ ማቋረጥ፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አተገባበር ጋር የተያያዙ በዋናነት መሠረታዊ የዘርፉን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ጥናቶች ቀርበው ውድድር የተካሄደባቸው ሲሆን በውድድሩ አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀውና በኮሌጃችን አሰልጣኝ መምህር ነዋይ ይልማ የተዘጋጀው ጥናትና ምርምር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር ድሬዳዋን ወክሎ የሚሳተፍም ይሆናል፡፡ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተመዘገበው ውጤት እንደ ተቋም የተገኘ ውጤት በመሆኑ ውድድሩን በበላይነት ላጠናቀቁ አሰልጣኝ መምህራን እንዲሁም ለኮሌጁ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት ይወዳል:: የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+4

photo content
+9

አድራ ኢትዮጵያ (ድሬዳዋ) በ"Solar Pv instalation and maintenance እያሰለጠናቸው የሚገኙ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን እያጠናቀቁ በመሆኑ በቀጣይ ምእራፍ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ:: አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እያሰለጠናቸው የሚገኙ 48 ሰልጣኞች ዋና ስልጠናቸውን ማጠናቀቃቸውና ወደ ምዘና ለመግባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ሰልጣኞች ወደ ስራ አለም ሲገቡ የሚያግዛቸውን የኢንተርፕረነርሺፕ ስልጠና ተሞክሮ ባላቸው ባለሙያዎች እየሰለጠኑም ይገኛሉ። ስልጠናው ለስራ እድል ፈጠራ የሚያግዛቸውን ክህሎት በማግኘት ተለዋዋጭ የሆነውን የንግዱን ስርአት ለመቀላቀል ትልቅ አቅም ከመሆኑም ባሻገር በራስ መተማመናቸውን እንዲያጎለብቱ ታሳቢ ተደርጎ እየተሰጠ የሚገኝ ስልጠና ነውም ተብሏል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ሰልጣኞችን ወደ ስራ ለማሰማራት የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ከ"Job Box " ዝግጅት እና የራስን ስራ ከመፍጠር ጋር ተያይዞ ሰልጣኞችን በማደራጀት ወደ ስራ የሚገቡበትን አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት የተደረ ሲሆን በቀጣይም በቅንጅት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል:: በዚህ መሰረትም ሰልጣኞች ከአሰልጣኞቻቸው ጋር በመሆን በገጠር ና በከተማ ያለውን የሶላር ጥገና ስራ እንዲሰሩና ከተቋማት ጋር በፕሮጀክት መልክ ተሰማርተው አቅማቸውን እንዲያሳዩ አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በራሳቸው ተደራጅተው የራሳቸውን የስራ እድል የሚፈጥሩበት ሁኔታ ተለይቶ እንዲመቻችላቸው መደረጉም ተገልፆል። በመጨረሻም ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ሰልጣኞች በተወሰነ መጠን የመንግስት ተቋማት ላይ የሚቀጠሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንዲቻል ለሚመለከታቸው አካላት ሀላፊነት በመስጠት መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሚያዝያ 18/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+7

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2016 በጀት አመት የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የግምገማ መድረክ አካሄደ። መድረኩን የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ የመሩት ሲሆን በተቋሙ የሚገኙ የስራ ሂደቶች የዘጠኝ ወር ተቋማዊ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለኮሌጁ ማኔጅመንት አቅርበዋል:: በመድረኩም በዋና ዋና ቁልፍ ተግባራት ፣ የማስፈፀም አቅም ፣በሀብት አጠቃቅም እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረገ የሪፖርት ግምገማ መደረጉ የተገለፀ ሲሆን የቀጣይ ሦስት ወር የስራ አቅጣጫን በማስቀመጥም መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ  "ብቃት" የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ሁለተኛ ዙር ትግበራ ለሁለት ተከታታይ ዙሮች የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰልጥነው ያጠናቀቁ ሁለት ሺ የሚጠጉ ሰልጣኞች የምርቃት መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በድምቀት ተካሂዷል በዚህ የሰልጣኞች የምርቃት ፕሮግራም ላይ  የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር ሀርቢ ቡህ በመገኘት ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አቶ ሀርቢ ተመራቂዎችን በቀጣይ በተለያዩ  ፋብሪካዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በምትቀላቀሉበት ወቅት በስነ-ምግባር የታነፃችሁና በታታሪነት የምታገለግሉ መሆን ይገባቹሀል በማለት የመከሩ ሲሆን፤ ለዚህ መርሀ ግብር መሳካትም አስታዎፆ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ  አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው ለተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በስልጠናው ወቅት ያሳዩትን የስራ ተነሳሽነትና ስነ-ምግባር በቀጣይም እንዲያጠናክሩት ተናግረዋል። በተለይም አሁን ላይ በድሬዳዋ ኢንደስትሪ እየተስፋፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወጣቱም አስፈላጊውን ስነ-ግባርና ክህሎት አግኝቶ ዘርፉን እንዲቀላቀል እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች ከፍተኛ ሚና አንዳላቸው የገለፁት ደግሞ  የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ዳንኤል ተሬሳ ናቸው። አቶ ዳንኤል አያይዘውም ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የወጣት ስራ አጦችን ቁጥር በመቀነሱ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል። ተመራቂዎች በበኩላቸው በስልጠና ቆይታቸው በርካታ ክህሎት እንዳገኙ ገልፀው ለስልጠናው አዘጋጆችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ©️ የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮምኒኬሽን

photo content
+5

photo content
+9

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች የዐቢይ ፆምን ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መርሃ-ግብር አካሄዱ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች በድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኝት በዐቢይ ጾም ስርዓተ ቅዳሴ አከናውነው ለሚመለሱ የክርስትና እምነት ተከታዮች የተለያዩ ምግቦች እና የታሸጉ ውሃዎችን በማቅረብ ማእድ የማጋራት መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ