cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ሃይማኖታችንስ✞?

✞የኦርቶዶክስ ቻናል✞ > የየዕለቱ ስንክሳር >ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎች ከነመልሱ > በቅርብ የጀመረው አስተማሪ ታሪኮች > መንፈሳዊ ዝማሬዎች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ > መንፈሳዊ ፊልሞች > መንፈሳዊ ትምህርቶችና የተለያዩ ፁፎች #ሁሉም_በየእለቱ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
941
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-57 أيام
-2430 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
Media files
581Loading...
02
                          †                           🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 ❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖 ❝ ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርአዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳዕ ዘተኃጕለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ ፤ ❞ ትርጉም ፦ [ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን በጻድቃን ላይ የሚያበራ ነው ፣ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ ነው ፣ የጠፋው ይረዳ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደ እኛ መጣ [ ሰው ሆነ ] ] [ ድጓ ዘአስተምህሮ ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
701Loading...
03
Media files
601Loading...
04
Media files
781Loading...
05
🕊 [ † እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † 🕊 †  አቡነ ተጠምቀ መድኅን  †  🕊 † ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ፲፮፻፲ [1610] ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ-ክርስቶስና ወለተ-ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ ፪ [2] ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር ፲፩ [11] ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ጸጋ-እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ:: ሕጻን እያሉ ቃለ-እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ:: ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: ፳፫ [23] ዓመት ሲሞላቸው ወደ መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ፴፯ [37] ዓመታት:- ፩. በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል ፪. ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል ፫. ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል [ካህን ናቸውና] ፬. ፯ "7" ገዳማትንና ፲፪ "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል:: † ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ፷ [60] ዓመታቸው በ፲፮፻፸ [1670] ዓ/ም [በአፄ ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን] ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል:: 🕊   †  ቅድስት ማርታ  †   🕊 † እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች:: መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን [በበዓለ ልደት] ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት:: ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት:: ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ፳፭ [25] ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች:: † የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: † 🕊 [ †  ሰኔ ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅድስት ማርታ ተሐራሚት ፪. አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ [ኢትዮዽያዊ] ፫. ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት ፬. ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን] ፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ ፭. አቡነ ዜና ማርቆስ ፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል † " አልሞትም : በሕይወት እኖራለሁ እንጂ:: የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ:: መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ:: ለሞት ግን አልሠጠኝም:: የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ:: ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ:: ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት:: ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ:: ሰምተኸኛልና: መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ:: " †  [መዝ.፻፲፯፥፲፯-፳፪] (117:17-22) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
872Loading...
06
Media files
761Loading...
07
💖                   🔔                     💖      [ የመርሐ-ግብር ማሳወቂያ ! ] የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በቅርብ ቀን በገድለ ቅዱሳን መርሐ-ግብር በተከታታይ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ ይከታተሉ ! †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
870Loading...
08
                       †                          [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒                [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ] [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🕊                            ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞ [ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [ ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]                 [   ክፍል - ፮ -  ]           💖   ድንቅ ትምህርት  💖 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬                        👇
780Loading...
09
Media files
750Loading...
10
Media files
710Loading...
11
Hello, Abri , Welcome! Nice to see you.
10Loading...
12
Media files
740Loading...
13
Media files
770Loading...
14
                      †                            🕊  💖  ኦርቶዶክሳዊነት  💖   🕊 🕊 " በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና። ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች። " [ ማቴ . ፳፩ ፥ ፲፰ ] መናፍቅነት በባዶ ሕይወት አልባ ቃላት የተሞላ ፍሬ አልባ የቢታንያ በለስነት ሲሆን የአባቶቻችን የቅዱሳን ሕይወት ግን በቅድስናና በንጽሕና ፤ በተጋድሎና በተግባራዊ ሕይወት የተሞላ የብርሃን ሕይወት ነው። ሰይጣን አምርሮ የቅዱሳንን ሕይወት የሚጠላው ክርስቶሳዊነት በመሆኑ ነው። ይህ በክርስቶስ ስም ሕይወት አልባ በሆኑ ባዶ ፕሮቴስታንታዊ ቃላት የመቀላመድ ጉዞ መላውን አውሮፓ እርቃን አስቀርቶ ለባዶነት ፣ ለሃይማኖት አልባነትና ለአስከፊ ርኩሰት ፣ ለሰዶማዊነትና ለጨለማ ሕይወት የዳረገ የሰይጣን ጎዳና ነው። እነሆም የሐሳዊው መሲህ ናፋቂዎች ሆነው ለመቀመጥ ተዳርገዋል። ባዶ የሞራልና የስሜት መቀላመዶች ሕይወት አይሆኑም። ሕይወትስ የቅዱሳን አባቶቻችን ክርስቶሳዊ የቅድስና ፍኖት ! በተዋሕዶ ሃይማኖታችን እስከ ፍጻሜው ያጽናን ! †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
800Loading...
15
                      †                            🕊  💖           †             💖   🕊 [ † ማግባትን ለምትሹ † ] 🕊 ❝ ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው ? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን ? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው ፤ እንዲህ ያለውን ፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው ፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" [ ፩ኛ ቆሮ.፯፥፪ ] ። " ከድህነት ይወጣ [ ትወጣ ] ዘንድ" ነው የሚለውን ? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን ? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው ? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው ፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡ ስለዚህ ልጆቼ ! እማልዳችኋለሁ ፦ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው ፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡ አባቶች ሆይ ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት ፦ ሀብትን አላየም ፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም ፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም ፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡ እናቶች ሆይ ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡ እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ ! ይስሐቅን ምሰሉት ፦ ዘፈንን ፣ ዳንኪራን ፣ ሳቅና ስላቅን ፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን ፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ ፣ ዝሙት ፣ ቅናት ፣ ጭቅጭቅ ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም ፥ አትነዋወፁም፡፡ እናንተ ልጃገረዶች ሆይ ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር ፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡ የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን ፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም ፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት ፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡ ❞ [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ] †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
842Loading...
16
Media files
781Loading...
17
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊 [ የተዘጋች ገነት የታተመች ጉድጓድ ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ ሕዝቅኤል ፦ "ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ በምሥራቅ አየሁ፡፡ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርሷ ገብቶ የወጣ የለም፡፡" አለ፡፡ [ሕዝ.፵፬፥፩] ይህ የተዘጋ በር የድንግልናዋ ዜና ነው፡፡ " እግዚአብሔርም ፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል። " [ሕዝ.፵፬፥፩] ሰሎሞንም ፦ "የተዘጋች ገነት የታተመች ጉድጓድ [ ያንቺ መንገዶች ናቸው ] አለ፡፡ " እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት ፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።" [ መኃ.፬፥፲፪ ] በገነት አካባቢ ምን ይገኛል ? የሚጣፍጥ ፍሬ አይደለምን ? የሚጣፍጠው ፍሬ ምንድን ነው ? የእናቱ የድንግል ማርያም ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን ? የተዘጋች ገነት ማለትስ በድንግልና ቁልፍ በተዘጋች በአንቀጸ ሥጋዋ ይተረጎማል፡፡ ዳግመኛ ከጉድጓድ ከሚጣፍጥ ውሃ በስተቀር ምን ይገኛል ? የሚጣፍጥ ውሃ ምንድን ነው ? በወንጌል ፦ " ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። " [ዮሐ.፯፥፴፯] ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የታተመች ጉድጓድ የተባለው የንጽሕይት እናቱ የድንግልናዋ ኃይል ነው፡፡ ሁሉም ነቢያት ስለ ሥጋዋ በር ፦ " የተዘጋች ፥ በድንግልና የታተመች" ብለዋታልና፡፡ ለቀደሳትና ላነጻት [ በንጽሕና ለጠበቃት ] ለእግዚአብሔር ለዘላለም ምስጋና ይሁን፡፡ ❞ [ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ] †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
980Loading...
18
Media files
930Loading...
19
Media files
810Loading...
20
                           †                            🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 ❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖 ❝ በከመይቤ መጽሐፍ ማእከለፈጣሪ ወፍጡራን ለዕረፍት ዘኮንኪ ጽላተ [ ትእምርተ ] ኪዳን ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተጽጌ ጻድቃን ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡ ❞ [ መጽሐፍ እንደተናገረ በፈጣሪ እና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የቃል ኪዳን ማደሪያ [ ምልክት ] የሆንሽ የብርሃን ቀን ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ሆይ በገነት ያሉ ጻድቃን በአንቺ ደስ ይላቸዋል፡፡ ኃጥአንም ከደይን በአንቺ ይወጣሉ፡፡ ] [   አባ ጽጌ ድንግል   ]      🕊       ክብርት ሰንበት       🕊 †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
880Loading...
21
Media files
660Loading...
22
Media files
531Loading...
23
🕊 [ † እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ † 🕊 † የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ :- - በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ - በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት - በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ - እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ - የጌታችንን መንገድ የጠረገ - ጌታውን ያጠመቀና - ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን :- ነቢይ : ሐዋርያ : ሰማዕት : ጻድቅ : ገዳማዊ : መጥምቀ መለኮት : ጸያሔ ፍኖት : ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች:: 🕊  †  ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ  †  🕊 † ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ :- - ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ - መናኔ ጥሪት የተባለ - በድንግልና ሕይወት የኖረ - የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት - እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ - አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው:: ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል:: ቅዱስ ዮሐንስ ፦ - ቁመቱ ልከኛ - አካሉ በጸጉር የተሸፈነ - የራሱ ጸጉር በወገቡ - ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ - ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር:: ቅዱስ ኤልሳዕ ፦ - በጣም ረዥም - ራሱ ገባ ያለ [ ራሰ በራ ] - ቀጠን ያለ - ፊቱ ቅጭም ያለ [የማይስቅ] ሽማግሌ ነበር:: በዚሕች ቀን በ፫፻፶ [350] ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ፸ [70] ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም ፫ [3] ጊዜ ፈረሰበት:: ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት:: ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል:: በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል:: † አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን:: 🕊 [ † ሰኔ ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት [ፍልሠቱ] ፪. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ [ፍልሠቱ] ፫. አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ [ †  ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ ፪. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ ፫. ቅዱስ አቤል ጻድቅ ፬. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ] ፭. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ፮. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ † " ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ :: " † [ማቴ.፲፩፥፯-፲፭] (11:7-15) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
602Loading...
24
Media files
631Loading...
25
Media files
950Loading...
26
                       †                          [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒                [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ] [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🕊                            ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞ [ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [ ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]                 [   ክፍል - ፭ -  ]           💖   ድንቅ ትምህርት  💖 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬                        👇
1060Loading...
27
Media files
1000Loading...
28
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [   †  ከመንፈሳዊ መጻሕፍት ቅኝት  †   ] 🔔 [   ሰይጣን ሊነካው የማይችለው ነገር ! ] 🍒 በአንድ ሐገር ድንገት የአንድ "ጠንቋይ ዝና ከዳር ዳር ተሰማ። ሰውዬው የማያሳየው ምትሐት የለም። አንበሳ ላለ አንበሳ ፣ ነብር ላለ ነብር ፣ የሞተ ዘመዴን ላለ የሞተ ዘመዱን ፣ የጠፋብኝን ዕቃ ከቤት ፈልገህ አምጣልኝ ላለ ዕቃውን ያመጣለታል። እንደሚታወቀው አጋንንት ከክብራቸው የተዋረዱ መላእክት ናቸው። መላእክት ደግሞ በፈለጉት ሁኔታ መገለጥ ይችላሉ። ይህ ጠንቋይ የሚሰጣቸውን ገጸ ባሕርይ ተቀብለው አንዴ አንበሳ ፣ አንዴ ነብር ፣ አንዴ ሰው እየሆኑ የሚተውኑት እንግዲህ አጋንንቱ ነበሩ። የዚህ ጠንቋይ ዝና ወደ ንጉሱ ደረሰ። ንጉሱ ደግሞ ክርስቲያን ቢሆንም ከመጸሐፍ ቅዱስ ይልቅ እንዲህ ያለ ተአምር እዚህ ቦታ ተፈጸመ ሲባል ለማየት የሚሮጥ ሰው ነበር። ተአምር የሚወድ ሰው ደግሞ ክርስቲያንም ቢሆን ሰይጣን በሚሰራው ምትሐት መታለሉ የማይቀር ነው። ስለዚህ ይህ ንጉስ የተማረውን መጽሐፍ ቅዱስ ዘንግቶ በጠንቋዩ ምትሐት አመነ። ይህንን የሰሙ የንጉሱ ንስሐ አባት ነገሩን ሰምተው ወደ ቤተ መንግሥት ሲሮጡ ደረሱ። ሲደርሱ ንጉሡ ከቁም ነገር አልቆጠራቸውም። እሱ የጠንቋይ ትርዒት ማየት ቀጠለ። " እስቲ አሁን ደግሞ ነጭ ፈረስ አምጣልኝ።" ማለቱን ቀጠለ፡፡ በነገሩ ያዘኑት አባት ፦ " ኧረ ንጉሥ ሆይ ይተው ይህ እኮ የሰይጣን ምትሐት ነው።" ብለው ሊያስረዱት ሲሉ በቁጣ አስቆማቸው። ተአምር የሚከተል ሰው መቼስ ቢነግሩት አይሰማም። ጭራሽ እንዲያው ለንስሐ አባቱ እንዲህ አላቸው። " የሰይጣን ስራ ነው አትበሉ ፤ ቅናት ነው ይሄማ ይልቅ እርስዎ የሚፈልጉትን ነገር ይጠይቁት ያምጣልዎት ! " አላቸው። ጠንቋዩም " የፈለጉትን ላምጣልዎት....ምን ይፈልጋሉ? የሞተ ዘመድ አለዎት.... ወይስ ከቤትዎ ዕቃ ላምጣልዎት ? " አላቸው በኩራት። ካህኑ ውስጣቸው በመንፈሳዊ ቅናት ተቃጠለ። " እንግዲያውስ የፈለኩትን ማምጣት ከቻልክ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደህ ልብሰ ተክህኖዬ ውስጥ መስቀል አለ እርሱን ይዘህልኝ ና ! " አሉት። ይህን ግዜ ጠንቋዩ ገና ድግምቱን ሲጀምር አጋንንቱ እላዩ ላይ ሰፍረው ጣሉት። በካህኑ ፊት ወደቀ። ሰይጣን ምንም ነገር ማምጣት ይችል ይሆናል። መስቀሉን ግን ማምጣት አይችልም። አባቶቻችን ሰይጣን እንኳን መስቀል ቀርቶ መስቀለኛ መንገድም አይወድም ይላሉ። የጌታችን ቅዱስ መስቀል ሆይ ቅዱስ ዳዊት እንዳለ ፦ " ብከ ንወግዖሙ ለኩሎሙ ጸርነ።" " በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን ! " [  ከሞት ባሻገር" መጽሐፍ   ] †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
1231Loading...
29
Media files
900Loading...
30
Media files
1231Loading...
31
Media files
1251Loading...
32
                           †                            🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 ❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ] ❝  እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው ፤ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ ፤ ሥጋዬም ደስ ይለዋል ፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ። ❞ [ መዝ . ፳፰ ፥ ፯ ] 🕊 †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
1271Loading...
33
Media files
882Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
                          †                           🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖 ❝ ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርአዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳዕ ዘተኃጕለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ ፤ ❞ ትርጉም ፦ [ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን በጻድቃን ላይ የሚያበራ ነው ፣ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ ነው ፣ የጠፋው ይረዳ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደ እኛ መጣ [ ሰው ሆነ ] ] [ ድጓ ዘአስተምህሮ ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
إظهار الكل...
👍 1
D.M.Silemayneger sitotaw hulu.mp33.90 MB
ያለፈው ዘመኔ ይበቃኛል ✞.mp39.33 MB
👍 1
🕊 [ † እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † 🕊 †  አቡነ ተጠምቀ መድኅን  †  🕊 † ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ፲፮፻፲ [1610] ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ-ክርስቶስና ወለተ-ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ ፪ [2] ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር ፲፩ [11] ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ጸጋ-እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ:: ሕጻን እያሉ ቃለ-እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ:: ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: ፳፫ [23] ዓመት ሲሞላቸው ወደ መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ፴፯ [37] ዓመታት:- ፩. በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል ፪. ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል ፫. ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል [ካህን ናቸውና] ፬. ፯ "7" ገዳማትንና ፲፪ "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል:: † ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ፷ [60] ዓመታቸው በ፲፮፻፸ [1670] ዓ/ም [በአፄ ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን] ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል:: 🕊   †  ቅድስት ማርታ  †   🕊 † እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች:: መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን [በበዓለ ልደት] ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት:: ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት:: ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ፳፭ [25] ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች:: † የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: † 🕊 [ †  ሰኔ ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅድስት ማርታ ተሐራሚት ፪. አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ [ኢትዮዽያዊ] ፫. ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት ፬. ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን] ፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ ፭. አቡነ ዜና ማርቆስ ፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል † " አልሞትም : በሕይወት እኖራለሁ እንጂ:: የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ:: መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ:: ለሞት ግን አልሠጠኝም:: የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ:: ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ:: ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት:: ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ:: ሰምተኸኛልና: መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ:: " †  [መዝ.፻፲፯፥፲፯-፳፪] (117:17-22) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...
[ ስንክሳር ሰኔ - ፫ - ] .mp36.35 MB
Photo unavailableShow in Telegram
💖                   🔔                     💖      [ የመርሐ-ግብር ማሳወቂያ ! ] የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በቅርብ ቀን በገድለ ቅዱሳን መርሐ-ግብር በተከታታይ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ ይከታተሉ ! †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
                       †                          [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒                [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ] [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🕊                            ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞ [ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [ ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]                 [   ክፍል - ፮ -  ]           💖   ድንቅ ትምህርት  💖 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬                        👇
إظهار الكل...
[ የእግዚአብሔር ሕግ - ፮ - ] .mp312.01 MB
Photo unavailableShow in Telegram