ar
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

الذهاب إلى القناة على Telegram

EEP Communication

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام EEP Communication

تُعد قناة EEP Communication (@eepcommuication) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 546 مشتركاً، محتلاً المرتبة 8 351 في فئة التكنولوجيات والتطبيقات والمرتبة 2 178 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 546 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 02 يوليو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 27، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 8، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.76‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 15.84‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 005 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 2 463 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 9.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
EEP Communication

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 03 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة التكنولوجيات والتطبيقات.

15 546
المشتركون
+824 ساعات
-227 أيام
+2730 أيام
أرشيف المشاركات
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1497ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1497ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ይመኛል፡፡ ኢድ ሙባረክ!! የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et

ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከልና በሥነ- ምግባር የታነፀ ሠራተኛና የሥራ መሪ ለመፍጠር እየተሠራ ነው ………///……… የሙያ ሥነ ምግባር እንዲዳብርና የተቋሙ ሀብትን ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በማድረግ ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ሥራ አስፈፃሚ ገለፁ፡፡ ሥራ አስፈጻሚው አቶ መርጋ ተረፈ እንደገለጹት ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከልና በሥነ- ምግባር የታነፀ ሠራተኛና የሥራ መሪ ለመፍጠር እየተሠራ ነው፡፡ በሥነ-ምግባር ጥሰትና በብልሹ አሰራር የሚከሰቱ የዲሲፕሊን ችግሮች ላይ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እና የአሰራር ጥናት በማድረግ ክፍተት ያለባቸው አሰራሮች እንዲታረሙ የማድረግ ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ አቶ መርጋ እንዳሉት በሥነ ምግባር የታነፀና ሙስናን የሚፀየፍ ሠራተኛ ለመፍጠር እንዲሁም በተቋሙ ውስጥ የሚፈፀሙ የሙስና እና የብልሹ አሰራሮችን በመጠቆምና በማጋለጥ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የፀረ-ሙስና ትግሉ አካል እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል፡፡ የተቋሙ ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ፤ ደንቦችና መመሪያዎች በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲውሉ፤ የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራር እንዲያጋልጡና በሚመለከተው አካል እንዲመረመር እንዲሁም በአጥፊዎች ላይ ተገቢው የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በ2014 በጀት ዓመት ለ780 ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች የሥነ - ምግባር ግንባታ ላይ ያተኮረ ሥልጠና መሰጠቱን ያነሱት አቶ መርጋ በ2015 በጀት ዓመት ለ800 የተቋሙ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ልዩ ልዩ የግንዛቡ መፍጠሪያ ሥልጠናዎች ለመስጠት መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ ለሙስና ተጋላጭ ናቸው ተብለው በተለዩ የሥራ ክፍሎች ላይ ትኩረት በማድረግ የሙስና መከላከል ሥራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡ በ2014 በጀት ዓመት በፋይናንስ የክፍያ ሥርዓት፤ በፕሮጀክቶች እና ኦፕሬሽን መካከል በሚካሄድ የንብረት ርክክብ፤ በሚወገዱ የተቋሙ ንብረቶች እንዲሁም በውጪ ሥልጠና አመራረጥ ላይ የአሰራር ጥናት በማድረግ ክፍተቶች እንዲታረሙ መደረጉን አቶ መርጋ አስታውሰዋል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለዘርፉ የቀረቡ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ የተለያየ የዲሲፕሊን ችግር የታየባቸውን አንድ የሥራ ኃላፊና ሰባት ሠራተኞች ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ሥራ ማሰናበት የሚደርስ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረጉን እና ከድርጅቱ አላግባብ የተወሰደ ከ3 መቶ ሺህ በላይ ለማስመለስ ጉዳዩ በፍርድ ቤት መያዙን ከሥራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content

ከሀገር ውስጥ የኃይል አቅርቦትና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ ከ2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል ………////……… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ሁለት ወራት ከሀገር ውስጥ የኃይል አቅርቦትና ከፋይበር ኦፕቲክስ (OPGW) ኪራይ ከ2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ሽያጭ ማከናወኑን የማርኬቲንግና ቢዝነስ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የሽያጭና ደንበኞች አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ አቶ ምኒሊክ ጌታሁን እንዳስታወቁት በሐምሌና ነሐሴ ወራት ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ እና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ ከ2 ነጥብ 74 ቢሊዮን ብር በላይ ሽያጭ ተከናውኗል፡፡ ይህም ከዕቅዱ የ1 ነጥብ 5 በመቶ ወይም የ40 ነጥብ 64 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከተከናወነው ሽያጭ ውስጥ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከ158 ነጥብ 85 ሚሊዮን ብር በላይ ለከፍተኛ የኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች፣ ከ62 ነጥብ 61 ሚሊዮን ብር በላይ ለኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር የኃይል አቅርቦት የተከናወነ ሽያጭ ነው፡፡ የፋይበር ኦፕቲክስ ለኢትዮ ቴሌኮም፣ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ዌብስፕሪክስ አይ ቲ ሶሉሽን ለተባሉ ኩባንያዎች በማከራየት ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡ ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ ለማግኘት ከታቀደው መካከል የኢትዮ - ምድር ባቡር ከዕቅዱ የ170 በመቶ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዕቅዱ 0 ነጥብ 45 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚዎች ደግሞ የ7 ነጥብ 37 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን ነው የተገለጸው፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለጻ ባለፉት ሁለት ወራት ለሀገር ውስጥ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ኃይል በመሸጥ የዕቅዱን 97 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡ በዚህ መሰረት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ1 ነጥብ 95 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት፣ ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ከ132 ነጥብ 88 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት እንዲሁም ለኢትዮ- ጂቡቲ ምድር ባቡር ከ13 ነጥብ 61 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል መሸጡንም አቶ ምኒሊክ አስታውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content
+1

1.jpg0.15 KB

ማመንጫ ጣቢያው በበጀት ዓመቱ 220 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማመንጨት አቅዷል ……..////……. የጢስ አባይ 2 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በተያዘው የ2015 በጀት ዓመት 220 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ማቀዱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለጹ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ደጀኔ ጉታ እንደገለጹት ዕቅዱን ለማሳካትና የኦፕሬሽን ሥራውን አስተማማኝ ለማድረግ መደበኛና ድንገተኛ የጥገና ሥራዎች በዕቅድ እየተመሩ በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ አቶ ደጀኔ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ ዕቅድ ላይ ከሠራተኞች እና ከሥራ መሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ በዕቅዱ ላይ መግባባት ተፈጥሮ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ በክረምቱ ወራት የሚፈጠረዉን ከፍተኛ የዉሃ አቅም በመጠቀም ተርባይኖቹ በሙሉ አቅማቸዉ እንዲሰሩ በመደረጉ ያለፉት ሁለት ወራት አፈፃፀምም የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል አመላክቷል ብለዋል፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ ባለፈው ዓመት የጣቢያው ዩኒቶች በራስ ኃይል በመጠገናቸው ተርባይኖቹ በአስተማማኝ ሁኔታና በሙሉ አቅማቸው ኃይል እያመነጩ ነው፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት በገበያ ላይ በቀላሉ ሊገኙ የማይችሉ እና ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጡ የመለዋወጫ ዕቃዎችን በራስ ኃይል በሌላ የመተካት (የሞዲፊኬሽን) ሥራ በመስራት ተቋሙን ከወጪ ለመታደግ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የኤሌክትሮ መካኒካል ክፍሎች በሆኑት የቮልቴጅ መቆጣጠሪያ (ኤግዛይቴሽን ሲስተም)፣ የተርባይን ፍሪኩዌንሲ መቆጣጠሪያ (ገቨርነር ሲስተም) እና ኮንትሮሊንግ ሲስተሙ ላይ የጥገና ሥራዎችን ለመስራት እቅድ መያዙንም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡ የጢስ አባይ ማመንጫ ጣቢያ ባለፈው የበጀት ዓመት 157 ነጥብ 8 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማመንጨት አቅዶ 182 ነጥብ 3 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መቻሉን ከጣቢያው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content

ማመንጫ ጣቢያው በበጀት ዓመቱ 220 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማመንጨት አቅዷል ……..////……. የጢስ አባይ 2 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በተያዘው የ2015 በጀት ዓመት 220 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ማቀዱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለጹ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ደጀኔ ጉታ እንደገለጹት ዕቅዱን ለማሳካትና የኦፕሬሽን ሥራውን አስተማማኝ ለማድረግ መደበኛና ድንገተኛ የጥገና ሥራዎች በዕቅድ እየተመሩ በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ አቶ ደጀኔ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ ዕቅድ ላይ ከሠራተኞች እና ከሥራ መሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ በዕቅዱ ላይ መግባባት ተፈጥሮ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ በክረምቱ ወራት የሚፈጠረዉን ከፍተኛ የዉሃ አቅም በመጠቀም ተርባይኖቹ በሙሉ አቅማቸዉ እንዲሰሩ በመደረጉ ያለፉት ሁለት ወራት አፈፃፀምም የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል አመላክቷል ብለዋል፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ ባለፈው ዓመት የጣቢያው ዩኒቶች በራስ ኃይል በመጠገናቸው ተርባይኖቹ በአስተማማኝ ሁኔታና በሙሉ አቅማቸው ኃይል እያመነጩ ነው፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት በገበያ ላይ በቀላሉ ሊገኙ የማይችሉ እና ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጡ የመለዋወጫ ዕቃዎችን በራስ ኃይል በሌላ የመተካት (የሞዲፊኬሽን) ሥራ በመስራት ተቋሙን ከወጪ ለመታደግ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የኤሌክትሮ መካኒካል ክፍሎች በሆኑት የቮልቴጅ መቆጣጠሪያ (ኤግዛይቴሽን ሲስተም)፣ የተርባይን ፍሪኩዌንሲ መቆጣጠሪያ (ገቨርነር ሲስተም) እና ኮንትሮሊንግ ሲስተሙ ላይ የጥገና ሥራዎችን ለመስራት እቅድ መያዙንም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡ የጢስ አባይ ማመንጫ ጣቢያ ባለፈው የበጀት ዓመት 157 ነጥብ 8 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማመንጨት አቅዶ 182 ነጥብ 3 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መቻሉን ከጣቢያው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content

በሁለት የመቆፈሪያ ማሽኖች ጥልቅ ጉድጓድ ለመቆፈር በቀን በአማካይ እስከ 10 ሺህ ሊትር ነዳጅ ያስፈልጋል ………////…….. የከርሰ ምድር የእንፋሎት ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ ለማከናወን ከፍተኛ የነዳጅ አቅርቦት እንደሚያስፈልገው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአሉቶ ላንጋኖ ጂኦተርማል ፕሮጀክት አስታወቀ፡፡ የፕሮጀክቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ልዑል አስፋወሰን እንዳስታወቁት በሁለት የጥልቅ ጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽኖች የቁፋሮ ሥራ ለማከናወን በቀን በአማካይ እስከ 10 ኪዩቢክ ሜትር ወይም 10 ሺህ ሊትር ነዳጅ ያስፈልጋል፡፡ የከርሰምድር እንፋሎት ጉድጓዶችን የቁፍሮ ሥራ ሂደት ማቋረጥ የቴክኒክና የፋይናንስ ችግር ሊያስከትልና በሂደትም ብዙ ወጪ ሊያስወጣ ስለሚችል ቁፋሮው በነዳጅ እጥረት መስተጓጎል አይኖርበትም ብለዋል፡፡ በተያያዘ ዜና በአሉቶ 1 ሳይት እየተከናወነ ለሚገኘው የከርሰ ምድር እንፋሎት ልማት እና በቦቤሳ ሳይት እየተካሄደ ለሚገኘው የእንፋሎት ፍለጋ ጉድጓድ ቁፋሮ የተያዘው ጊዜ እስከ ቀጣዩ ዓመት ታህሳስ ወር ቢሆንም ሥራው ከተያዘው ጊዜ አስቀድሞ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተገልጿል፡፡ እንደ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ገለፃ በፕሮጀክቱ እስከ ታህሳስ 2015 ድረስ እስከ አራት ተጨማሪ ጥልቅ የእንፋሎት ጉድጓዶችን በመቆፈር የእንፋሎት ምርት መጠኑን ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ ነው፡፡ የጉድጓድ ቁፋሮው ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ እንፋሎቱን ከጉድጓዶች የሚያሰባስብ የቧንቧ ኔትወርክ (Steam Gathering Pipe Line Network) ተዘርግቶ ወደ ኃይል ማመንጨት ሥራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የቁፋሮውን ሥራ መጠናቀቅ ተከትሎ የጉድጓዶቹን እንፋሎት የማመንጨት አቅም፣ የሙቀት ባህርይ እና ከእንፋሎቱ ጋር የሚወጣውን ፈሳሽ ዓይነት የሚለይ (Geo - Chemistry) ጥናት ከተካሄደ በኋላ ምን ዓይነት ተርባይን በምን ዓይነት ዲዛይን እንደሚያስፈልግ እንደሚወሰን ገልፀዋል፡፡ የአሉቶ የከርሰምድር እንፋሎት ቁፋሮ በላንጋኖ ሳይት እስከ 35 ሜጋ ዋት ለማመንጨት እየተሰራ ሲሆን ቦቤሣ በተባለው ሳይት ደግሞ የከርሰ ምድር እንፋሎት ፍለጋ ቁፋሮ በ 2 የሙከራ ጉድጓዶች የሚከናወን ይሆናል፡፡ የከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይል ከታዳሽ የኃይል ምንጮች ጎራ የሚመደብ ሲሆን ኢትዮጵያም በዚህ ዘርፍ ያልተነካ እምቅ ሀብት እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የፍለጋና የማልማቱ ሥራም በቂ የካፒታል አቅም፣ ቴክኖሎጂና የዓለም አቀፍ ተሞክሮ ሽግግርን ይጠይቃል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content
+2

ተቋሙ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ሥምምነት ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዷለም ሲዓ እና የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱ በጥናትና ምርምር፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በማማከር ሥራዎችና መሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረትን ያደረገ መሆኑን በተቋሙ የሰው ኃይል ስልጠናና ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድወሰን ካሳ ገልፀዋል፡፡ በዘርፉ ላይ የሚካሄዱ ጥናቶችን በጋራ ለመስራት እንደሚያስችል የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በተቋሙ የሠው ኃይል አቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ስምምነት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በኃይል ልማት ዘርፉ የሠለጠኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት በሚሰራው ሥራ ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የተናገሩት ዳይሬክተሩ ስምምነቱ በሠው ኃይል አቅም ግንባታ ሂደት የተቋሙ ሠራተኞች በፓዎር ኢንጅነሪንግ የሦስተኛ ድግሪ ትምህርት እንዲያገኙ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና መምህራን በተቋሙ የሥራ ላይ ልምምድ የሚያደርጉበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ ስምምነቱ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን ተቋሙ የያዘውን የረጅም እና የአጪር ጊዜ ዕቅድ ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን ዶ/ር ወንድወሰን ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ከዚህ በፊት ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን የትብብር ስምምነት መፈራረሙ የሚታወስ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content
+1

አሦሳ የኤሌክትሪክ ኃይል አገኘች በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ ከአራት ቀን በኋላ የኤሌክተሪክ ኃይል አገች፡፡ በከተማዋ በታወር ብረት ስርቆት ምክንያት ለአራት ቀናት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል በተደረገው ጊዚያዊ ጥገና ከመስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ኃይል አንድታገኝ መደረጉን አቶ ተስፋዬ መንግስቱ የትራንስሚሽን መስመር ጥገና ቴክኒካል ሰፖርት ሥራ አስኪያጅ ገልፀዋል፡፡ የኃይል መቋረጥ የተከሰተው ከመንዲዳ አሶሳ በሚሄደው 132 ኬ.ቪ የትራንስሚሽን መስመር ከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ መስመር በተደረገ ስርቆት ታወሮች መውደቅ ምክናንያት ነው፡፡ የወደቀውን ታወር በእንጨት በመቀየር የተቋማችን የምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽን ባለሙያዎች እና የኢትዮጵያ ኤሌክትክ አገልግሎት አሶሳ ቅርንጫፍ ባለሙያዎች ጋር በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ ጥገናው መከናወኑን ሥራአስኪያጁ አሳውቀዋል፡፡ እንደ ስራ አስኪያጁ ገለፃ በክልሉ የሚፈፀም ተደጋጋሚ የመሰረተ ልማት ስርቆት ክልሉን ለተደጋጋሚ የኃይል መቋረጥ ዳርጎታል፡፡ ህብተሰቡ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶች የሚያደርሱትን ጫና ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ወንጀለኞችን ተከታትሎ ማጋለጥ እንዳለበት እና ክልሉም ወንጀለኞች ላይ ተገቢውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ የገለፁት አቶ ተስፋዬ የመሰረተ ልማት ስርቆት የሚፈጥረው ጫና በመረዳት የታወር ምሶሶዎችን ደህንነት ትኩረት ሰጥቶ እንዲያስጠብቅ አሳስበዋል፡፡ በጥገናው ወቅት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ከበደ ላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍ የኢትዮጵያ አሌክትሪክ ኃይል ልባዊ ምስጋና ያቀርባል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content
+6

EEP Communication - إحصائيات وتحليلات قناة تيليجرام @eepcommuication