ar
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

الذهاب إلى القناة على Telegram

EEP Communication

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام EEP Communication

تُعد قناة EEP Communication (@eepcommuication) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 553 مشتركاً، محتلاً المرتبة 8 395 في فئة التكنولوجيات والتطبيقات والمرتبة 2 164 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 553 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 22 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 5، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 1، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.99‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 15.38‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 043 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 2 393 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 9.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
EEP Communication

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 23 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة التكنولوجيات والتطبيقات.

15 553
المشتركون
+124 ساعات
+47 أيام
+530 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+1

በኃይል መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች ለሕግ ቀርበዋል ….....///…...... በኃይል መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ 27 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ ማቅረቡን የቢሾፍቱ የከተማ አስተዳደር ገለፀ። የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ እንደገለፁት ከተማዋ ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት የሚፈልጉ በርካታ የብረታ ብረትና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች መገኛ ናት፡፡ የኃይል መሰረተ ልማቶች በባህሪያቸው ለጥቃት የተጋለጡ በመሆናቸው እና በሚደርስባቸው ጉዳት አገልግሎቱ ቢቋረጥ በከተማዋ ነዋሪዎችና በፋብሪካዎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የሚያደርስና የከተማዋን ዕድገት የሚያቀጭጭ ነው ብለዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ የቴሌኮሙኒኬሽንና የኤሌክትሪክ አውታሮችን ደህንነት ለመጠበቅ በወጣው አዋጅ መሰረት በአካባቢው የሚገኙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት ተገንዝቦ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በ2017 በጀት ዓመት አስር ወራት ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት በኃይል መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ 27 ተጠርጣሪዎችን ለሕግ መቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በሠራቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትና በአጥፊዎች ላይ በሚወስደው የተጠናከረ እርምጃ አሁን ላይ በአካባቢው የነበሩ ችግሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መቀረፋቸውን ገልጸዋል። የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመጠበቁ ኃላፊነት ለአንድ ተቋም ወይም ለመንግስት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ በቀጣይ ሕዝቡን በማሳተፍ መስራት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

በኃይል ዘርፉ ያሉ ችግሮችን የሚያቃልሉ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን እያከናወንኩ ነው - ዩኒቨርስቲው ........///…….. በኢትዮጵያ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጥናትና ምርምር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የአዳማ ሣይንስና ቴክኒዮሎጅ ዩኒቨርስቲ ገለፀ። በዩኒቨርስቲው የኤሌክትሪካል ምህንድስና እና ኮምፒውቲንግ ኮሌጁ ምክትል ዲን መስፍን መገራ እንደገለጹት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ዓለም አቀፍ መለኪያ እየሆነ መጥቷል፡፡ ዘመኑ ያለ ኤሌክትሪክ ኃይል ምንም ዓይነት አገልግሎት መስጠትም ሆነ ማግኘት የማይታሰብበት በመሆኑ ከተሞችና ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ግብርናን በማዘመን የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የፋይናንስን አገልግሎቶችን ለማሳለጥ እና መረጃዎችን ለመለዋወጥ እንዲሁም መሠረታዊ የሕዝብ ፍላጎቶችን ተደራሽ ለማድረግ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት አስፈላጊ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያም እንደሀገር ያሉ ሀብቶቿን አሟጣ በመጠቀም ሁሉን አቀፍ ዕድገት ለማስመዝገብ እና የማህበረሰቡን ሕይወት ለማዘመን ታዳሽ ኃይል አቅርቦት ላይ ትኩረት ሰጥታ በርካታ ተግባራትን እያከናወነች እንድምትገኝ አብራርተዋል። እንደ አቶ መስፍን ገለፃ ባለፉት ዓመታት ኃይል በማመንጨት ከሀገር ውስጥ አልፎ የጎረቤት ሀገራትን በማስተሳሰር በኩል የተሻሉ ውጤቶች ቢመዘገቡም ሁሉንም የሀገሪቱን አካባቢ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ያሉ ውስንነቶችን መፍታት ይገባል፡፡ የአዳማ ሳይንስና ቴክኒዮሎጅ ዩኒቨርስቲ በኃይል ዘርፉ ላይ እንደሚሳተፍ የትምህርት ተቋም ቀደም ሲል በአዳማ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ላይ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን የማማከር ሥራ ላይ መሳተፉን ጠቁመዋል፡፡ ዩኒቨርስቲው ከዋናው ግሪድ ራቅ ባሉ የገጠር አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ፀሐይን በመጠቀም በሶላር ኃይል በሚያገኙበት አማራጭ ላይ ሲሰራ መቆየቱን አውስተዋል፡፡ ዩኒቨርስቲው በኃይል ማመንጨትና በስብጥሩ ዙሪያ ያሉ ክፍተቶች በሚሞሉበት ዙሪያ ጥናትና ምርምሮችን እየተሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ ዘርፉን ይበልጥ ለማዘመን እና የኃይል አማራጮችን በማስፋት እንዲሁም የኃይል ብክነትን በመቀነስ ከግሪድ ውጭ የኃይል አቅርቦቱን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች ተግባራዊ በሚሆኑበት ዙሪያም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል። ዩኒቨርስቲው በቀጣይ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በጥናትና ምርምር እንዲሁም በአቅም ግንባታ ሥራዎች ዙሪያ ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

የሁለቱ ተቋማት የኮሙዩኒኬሽን የሥራ ክፍሎች በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ ……...///……... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን የሥራ ኃላፊዎች በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ለውይይቱ የመነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደተናገሩት የሁለቱ ተቋማት የአብሮነት ጉዞ አንድ ምዕተ ዓመትን የተሻገረ ነው። ተቋማቱ ወደ ሁለት ከተከፈሉበት ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የኮሙኒኬሽን የሥራ ክፍሎች የተቋማቱን ገጽታ ከመገንባት እና ከመረጃ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ በርካታ ሥራዎች ማከናወናቸውን ገልጸዋል። ይሁንና ከቃላት አጠቃቃም እና ተቀናጅቶ ከመስራት አንጻር ክፍተቶች መኖራቸውን ያነሱት አቶ ሞገስ በቀጣይ የጋራ የግንኙነት ጊዜ በማስቀመጥ የታዩ ችግሮችን መቅረፍ እና በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተናቦ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት የሚሰሩት ሥራ ተመጋጋቢ በመሆኑ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር እና ችግሮችን በማረም በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። አላስፈላጊ መሳሳቦችን በማስወገድ የመረጃ ልውውጡን ማዘመን፣ የጋራ የውይይት መድረኮችን መፍጠር እና ችግሮችን በየጊዜው እየለዩ የጋራ መፍትሄ ማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱ ተቋማት የኮሙዩኒኬሽን የሥራ ክፍሎች እስከ አሁን የነበሩ ችግሮችን በሚቀርፍ መልኩ አብረው መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ኮሚቴ አዋቅረዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

ተቋሙ የከተማዋን የኃይል ፍላጎት ታሳቢ አድርጎ እንዲሰራ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቀረበ ........///......... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የቢሾፍቱ ከተማን የወደፊት የኃይል ፍላጎት ታሳቢ አድርጎ የኃይል መሰረተ ልማቶችን እንዲገነባ የከተማ አስተዳደሩ ጠየቀ። የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ እንደተናገሩት ከተማው 63 ሺ ሄክታር የሚሸፍን ስፋት ያለው ሲሆን አሁኑ ወቅት በከተማው 2 ሺ 200 አካባቢ ኢንቨስትመንቶች ይገኛሉ። ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪው መሆኑንና በዘንድሮው በጀት ዓመት ከ250 በላይ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን እንዲሁም ነባሮቹ ትልልቅ የማስፋፊያ ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። ይህም ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ የሥራ ዕድልን እየፈጠረ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው ለአብነትም ኢንቨስትመንት በመኖሩ ብቻ በዚህ ዓመት 62 ሺ ለሚሆኑ ወጣቶች በቋሚነት የሥራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰዋል። እንደ ምክትል ከንቲባው ገለፃ ፋብሪካዎቹ የሥራ ዕድል ከመፍጠር በተጨማሪ ከውጭ የሚገባውን ምርት በመተካት፣ የውጭ ምንዛሬን በማዳንና የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር እንዲኖር በማድረግ የጎላ ሚና አላቸው። የብረታ ብረት ፋብሪካዎችን ጨምሮ አብዛኛዎቹ በከተማዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት የሚጠይቁ ቢሆንም ተቋሙ ቀደም ብሎ ባከናወነው ሥራ አሁን ላይ የኃይል አቅርቦት ችግር አለመኖሩን አንስተዋል። የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ የግብርና ሥራን ለማስፋፋት፣ አምራች ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ እና ከተማዋን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አቅዶ እየሰራ ነው ያሉት አቶ ገዛኸኝ በ5 ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ትልቁ የአየር ማረፊያ በከተማዋ ወደ ግንባታ መግባቱን ገልጸዋል። በዚህም በየዓመቱ ከ110 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ወደ ከተማዋ ይመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅና ይህን ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎች አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል። ከተማ አስተዳደሩ እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎችና ወደ ከተማዋ እየመጡ ያሉ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን አሁን ላይ ባለው የኃይል አቅርቦት ለማስተናገድ የሚቻል አለመሆኑን ከማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት መረዳታቸውን ተናግረዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በከተማዋ በቀጣይ ዓመታት ሊኖር የሚችለውን የኃይል ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ሥራ ቀድሞ እንዲያከናውን ምክትል ከንቲባው ጠይቀዋል። ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግና ከተቋሙ ጋር ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው .....….///…...... የደጀን-ደብረማርቆስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ሥራ ከ87 በመቶ በላይ መጠናቀቁን ፕሮጀክቱ አስታወቀ፡፡ በፕሮጀክቱ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ሥራ አስኪያጅ አቶ እንዳለ ላቀው እንዳስታወቁት የመስመር ዝርጋታው የደጀን ባለ 230/33 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል ነው፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ 48 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የደጀን-ደብረማርቆስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር 111 የኃይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶዎች አሉት፡፡ በአሁኑ ወቅት የ110 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች የመሠረትና የኮንክሪት ሥራ እንዲሁም የ106 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች የተከላ ሥራ መጠናቀቁን ሥራ አስኪያጁ ጠቅሰው ቀሪ የመሠረት እና ተከላ ሥራዎች በቅርቡ እንደሚጠናቀቁ ነው የገለፁት፡፡ በ55 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ የኮንዳክተር ዝርጋታ መከናወኑን የገለፁት አቶ እንዳለ በቀሪ 56 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ኮንዳክተር ለመዘርጋት ከወዲሁ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ሥራው በራስ አቅም እየተከናወነ በመሆኑ ከፍተኛ ወጪ ማዳን መቻሉን የጠቀሱት አቶ እንዳለ በዝርጋታ ሥራው ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ሠራተኞች የዕውቀትና ልምድ ሽግግር እንዲያገኙም ዕድል መፍጠሩን አብራርተዋል፡፡ የደጀን- ደብረማርቆስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ከ73 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለት ሲሆን የፋይናንስ ወጪውም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸፈን ነው፡፡ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቱን እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ነው አቶ እንዳለ የጠቆሙት፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

የምስራቁን ግሪድ የኃይል ፍሰት ለማመጣጠን እየተሰራ ነው ….....///…….. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምስራቁን ግሪድ የኃይል ፍሰት ለማመጣጠን የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ። በተቋሙ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና ማስተባበሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ መንግስቱ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት እስከ ጅቡቲ ያለው የምስራቁ ኮሪደር የኃይል ፍሰት በጣም የተጨናነቀ ነው። ችግሩን ለመቅረፍ የአደጋ ጊዜ የከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን (emergency restoration tower) ወደ ሥራ በማስገባት ቀደም ሲል የተጨናነቁ መስመሮችን አነስተኛ የኃይል ፍሰት ወደሚገኝባቸው መስመሮች በማዘዋወር እና ከአገልግሎት ውጭ የነበሩ መስመሮችን ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። የአደጋ ጊዜ የከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች በተለያየ ምክንያት የሚወድቁ የብረት ምሰሶዎችን በአጭር ጊዜ ለመተካት የሚኖራቸው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ወደ ሥራ እንዲገቡ አቅጣጫ መቀመጡን አስረድተዋል። በቢሾፍቱ ቁጥር 3 ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ያላለቁ ሥራዎች የነበሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማከፋፈያ ጣቢያ ሰርኪዩቶችን ለማገናኘት የሚያገለግለው የቤይ እጥረት በመኖሩ ምክንያት አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየ መስመር መኖሩን አቶ ተስፋዬ አንስተዋል። ከፍተኛ የኃይል ጭነት የሚታይበትን የገላን ቆቃ መስመር ኃይል ለማመጣጠን ከቢሾፍቱ 3 ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል እንዲያገኝ ለማስቻል የአደጋ ጊዜ የብረት ምሰሶዎች ጣቢያው ውስጥ የመትከል ሥራው ዛሬ ይጀመራል ብለዋል። እንደ አቶ ተስፋዬ ገለፃ በአዋሽ 7 በአደጋ ምክንያት የወደቁ ከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን ለመተካት ጊዜ የሚወስድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የአደጋ ጊዜ የብረት ምሰሶዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በመትከል በመስመር ላይ የተቋረጠውን ኃይል መልሶ ለማገናኘት ታቅዷል። የእውቀት ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የተከላ ሥራው ከሁሉም ሪጅን በተውጣጡ የጥገና ባለሙያዎች፣ በዋናው መ/ቤት መሐንዲሶች እንዲሁም የሰርቬይና የትራንስሚሽን ዲዚይን ባለሙያዎች እንደሚከናወን ተናግረዋል። ይህም የምስራቁን ግሪድ የኃይል ፍሰት ከማመጣጠን በተጨማሪ ከኢስት የኢንዱስትሪ ዞንና ከገዳ ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ ላለው የኃይል ፍላጎት ለሟሟላት በቂ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አቶ ተስፋዬ አብራርተዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በመኖሩ የፋብሪካው ምርታማነት ጨምሯል ....///..... አስተማማኝ ኃይል እየቀረበ በመሆኑ ምርታማነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የሲ ኤንድ ኢ ወንድማማቾች ብረታ ብረት ፋብሪካ ፋብሪካ አስታወቀ። የፋብሪካው ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ሙሉጌታ እንዳስታወቁት ፋብሪካው በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኝና በአርማታ የብረት ምርት በሀገሪቱ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፍ ነው። በ2003 ዓ.ም ሥራ የጀመረው ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት ከ650 በላይ ቋሚ፣ ከ45 በላይ ጊዜያዊ እና የተለያየ ሙያዊ ድጋፍ የሚሰጡ የውጭ አገር ሠራተኞችን መያዙን ተናግረዋል። የብረት ፋብሪካ ከፍተኛ ኃይል የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከአሁን ቀደም በምርት ሥራው ላይ እንቅፋት የሚፈጥር የኃይል መቆራረጥ እንደነበር አስታውሰዋል። የኃይል መቆራረጡ በፋብሪካው ላይ የሚያደርሰውን ኪሳራ ለማስቀረት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመነጋገር ከቆቃና ከገላን በሁለት አቅጣጫ ኃይል የሚያገኝ የራሱን ባለ 132 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን ገልጸዋል። ይህም የኃይል መቆራረጡን በማስወገድ የፋብሪካውን ምርታማነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዳሳደገው ነው ምክትል ሥራ አስኪያጁ የተናገሩት። ከተቋሙ ጋር በተደረገ የአገልግሎት ሥምምነት (service level agreement) መሠረት የማከፋፈያ ጣቢያውን የኦፕሬሽን ሥራ እና ሌሎች ሙያዊ ድጋፎች በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው እስከ 10 ሜጋ ዋት የሚደርስ ኃይል እየተጠቀመ ሲሆን አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት መኖሩን ታሳቢ በማድረግ 10 ሺ ሄክታር ከከተማ አስተዳደሩ ተቀብሎ የማስፋፊያ ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል። በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ስርቆት የፋብሪካውን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት አቶ ዮሴፍ እንደ ድርጅት ችግሩን ለመከላከል ወደ ፋብሪካው የሚመጡ ቁርጥራጭ ብረቶችን የሚረከብበት ጠንካራ የቅበላ መመሪያ እንዳለው ተናግረዋል። ድርጅቱ የሚመጡ ቁርጥራጭ ብረቶች ከመሰረተ ልማቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸውና ከስርቆት የጸዱ መሆኑን እያረጋገጠ ከመቀበል በተጨማሪ አጠራጣሪ ነገሮች በሚስተዋልበት ጊዜ ከጸጥታ አካላት ጋር በመነጋገር ጭምር እንደሚሰራ አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሲ ኤንድ ኢ ወንድማማቾች ብረታ ብረት ፍብሪካ ባለ132 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ጣሰው ተክሌ በበኩላቸው ጣቢያው ከቆቃና ከገላን በሁለት አቅጣጫ ኃይል የሚያገኝ በመሆኑ ያልተቋረጠ የኃይል አማራጭ ለማግኘት አስችሎታል ብለዋል። ተቋሙ እስከ 40 ሜጋ ዋት ለማቅረብ ዝግጁ ቢሆንም እስከ አሁን ፋብሪካው እየተጠቀመ ያለው ከ10 ሜጋ ዋት ያልበለጠውን መሆኑን አቶ ጣሰው ተናግረዋል። ፋብሪካው አሁን ላይ ከሚያከናውነው ማስፋፊያ በተጨማሪ ሌሎች የማስፋፊያ ሥራዎችን ቢሰራም አስተማማኝ ኃይል የማቅረብ አቅም መኖሩን አስረድተዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+8

ቅንጅታዊ አሰራርን በመዘርጋት የኃይል መቆራረጡን መቀነስ ተችሏል ....///.... ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት የኃይል መቆራረጥን መቀነስ መቻላቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አዳማ 1 ማከፋፈያ ጣቢያ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዳማ ሪጅን የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ። የአዳማ 1 ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ቦንገር እንደገለጹት ሁለቱ ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎት ተያያዥነት ያለው በመሆኑ በማህበረሰቡ የሚቀርቡ የኃይል ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲሁም የኃይል ተደራሽነቱን ለማሳደግ ተቋማዊ አሰራሩን በጠበቀ መልኩ ተናበው እየሰሩ ነው፡፡ በከተማዋ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ላላቸው ፋብሪካዎች አስተማማኝ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ የኃይል መቆራረጥ መንስኤዎችን በትብብር ለመቅረፍ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የከተማዋንናና የኢንዱስትሪዎችን ቀጣይ የኃይል ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ በቅርቡ አዳማ ሁለት ባለ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ገንብቶ ወደ ሥራ ማስግባቱንም አውስተዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዳማ ሪጅን የኔትወርክ መሰረተ ልማት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ ዓለሙ በበኩላቸው ከማከፋፈያ ጣቢያው 80 ሜጋ ዋት አካባቢ ኃይል እንደሚወስዱና ከጣቢያው ጋር የዕለት ተዕለት ግንኙነት እንዳላቸው አብራርተዋል። በከተማዋ ያለውን የኃይል ተደራሽነትና የአገልግሎት ጥራቱን ለማሳደግ እንዲሁም በአገልግሎቱ በኩል ምንም የኃይል መቆራረጥ እንዳይኖር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። አሁን ላይ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ያለ ኤሌክትሪክ ማግኘት የማይታሰብበት ጊዜ ላይ በመደረሱ የሚመጡ የኃይል ጥያቄዎችን ለመመለስ ቅንጅታዊ አሰራሩን ማጠናከር አማራጭ የሌለው  መሆኑን ነው ሥራ አስኪያጁ የተናገሩት። የኃይል መቆራረጡ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካ እና ደህንነት ላይ ተጽዕኖ እንዳለው በመረዳት ችግሩን በዘላቂነት በመቅረፍ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲኖር በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 22 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

#News Update በጣቢያው ሲከናወን የቆየው የትራንስፎርመር ቅየራ ተጠናቋል ....///.... በወልቂጤ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሲከናወን የቆየው የ63 ሜጋ ቮልት አምፔር የትራንስፎርመር ቅየራ ሥራ መጠናቀቁን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለፁ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ሙጀረብ የኑስ እንደገለፁት የትራንፎርመር ቅየራ ሥራው በመጠናቀቁ በፈረቃ ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ አካባቢዎች ማምሻውን አስተማማኝ ኤሌክትሪክ ማቅረብ ይጀመራል። በዚህም በ66 ኪሎ ቮልት የወሊሶ፣ ቱሉቦሎ፣ ጎሮ፣ አመያ እና አጨበር እንዲሁም ቁሳ ከተሞች ያለ ፈረቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት እንደሚጀምሩ ገልፀዋል። በጉራጌ ዞን ሥር ለሚገኙ አካባቢዎች በ15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመር  ኃይል እንደሚያገኙም ነው የተናገሩት። በወልቂጤ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አንድ ትራንስፎርመር ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አካባቢዎቹ ላለፉት 3 ሳምንታት የተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል በፈረቃ ሲያገኙ መቆየታቸው ይታወሳል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4

የክረምቱን ወራት ታሳቢ ያደረገ የግድብ ደህንነትና ክትትል ሥራ እየተከናወነ ነው .....///..... በቆቃ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ መጪውን የክረምት ወራት ታሳቢ ያደረገ የግድብ ደህንነት ክትትል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የጣቢያው የጥገና ክፍል ኃላፊ አስታወቁ። ኃላፊው አቶ ያፌት ተስፋዬ እንዳስታወቁት በክረምት ወራት ሊኖር የሚችለው ዝናብ ለኃይል ማመንጫዎች አስፈላጊ ቢሆንም በግድቦች ላይ ተገቢው የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ ካልተከናወነ ለአደጋ ሊያጋልጥ  ይችላል ። በክረምት ወራት በእድሜ ምክንያት እያጋጠሙ ያሉ ስንጥቆች እንዲሁም የእንቦጭ አረምና ደለል በግድቡ ደህንነትና ኦፕሬሽን ሥራ ላይ አሉታዊ ጫና እንደሚያሳድሩ ጠቁመዋል። በመሆኑም መጪውን የክረምት ወራት ታሳቢ በማድረግ እነዚህን ችግሮች ለመከላከል አጠቃላይ የግድብ ፍተሻ እና የቅድመ መከላከል የጥገና እንዲሁም የክትትል ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል። የክትትልና ቁጥጥር ሥራው በውኃ መግቢያው፣ በውኃ ማስተንፈሻ (Spillways) እና በግድቡ የተለያዩ ክፍሎች ላይ  እንደሚከናወን ገልፀዋል። በዚህም የግድቡን የውኃ ማስተንፈሻ እና መቆጣጠሪያ በሮች በመጠገንና ብረቶቹን ከዝገት በመከላከል ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል። በግድቡ የላይኛው ክፍል ላይ የሚገኙ ስንጥቆች እየሰፉ እንዳይሄዱ ክፍተቶቹን የሙሙላት ሥራ መከናወኑንም አብራርተዋል። እንደ አቶ ያፌት ገለፃ የግድብ ደህንነት ሥራው በክረምት ወራት ወደ ግድቡ የሚገባውን ክፍተኛ ውኃ ለማስተንፈስ በሮቹ በትክክል አንደሚከፈቱ፣ እንደሚዘጉ እና ብሬከሩ በትክክል እንደሚስራ አስቀድሞ ለመለየት ይጠቅማል። የቅድመ ፍተሻና እና ጥገና ሥራው ግድቡ ውኃ ከሞላ በኋላ የተበላሹ በሮች፣ ሞተሮች፣ ብሬከሮች እና የተለያዩ መሣሪያዎችን ለመጠገን የሚፈጥረውን የሥራ ጫና እንደሚያቀል አብራርተዋል። የክትትልና ቁጥጥር ሥራው የግድቡን ደህንነት በመጠበቅና የኦፕሬሽን ሥራውን በማቀላጠፍ የኃይል ማመንጫ ጣቢያው የሚጠበቅበትን ኃይል በአግባቡ እንዲያመርት ከማድረጉም ባሻገር በታችኛው ተፋሰስ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ከጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል መሆኑንም አቶ ያፌት ገልጸዋል፡፡ በግድቡ አካላት ላይ ከሚከናወኑ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች በተጨማሪ በግድቡ ሠው ሰራሽ ሀይቅ ላይ በፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኝውን የእንቦጭ አረም ክረምቱ ከመግባቱ በፊት ለማስወገድ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ባሳተፍ መልኩ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። የቆቃ የውኃ ኃይል ማመንጫ ከ1952 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥጌ/ሞመ ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም