cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

@🇲 🇪 🇿 🇲 🇺 🇷 🇪 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇩 🇴

የኢት/ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያሬዳዊ ዝማሬወችን ፣ ወረቦችን በጽሁፍም ሆነ በድምጽ የምናጠናበት ቻናል ነው"" ስለቻናሉ አስተያየት ካላችሁ @Kulentaha ወይም ላይ መላክ ትችላላችሁ! ዲ/ን ተክለ ዮሃንስ ገብረ ፃድቅ @mezmuretewahdo YOSTINA TUBE

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
246
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Repost from Hilina Belete
ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ (ዲ/ን ሕሊና በለጠ) በማኅሌተ ጽጌ "አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ክበበ ጌራ ወርቅ" እያልን እንዘምራለን። ግን ለምን እንዲህ እንላለን? በቅድሚያ ሙሉ የማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱን ከነ ትርጉሙ ላስቀምጥ:- "ክበበ-ጌራ-ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ፣ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፣ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፣ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፣ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።" #ትርጉም:- "ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቁ ይልቅ የጠራ የወርቅ ጌጥ የኾንሽለት፣ (የጊዮርጊስ) የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ፣ ለጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ የሆንሽ የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ፣ አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ፣ እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል።" ቅዱስ ጊዮርጊስ የ7 ዓመታት ተጋድሎውን የጀመረው በ20 ዓመቱ ነበር። ለሰባት ዓመታት ያክል እየሞተ እየተነሣ ተጋድሎውን ፈጽሞ በ27 ዓመቱ፣ በሚያዝያ 23፣ በ304 ዓ.ም. ዐረፈ። እስከዚያው ጌታችን ቃል እንደ ገባለት 3 ጊዜ ሞቶ 3 ጊዜ ተነሥቷል። በዐራተኛው ሞቱ ፈጽሞ ዐረፈ። ያረፈውም በዕለተ ዓርብ በ9 ሰዓት ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ጊዜ መሞቱን "ማርያም" ከሚለው ባለ 4 ፊደል ቃል ጋር ያመሣጠረው ደራሲው "ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ - የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ" ሲል እመቤታችንን በማኅሌተ ጽጌ አመሰገናት። ቅዱስ ጊዮርጊስን ያንገላታ የነበረው ንጉሥ ዱድያኖስ ንግሥት እለስክንድርያ የምትባል ሚስት ነበረችው። መሳፍንቱና መኳንንቱ ኹሉ ለእርሷ ይሰግዱ ነበር። በሰማዕቱ ትምህርት አምና ለቅዱስ ጊዮርጊስ የፀጋ ስግደትን ሰገደችለት። በዚህም ምክንያት በሚያዝያ 15 አንገቷን በሰይፍ እንድትቆረጥ ተደርጋለች። ያቺ ሣር ቅጠሉ ኹሉ ይሰግድላት የነበረች ንግሥት ለቅዱስ ጊዮርጊስ መስገዷን ያስተዋለው ሊቁ ግን በማኅሌተ ጽጌው "አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ - አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ" ሲል በእመቤታችንና በሰማዕቱ ምስጋና ላይ ዘከራት። ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍጥረት ኹሉ "ብፅዕት" ለሚላት ለድንግል እንደሚሰግድም "ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ - እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል" ሲል ገልጾአል። "የደናግል መመኪያ፣ የሰማዕታት አክሊል፣ ..." የምትባለው እመቤታችን: ቀደም ሲል ባነሣናቸው ምክንያቶች የተነሣ: ይልቁንስ ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ የከበረች አክሊሉና ዘውዱ መኾኗን ሲገልጽም "ክበበ-ጌራ-ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ... አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ - ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቁ ይልቅ የጠራ የወርቅ ጌጥ የኾንሽለት... ለጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ የሆንሽ የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ" ብሏል። እኛም እንደ አባ ጽጌ ድንግልና እንደ አባቶቻችን በማኅሌተ ጽጌ "ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ" እያልን እመቤታችንንና ሰማዕቱን እንዘክራለን። ዘመነ ጽጌ፣ 2013 ዓ.ም.
إظهار الكل...
✞በብርሃን ፀዳል✞ በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ የጽጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ በምስጋናሽ መጠጥ/ሲሰማኝ እርካታ/(፪) እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው የሌሊቱ ህልሜ /የቀን ምኞቴ ነው/(፪)       አዝ= = = = = ሩኅሩኅ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ አመስግኜሽ ድንግል ህልናዬ ረክቶ ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ አንቺን በማመስገን/ህሊናዬ ይትጋ/(፪)        አዝ= = = = = ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርካ የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን ስምሽ ይፃፍብኝ /በልዩ ህብር/(፪)      መዝሙር          ይልማ ኃይሉ "እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና።"               መዝ፻፵፯፥፩
إظهار الكل...
💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇 👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት   👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት 💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ Buy ads:

https://telega.io/c/yamazemur_getemoche

📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako

#ቃል_ኪዳንዋ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰውና ጌታችን ምድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማዕቷ ለትውልድ የሚተላለፍ የዘላለም ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ መታሰብያዋን ያደረገ ስሟን የጠራ፣ በስሟ ቤተ ክርስትያን የሠራ፣ የተራበውን በስሟ ያበላ፣ የተጠማውን በስሟ ያጠጣ፣ የገድሏን መጽሐፍ የጻፈውን፣ ያጻፈውን፣ ያነበበውን፣ የተረጎመውን፣ ሰምቶም በልቡ ያኖረውን፣ የልቡን መሻት እንደሚፈጽምለት እና በመንግስተ ሰማያት እንደ እርሷ የክብር አክሊል እንደሚያቀዳጀው፤ ሥዕሏን አሥሎ በክብር በቤቱ አስቀምጦ ሽቶ እየረጨ ቢጸልይበት ጸሎቱ እንደሚሰማና ልብን የሚመስጥ ጣፋጭ የሆነ መዓዛ እንደሚያሸተው፣ ወንድ ልጁንና ሴት ልጁን በስሟ የሰየመ በመንግስተ ሰማያት የበለጠና የከበረ ስም እንደሚሰጣቸው፣ ዕጣን፣ ስንዴና መብራትን፣ ልብሰ ተክህኖ፣ መጋረጃ ቢሰጥ በሞቱ ቀን የብርሃን ልብስ እንደሚለብስ፣ ያለ ወቀሳ ያለከሳ ባህረ ሲኦልን ተሻግሮ መንግስቱን እንደሚወርስ ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ፨ ሰማዕቷን ከሌሎች ቅዱሳን ልዩ የሚያደርጋት ታሪክ ፨ በግብጽ አገር አርባ ዓመታት የነገሠ ባለ 12 ክንፉ ብጹአዊ አቡነ ሙሴ የሚባሉ ታላቅ ጻድቅ አሉ፡፡ እኝህ ጻድቅ ከንግስና ወደ ምንኩስና የተሸጋገሩ መንፈሳዊ አርበኛ ናቸው፡፡ ታድያ እኝህ ጻድቅ የቅዱሳን፣ የሰማዕታትን ዓጽም እሰበሰቡ ደግላቸውን እያጻፉ፣ ቤተ ክርስትያን በመስራት፣ ታቦታቸውን በማክበር፣ በበዓላቸውም ቀን ይቀድሱ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ታቦት ለማሰናዳት፣ ሜሮን ለመቀባት ወደ ቤተ መቅደስ በገቡ ጊዜ በወርቅ የተለበጠ እና በላዩ በሮማይስጥና በጽርዕ ቋንቋ የብጽዕት ቅድስት አርሴማ ስም የተጻፈበት አንድ ጽላት ያገኛሉ፡፡ ያን ጊዜ የቅዱሳንን ስማቸውን አሰቡ፡፡ የገድላቸውንም ዜና መረመሩ፡፡ ግን የቅድስት አርሴማን ግድልና የሞቷን ዜና አላገኙም። ስለዚህም ነገር በምን ዘመን ሰማዕት እንደሆነች እና የሰማዕትነቷን ሥራ ያስረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አመለከቱ፡፡ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለአቡነ ሙሴ ተገልጦ ‹‹ብጽአዊ ሙሴ ሆይ የብጽእት አርሴማን ሥራ እነግርህ ዘንድ ስማ፡፡ ይህቺ ሰማዕት ገና አልተጸነሰችም፣ አልተወለደችም፤ በወርቅ ዓምድ በሕይወት መጽሐፍ ስሟ ተጽፏል እንጂ፡፡ ነብዩ በመጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ይጻፋል እንዳለ እርሷም በኋለኛው ዘመን ሰማዕት ትሆናለች፤ በዓለም ዳርቻ ሁሉ የገድሏ ዜና ይታወቃል፡፡ ተአምሯ የሚነገረው በኢትዮጲያ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብጽዕት ቅድስት አርሴማን የስም መታሰብያ መጥራት አትተው፡፡ ጽላትዋም ከአንተ ጋር ይኑር፡፡ የመቅደስዋም ህንጻ በህንጻህ ቦታ ጎን ይኑር፡፡ ስምህ በተጠራበትም የስሟ መታሰብያ ይጠራል›› ብሎ መልአኩ ወደ ላከው እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡ አቡነ ሙሴም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ ሰማዕቷም ገና ሳትወለድ በፊት እንደ እመቤታችን በእግዚአብሔር ህሌና ታስባ ትኖር ነበር፡፡ እኛም እንደ እንደ ጻድቁ አቡነ ሙሴ በሰማዕቷ ጸሎት እና ቃል ኪዳን ልንጠቀምባት ይገባል፡፡ ተወዳጆች ሆይ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዮንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶም ስለ ዮፍታሔ ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነብያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና›› ነው ያለው፡፡ /ዕብ 11÷32/ እኔም ስለ እዚች ድንቅ ብርቅ እና ከወርቅ በላይ የከበረች ከአልማዝም በላይ የተወደደች ስለ ሰማዕቷ ለመተረክ ጊዜ ስለማይበቃን እዚህ ላይ ይብቃን፡፡ የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ጸሎት፣በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ በሰማዕቷ በቅድስት አርሴማ ስም ‹‹ሼር›› አድርገው ለወዳጆ ይዘክሩ፡፡
إظهار الكل...
የጽጌ ወር ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው፡፡ ጽጌ፣ ምድር በአበባ፣ ማኅሌቱ በያሬዳዊ ዜማ የሚፈካበት ልዩ ወቅት፣ ምድር የምትዋብበትና የምትቆነጅበት፣ ተራሮች የሚንቆጠቆጡበት የጌጥ፥ የውበት ወቅት እንደሆነ ጠቢቡ ሲገልጽ “እነሆ ክረምቱ አለፈ፤ ዝናቡም አልፎ ሄደ፤ አበቦችም በምድር ላይ ተገለጡ፤ የዜማም ጊዜ ደረሰ” ይላል፡፡ (መሓ. ፪፥፲፩) “አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ ተመልከቱ፤ አይደክሙም፤ አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳን በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዲቱ አለበሰም” እንዲል፤ (ሉቃ.፲፪፥፳፯) ተራሮችና ኮረብቶች በሰው እጅ ያልተጌጠውን  ውብ የሆነ ልብሳቸውን ተጎናጽፈው የሚመለከታቸውን ሁሉ ትኩረት የሚስቡበት፣ ለአፍንጫ ተስማሚ የሆነውን ጥዑም መዓዛቸውንም እንካችሁ ብለው ያለስስት የሚቸሩበት፣ አዕዋፍ ዝማሬያቸውን ከወትሮው በላቀ ሁኔቴ  የሚያንቆረቁሩበት፣ ንቦች ከአበባ ወደ አበባ እየባረሩ ጣፋጭ ማርን የሚያዘጋጁበት፣ ሁሉ አምሮ፣ ሁሉ ደምቆ፣ አዲስ ሆኖ የሚገኝበት ወቅት በመሆኑ ይህ ጊዜ ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጽጌ በመባል ይታወቃል፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ዝማሬዋን፣ ትምህርቷን፣ ዜማዋን፣ ንባቧን፣ ለወቅቱ እንዲስማማ እያደረገች በምሳሌና በኅብር፣ በሰምና ወርቅ እያዋዛች ለጀሮ እንዲስማማ፣ ለልብ እንዲያረካ፣ ለሥጋ ስክነትን ለነፍስ ዕረፍትን እንዲሰጥ አድርጋ ታቀርብበታለች፡፡ በሰማዩ ፍካት፣ በውኃው ጥራት፣ በኮከቦች መውጣት፣ በአበቦች ውበት፣ በተዘሩት አዝርዕት፣ በጸደቁት አትክልት፣ በዛፎቹ ልምላሜ፣ በአዝርዕቶቹ ፍሬ ሁሉ ቃሉን እየመሰለች ታስተምራለች፤ ትዘምራለች፤ ትቀድሳለች፤ በጥበብ ረቅቃ ታራቅቃለች ተቀኝታ ታስቀኛለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን በምልዓትና በሙላት ያለች ናት፡፡ ይህን ዘመነ ጽጌንም እንደ ሌሎች ወቅቶች/ወንጌልን ለማስተማር፣ የራቀውን አቅርባ የረቀቀውን አጉልታ፣ የጎደለውን ሞልታ፣ የጠመመውን አቅንታ ለማስተማር በብዙ መልኩ ትጠቀምበታለች፡፡ በልዩ ሁኔታ ነገረ ማርያምም ነገረ ክርስቶስም በስፋት የሚሰበክበት ወቅት በመሆኑ ዘመነ ጽጌ እጅግ ተወዳጅ ወቅት ነው፡፡ ወርኃ ጽጌን ልዩ የሚያደርገው አንዱና ዋናው የእመቤታችን እና የተወዳጅ ልጇ ስደት የሚታሰብበት ወቅት በመሆኑ ነው፡፡ ውድ የዚህ ጽሑፍ ተከታታዮች ‹‹ሱላማጢስ ሆይ ተመለሺ ተመለሺ›› በሚል ርእስ ስለ ስደቷና ተያያዥ ታሪኮች በቀጣይ ክፍል ሰፋ አድርገን እናቀርብላችኋለን፡፡ እስከዚያው ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን!
إظهار الكل...
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
#ጰራቅሊጦስ ብሂል(ማለት) 1. #መጽንዒ፦ የሚያጸና ማለት ነው፡፡ 2. #መንጽሒ፦ የሚያነጻ ማለት ነው፡፡ 3. #ናዛዚ፦ የሚያፅናና ማለት ነው፡፡ 4. #አራኃዊ፦ የሚከፍት ማለት ነው፡፡ 5. #መስተፍሥሒ፦ ደስ የሚያሰኝ ደስታን የሚመላ ማለት ነው፡፡ 6. #ከሣቲ፡- ምሥጢርን የሚገልጥ ማለት ነው፡፡ 7. #አለባዊ፦ ማስተዋልን የሚሰጥ ማለት ነው፡፡ 8. #መስተናግር፦ ሃይማኖትን፣ የጥበብን ቃል፣ ምሥጢርን የሚያናግር የሚያስተረጉም ማለት ነው፡፡ 9. #መስተሥርዪ፡- ኃጢአትን የሚያርቅ የሚያስወግድ የሚደመስስ ማለት ነው፡፡ 10. #መንፈሰ_ጽድቅ፡- የእውነት መንፈስ፣ #መንፈስ #ቅዱስ ማለት ነው። ስብሐት ለከ ጰራቅሊጦስ በስብሐተ አብ ቅዱስ ስብሐት ለከ ጰራቅሊጦስ በስብሐተ ወልድ ውዱስ ስብሐት ለከ ጰራቅሊጦስ በስብሐተ ስምከ ዘይሤለስ ስብሐት ለከ አምላኪየ በአፈ ኵሉ ዘነፍስ በሰማይ ወበምድር በባሕር ወበየብስ፠ እሰግድ ለርደትከ እሰግድ ለርደትከ እሰግድ ለርደትከ
إظهار الكل...
#ዐውደ_ዓመት ዐውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዐውደ ዓመት/2/ ንዒ ማርያም ለምህረት ወሳሕል/2/
إظهار الكل...
ዕንቁጣጣሽ በወርኃ መስከረም ስለመከበሩ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዕይታ፡-   የዕንቁጣጣሽ በዓል በመስከረም ወር ላይ ለምን እንደሚከበር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚከተለው ያብራራሉ፡፡ ብርሃናት (ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት) የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜን ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ይጀምራሉ፤ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል ዐሥራ ሁለት ሰዓት ይሆናል፡፡ ለዘመን መታወቂያ ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትን ፈጠረ እንዳለ፤ (መጽሐፈ ሄኖክ ፳፩፥፵፱)፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ዓለምን ውኃ አጥለቅልቋት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ከነበረው ውኃ የተገለጠችበት ወር «በመጀመሪያም ወር በምድር ታየች የንፍር ውኃው ከምድር ደረቀ» የሚለውን መሠረት አድርገው የአቡሻኽር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስረዳሉ፡፡ (መጽሐፈ ኩፋሌ ፯፥፩)   ዘመን ሲለወጥ የሰው ልጆች ሕይወት ሊለወጥ ይገባል፡፡ ተማሪው ተምሮ ወደ ቀጣዩ ክፍል ያልፋል፤ በዚህ መልኩም ከኬጂ እስከ ዩኒቨርስቲ ደረጃ ይደረሳል፡፡ ገበሬውም የክረምትን ወራት በሚገባ ተጠቅሞ የሚቀጥለውን የበጋ ወራት የልፋቱን ዋጋ የምድርን በረከት የሚያገኝበት፣ ሠራተኛው የክረምቱን ዝናብ ታግሦ ከፀሐይ ወራት ይደርሳል፤ ክርስቲያንም ዓመት ሲለውጥ በኃጢአት የነበረ ሰው ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣  ከክፋት ወደ በጎነት፣ ከጥላቻ ወደ ፍቅር፣ ከመጀመሪያው የክርስትና ደረጃ እስከ ዐሥረኛው ማዕረግ የሚደረስብትን እያቀደ መኖር ይገባዋል፡፡ ምን ጊዜም ዘመን በተለወጠ ጊዜ የዓመታት እና የወራት ለውጥ ብቻ ሳይሆን የክርስቲኖችም የሕይወት ለውጥ የሚገባ መሆኑን ከተፈጥሮ ክስተት መረዳት ይቻላል፡፡ መጪውን አዲሱ ዓመት ዘመነ ዮሐንስን የቤተ ክርስቲያን ከፍታ የምናይበት፣ በክርስትናችን  የሕይወት ለውጥ የሚያድግበት፣ ሰላም፣ አንድነት፣  የምናይበት እንዲሆንልን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁንልን፤ አሜን፡፡   ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
إظهار الكل...