ar
Feedback
የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command ️

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command ️

الذهاب إلى القناة على Telegram

🚩 Channel was restricted by Telegram

إظهار المزيد
1 379
المشتركون
-224 ساعات
-1097 أيام
-1 20930 أيام
أرشيف المشاركات
ሃምሌ 20/2018 ዓ.ም የ5ኛ ንስር ኮማንዶ ሬጅመንት በዛሬው ዕለት በአርመኒያና ማፉድ ቀበሌ ባፈፀምችው ኦፕሬሽን የተገኘ ውጤት ጠላት ፍላጎት የነበረው ማፉድ በነበረው በወገን ሁለት ሻምበሎች ላይ
+9
ሃምሌ 20/2018 ዓ.ም የ5ኛ ንስር ኮማንዶ ሬጅመንት በዛሬው ዕለት በአርመኒያና ማፉድ ቀበሌ ባፈፀምችው ኦፕሬሽን የተገኘ ውጤት ጠላት ፍላጎት የነበረው ማፉድ በነበረው በወገን ሁለት ሻምበሎች ላይ ቀድሞ ተኩስ ከፍቶ ሌላው የሸዋ ፋኖ ተወርዋሪ ሻለቃ የሚትባለውን የሰው ሃይላቸው 150 የሆኑ ከተሰማ እሬገጤ 3ኛ ሻለቃ የሰው ሃይላቸው 142 ከአስቻለው ደሴ 1ኛ ሻለቃ የሰው ሃይላቸው 149 የራምቦ ክ/ጦር 3ኛ ሻለቃ 129 በድምሩ 570 የሰው ሃይል ያላቸው 04 ሻለቃዎችን አሰማርቷል። የጠላት ፍላጎት አርሜኒያ እንደየሱስ ተራራ ላይ የነበረችውን የወገን አንድ ሻምበል በማፈን ቦታውን በመቆጣጠር ሳርአምባ እና ዶቃቂት ቀበሌ የነበሩትን ሻምበሎችን በማጥቃት አርሜኒያ ቀበሌን የመቆጣጠር አለማን አንግቦ የወገን ምሽግ ድረስ በመጠጋት ቦምብ በመወርወር በወገን 2ኛ ሻምበል 11:20 ማጥቃት ከፈተ። ማፉድ ባሉት በሁለቱ ሻምበል ላይም በተመሳሳይ ሰዓት በድሽቃ የተጋዛ ማጥቃት ጀመረ። ሆኖም የጠላት ፍላጎት የማፉድን በማሳሳት አርመኒያን ለመቆጣጠር ፍላጎት መኖሩን በመረዳት ከ1ኛ ሻምበል እና ከ3ኛ ሻምበል ሁለት መቶዎችን በማወጣት ከጠላት ጀርባ ቆረጣ በማስገባት የጠላትን ማጥቃት ወደ ፀረማጥቃት በመቀየር የገባውን ሃይል ማስቀረት ተችሏል። ነገር ግን የጠላት ፍላጎቱ ህልም ሆኖ እንድቀር ተደርጓል። የወገን ቅፅባታዊ የፀረመጥቃት እርምጃ የጠላትን አለማ አክሽፏል። አሁንም በየማሳው በየማሽለው እየተንጠባጠበ የቀረውን እየለቀምን እንገኛለን። የተገኘው ድል ቢንያም አስፈው የራምቦ ሻለቃ አዛዥ ተገሏል። ፍቅሩ ራንቦ አመራር ጎሹ ምክትል ሻለቃ መሪ የተሰማ ርገጤ ነጋሽ አመራር የሸዋ ፋኖ ተወርዋሪ/ቃኝ ጠርናፊ ሻለቃ መሪ የተሰማ እርገጤ ተሰማ ቃኝ ብሩክ ዘመቻ ሃላፊ 10 ተራ እግረኛ ጦር እነዚህ በአመራር ደረጃ የተደመሰሱ ናቸው። የተማረኩት አወራሪስ በላይ የአስቻለው ደሴ 1ኛ ሻለቃ ብሬን ተኳሽ ወንድወሰን ዳምጠው የተወርዋሪ ሻለቃ ብሬን ተኳሽ ታዴ ስዩም ተሰማ እርገጤ ክ/ጦር ብሬን ረዳት ናቸው ከተማረኩት ውስጥ ሽፈረው ሳህላ በህክምና ላይ እያለ X አድርጓል። 👉 የተገደለ ፅንፈኛ 42 👉 የተማረከ ቁስለኛ 04 👉 መገናኛ ሬድዮ 02 👉 መገናኛ ቅያሪ ባትሪ 02 👉 ብሬን 01 👉 የብሬን ዝናር 01 👉 ብሬን አፈሙዝ 01 👉የብሬን ጥይት 540 👉 ጥቁር ክለሽ 01 👉 ክላሽ 02 👉 ቆመህ ጠብቀኝ 01 👉 የክላሽ ካዜና 19 👉 የክላሽ ጥይት 432 👉 የስናይፐር ካዜና 01 👉 የወገብ ትጥቅ 04 👉 F1 ቦምብ 05 በወገን የደረሰ ጉዳት 04 መጠነኛ ቁስለኛ

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ መዝሙር #habesha #duet #africa #ebs https://youtube.com/shorts/ngYt1DIdLhs?si=VRbANPkYf-BFJQxG

ሰሞኑን በወሎ የተደመሰሱ ፅንፈኛ ፋኖዎች መርዶ ለቤተሰባቸው አድርሱላቸው።
+9
ሰሞኑን በወሎ የተደመሰሱ ፅንፈኛ ፋኖዎች መርዶ ለቤተሰባቸው አድርሱላቸው።

በዶቃቂት ቀበሌ በተደረገ ድንገተኛ ኦፕሬሽን ስድስት የፅንፈኛ ቡድን አመራሮችና አባላት እንዲሁም እህል በቁጥጥር ስር ዋሉ። ​ ሰኔ 5/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ​የ103ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦ
+4
በዶቃቂት ቀበሌ በተደረገ ድንገተኛ ኦፕሬሽን ስድስት የፅንፈኛ ቡድን አመራሮችና አባላት እንዲሁም እህል በቁጥጥር ስር ዋሉ። ​ ሰኔ 5/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ​የ103ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር 5ኛ ኮማንዶ ንስር ሬጅመንት በሰሜን ሸዋ ዞን ዶቃቂት ቀበሌ አይርስ ጎጥ ባደረገው ድንገተኛ ኦፕሬሽን፣ ስድስት የፅንፈኛ ቡድን አመራሮችንና አባላትን ከነዘረፉት እህል ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። ​የሬጅመንቱ አዛዥ ሻለቃ ታሪኩ ሻሜቦ ለሚዲያ እንደገለጹት ኦፕሬሽኑ የተከናወነው የፅንፈኛ ቡድኑ አመራሮች ከህብረተሰቡ የሰበሰቡትን እህል ለቡድናቸው አባላት ሊጭኑ ሲሉ ከህዝብ በተገኘ ጥቆማና በጥምር ጦሩ በተቀናጀ ፈጣን እርምጃ ነው። ​በዚሁ ስኬታማ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር የዋሉት የፅንፈኛው አመራሮችና አባላት፦ 1 ​መንግስቱ በላይሁን (የፅንፈኛው ሻምበል አዛዥ) 2 ​የኋላእሸት ማሞ (የፅንፈኛው ምክትል ሻምበል አዛዥ) 3 ​አያሌዉ ንጉሴ (ቀደም ሲል ሰላም አስከባሪ የነበረና ታጥቆት የነበረውን መሳሪያ ለፅንፈኛው ያስረከበ) 4 ​በለጠ ደለለኝ (ሰላም አስከባሪ የነበረና በኋላም መሳሪያ ይዞ ወደ ፅንፈኛው የተቀላቀለ) 5 ​ተቻለ ንጉሴ (የአባት አርበኛ ተዋጊ) 6 ​ሙሉጌታ ኪዳኔ (ፅንፈኛና ሰላም አስከባሪዎችን ለማስከዳት እንዲሁም የኮንትሮባንድ እቃዎችን የሚያቀባብል) ሲሆኑ ተጠርጣሪው ሙሉጌታ ኪዳኔ ሰላም አስከባሪዎችን ለማስከዳት በመጣበት ወቅት ከተጠቀመበት ሞተር ሳይክል ጋር እጅ ከፍንጅ መያዙን ሻለቃ ታሪኩ አብራርተዋል። ​ከተጠርጣሪዎቹ በተጨማሪ የፅንፈኛው ቡድን ከህዝብ የዘረፈው 8 ኩንታል ጤፍ እና 2 ኩንታል ማሽላ በጥምር ጦሩ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። ​በተመሳሳይ ዜና በፅንፈኛው አጠራር "የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ተወርዋሪ ሻለቃ" አባልና የሞርተር ምድብተኛ የሆነው ባቢል ካሳ የጥምር ጦሩን ጥሪ ተቀብሎ በሰላም ለመንግስት እጁን መስጠቱን ሻለቃ ታሪኩ ሻሜቦ አስታውቀዋል። ​የሬጅመንቱ አዛዥ አሁንም በፅንፈኛው ጎራ ተሰልፈው የሚገኙ አካላት የጥፋት መንገድ እንደማያዋጣ ተገንዝበው በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ለማድረግ የሚወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋልዋሉ። ዘገበው የጣርማበር ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው። የኮማንዶና አየር ወለድ ሃይሎች የግዳጅ ውሎ - Commandos & Airborne Battlefield ተጨማሪ መረጃዎችን በቴሌግራም ያግኙ https://t.me/Commando_And_Airborne_Command